ምርኮኛ - በፓስወርድ መነጽር ስር

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ምርኮኛ - በፓስወርድ መነጽር ስር

Postby password » Thu Feb 10, 2011 4:00 pm

ሰላም ዋርካዊያን በሙሉ / ፓስወርድ ነኝ። እንዴት ናችሁ።

የምስራች ይዤ ነው የመጣሁት፣ የአንድ ኮከብ መወለድን ላልሰማችሁ ላበስር።

ምርኮኛ
ታሪካዊ ልቦለድ

ደራሲ/ቆንጂት ብርሃን
የገጽ ብዛት/ 491

በዘመነ ደርግ የመጀምሪያዎቹ ቀውጢ ዓምታት በነበረው ማህበራዊና ፖለቲካዊ ህይወት ላይ የሚያጠነጥን ታሪክ ቀመስ ልቦልድ ነው። ያ ዘመን የኢትዮጵያን አጠቃለይ ገጽታና የህዝቡዋን ህይወት በከፍተኛ ደረጃ የለወጠና አገሪቱ አሁን ካለችበት አጠቃላይ ሁኔታ እንድትገኝ ወሳኝ ተግባራት የተከወኑበት ወቅት እንደምሆኑ የዚያ ዘመን ታሪክ ከብዙ መዓዘናት በመጻፍ ላይ ነው። የደርግ ባለስልጣኖች፣ ኮ/መንግስቱን ጨምሮ፣ ከፍተኛ የጦር መኮንኖችና የሲቪል ባለስልጣኖች፣ የተለያዩ ታሪካዊ ዘገባዎችን የያዙ መጸህፍት ጽፈው ለንባብ አብቅተዋል። እነዚህ መጻህፍት ከዚያው ከባለስልጠኖቹ የእይታ መዐዘን የተጻፉ፣ እገሌ ይህን አለ፣ በዚህ ቀን ያ ተወሰነ፣ ጦሩ ወዲህ ተላክ፣ ያን ያህል ጉዳት አደረሰ ወዘተ የሚሉ እንጂ በሰዎች ላይ በግል ስለደረሰው መከራ አይተርኩም። የአጻጻፍ ዘርፉም እንዲያ ያለውን ጉዳይ ሊዳስስ አይመችም።

የዚያን ዘመን ማህበራዊ ህይወት ተመርኩዘው በልቦለድ መልክ የተጻፉ የግለሰቦችን ህይወት የሚዳስሱ መጻህፍት ተጽፈዋል። የሙሉጌታ ጉደታ "እንዳይደገም"፣ የመኮንን ገ/እግዚ "መቅሰፍትና በዘመነ ሽብር" በልቦለድ መልክ የተጻፉ የዚያን ዘመን ማህበራዊ ህይወትና በሰዎች ላይ የደረሰውን ግፍና መከራ የሚተርኩ ናቸው። ያን ዘመን አስመልክቶ እስካሁን የተጻፉት መፃህፍት በሙሉ በተባእት ደራሲያን የተጻፉ ናቸው። የማህበረሴቡ ግማሽ አካል፣ የዚያን ዘመን ግፍና መከራ እኩል የተካፈሉት አንስት ዜጎቻችን ልባቸው በሃዘን የፈረጠውን ያህል መንፈሳቸውም ዳሽቆ እስካሁን ብእር ለማንሰት እልተነሱም፣ ያን የትውልድ አደራ፣ ያን የትግል ጉዋድ ቃል፣ ያን ያኔ የተማማሉትን መሃላ ግን ለእንድ ቀን ዘንግተውት አያውቁም።

የኒያ ጀግኖች አደራ፣ "ሓወልት አሰሩልን" አልነበረም።
የኒያ ሰማእት ቃል "አባዬን ወይም እማዬን ወይም መሙሽን" አደራ የሚል አልነበረም።
"አትርሱን፣" "ብቻ አትርሱን" የሚል ቀላል የአደራ ቃል ነበር።

ያን አደራ ቆንጂት ምርኮኛን በማበርከት እክብራለች። በእጅጉ አመሰግናታለሁ።

በምርኮኛ ገጸባህሪያት በነፍሬህይወትና በላይሁን፣ በነወ/ሮ ስርጉት ውስጥ በዚያን ጊዜ የነበሩት ወጣት ወንዶችችና ሴቶች፣ አርጋዊያን እናትና አባቶች ያን የመከራ ጊዜ እንዴት እንዳሳለፉት ቆንጂት ከአንስታይ እይታ አኩዋያ ቁልጭ አድርጋ አሳይታለች። ፍቅርን ብቻ ሰይሆን ትግልንም ከሴት ልጅ ልብ አኩዋያ አብራርታዋለች። ለእንድ ተባእታይ ደራሲ ሊታሰበው ወይም ሊታዬው የማይቻለውን ከናት ጉዋዳና ከእህት መቀነት ጀርባ ያለውን ህይወት ገልጣለች። ምርኮኛው እስካሁን ከተጻፉት ልቦለዶች ልዩ የሚያደርገው ከአንስት አኩዋያ መጸፉ ብቻ ሳይሆን ስሜት የሚኮረኩሩ፣ ትዝታ የሚቀሰቅሱ፣ ቁጭት የሚያባብሱ፣ መሳጭ ገለጣዎችና ጭውውቶች የተሞላ መሆኑም ነው።

ገጽ 205 ላይ ነኝ። እዚህ ገጽ ላይ ያለውን ደብደብ ሳነብ ለምን ያህል ጊዝ እንባዬ ይንጠባጠብ እንደነበር እላወቅሁም። ውስጤን ያመሰው ሃዘንና ቁጭት የቀላቀለ ሃይለኛ ስሜት ለመግለጽ የቆንጅት ተሰጥኦ እንዲኖህ ይጠይቃል። ከዚያ ስሜት ራሴን ማሳረፍ ነበረብኝ። ይህን የምጽፈው በዚያ እረፍት ሰዐት ላይ ነው። መጽሃፍን ስጨርስ አጠቃላይ አስተየየት እሰጠበታለሁ። ጠንካራና ደካማ ጎኑን እዳስሳለሁ። እስከዚያው መጽሃፉን ፈልጋችሁ ብታነቡ፣ ያነበባችሁም ደግሞ ሀሳብ፣ እስተያየት፣ ሂስ ወዘተ ብታካፍሉን ለማለት ነው...

ቆንጅትን በኢሜል አግኝቼአት መጽሃፍዋን አንብቤ ከጨተስኩ በሁዋላ ዋርካ ላይ ከዋርካዊያን ጋር ልንወያይበት ፈቃድዋ እንደሆነ ጠይቄአት የሚከተለውን መልስ ሰጥታኛለች፣

"Konjit Berhan" <merkognakon@gmail.com>

To:
<iandu98@yahoo.com>

Tenayestelegne Stif;

I am glad you started reading my book. Making a tour through the pages you gave me, I can now assume that this book is reaching many critical people. Thank you for introducing me to the forums.

I will be honored to be discussed in your open forum, being sure that you are interested in the literature. I want to grow in the area of literature and have to receive critical feed backs to continue to write.

I am very eager to read your comment.

Sincerely;
Konjit


ኮከብ ተወልዳለች፣ እንድትደምቅ ግን ቀና ብለን እንያት። ኮከብዋ የተጣለባትን፣ "አትርሱን" የሚለውን የዚያን ትውልድ አደራ እንደተወጣች ሁሉ፣ አንባቢያንም ያን ታሪክ በማንበብ (በማወቅ) ያን አደራ መወጣት ይኖርብናል።

መጽሃፍን ያገኘሁት ከአዲስ አበባ እንዲላክልኝ በማድረግ ነው። ዋጋው 54 ብር ብቻ ሲሆን፣ በተራ መልእከት 50 ብር የፖስታ በመክፈል አምስት ቀን ባልሞላ ጊዜ ውስጥ እጄ አስገብቻለሁ። የኢሮፕን አላውቅም አሜሪካ ግን ብዙ ቦታ ሳይሸጥ አይቀርም። በተረፈ የደራሲዋ ሜል ላይ የምታዩት አድራሻ መጽሃፉ ላይ የሰፈረው e-ሜል አድራሻ ነውና እሱን በመጠቀም ከደራሲዋ ጋር መገናኘትና መጽሃፉን ስለምታገኙበት መንገድ መነጋገር ትችላላችሁ ብዬ እገምታለሁ።

ፓስ/ ከአክብሮት ጋር


......
Last edited by password on Sun Feb 20, 2011 10:30 am, edited 6 times in total.
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 330
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Postby ሙዝ1 » Thu Feb 10, 2011 5:07 pm

ሰላም ፓስ! እንደዉ ወጉ አይቅርብኝ ብዬ እንጂ እኔንኩዋን ያንተን ያክል በስነጽሁፍ ፍቅር የናወዝኩ አይደለሁም:: እንደዉ ግን ሁሌም እንደማደርገዉ የስነጽሁፍ ህይወት እንዳይቋረጥ በማለት ፊት ለፊቴ የማገኛቸዉን መጻህፍት እገዛለሁ--:: የደራሲዉን ልፋት ለማክበር::ዋጋቸዉም ርካሽ ስለሆነ:: አሁን አሁን እንደ አሸን እየፈሉ ያሉ የዛ ዘመን ተዋንያን ግለ ታሪክ ለማንበብ ጊዜ በፈቀደ ልክ እሞክራለሁ:: ብዙ በእዉቀት የዳበሩ እንዳሉ ሁሉ የዛኑ ያክልም የዛን ትዉልድ አይነኬ ታሪካዊነት እንደ ታቦት ስገዱለት ብትችሉም ድምጻችሁን ከፍ አድርጋችሁ ዘምሩለት አይነት ጽሁፎች በመጻህፍትም በአጫጭር መጣጥፎችም እያየሁ ከማዘን ያለፈ ምንም ማድረግ አልቻልኩም::

ታሪካዊ ልቦለዶችን ማለቴ አይደለም አይደለም ...!! ታሪካዊ ጽሁፎች ከስሜት በጸዳና በሰከነ የህሊና ፍርድ ላይ ተመስርተዉ ቢጻፉ እንዴት ሸጋ ነበር? አልታደልንም:: አብዛኞቹ ታሪካቸዉ በስሜታዊነት የተቀባ ሆኖ ዛሬም ድረስ ያዉ ስሜታዊነት ከታሪክነት እንዲያልፍና ህያዉ እንዲሆን ግፊት ሲደረግ ስለማይ በዛ ትዉልድ ታሪካዊ ፋይዳ ላይ ከባለቤቶቹ በተጓዳኝ ላለመቆም ምንም መነሻ እያጣሁ ተቸግሪያለሁ::

ለሁሉም ግን እንዲህ አቅልህን ያሳጣህን የቆንጂትን መጻህፍት ለማንበብ ትንሽ ጉጉት አልጨመርክብኝም አልልህም:: ጥሎብኝ ሴቶች ወጋቸዉና ጉያቸዉ ይመቸኛል:: ይሞቀኛል:: አምላክ እነሱን ለኔ እኔንም ለነሱ ብቻ የፈጠረኝ ይመስለኛልና እስኪ አዲስ እይታ አያለሁ በሚል ተስፋ አነበዋለሁ:: ግን ለዉይይት የምታክል ቅንጣትም ያክል የስነጽሁፍ ቴክኒኮችን አላዉቅምና ከማንበብ ባለፈ ተሳታፊህ አልሆንም መሰረታዊ የትዉልድ ጥያቄዎችን ካላነሳህ በቀር::

ሙዘይድ ነኝ ከጫታሙ ትዉልድ
የትዉልድ ዘመን 1968 በሀበሾች አቆጣጠር!!!
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Postby እባካችሁን » Tue Feb 15, 2011 8:41 pm

password- አዲስ መጽህፍ ስላስተዋወከን አመሰግናለሁ:: ሆኖም በአማርኛ ባይተረጎምም በመዓዛ መንግስቴ ለንባብ የቀረበው ባለአራት ክፍል የመጀመሪያ መጽሀፍ Beneath the Lion's Gaze ግሩም ታሪካው ልብ ወለድ ይመስለኛል:: ታሪኩ ኢትዮጵያን መሰረት ያደረገ ቢሆንም እስካሁን ወደአማርኛ አልተተረጎመም። ወደሌሎች የውጪ ቋንቋዎች መተርጎሙን ግን አንብቤያለሁ።
እባክህ እርስዋንም ከሚመሰገኑት ተርታ አስገባልኝ:: ምክንያቱም ካልተሳሳትኩ የዚያን ወቅት ታሪክ በልብወለድ መልክ በእንግሊዘኛ ያቀረበች የመጀመሪያው ጸሀፊ ትመስለኛለች::
እባካችሁን
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 77
Joined: Wed Sep 17, 2008 10:02 pm

Postby password » Wed Feb 16, 2011 3:18 pm

ምርኮኛ
ደረሲ / ቆንጅት ብርሃን
የድርሰት ዓይነት/ ልቦለድ
የገጽ ብዛት/ 491

ገምጋሚ - ፓስወርድ


የአማርኛ ልቦለዶች አንብቤ የረካሁባቸውን ጊዚያት ብዙ ናቸው ማለት ያዳግተኛል። ከዘመናይ መጻህፍት የበዓሉ ኦሮማይና ከአድማስ ባሻገር፣ የተስፋዬ ያልተመለሰው ባቡርና የቡርቃ ዝምታ፣ የሙሉጌታ ጉደታን እንዳይደገምና ጭምብል፣ የብርሃኑ የአብዮት ዋዜማና የአብዮት መባቻ ወዘተ አንቢአቸዋለው። ብዙ የተወራላቸው የይስማቅ ዴርቶጋዳና የእንዳለጌታን ዛጎልም እንብቤአለሁ። አንብቤ ከጨርስኩ በሁዋላ እውስጤ ቀርቶ ያለፍንበትን ታሪክ መለስ ብዬ እንድመለከት፣ የአሁኑን ዝግ ብዬ እንዳጤንና መጻኢ ደሞ ምን ይዞልን ይመጣ ይሆን ብዬ እንዳስብ ያደረገኝ አንድ መጽሃፍ ቢኖር ግን ምርኮኛ ነው።

ምርኮኛን ለመገምገም ያቀድኩበት ምክንያት መጽሃፉ ያነሰው ታሪክ የብዙ ቤተሰብ ታሪክ ስለሆነና ለስነጽሁፉም ከፍተኛ ግምት ስለሰጠሁት ነው። ግምገማውን የማደርገው የፓስዎርድን መነጽር አጥልቄ ስለሆነ ስነጽሁፉን እንጂ ደረሲዋን ለጊዜው አላያትም። ነቀፈና ስህተት ጥቆማ የማይሰማው ሰው የለም፣ ለነገው ስራቸን ጥራት ሲባል ግን ያን መቻል የግድ ይሆናል። ግምገማ በቁንጽል ሲተረጎም እንደምንሰማው ...አድናቆት ሲሆን በከንቱ ውዳሴ ደራሲውን ለመካብ፣ ነቀፋ አዘል ሲሆን ደግሞ ድርሰቱን ለማጣጣል፣ ወይም የደራሲውን የትጋት መንፈስ ለመግደል እንዳልሆነ መታወቅ አለበት። በተጨማሪም ጀማሪ ደራሲያን ከሚያነቡት መጽሀፍ ላይ የአጻጻፍ ስልት ከነ ህጸጹ የመቅዳት ልምድ ሰላላቸው ፍሬውን ከገለባው ለይቶ በማሳየት ጥራት ያለው ስራ እንዲያበረክቱም አስተወስኦ ይኖረዋል።

ምርኮኛ እኔ የኖርኩበትን ማህበረስብና ባህል፣ ወቅትና ሁኔታ የሚተርክ መጽሃፍ ስለሆነም እንደሆን አላውቅም፣ ቁጭትና ሃዘን በተቀላቀለበት መንፈስ ነው አንብቤ የጨረስኩት። እንዲህ ዓይነት መጽሃፍ መገምገም አስቸጋሪ ነው። መቸትና ገጸባህሪያት በሚገባ መቀረጻቸውን፣ ግጭት ተኣማኒ በሆነ ስልት መገለጹን፣ መክረሩና መፈታቱን፣ የትረካ ፍሰቱን ባጠቃላይ ስነጽሁፋዊ ውበቱን ለመገምገም ከታሪኩ ዳር መቆምና ይዘቱን ከውጭ ሆኖ ማየትን ይጠይቃል። ምርኮኛ ሳነብ እውስጡ እዘፈቅ ስለነበር ያን እድል አልሰጠኝም።

ይህ የሆነበት ምክንያት ከስነጽሁፋዊ ውበትና የትረካው አወራረድ ይበልጥ የታሪኩ ጭብጥ እውነት ስለሆነና እኔም እንደ ግለስብ ታሪኩ የሚነካኝ ስለሆነ ይመስለኛል። መቸቱ ቢገለጽ ባይገለጽ፣ ገጸባህሪያቱ ቢሳሉ ባይሳሉም፣ እንቅፈት ተካዩ ቢታወቅ ባይታወቅ ለኔ ያው ነው። በዚህም በዚያም ታሪኩ ደራሲዋ ልታስተላልፈው በፈለገችው መንገድ ይገባኛል፣ ገብቶኛልም። በዚያ ዘመን ያልነበሩ ወይም ታሪኩን በውል ለማያውቁ ሰዎች ወይም መጽሃፉ እንዳለ ለውጭ ሰዎች ተተርጉሞ ቢቀርብላቸው፣ እኔ ላይ የፈጠረውን ዐይነት ስሜት ሊፈጥር የመቻሉን ነገር ሳስበው ግን ታሪኩን በውል ላይረዱትም ይችሉ ይሆናል የሚል ጥርጣሬ ጭምር ይመጣብኛል። ምክንያቱን ሁዋላ በግምገማ እመለስበታለሁ።

ደረሲዋ አንባቢዎችዋን ለይታ በዚያ ዘመን ለነበሩ ሰዎችና የዚያን ዘመን ታሪክ በሚገባ ለሚያውቁ ሰዎች ጽፋው ከሆነ ግን እጅግ የተዋጣለት ልቦልድ ደርሳለች ባይ ነኝ። ለእኒያ ሰዎች መቸቱ፣ ገጽባህሪያቱ፣ ትግሉ ለምን እንደሆነ፣ እንቅፋቶቹ እንማን እንደሆኑ፣ ግጭቱ ምን እንደሆነ የታወቀ ስለሆነ መጽሀፉ ላይ እንዳለው ጨረፍ ማደርግ ብቻ በቂ ሊሆን ይችላል። ግን ለምን? መጽሃፍ ዘመናት ከትውልድ የሚሰግር ቅርስ እንደመሆኑ መጠን የተጠቀሱትን ርእሰ ነገሮች በሚገባና በሚቻል አሙዋልቶ ቢገኝ በአስተማሪነቱና በቅርስነቱ የሚኖረው እሴት ወደር የለውም ፣ በተለይ ለእንደ ምርኮኛ አይነት ታሪካዊ ይዘት ያለው መጽሃፍ።

ደራሲዋን በአካልም ሆነ ከዚህ በፊት በሰራቸው ስራ አላውቃትም። "አንቺ" የምላት በስራዋ ስለወደድኩዋትና የጥበብ ሰው ስለሆነች ብቻ ነው። ትከፋለች የሚል አንዳች ጥርጣሬ የለኝም። ስራዋን በተለያዩ የስነ ጽሁፍ መገምገሚያ ሚዛን ላይ እየሰፈርኩ ጥንካሬና ድክመቱ ለማየት እሞክራልሁ፣

ይቀጥላል
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 330
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Postby password » Wed Feb 16, 2011 3:24 pm

በመችትና ገፀባህሪያት ኣሳሳል እንጀምር።

መቸት
መቸት ታሪኩ የተከወነበት ጊዜና ቦታ ብቻ ሳይሆን በወቅቱ የነበረውን አጠቃላይ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ገጽታ ጭምር ነው። መቸት ከአንድ ገጸበህሪ የሚለይበት ነገር ቢኖር አፍ አውጥቶ ቃላት አለመተነፍሱ ብቻ ነው። በተረፈ በባለታሪኮቹ ላይ ያለው ተጽእኖ ህይወትንና ስነልቦንና ከጊዜ ወደ ጊዜ በመለወጥ አቅሙ እንደ አንድ ገጽባህሪ ይቆጠራል። ስለሆነም በሚገባ መገለጥና መሳል ይኖርበታል። ለታሪኩ ፋይዳ ያለው የህብረተሰቡ ልማድ፣ ፋሽን፣ አስተሳሰብና ርእዮተ ዓለም ወዘተ የመቸቱ አካል ናቸው። በተለይ በማህበረስቡ ላይ ያጠላ አደጋ ወይም የሰፈነ የተስፋ ወይም የስጋት ወይም የውጥረት ድባብ ራሱ የመቸት ዋናው ክፍል መሆኑን መዘንጋት የለብንም።

ከላይ እንድገለጽኩት ወቅቱን ለሚያውቁ አንበቢያን የመቸቱ መገለጽ አለመገለጽ እምብዛም ለውጥ አያመጣም። ስለ ወቅቱ ምንም ግንዛቤ የሌላቸውን አንባቢያን ስሜት ለመያዝ ግን መቸቱን መግለጽ አንድ የልቦለድ ድርሰትን መሳጭና አጉወጊ ከሚያደርጉት ዘዴ አንዱ ነው። በዚህ ረገድ ምርኮኛ የታሪኩን ዘመንና ታሪኩ የተከናወነባቸውን ቦታዎች ገና ከጅማሮው ገልጾአል።

አስረጅ 1. ዕለቱ ሰኞ ጥር 12 ቀን 1967 ዓም ነው። ሁለተኛው የዘማች ቡድን የሚንቀሳቀስበት ቀን። ፍሬህይወት በጠዋት ተነስታ ለጉዞ ተዘጋጀች።

አስረጅ 2. የፖለቲካ ውጥረቱ መንግስትን ፋታ ነሳው። ውጥረቱን ለማስታገስ ማሰነ። ያለተጠበቁ የቤት ለቤት አሰሳዎች በተደጋጋሚ ተካሄዱ። ስጋቱ የጋራ እየሆነ መጣ። ፍሬና አንተነህ መገናኘት የማይችሉባቸው ሁኔታዎች ተፈጠሩ። እያደር ሁኔታዎች እየተባባሱ ይሄዳሉ። በሚዞሩ ታጣቂዎች መገደል የወጣቱ የእለት ተለት ገጠመኝ ሆነ። በዚያው መጠን በህቡዕ በሚታገለው ፓርቲ የሚመቱ የመንገስት ሃይሎች ቁጥርም ተበራከተ። በነጻነት መንቀሳቀስ ትዝታ ሆነ።


ከላይ የተጠቀሰው ማስራጃ መቸቱ በህብረተስብ ላይ "አሁን" የሰፈነውን ድባብ የሚገልጽና ይህም በተራው ገጸባህርያት ላይ የራሱን አዲስ ጫና እንዳሳረፈ የሚያሳይ ነው።

በትረካው ውስጥ የተለየዩ ገጸባህሪያት እንዳሉና ከነዚህም ውስጥ ዋና ገጸባህሪ የምንለው እንዳለ ሁሉ መቸትም ከታሪኩ ሂደት ጋር የሚመጡና የሚሄዱ ከላይ የተጠቀሱትን ዐይነት ንኡስ መቸቶች ሲኖሩት የታሪኩ ዋናው ወይም አጠቃላይ መቸት የምንለው፣ የዘመነ ደርግን መንፈስ የሚያሳይ ስእል አለ። ለምሳሌ ምርኮኛ የሚተርከውን ዘመን ብንወስድ፣ በሀገሪቱ ውስጥ ያለው የፖለቲካና የማህበራዊ ኑሮ ቀውስ፣ ግራ ዘመሙ ርዕዮተ ዐለም፣ የፖለቲካ ሓይላት ፍጥጫ፣ የምሁሩ፣ የወታደሩ፣ የሰራተኛውና የወጣቱ የትግል መንፈስና ሚና ወዘተ በአጣቃላይ በወቅቱ ሰፍኖ የነበረውን አየር (ድባብ) ዋናው መቸት ነው ሊባል ይችላል። ይህን መቸት በአግበቡ አልያ በመጠኑ መግለጽ ያስፈልጋል። በዚህ ረገድ ምርኮኛ ድክመት እንዳለበት መገንዘብ አስቸጋሪ አይደለም።

አገሪቱን የሚያስተዳድረው ሃይል ማን እንደሆነ፣ የአስትዳደር መርሁ ምን እንደሆነ፣ ተማሪዎች ለምን እንደሚዘምቱ፣ ከዘመቱ በሁዋላም ለምን አቁዋርጠው እንደተመለሱ፣ በዘመቻ ላይ እያሉ የመላ ሀገሪቱን ገጽታ የቀየረው የገጠር መሬት የህዝብ እንዲሆን መታወጁና ይህም በገጸባህሪያቱ ላይ የፈጠውረው ጫና፣ በሬዲዮና በቴሌቪዥን በይፋ ይነገሩ የነበሩ ህብረተሰቡን ያስደመሙ የሞት ቅጣቶች፣ ለ17 ዓመታት ሀገሪቱን ደም በደም ያደረገው የደርግ ስርአት አበይት ተግባራትና የመጨረሻ ውድቀቱ በትረካው ውስጥ በጭራሽ አልተነሱም። አብዮት፣ አናርኪስት፣ ንኡስ ከበርቴ፣ ኢምፐሪያሊዝም፣ የመሳፍንት ርዝራዥ፣ መሃል ሰፋሪ ወዘተ የሚሉ በጊዜው በሰፊው ይነሱ የነበሩ፣ ወቅቱንና ድባቡን ሊገልጹ የሚችሉ ቃለቶችን አንድ ቦታ አላነበብኩም። የወቅቱ አሳዛኝ ድራማ ዋና ተዋኒያን የነበሩት ደርግ፣ ኢህአፓና መኢሶን እያንዳዳቸው ስማቸው ከእንድ ጊዜ በላይ አልተጠቀሰም። የመጽሃፉ አቢይ ሴራ ቀይ ሽብር እንኩዋ ቃሉን ከእንዴ በላይ አላየሁትም። በዚህ ምክንያት ስለዚያ ዘመን የማያውቅ አንበቢ በወቅቱ ሰፍኖ የነበርውን አጠቃላይ ሁኔታ በሚገባ ሊያጤን የሚችል አይመስለኝም። ደራሲዋ ይህን ያላደረገችበትን ምክንያት አላውቅም። መጽሃፉ እንደ አንድ ታሪካዊ ልቦለድ የሚመዘንበት መድሎት ላይ ሲወጣ ግን ክብደቱ ዝቅ እንደሚል በእርግጠኝነት መናገር እችላለሁ።

ይቀጥላል
ቀጣዩ ርእስነገር ገጸባህሪያትን የሚመለከት ይሆናል።

ፓስ
/////
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 330
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Postby password » Wed Feb 16, 2011 4:06 pm

እባካችሁን wrote:password- አዲስ መጽህፍ ስላስተዋወከን አመሰግናለሁ:: ሆኖም በአማርኛ ባይተረጎምም በመዓዛ መንግስቴ ለንባብ የቀረበው ባለአራት ክፍል የመጀመሪያ መጽሀፍ Beneath the Lion's Gaze ግሩም ታሪካው ልብ ወለድ ይመስለኛል:: ታሪኩ ኢትዮጵያን መሰረት ያደረገ ቢሆንም እስካሁን ወደአማርኛ አልተተረጎመም። ወደሌሎች የውጪ ቋንቋዎች መተርጎሙን ግን አንብቤያለሁ።
እባክህ እርስዋንም ከሚመሰገኑት ተርታ አስገባልኝ:: ምክንያቱም ካልተሳሳትኩ የዚያን ወቅት ታሪክ በልብወለድ መልክ በእንግሊዘኛ ያቀረበች የመጀመሪያው ጸሀፊ ትመስለኛለች::


ሰላም እባካችሁን

የጠቀሰከው መጽሀፍ ጎግዬ reviewን አይቼለሁ። በአካባቢዬ ካለ እገዛለሁ። ለጥቆማው በጣም አመሰግናለሁ።

http://www.nytimes.com/2010/01/03/books/review/Adams-t.htm
l
ሰላም ሙዝ

ምርኮኛን ካነበብክ በሁዋላ ካንተ ትውልድ አንጻር የተሰማህን ብትገለጽልን ምስጋናችንን አትችለውም። በተረፈ ጫት ስንት ገባ?

ፓስ
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 330
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Postby ሾተል » Wed Feb 16, 2011 4:12 pm

ወዳጄ ፓስ ሰላም ላንተ ይሁን::ከረጅም ጊዜ በሁዋላ ዋርካ ስነጽሁፍ ስምህን ስላየሁት ደስ ብሎኛል::ስምህን ሳይ ዘው ብዬ ብገባ ለረዥም ጊዜ ከስነጽሁፍ ሙድ ወጥቼ የአለም ፖለቲካ ሙድ ውስጥ ገብቼ በዛውም ዋርካ ፖለቲካ ሩም ተዘፍቄ ከብቶች ማርባት በጀመርኩበትና ከስነጽሁፍ ውጭ የሆኑ የአለም ፖለቲካ የዳሰሳቸው እውነቶች ውስጥ ገብቼ ስለዛ ሳነብ ሳይና ስከታተል ባለበት ሰአት ላይ የስነጽሁፍፍ አድባር አለባብሳና አከናንባ ሀይል ሰጥታ እዚህ አምጥታ አንተን ብታሳየኝ እንዴ ለካስ ድሮ ድሮ ስነጽሁፍ ሩም ውስጥ እገባ ነበር መግባት ብቻ ሳይሆን ትንሽ ትንሽ እሳተፍ ነበር ብዬ ሁዋላዬን እንዳይ አደረገኝና ሙዴን ለመመለስ እንደድሮው እንድሆን አንተነትህ አመላከተኝ::

መቼም አገር ቤት ሰዎች ሲሄዱ ሽሮ በርበሬ እንጀራ ያበሻ ልብስና ጌጣጌጥ ሳይሆን አምጡልኝ የምለው ቢችሉ ያገራችን ታሪክ ነክ የሆነ መጽሀፍትን እንዲሁም መጽሄቶችን እንዲያመጡልኝ ስለሆነ የምላመነውና እንዲሁም እንደውለታ ይቆጠርልኝ ዘንድ የሚሰራ ስራም ካላቸው የምሰራው በዛ መሰረት አንድ እህታችን ሰሞኑን አገር ቤት ሄዳ ስለነበር የሆኑ ያሳለፍናቸውን ታሪክ የሚያወሱ የወያኔም ይሁን ኢሀዴግ የደርግም ይሁን የሀይለስላሴ ወይም ከሳቸው በፊት ብቻ ታሪክ ይሁን ያንን የሚነካኩ መጽሀፍቶችን አምጪልኝ ብዬ የመጽሀፍ ዝርዝር ሰጥቻት ሄዳ ብትመጣ ያልኩዋትን ትታ ያላልኩዋትን የተወሰኑ መጽሀፍቶችን ይዛልኝ ከች አለች::ትንሽ ብናደድም እንዲሁም ባገራችን ጸሀፊዎች የሚጻፉ ልብወለድ የፍቅር መጽሀፍቶችን ማንበብ ስለማልፈልግ ቢመጣም ለቤት ጌጥ ይሆናል ብዬ መቀበሌ ባይቀርም ያው ያመጣቻቸውን መጽሀፍቶችን ከኮምፕሌን ጋር አመስግኜ ተቀብዬ ነበር::

ከነሱ ውስጥ አንዱ ምርኮኛ ነው::ሌላው ጽናት ሲሆን ጽናት የሚለውን መጽሀፍ ቶሎ አነበብኩት::ከዛ ሌሎች የውጮቹን ስለፖለቲካ ምናምን የተጻፉ መጽሀፍትን እያነበብኩ ባለበት ሰአት ነው ይኼንን ምርኮኛ የሚሉትን መጽሀፍ እንድናነበው ሬኮማንድ አድርገኸን ጭራሽ እንደምትገመግመው ቃል የገባኽልንና ቃል መግባት ብቻ ሳይሆን ግምገማ የጀመርክልን::ታድያ ይኼንን አይቼ መደርደርያ ላይ በቀጣይነት አነበዋለሁ ብዬ ያስቀመጥኩትን ምርኮኛን እንዴት ስቤ ከ 10 ደቂቃ በፊት አውጥቼ ዛሬውኑ እንድጀምረው እንዳደረከኝ ስነግርኽ ሾተል ለካስ አንዳንዴም ስሜታዊ ነው ሳትለኝ አትቀርም::

በል ባንተ አነሳሽነት መጽሀፉን አሁን ላነበው ነውና አንብቤ ስጨርስ ወይ ሳላመሰግንኽ ወይም ደግሞ ሳልወቅስኽ አይቀርምና ተዘጋጅ....ቅቅቅቅ....ባለፈው ቴርቶጋዳን አዳንቀው አንብበው ብለው አስነብበውኝ እንደተወራለትና እንደተደነቀው ሳይሆን አግኝቼው የዋርካ መሰዳደብያ ጊዜዬን እምሽክ አድርጋችሁ አስበላችሁብኝ ብዬ የወቀስኩዋቸው ሰዎች አሉ::

ይኼ ምርኮኛ የሚሉት መጽሀፍ ግን አንተ እንደጻፍከው አጉዋጊና ያለፈውን ታሪካችንን ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ምርጥ መጽሀፍቶችኽ እንደነ ፍቅር በዘመነ ሽብርና ያ ዘመን አይነት እንደሚሆን ተስፋ በማድረግ ምርኮኛን አነበዋለሁ::

ለዛውም ባንተ የተነሳ ደራሲዋን ሳላደንቃት አላልፍም::ልገመግምሽ ነው...የጻፍሽውን መጽሀፍ በስነጽሁፍ አቡዋራ መትረግያ ብን አድርጌ ጠርጌ ቆሻሻም ካሉት ቆሻሻዎችን ላሳይልሽና ላሳይሽ ነው ስትላት በደስታ በማለትዋ ምንኛ እንዳከብራት ሆኛለሁ::ምናለ የዋርካ ጸሀፊዎች እንደዚች ክብርት እህታችን ሆነው ቢሆን::ዋርካ ስነጽሁፍ እንደዚህ በምች ባልተመታች ነበር::ተገመገምን ብለው ጥርግ ብለው ጠፉ::ውዳሴ ከንቱ የትም ስለማያደርስ ትልቅ ቦታ የሚደርሱ መስሎዋቸው ነበር ውዳሴው ሲጉዋደል ወይም ውዳሴ ባግባቡ ሲባሉ እዩኝ እዩኝ እያሉ እንዳልነበር በየዋሻቸው ተደበቁና አረፉት....ዋርካ ስነጽሁፍም ዳዋ ዋጣት::

አሁን ግን እድሜ ላንተ እንደገና እንደነበረች ትመለሳለች::ጸሀፊ ዋናውም እንደሚመለስ ቃል ገብቷል::ዋናው ከዚች ጸሀፊ ተምሮ ሲገመገም ወይም እዚች ጋር ጥሩ ነኽ እዚች ጋር ደከም አድርገኽ ጽፈኸዋል ሲባል የማንንም ቲፎዞ ሳይፈልግ ለመማማር ግምገማን በጸጋ ተቀብሎ ሊያድግ ቶሎ ቶሎ እንደሚጽፍ ተስፋዬ የጸና ነው::

ይኽንን ካልን በሁዋላ ትገመገም ዘንድ ለፈቀደችልኽ የምርኮኛ ደራሲ ቆንጅት ብርሀን ስራ ማስታወቅያ ይረዳ ዘንድ መጽሀፏን በሰሰአት ለራሴ እያነበብኩ ድምጼን በአውድዮ እየቀረጽኩ መጽሀፉን ለማያገኙ ሰዎች ይረዳ ዘንድና መጽሀፉን ተርኬ ብሎጌ ላይ ከአሁኑ ሰአት ጀምሮ እለጥፈዋለሁ::

እስቲ ከተመቸህ ወደ በሁዋላ አንድ ምእራፍ ከተወጣሁ በሁዋላ ላናግርኽ በምንገናኝበት ቦታ እፈልግሀለሁ::

አክባሪ ወንድምኽ

ሾተል ነኝ.......ምርኮኛ....ደራሲ ከ ቆንጅት ብርሀን::ተራኪ ሾተል...ገምጋሚ ፓስዎርድ.....ምርኮኛ
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9658
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Wed Feb 16, 2011 4:23 pm

ፓስ በዚህ አጋጣሚ ካንተ ግምገማ ብዙ እንደምማር ተስፋዬ የጸና ነው::ብርታቱ ይስጥኽ::

ሾተል ነን
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9658
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby password » Wed Feb 16, 2011 10:37 pm

ሾተል wrote:ፓስ በዚህ አጋጣሚ ካንተ ግምገማ ብዙ እንደምማር ተስፋዬ የጸና ነው::ብርታቱ ይስጥኽ::

ሾተል ነን


ሰላም ሾተል

ምስጋናውን ተቀብያለሁ..... መስመር ላይ ጠብቄህም ነበር ...

ቆንጂት ከሴቶች ማህበር ጋር ያደረገችው ቃለመጠይቅ አግኝቼዋለሁ

እነሆ1.
Konjit Berhan's interview on her book MERKOGNA :

http://www.archive.org/details/KonjitBerhansInterviewOnHerBookMerkogna

2.
Konjit Berhane's interview on her book MERKOGNA,

http://www.archive.org/details/KonjitBerhanesInterviewOnHerBookMerkognaPart2......................
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 330
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Postby early_bird ! » Thu Feb 17, 2011 1:15 am

ውነትም ዋርካ አዚማም ነች ልበል... ? ፓስ ማመን እስኪያቅተኝ ነው ሳይህ ተንደርድሬ የገባሁት..... ዋው :D :D ሌላው የገረመኝ ነገር ምርኮኛ መፃፍ እጀለይ መኖሩ.......ህም.......አንብቤ ሳልጨርስ ግምገማህን አላየውም.........ስጀምረው ብዙም አልሳበኝም ነበር ና በ ዝግታ...ነበር እማየው አሁን ስፒድ ልጨምር ነው.... :lol:
አማን ነህልኝ ግን ?? ሾተላችንስ ሰላም ነውውው ??
“Make the Most of Yourself, For that is all there is of you.”
early_bird !
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 143
Joined: Mon Sep 08, 2008 4:21 pm
Location: Always On The Move.....

Postby sleepless girl » Thu Feb 17, 2011 7:11 pm

የሚገርም ነገር ነው:: አሁን በቅርብ ይህንን መጽሀፍ ፋኬሽን በሄድኩበት ስቴት ደራሲዋን ቆንጂት በአካል ባጋጣሚ አግኝቻት ስለመጽሀፏ ስትናገርና ሌሎችም ያነበቡት ስለመጽሀፏ ሲመሰክሩላት ሰምቼ ወዲያው ነበር መጽሀፉን ገዛሁት:: አጋጣሚውን በመጠቀምም መጽሀፉ ላይ አስፈርሜያታለሁ::
ገምግሞ አስተያየት መስጠት ግን ችሎታውም የለኝም...... አንብቤ ከጨረስኩ በሁዋላ የናንተን ግምገማ አነበዋለሁ::
Nothing is impossible!!
sleepless girl
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1510
Joined: Sun Feb 19, 2006 3:56 am
Location: near u!

Postby password » Thu Feb 17, 2011 7:12 pm

early_bird ! wrote:ውነትም ዋርካ አዚማም ነች ልበል... ? ፓስ ማመን እስኪያቅተኝ ነው ሳይህ ተንደርድሬ የገባሁት..... ዋው :D :D ሌላው የገረመኝ ነገር ምርኮኛ መፃፍ እጀለይ መኖሩ.......ህም.......አንብቤ ሳልጨርስ ግምገማህን አላየውም.........ስጀምረው ብዙም አልሳበኝም ነበር ና በ ዝግታ...ነበር እማየው አሁን ስፒድ ልጨምር ነው.... :lol:
አማን ነህልኝ ግን ?? ሾተላችንስ ሰላም ነውውው ??ወፊቱ

እንዴት ነሽ ... አቤት ስንት ጊዜ ሆነ.... እንኩዋን መጣሽ
አንድ ሄሮን የምትባል ዋርካዊት ጉዋደኛ ነበረችኝ .... ከጠፋች ቆይቶአል እና አንቺም እንደስዋ ጠቅልለሽ የሄድሽ መስሎኝ ነበር.... ብቅ በማለትሽ ደስ ብሎኛል....

ምርኮኛን አንብበሽ ጨርሽና ... እንወያይበታለን...

እስከዚያው ....

-------
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 330
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Postby password » Sat Feb 19, 2011 12:49 am

ምርኮኛ
ደረሲ / ቆንጅት ብርሃን
የድርሰት ዓይነት/ ልቦለድ
የገጽ ብዛት/ 491

ገምጋሚ - ፓስወርድ

ገጸባህሪያት

ልቦለድ ድርሰት በሚገባ የተሳሉ ገጸባህሪያት ከሌሉት ታሪኩ አንባቢን የሚመስጥ ይሆናል ማለት ዘበት ነው። ትረካ ለአንባቢው የሚጥም ብቻ ሳይሆን ደራሲም ሲጽፈው የሃሰብ ፍሰትን ከማፋጠን አልፎ የትረካውን ዋና መስመር እንዳይለቀቅ ገጸባህሪያት ትልቅ ሚና ይጫወታሉ። በደንብ ተስሎ የወጣ ገጸባህሪ በድርሰቱ ላይ ከደራሲው እኩል መብት እስከመያዝ ይደርስና ብእር ለመንጠቅ ሁሉ ይከጅላል። በል የተባለውን የማይል፣ ሂድ እተባለበት የማይሄድ ገጽባህሪ ያጋጥማል። እንዲህ ዓይነት ራሱን የቻለ ገጸባህሪ ሲንሳ የሚገባውን አክብሮት ሳይነፍጉ የገዛ ታሪኩን ራሱ እንዲጽፍ እድል መስጠት የሚሻልበት ጊዜ አለ።

ምርኮኛን ተነባቢ ካደረጉት ምክንያቶች አንዱ ዋናዋ ገጸባህሪ ፍሬህይወትና ቤተሰቦች በቅርበት እንዲታወቁ ሆነው በመቀረጻቸው ነው። ደረሲዋ የምርኮኛን ትረካ በዚህ ቤተሰብ በኩል ለማቅረብ መምረጥዋ ስራዋን የተሳካ አድርጎላታል። የፍሬህይወት ቤተሰብ በኢትዮጵያ በተለይም በዋና መዲናይቱ ብዙዎችን ሊወክል የሚችል መደበኛ ቤተሰብ ነው። የነሱን ኑሮ ሁሉም ይኖረዋል ባይባልም የዚያን ቤተሰብን ኑሮ አይነት የማያውቅ ብዙ ሰው አለ ማለት ያዳግታል። ስለሆነም ገጸባህሪያቱ ጠልቅ ብሎ የመሳሉን ስራ በእጅጉ አቃሎላታል ማለት ይቻላል።

የአንድን ገጸባህሪ የአሁን ማንነትና ምንነት በሚገባ ለመሳል፣ ትረካው ከመጀመሩ በፊት የነበረውን የቤተሰብ ሁኔታ ከመግለጽ የበለጠ ሌላ መንገድ የለም። ደራሲዋም ያደረገችው ይህንኑ ነው።

ቤቴሰቦችዋ በዝቅተኛ የኑሮ እርከን ላይ የሚገኙ ድሆች ናቸው። አባትዋ አናጺ ነበሩ፣ በቀዋሚነት ባይቀጠሩም ስራ ፈትተው አያውቁም። ... በአባትዋ ጥረት ይውተረተር የነበረው የቤተስብዋ የኢኮኖሚ አቁዋም ከሁለት ዐመት በፊት አባትዋ በድንገት ሲሞቱ ተሽመድምዶ ወደቀ። በቤታቸው የሚላስ የሚቀመስ ጠፍቶ በባዶ ሆድ መጠቅለል ሲመጣ ነበር "ትምህርቴን ጨርሼ ... ስራ ይዤ ...ለናቴ" የሚል ምኞትዋን ፈተና የገጠመው። ... የመጀመሪያ ልጅ እንደመሆንዋ አባታቸውን ተክቶ ቤተሰቡዋን መደገፍ የሚችል ከስዋ የተሻለ ትከሻ አልነበረም።
ይህ አግላለጽ የዚያን ቤት ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ፍንትው አድርጎ ከማሳየቱ በተጨማሪ፣ አንበቢ ለፍሬህይወት ሃዘኔታ (sympathy) እንዲኖረው አድርጎአል። ገጸባህሪ የሚወደደ ወይም የሚታዘንለት ሆኖ ሲቀርብ አንባቢው ከዚህ ገጸባህሪ ጋር ሳይወድ ይወግናል። ክፉ እንዳይደርስበት፣ አላማውም እንዲሳካ ይመኛል፣ ብሎም ከችግሩ ወጥቶ እስኪያይ ወይም መጨረሻውን እስኪያውቅ አብሮት ይቆያል።

ገጸባህሪ ሙሉ ሆኖ እዲወጣና አንበቢው በገሃዱ ዓለም የሚያውቀውን ሰው ያህል እንዲያውቀው አካላዊ ቅርጹንና ተክለ ሰውነቱን፣ ማህበራዊ ግንኙነቱንና ስነልቦናዊ አባዜውን መግለጽ የሚያስፈልግበት ጊዜ ይኖራል። ለታሪኩ አስፈላጊ ካልሆነ፣ ወይም የትረካ ፍስትን ጋብ ለማድረግ ካለሆነ የገጸባህሪን አካላዊ ቅርጽዋን ረጅም፣ ቀይ፣ ጸጉረ ዞማ ወዘተ ብሎ መግለጽ ያን ያህል አስፈላጊ አይደለም። በርግጥ ገጸባህሪአችን በባዶ እጁ ሰባት ገድሎ ሰባት የሚማርክ ጀግና ከሆነ አካላዊ ጥንካሬውን የግድ መገልጽ እንዳለበን ሁሉ፣ እንደ በላይሁን ልበሙሉና መንፈሰ ጠንከራ ዓይነቱን ገ/ባ ሲኖር ደግሞ የግድ ስነልቦናዊ ጥንካሬውን መግለጽ ያስፈልጋል። በላይሁን ደርግ ጽ/ቤት በእስር ላይ ሆኖ የምርመራ ሰቆቃ ሲፈራረቅበት እስክ ህይውቱ ህልፈት ማንንም ሳያጋልጥ በጽናት እንደሚቆይ ያወቅነው፣ ቀደም ብሎ፣
"በላይሁን ጠንካራ ልብ እንጅ ጠንካራ ሰውነት የለውም" የሚል ውብ ገለጣ ስላነብብን ነው።

ይቀጥላል
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 330
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Postby password » Sat Feb 19, 2011 1:09 am

የፍሬህይወትን ተከለሰውነት ራሴ የቀረጽኩት ካልሆነ ከድርሰቱ የወሰድኩት ትዝ አይለኝም። ማሀብራዊ ግንኙነትዋንና ስነልቦናዋን በተመለከት ግን በቂ መረጃ አግኝቼአለሁ። ፍሬህይወት ለቤተስቡዋ ያላት ፍቅር...ለሮቤል እንደ እናትም ነች፣ ከጎረቤቶችዋ ጋር ያላት ቅርበት ...ለበላይሁን እንደ እህት ነች፣ ከጉዋደኞችዋ ጋር ያላት ግንኙነት ... ሁሉንም ከልብ ነው የምትወዳቸው፣ በጥሩ ሁኔታ ተገልጾአል። ይህ ማህበራዊ ግንኙነት ባይገለጽ ኖሮ፣ ሁዋላ ቤቴሰቦችዋን፣ ወዳጅዎችዋንና የትግል ጉዋዶችዋን በእስራት፣ በስደትና በሞት አንድ በአንድ ስትነጠቅ ስናይ እንዲያ አንጀታችን አያርም ነበር።

የፍሬህይወት እናት፣ እህትና ሁለት ወንድሞች ትረካው ውስጥ ካላቸው ተራ አንጻር ሲታዩ የተሳሉበት ብቃት አያስከፋም የሚል እምነት አለኝ። ስለሆነም አንባቢው የሁሉንም እንቅስቃሴ እስከ መጨረሻቸው በተመስጦ እንደተከታተለ፣ የተስፋቸውና የፍርሃታቸው፣ የደስታቸውና የሃዘናቸው ተካፈይ ሆኖ እንደዘለቅ እምነቴ ነው።

ከፍሬህይወት ቤተሰብ ውጭ አንተነህ፣ የሚባለው ገፀባህሪም እንደ አንድ ህያው ሰው ከገጽ ገጽ እየዘለለ ሲንቀሳቀስ በመታየቱ ማንነቱን በሚገባ ማወቅ ይቻላል።
"አንተነህ ከቁምነገረቹና ከፖለቲካ ውጭ በጣም ተጫዋችና ቀልድ አዋቂ፣ ርህሩህና ተንከባካቢ ነው። አብረውት ለስራ ለተመደቡት ሁሉ የሚያደርገው እንክብካቤ በቡድን መሪነቱ ያለበትን ሃላፊነት ከመወጣት እኩዋያ ብቻ ሳይሆን ተፈጥሮአዊም ነው። ለሴቶች ልዩ አክብሮት አለው 'አረፍ በሉ ይደክማችሁአል፣ ውሃ ጠጡ ይጠማችሁአል' ከማለት ባሻገር .... እንዲያነቡ ማበረታተት፣ የሚነበቡ መጻህፍት መስጠት፣ በስብሰባ ላይ ያላቸው ተስሳትፎ እንዲጎለብት እደሉን ማመቻቸት የዘወትር ተግባሩ ነው።"
ራፖርታዥ መሰል ቀጥተኛ ገለጻ ቢሆንም አንተነህ ቀንደኛ የኢህአፓ ምልምልና መልማይ መሆኑን የሚያሳይ ነው።

ሌሎቹን ገጽባህሪያት በተመለከተ ባህሪያቸው በተግባራቸውና በጭውውት ማለትም በንግግራቸው የተገለጸበት ስልት መኖሩ እንደተጠበቀ ሆኖ ድክመት ብዬ የምጠቁመው የብዙዎቹ ባህሪ ላይ የሚታየው መመሳሰል ነው። በላይሁን፣ ቅዱስ፣ አስቻለው፣ ዳኙ መሀል የባህሪ ልዩነት እምብዛም የለም። ፈቃደና ታረቀኝም እንዲሁ። ሁሉም ሃቀኞች ናቸው። ብዙዎቹ ፍሬህይወትን በፍቅር ዐይን ያዩዋታል። ሁሉም የዓላማቸው ጽናት ይታይባቸዋል። ከነዚህ ወጣ ያለው የመኢሶን ሰው ነው የሚባለው ዳንኤል ብቻ ነው። ስለ እሱም ቢሆን ከመኢሶንነቱና ፍሬህይወትን ከመሻቱ በቀር ምንም የሚታወቅ ነገር የለም። ዳንኤል ተጻራሪ ገጸባህሪ እንደመሆኑ መጠን ትንሽ መዳበር ነበረበት፣ ቢያንስ ለሞቱ ምክንያት የሆነ ተንኮል ብጤ ነገር ሲሰራ፣ ለምሳሌ ወጣቱ ላይ በመጠቆም ኢህአፓን ሲያስጠቃ ቢታይ።

ገጸባህሪያትን አስመልክቼ የምተቸው ሌላ ነጥብ ቢኖር ፍሬህይወት የተመደበችበት ህዋስ አባላት ስም ነው። የኢፌዴሪ ሚንስትሮች ስም ይመስለል፣ ከየብሄረሰቡ የተውጣጡ ሰዎች ስም። ይህ አስፈላጊ መስሎ አልታየኝም። በዚያን ጊዜ እንዲህ ዓይነት እሳቤ የነበረ አይመስለኝም። ይህ አሁን በአገራችን ያለው ፖለቲካዊ ስርአት ያመነጨው እሳቤ ሊሆን ይችላል። በወቅቱ ኢህአፓ ህዋሳት የብሄረሰብ ስብጥር እንዲኖራቸው የሚጨነቅበት ጉዳይ ካለመሆኑ በተጨማሪ ልጆቹ የመዲናይቱ ታዳጊዎች ስለሆኑ ስማቸው ጋዲሳ ሆነ ዘርዓይ ወይም አስቻለው የብሄረሰብ ማንነትን ከቁብ እንደማይቆጥሩት 99.6 በመቶ እርግጠኛ ሆኜ መናገር እችላለሁ። የዚያን ዘመን ታሪክ ስንጽፍ በዚህኛው ዘመን መንፈስ ሰንበረዝ እንዲሆን መጣር ይኖርብናል። እኩልነት እንደነበር ለመግለጽ በቅንነት የታሰብ እንደሆነ ይገባኛል ግን የብሄረሰብ ጉደይ ያን ያህል ገጦ ባለወጣበት በተለይ በዋና መዲናይቱ ልጆች አካባቢ የማይታወቅና የሌለ ነገርን እንደነበረ አድርጎ ማቅረብ ይሆናል ብዬ ነው።በቀጣዩ ርእሰ ነገር እስክንገናኝ።

ፓስ
////
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 330
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Postby በይሉል » Sat Feb 19, 2011 7:09 am

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን.

ቆንጆ ትምህርት አዘል ነገር ነው ባጋጣሚ እዚህ የማነበው.በርቱ!!!

እኔ ያልገባኝ እና የገረመኝ ካልጠፋ ስም ለምን ''ምርኮኛ"" ብላ ስየመችው?
እኔ መጽሀፉን አላነበብኩትም........ምናልባትም ሳልዘገይ አልቀርም እጄ ለማስገባት....
አሁን ፓስ እንደሚገልጸው ከሆነ ታላቅ ታሪካዊ ድርጊት የተፈጸመበትን ጉዳይ እንደሽንፈት አውርዶ "" ምርኮኛ" ማለቱ ይህም የልብወለድ ምስጢር ይሆንን?? በማለት ጥያቄየን አቀረብኩ.
ሁለተኛው ጥይቄየ ደግሞ ታሪኩ እውን የሆነ የ1960 ወቹ ድርጊት ከሆነ ልብወለድ ማለቱ ትክክል ነው ወይ?

ለመልሳችሁ በቅድሚያ አመሰግናለሁ.

በይሉል........
*The hardest thing about any political campain is how to win without proving that you are unworthy of winning!! E.stevenson

*Even if you win the rat race,you are still a rat!!!
በይሉል
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1075
Joined: Thu Sep 16, 2004 9:30 pm
Location: Beylul-60km North of Assab.

Next

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest