ምርኮኛ - በፓስወርድ መነጽር ስር

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ሾተል » Sat Feb 19, 2011 12:14 pm

በይሉል wrote:ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን.

ቆንጆ ትምህርት አዘል ነገር ነው ባጋጣሚ እዚህ የማነበው.በርቱ!!!

እኔ ያልገባኝ እና የገረመኝ ካልጠፋ ስም ለምን ''ምርኮኛ"" ብላ ስየመችው?
እኔ መጽሀፉን አላነበብኩትም........ምናልባትም ሳልዘገይ አልቀርም እጄ ለማስገባት....
አሁን ፓስ እንደሚገልጸው ከሆነ ታላቅ ታሪካዊ ድርጊት የተፈጸመበትን ጉዳይ እንደሽንፈት አውርዶ "" ምርኮኛ" ማለቱ ይህም የልብወለድ ምስጢር ይሆንን?? በማለት ጥያቄየን አቀረብኩ.
ሁለተኛው ጥይቄየ ደግሞ ታሪኩ እውን የሆነ የ1960 ወቹ ድርጊት ከሆነ ልብወለድ ማለቱ ትክክል ነው ወይ?

ለመልሳችሁ በቅድሚያ አመሰግናለሁ.

በይሉል........

ፈጠነ በባዶ መፍጠንህን ቆም አድርግና ደራሲዋ ለምን ምርኮኛ ብላ መጽሀፍዋን እንደሰየመችው ለማወቅ መጽሀፉን ካለበት ፈልግና እጥብ አድርገኽ በማስተዋል አንብብ::

በእኛ በጣም የማዝነው ሁሉም ፖለቲከኛ ሆኖ ሞተና የፖለቲካን ትርጉም ደግሞ መቃወም ነው ብሎ እራሱን ስላሳመነ ምድረ አዳሜ ሁሉንም መቃወም መቃወም መቃወም...ከወደአፍ ቀደም ከወደደደብነት ፈጠን ሆኖ እንደዚህ ለግምት ይዳረጉልን ገቡ::በይሉል ያ የፖለቲካ ሩም ምች ያጠናገረኽን ባህሪ እዚህ ይዘህ መጥተኽ አትገመት::ስነጽሁፍ አንጎል ይጠይቃል::ፖለቲካ ግን ደደብነት ይበቃዋል::እና አትገመት ያገሬ ልጅ::

በይሉል እንዴው አታፍርም?ላናነበብከው መጽሀፍ የመጽሀፉን ስም አሰጣጥ ሀላፊነቱን ወስደህ ለመከራከር ስትከጅል?

ቆንጅት ብቻ ነች እንዴ እውነት ቀመስ ልብ ወለድ በአገራችን የጻፈችው?እነ ብርሀኑ ዘሪሁን እነ ማእበልን እነ በአሉ ግርማ ኦሮማይን እረ ስንቱ ታሪክ ቀመስ ልብ ወለዶች እኮ ተጽፈዋል::እንዲሁም የዚህ ቤት ባለቤት ደራሲ መኮንን ገብረዝጊ (ፓስዎርድ) እንዲሁ ታሪ ቀመስ ልብ ወለድ ጽፎ አስነብቦ በዛ ዘመን ያልነበርነውን ስለዛ ዘመን አስኮምኩሞናል::መጽሀፎቹን ካላነበብክ "ፍቅር በዘመነ ሽብር" እና "ያ ዘመን" የሚባሉትን መጽሀፍት ከ ፓስዎርድ ጋር በፕራይቬት ተገናኝና ዶላርኽን መዥረጥ አድርገኽ ገዝተኽ አንብብ::

አንድ ደራሲ እውነተኛ ታሪክን ሲያሻው እንደ ተክለጻዲቅ መኩርያ ሲለው እንደ መኮንን ገብረእዝጊ ሆነ በአሉ ግርማ በልብ ወለድ መልክ የመጻፍ መብት አለው::ደራሲ ምንም በስነጽሁፍ ቱልሶች ገደብ ቢደረግም በራሱ እንደፈለገው የመጻፍ መብት በህግም ሆነ በተፈጥሮ ተሰጥቶታል::

ስለዚህ በይሉል ስለማያዋጣኽ ፖለቲካውን ለመደበርያ እንጂ ሲርየስ አድርጎ መያዙን ተወውና ወደ አዋቂዎቹ መንደር ለመቀላቀል ከፖለቲካ ውጭ የሆኑትንም ነገሮች ለማወቅ አንብብ....ከፖለቲካ ውጭ ከሆኑ ሰዎችም ጋር ለመዋል ሞክር::ይኽን ስታደርግ ትቀየራለኽ::

ሌላው የምመክርኽ የማታውቀው ያላየኸው ያልሰማኸው ነገር ከሆነ ለማወቅ ከመጠየቅ በቀር እንደምታውቀው ሆነኽ ለመከራከር ወይም በዛ ላይ ሀሳብ ለመሰንዘር እንዲሁም ለግምገማ እራስኽን ለማስገመት አትስጥ::

ስለዚ ሬኮማንድ የማደርግህ ምርኮኛን አንብብና ያልገባህ ነገር ካለ ጊዜውን ለእኛ ሰውቶ ሊገመግም የጀመረንልን ፓስዎርድን ጠይቀው::ወይም ደራሲዋን በኢሜልዋ ይኼ አልገባኝምና ለምን እንዲህ አልሽው ብለኽ ጠይቅ::

ምክራችንን በክፉ እንደማታየው ተስፋ በማድረግ ካየኸውም በፖለቲከኛነት አይንኽ ስላየኸው ምንም ልረዳኽ ከቶም አልችልም::

በዚህ አጋጣሚ መጽሀፉን አግኝተኽ እስክታነበው ድረስ ወደ በሁዋላ ላይ መጽሀፉን ሳነብ ድምጼን የቀረጽኩትን መቆያ ይሆንኽ ዘንድ እለጥፍልኻለሁ::

ሾተል ነን.....የመጽሀፍ ቂጥ አይተው መጽሀፍ ከሚገመግሙ አድነን::
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9658
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby password » Sat Feb 19, 2011 1:40 pm

ሾተል wrote:

...........በእኛ በጣም የማዝነው ሁሉም ፖለቲከኛ ሆኖ ሞተና የፖለቲካን ትርጉም ደግሞ መቃወም ነው ብሎ እራሱን ስላሳመነ ምድረ አዳሜ ሁሉንም መቃወም መቃወም መቃወም...ከወደአፍ ቀደም ከወደደደብነት ፈጠን ሆኖ እንደዚህ ለግምት ይዳረጉልን ገቡ::........

መጽሀፎቹን ካላነበብክ "ፍቅር በዘመነ ሽብር" እና "ያ ዘመን" የሚባሉትን መጽሀፍት ከፓስዎርድ ጋር በፕራይቬት ተገናኝና ዶላርኽን መዥረጥ አድርገኽ ገዝተኽ አንብብ::

ሾተል ነን.....የመጽሀፍ ቂጥ አይተው መጽሀፍ ከሚገመግሙ አድነን::

ሰላም ሾተል

ከላይ የጠቀስካቸው "ፍቅር በዘመነ ሽብር " እና "ያ ዘመን ] የሚባሉትን መጽሀፍት ስቲፍሀብ መጻህፍት ክበብ ድረገጽ ዘንድ በመሄድ በነጻ መጫን ይቻላል...

http://babile.webs.com

http://babile.webs.com/WEBPROTECT-ebooksinpdf.htm

መጻህፍቱ በገበያ ላይ ስለሌሉ ሁለቱም በPDF እንዲወጡ ከተደረገ ቆይተዋል...
አንባቢው የሚፈለግበት ነገር ቢኖር የክበቡ አባል መሆን ብቻ ነው...
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 330
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Postby ሾተል » Sat Feb 19, 2011 4:59 pm

ሰላም ፓስ እንዲሁም ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን:: የቆንጅት ብርሀን መጽሀፍ ምርኮኛ በእጃችሁ ያልገባና እስኪገባ ድረስ በአውድዮም ቢሆን ለማዳመጥ የጉዋጉዋችሁ የስነጽሁፍ ወዳጆች እነሆ በገባንላችሁ ቃል መሰረት ያቅማችንን አንብበን ድምጻችነን ለታሪክ ቀርጸን ልናቀርብላችሁ ጀምረናልና እንደ ፍላጎታችሁ ከታች ያለውን ተጭናችሁ ምርኮኛን በማዳመጥ ፓስ ወንድማችን በጀመረው ግምገማ መሰረት እናንተን ያቅማችሁን በግምገማው ተሳተፉ::

ምርኮኛን ለማዳመጥ ይኼንን ይጫኑ::

ፓስ በጀመረው ብእርኽ የኛንም አነባበብና ኢዲቲንግ ገረፍ አድርግልን::

ካክብሮት ጋር

ሾተል ነን...ምርኮኛ...ደራሲ በቆንጅት ብርሀን...ተራኪ ሾተል...ገምጋሚ ፓስዎርድ...ምርኮኛ
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9658
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby በይሉል » Sun Feb 20, 2011 1:47 am

በይሉል wrote:ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን.

ቆንጆ ትምህርት አዘል ነገር ነው ባጋጣሚ እዚህ የማነበው.በርቱ!!!

እኔ ያልገባኝ እና የገረመኝ ካልጠፋ ስም ለምን ''ምርኮኛ"" ብላ ስየመችው?
እኔ መጽሀፉን አላነበብኩትም........ምናልባትም ሳልዘገይ አልቀርም እጄ ለማስገባት....
አሁን ፓስ እንደሚገልጸው ከሆነ ታላቅ ታሪካዊ ድርጊት የተፈጸመበትን ጉዳይ እንደሽንፈት አውርዶ "" ምርኮኛ" ማለቱ ይህም የልብወለድ ምስጢር ይሆንን?? በማለት ጥያቄየን አቀረብኩ.
ሁለተኛው ጥይቄየ ደግሞ ታሪኩ እውን የሆነ የ1960 ወቹ ድርጊት ከሆነ ልብወለድ ማለቱ ትክክል ነው ወይ?

ለመልሳችሁ በቅድሚያ አመሰግናለሁ.

በይሉል........

ሰላም ለፓስ

1. ጥያቄ ማለት መልስ የሚፈልጉ አረፍተነገሮች ማለት ነው!!!
የኔ አረፍተነገሮች ጥያቄወች እንጂ ግምገማ ወይም የግምገማ ሀሳቦች አያንጸባርቁም.መጽሀፉንም ለመገምገምም አልተነሳሁም. ባልተሳሁበት ጉዳይ ላይ ተምርኩዞ አስተያየት መስጠት ቢያንስ ችኩልነት አለበልዚያም አሉባልታ ነው የሚሆነው.ስለዚህ ለግምገማየ ሳይሆን ለጥያቄየ መልስ ከሰጠህ ስጥ!!! ካልሰጠህም ተወው.
ጥያቄወቼ የተነተራሱት ደግሞ ያንተን ሀተታ መሰረት አድርገው ስለሆነ ስለመጽሀፉ ትክክለኛም ይሁን ስህተተኛ አንደምታ ብትፈጥር ተጠያቂው እራስህ ነህ!! ፓስ!!

2.ለተራኪው-----የዚያ ትውልድ አካላት እና አባላት ይህን መጽሀፍ አንተ ስትተርከው ቢያውቁ /ቢያዩ ተመልሰው ወደመቃብራቸው ይወርዳሉ. ደራሲዋም ስለአንተ ማንነት ብታውቅ በወንጀል ትከስሀለች. እስካሁንም አንዱ ሳይጠቁማት አይቀርም.ምክንያቱም ያንን መጻህፍ አንተ አፍህን እንድትከፍትበት አይፈቀድልህም.
ምርኮኛ የአንተ እና የምታገለግለው ወያኔ ቀንደኛ ጠላቶች ናቸው...ስለዚህ የወያኔ ሎሌ በምን ተአምር የምርኮኛ ተራኪ ሆነ??? እርስዋ መልስ የምትሰጥህ ይመስለኛል.ያንን እንጠብቅ!!
*The hardest thing about any political campain is how to win without proving that you are unworthy of winning!! E.stevenson

*Even if you win the rat race,you are still a rat!!!
በይሉል
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1075
Joined: Thu Sep 16, 2004 9:30 pm
Location: Beylul-60km North of Assab.

Postby ሾተል » Sun Feb 20, 2011 2:13 am

በይሉል....አንጎልህን በመምታት እራስህን ማሳወቄን እንደዚህ አላወቅኩትም ነበር.....ለካስ ማሰብያህን እንጉልፋቶ አድርጌዋለሁ?ሞራልህና ነርቭህ ላይ ለካስ ጥባ ጥቤና ዳማ ተጫውቼበታለሁ::ይመቸኝ::ምን ላድርግ እራቁትህን አግኝቼህ ልብስ ላለብስህ ስለፈለኩ ነው::እዚህ ስነጽሁፍ ሜዳ ስትመጣ በተቻለህ መጠን ከብትነትህን አውልቀኽ ለመምጣት ሞክር::እዚህ የእኛ የአዋቂዎች የባለ ተሰጥኦዎች የባለ በሳሎችና የአዋቂዎች መንደር ነው::ፖለቲካ የናንተ ሩም ደግምሞ የከብትና ---- መሰባሰብያ ስለሆነ እዚህ ስትመጣ በተቻለህ መጠን ከእኛ ከ ጠቢባኖቹ ለመማር ምጣ::

ስለትረካውና ደራሲዋ ያልከው እስቲ ሌት ሚ ሲ ዩ ሀው ፋር ዩ ካን ጎ.....እስቲ 5000 ፊርማ አሰባስበህ እኔን ለማስከሰስ ፔቴሽን ፈርሙልኝ በል::

ደራሲዋ ሁለመናዬን ታውቀዋለች እንዲሁም መጽሀፍዋን እንድተርክላት ፈቅዳልኝ ነው ብልኽ ያ ያደደበህን ፖለቲካ ትተህ እንደሰው ለማወቅ ከዛሬ ጀምሮ ከአዋቂዎች ከእኛ ለመማር እመጣለሁ ትለኛለህ?ቃል ግባልኝ እስቲ....ቃል ይጠርህና::

ውይ ግን የሚገባህ ነገር ስላልሆንክና የመጽሀፍ አርስት አይተህ ለመገምገም የተነሳህ ሉዘር ስለሆንክ አንተን በእውቀት ውቅያኖስ ቢዘፍቁህ የማትርስ ነገር ስለምትመስል አንተን ማስተማሩ ትንሽ የሚከብድ ይመስላልና እንግዲህ እኛ ኢንቴሌክቹዋሎቹ ሬድ ቡል በመጠጣት ኢነርጂ ካሁኑ ላንተ ስንል እንናሰባስብ መሰል::

ድሮም አመጣጥህ ገብቶኝ ነበር ያው ያ የከረፋው ፖለቲካህን አቀረሸኽ::ወያኔ ወያኔ እንድልክ ትሞታለኽ...ዘር ማንዘርህም አገር ቤት ከእኔ ዘር ማንዘር ጀምሮ በወያኔ ይገዛሉ::ወደድክም ጠላህም::አንተ ስታለቅስ እድሜህ ሲያጥር እኛ ስነጽሁፍ ሩም ስለኢትዮዽያ ስነጽሁፍ እድገት ስንወያይ እኛ ኖረን አንተ ደግሞ ተኖረና ተሞተ ሆነን ጊዜያችን ሲደርስ ፍግም እንላለን::

ዌል ካም

ሾተል ነን.....እራሳቸውን ሰዎች ሲረሱ ---- ናችሁ እንላለን ስንል በይሉልን አላልነውም ለማለት አይደለም::
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9658
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby password » Sun Feb 20, 2011 3:50 pm

በይሉል wrote:
ሰላም ለፓስ

1. ጥያቄ ማለት መልስ የሚፈልጉ አረፍተነገሮች ማለት ነው!!!
የኔ አረፍተነገሮች ጥያቄወች እንጂ ግምገማ ወይም የግምገማ ሀሳቦች አያንጸባርቁም.መጽሀፉንም ለመገምገምም አልተነሳሁም. ባልተሳሁበት ጉዳይ ላይ ተምርኩዞ አስተያየት መስጠት ቢያንስ ችኩልነት አለበልዚያም አሉባልታ ነው የሚሆነው.ስለዚህ ለግምገማየ ሳይሆን ለጥያቄየ መልስ ከሰጠህ ስጥ!!! ካልሰጠህም ተወው.
ጥያቄወቼ የተነተራሱት ደግሞ ያንተን ሀተታ መሰረት አድርገው ስለሆነ ስለመጽሀፉ ትክክለኛም ይሁን ስህተተኛ አንደምታ ብትፈጥር ተጠያቂው እራስህ ነህ!! ፓስ!!
!

ሰላም በይሉል

ጥያቄዎቼ... ላልካቸው ነገሮች የትም ቦታ መልስ አልሰጠሁም ...
መልስ ሳልሰጥህ መለስክልኝ ማለትህ እንዳንተ አባባል ችኩልነት ሊሆን ይችላል አሉባልታ ግን አይመስለኝም ...

በተረፈ ጥያቄዎችህ በዚህ ግምገማ ሊዳሰሱ ስለሚችሉ እስኪያልቅ ተከታተል , አልያ መጽሃፉን በማንበብ ልትረዳ ትችላልህ ብዬ እገምታለሁ ....

አክብሮት ሳላጓድል ነው .....

ፓስ
......
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 330
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Postby በይሉል » Sun Feb 20, 2011 7:46 pm

ሾተል wrote:በይሉል
ሰላም ለፓስ

1. ጥያቄ ማለት መልስ የሚፈልጉ አረፍተነገሮች ማለት ነው!!!
የኔ አረፍተነገሮች ጥያቄወች እንጂ ግምገማ ወይም የግምገማ ሀሳቦች አያንጸባርቁም.መጽሀፉንም ለመገምገምም አልተነሳሁም. ባልተሳሁበት ጉዳይ ላይ ተምርኩዞ አስተያየት መስጠት ቢያንስ ችኩልነት አለበልዚያም አሉባልታ ነው የሚሆነው.ስለዚህ ለግምገማየ ሳይሆን ለጥያቄየ መልስ ከሰጠህ ስጥ!!! ካልሰጠህም ተወው.
ጥያቄወቼ የተነተራሱት ደግሞ ያንተን ሀተታ መሰረት አድርገው ስለሆነ ስለመጽሀፉ ትክክለኛም ይሁን ስህተተኛ አንደምታ ብትፈጥር ተጠያቂው እራስህ ነህ!! ፓስ!!

2.ለተራኪው-----የዚያ ትውልድ አካላት እና አባላት ይህን መጽሀፍ አንተ ስትተርከው ቢያውቁ /ቢያዩ ተመልሰው ወደመቃብራቸው ይወርዳሉ. ደራሲዋም ስለአንተ ማንነት ብታውቅ በወንጀል ትከስሀለች. እስካሁንም አንዱ ሳይጠቁማት አይቀርም.ምክንያቱም ያንን መጻህፍ አንተ አፍህን እንድትከፍትበት አይፈቀድልህም.
ምርኮኛ የአንተ እና የምታገለግለው ወያኔ ቀንደኛ ጠላቶች ናቸው...ስለዚህ የወያኔ ሎሌ በምን ተአምር የምርኮኛ ተራኪ ሆነ??? እርስዋ መልስ የምትሰጥህ ይመስለኛል.ያንን እንጠብቅ!!

በይሉል....አንጎልህን በመምታት እራስህን ማሳወቄን እንደዚህ አላወቅኩትም ነበር.....ለካስ ማሰብያህን እንጉልፋቶ አድርጌዋለሁ?ሞራልህና ነርቭህ ላይ ለካስ ጥባ ጥቤና ዳማ ተጫውቼበታለሁ::ይመቸኝ::ምን ላድርግ እራቁትህን አግኝቼህ ልብስ ላለብስህ ስለፈለኩ ነው::እዚህ ስነጽሁፍ ሜዳ ስትመጣ በተቻለህ መጠን ከብትነትህን አውልቀኽ ለመምጣት ሞክር::እዚህ የእኛ የአዋቂዎች የባለ ተሰጥኦዎች የባለ በሳሎችና የአዋቂዎች መንደር ነው::ፖለቲካ የናንተ ሩም ደግምሞ የከብትና ---- መሰባሰብያ ስለሆነ እዚህ ስትመጣ በተቻለህ መጠን ከእኛ ከ ጠቢባኖቹ ለመማር ምጣ::

ስለትረካውና ደራሲዋ ያልከው እስቲ ሌት ሚ ሲ ዩ ሀው ፋር ዩ ካን ጎ.....እስቲ 5000 ፊርማ አሰባስበህ እኔን ለማስከሰስ ፔቴሽን ፈርሙልኝ በል::

ደራሲዋ ሁለመናዬን ታውቀዋለች እንዲሁም መጽሀፍዋን እንድተርክላት ፈቅዳልኝ ነው ብልኽ ያ ያደደበህን ፖለቲካ ትተህ እንደሰው ለማወቅ ከዛሬ ጀምሮ ከአዋቂዎች ከእኛ ለመማር እመጣለሁ ትለኛለህ?ቃል ግባልኝ እስቲ....ቃል ይጠርህና::

ውይ ግን የሚገባህ ነገር ስላልሆንክና የመጽሀፍ አርስት አይተህ ለመገምገም የተነሳህ ሉዘር ስለሆንክ አንተን በእውቀት ውቅያኖስ ቢዘፍቁህ የማትርስ ነገር ስለምትመስል አንተን ማስተማሩ ትንሽ የሚከብድ ይመስላልና እንግዲህ እኛ ኢንቴሌክቹዋሎቹ ሬድ ቡል በመጠጣት ኢነርጂ ካሁኑ ላንተ ስንል እንናሰባስብ መሰል::

ድሮም አመጣጥህ ገብቶኝ ነበር ያው ያ የከረፋው ፖለቲካህን አቀረሸኽ::ወያኔ ወያኔ እንድልክ ትሞታለኽ...ዘር ማንዘርህም አገር ቤት ከእኔ ዘር ማንዘር ጀምሮ በወያኔ ይገዛሉ::ወደድክም ጠላህም::አንተ ስታለቅስ እድሜህ ሲያጥር እኛ ስነጽሁፍ ሩም ስለኢትዮዽያ ስነጽሁፍ እድገት ስንወያይ እኛ ኖረን አንተ ደግሞ ተኖረና ተሞተ ሆነን ጊዜያችን ሲደርስ ፍግም እንላለን::

ዌል ካም

ሾተል ነን.....እራሳቸውን ሰዎች ሲረሱ ---- ናችሁ እንላለን ስንል በይሉልን አላልነውም ለማለት አይደለም::የማይማኖች ድፍረት!!!!!አለማወቅህን ማመን ያቃተህ የዋርካ ታላቁ ጂል!!!

በአንተ አፍ ምርኮኛ ሲተረክ እና በአንተ ጠማማ-ወያኔያዊ
እይታ ሲገመገም እንዴት ያቅለሸልሻል!!!

ባለጌ ነህ.....ይህን ድፍረትህን ደግሞ እንደአይነተኛ መሳርያ በመጠቀም እንደንቁራሪት ራስህን ልታሳብጥ ትሞክራለህ.
*The hardest thing about any political campain is how to win without proving that you are unworthy of winning!! E.stevenson

*Even if you win the rat race,you are still a rat!!!
በይሉል
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1075
Joined: Thu Sep 16, 2004 9:30 pm
Location: Beylul-60km North of Assab.

Postby በይሉል » Sun Feb 20, 2011 7:58 pm

password wrote:
በይሉል wrote:
ሰላም ለፓስ

1. ጥያቄ ማለት መልስ የሚፈልጉ አረፍተነገሮች ማለት ነው!!!
የኔ አረፍተነገሮች ጥያቄወች እንጂ ግምገማ ወይም የግምገማ ሀሳቦች አያንጸባርቁም.መጽሀፉንም ለመገምገምም አልተነሳሁም. ባልተሳሁበት ጉዳይ ላይ ተምርኩዞ አስተያየት መስጠት ቢያንስ ችኩልነት አለበልዚያም አሉባልታ ነው የሚሆነው.ስለዚህ ለግምገማየ ሳይሆን ለጥያቄየ መልስ ከሰጠህ ስጥ!!! ካልሰጠህም ተወው.
ጥያቄወቼ የተነተራሱት ደግሞ ያንተን ሀተታ መሰረት አድርገው ስለሆነ ስለመጽሀፉ ትክክለኛም ይሁን ስህተተኛ አንደምታ ብትፈጥር ተጠያቂው እራስህ ነህ!! ፓስ!!
!

ሰላም በይሉል....ጥያቄዎቼ... ላልካቸው ነገሮች የትም ቦታ መልስ አልሰጠሁም ...በቀይ ያቀለምከው ምንድን ነው? መልስ ነው እኮ.አግባብ ያልሆነ መልስ በመስጠት መድረክን አበላሸከው!!! ፓስ እንደዚህ አይነት ገምጋሚ ነው ወይስ ተገምጋሚ ብያለሁ!!!!መልስ ሳልሰጥህ መለስክልኝ ማለትህ እንዳንተ አባባል ችኩልነት ሊሆን ይችላል አሉባልታ ግን አይመስለኝም ...

ከአሉባልታም በላይ ለአሉባልተኛ አሳልፈህ ሰጥተከኛል.
ለግመገማ ስንነሳ ግራ ና ቀኙን ሚዛናዊ በሆነ መንገድ ልንቃኝ ነው ማለት ነው. ንጹህ ልብ እና ንጹህ አይን ይዘን ስንገመግም እኛም ተገምጋሚወች መሆናችንን አትርሳ!!!

በተረፈ ጥያቄዎችህ በዚህ ግምገማ ሊዳሰሱ ስለሚችሉ እስኪያልቅ ተከታተል , አልያ መጽሃፉን በማንበብ ልትረዳ ትችላልህ ብዬ እገምታለሁ ....

መነሻየም ሆነ መድረሻየ ያንተው የግም-ገማ ሀተታ ስለሆነ ለሚቀርቡልህ ጥያቄወች ተገቢዉን መልስ መስጠት አለብህ.ጉዋደኝነት እና እከክኝ ልከክልህ!!!! በለው..ፍለጠው ቁረጠው ግምገማ ላይ አይሰራም.በጉዋደኝነትም ጊዜያዊ ቲፎዞ ፍለጋ ያን ያህል ቀይ አቅልመህ መጉዋዝህ ሰበናህን ብቻ ሳይሆን የግምገማ ጥበብህን ልክ-ዳርቻ እንድጠራጠርወ አድርጎኛል.

አክብሮት ሳላጓድል ነው .....

ዋርካ ላይ እንዲህ አይነት ባህል የለንም!!!!!ከሰላምታ ጋር.
*The hardest thing about any political campain is how to win without proving that you are unworthy of winning!! E.stevenson

*Even if you win the rat race,you are still a rat!!!
በይሉል
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1075
Joined: Thu Sep 16, 2004 9:30 pm
Location: Beylul-60km North of Assab.

Postby password » Mon Feb 21, 2011 1:35 am

በይሉል wrote:
password wrote:
በይሉል wrote:
ሰላም ለፓስ.........................
....................................

......................መነሻየም ሆነ መድረሻየ ያንተው የግም-ገማ ሀተታ ስለሆነ ለሚቀርቡልህ ጥያቄወች ተገቢዉን መልስ መስጠት አለብህ.ጉዋደኝነት እና እከክኝ ልከክልህ!!!! በለው..ፍለጠው ቁረጠው ግምገማ ላይ አይሰራም.በጉዋደኝነትም ጊዜያዊ ቲፎዞ ፍለጋ ያን ያህል ቀይ አቅልመህ መጉዋዝህ ሰበናህን ብቻ ሳይሆን የግምገማ ጥበብህን ልክ-ዳርቻ እንድጠራጠርወ አድርጎኛል.

አክብሮት ሳላጓድል ነው .....

ዋርካ ላይ እንዲህ አይነት ባህል የለንም!!!!!

ከሰላምታ ጋር.

በይሉል

የፈጠራ ድርሰት ስንገመግም ገጸባህሪያት እንዴት እንደተሳሉ እንመረምራለን.... መሳል (characterazation) ማለት ገጸባህሪ ለአንባቢው ምን ያህል እንዲታወቅ ሆነ ማለት ነው... ታዲያ ደራሲያን አንድ ገጸባህሪ ውሸታም መሆኑን አንባቢው እንዲያውቅ ሲፈልጉ በቀጥታ ""በይሉል ውሸታም ነው"" ከማለት ... በተዘዋዋሪ ከአፉ በሚወጣው ቃል (dialogue) ይጠቀማሉ..... ገጻባህሪ በሚናገረው ይበልጥ ደግሞ በሚጽፈው ቃላት ከዚያም ባለፈ በሚስለው ስእል ራሱን ይገልጣል..... ያስተዋውቃል.... በጥቂት ቃላት አንድ ሰው ምን ያህል እንደተማረ ... የት እንዳደገ .... ምን አይነት እምነት እንዳለውና ስነልቡናዊ አባዜው ምን እንደሆነ ማወቅ ይቻላል...

ምሳሌ

የት/ቤት ክፍል ውስጥ የተገለለ መስሎ የሚሰማው ተማሪ ... ከአንዱ ጋር ሲጣላ የክፍሉን ልጆች በሙሉን ጠቅልሎ የመሳደብ አባዜ ይታይበታል...

ዋርካን ወይም ዋርካዊያንን በሙሉ ጠቅልሎ የሚሳደብ ሰው የዝቅተኝነት ስሜት (inferiority complex) እንደሚያጠቃው 99.6 በመቶ እርግጠኛ ሆኜ መናገር እችላለሁ..... የችግሩ መንስኤዎች ብዙ ናቸው ... መፍትሄው ግን አንድ ነው... ወደ ልጅነት ዘመን ምናባዊ ጉዙ ማድረግና በመልከ ጥፉነትህ ወይም በከሲታነትህ,... በአነጋገርህ ኮልታፋነት ወይም በአካሄድህ ወልጋዳነት... በውራጅ ልብሶችህ ወይም በድሆች ቤተሰቦችህ እንዲሁም በጎጥህና በጎሳህ ምክንያት የተሰደብክባቻውን... የተዋረድክባቸውን የተሳቀብህን... ክፉ ጊዚያት ደጋግመህ ማጤንና ከንቱ እንደነበሩ ከራስህ ጋር መወያየት ነው... ባጭሩ

አይ ካልክ ግን እኔ በዚሁ አበቃና ደህና አድርገው ለሚያስቁህ ... እተውሃለው......

ፓስ
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 330
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Postby በይሉል » Mon Feb 21, 2011 3:10 am

password wrote:
በይሉል wrote:
password wrote:
በይሉል wrote:
ሰላም ለፓስ.........................
....................................

......................መነሻየም ሆነ መድረሻየ ያንተው የግም-ገማ ሀተታ ስለሆነ ለሚቀርቡልህ ጥያቄወች ተገቢዉን መልስ መስጠት አለብህ.ጉዋደኝነት እና እከክኝ ልከክልህ!!!! በለው..ፍለጠው ቁረጠው ግምገማ ላይ አይሰራም.በጉዋደኝነትም ጊዜያዊ ቲፎዞ ፍለጋ ያን ያህል ቀይ አቅልመህ መጉዋዝህ ሰበናህን ብቻ ሳይሆን የግምገማ ጥበብህን ልክ-ዳርቻ እንድጠራጠርወ አድርጎኛል.

አክብሮት ሳላጓድል ነው .....

ዋርካ ላይ እንዲህ አይነት ባህል የለንም!!!!!

ከሰላምታ ጋር.

በይሉል

የፈጠራ ድርሰት ስንገመግም ገጸባህሪያት እንዴት እንደተሳሉ እንመረምራለን.... መሳል (characterazation) ማለት ገጸባህሪ ለአንባቢው ምን ያህል እንዲታወቅ ሆነ ማለት ነው... [color=red]ታዲያ ደራሲያን አንድ ገጸባህሪ ውሸታም መሆኑን አንባቢው እንዲያውቅ ሲፈልጉ በቀጥታ ""በይሉል ውሸታም ነው""
ከማለት ... በተዘዋዋሪ ከአፉ በሚወጣው ቃል (dialogue) ይጠቀማሉ..... ገጻባህሪ በሚናገረው ይበልጥ ደግሞ በሚጽፈው ቃላት ከዚያም ባለፈ በሚስለው ስእል ራሱን ይገልጣል..... ያስተዋውቃል.... በጥቂት ቃላት አንድ ሰው ምን ያህል እንደተማረ ... የት እንዳደገ .... ምን አይነት እምነት እንዳለውና ስነልቡናዊ አባዜው ምን እንደሆነ ማወቅ ይቻላል...

ምሳሌ

የት/ቤት ክፍል ውስጥ የተገለለ መስሎ የሚሰማው ተማሪ ... ከአንዱ ጋር ሲጣላ የክፍሉን ልጆች በሙሉን ጠቅልሎ የመሳደብ አባዜ ይታይበታል...

ዋርካን ወይም ዋርካዊያንን በሙሉ ጠቅልሎ የሚሳደብ ሰው የዝቅተኝነት ስሜት (inferiority complex) እንደሚያጠቃው 99.6 በመቶ እርግጠኛ ሆኜ መናገር እችላለሁ..... የችግሩ መንስኤዎች ብዙ ናቸው ... መፍትሄው ግን አንድ ነው... ወደ ልጅነት ዘመን ምናባዊ ጉዙ ማድረግና በመልከ ጥፉነትህ ወይም በከሲታነትህ,... በአነጋገርህ ኮልታፋነት ወይም በአካሄድህ ወልጋዳነት... በውራጅ ልብሶችህ ወይም በድሆች ቤተሰቦችህ እንዲሁም በጎጥህና በጎሳህ ምክንያት የተሰደብክባቻውን... የተዋረድክባቸውን የተሳቀብህን... ክፉ ጊዚያት ደጋግመህ ማጤንና ከንቱ እንደነበሩ ከራስህ ጋር መወያየት ነው... ባጭሩ

አይ ካልክ ግን እኔ በዚሁ አበቃና ደህና አድርገው ለሚያስቁህ ... እተውሃለው......

ፓስ [/color]

እንዲህ አይነቱ ጭንቅላት ምርኮኛን ሲገመግም ከማይ ዋርካ ጋር በፈቃዴ የገባሁትን ኮንትራት ጨርቼ ዘወር ማለቱ ይሻላል.

ውሾቼን እለቅብሀለሁ ማለትህ በጣም አስቆኛል.ቀላል ነገር ነህ.
*The hardest thing about any political campain is how to win without proving that you are unworthy of winning!! E.stevenson

*Even if you win the rat race,you are still a rat!!!
በይሉል
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1075
Joined: Thu Sep 16, 2004 9:30 pm
Location: Beylul-60km North of Assab.

Postby password » Sat Feb 26, 2011 2:39 pm

ታሪክን ... ከታሪካዊ ልቦለድ

በአገራችን የትምህርት ካሪኩለም የኢትዮጵያ ታሪክ እንደ አንድ 'ሰብጀክት ' ስለማይሰጥ እንደኔ የአገራችንን ታሪክ ሳያውቅ ሁለተኛ ደርጃ ትምህርቱ አጠናቅቆ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ቤት ወይም ወደ ስራ አለም የገባው ሰው ብዛት በሚሊዮን ይቆጠራል ብዬ እገምታለሁ። የአገሪቱ ታላላቅ ቅርሶችና እሴቶች፣ የህዝቧን አመጣጥና አሰፋፈር፣ ስለየብሄሬሰቡ ባህልና ቁዋንቁዋ ምናልባት በግሉ ያነበብ ካልሆነ በትምህርት ቤት የተማረ ሰው መኖሩን ኣላውቅም። ሰፊው የቀድሞውና የአሁኑ ተማሪ ከሃገሩን ታሪክ ይበልጥ ስለውጩ ነው የሚያውቀው። ቀዳማዊ ሃይለ ስላሴ ዘውድ ከጫኑበት ጊዜ ወዲህ ስላለው ዘመናይ ታሪክ እንኩዋ በውል የምናውቅ ብዙዎች አይደለንም። ይህ ሁኔታ በእጅጉ አስከፍሎናል ብዬ አምናለሁ። በኛ ትውልድ ላይ አሁን የሚታየው የአለመግባባትና የመወነጃጀል፣ የትንንቅና የመጠፋፋት ችግር አንዱ ምክንያት ይኽው ታሪክን በቅጡ አለማወቃችን እንድሚሆን የሚያጠራጥር አይመስለኝም።

የጠላትን ወረራ ዐላማ በውል ብናውቅ ናሮ ዛሬ የነጻነትን ትርጉሙ እንደማያውቅ ህዝብ አገራችን በነጻ አውጭ ድርጅቶች ባልተጥለቀለቀች ነበር። በገዛ አገር እንደ ሁለተኛ ዜጋ መቆጠር ማለት ምን እንደሆን የደረሰባቸው ቢተርኩልን ኖር፣ ዛሬ ኢትዮጵያ ቅኝ ገዛችን የሚሉ ጉዶች ባላየን ነበር። ጠላት የተቆጣጠራቸውን ግዛቶች ያሰተዳድር በነበረ ጊዜ በየቤቱ ይፈጸምው የነበረው ግፍ ቢነገረን ኖሮ፣ ዛሬ አይ ጣሊያን ትንሽ ቢገዛን የሚል ቀልደኛ ባልሰማን ነበረ። ስለ ሃገራችን ጄግኖች ተምረን ቢሆን ኖሮ፣ ፋኖ ተሰማራ፣ እንደ ሆቺሚን እንደቸጉቬራ እያልን በሰው አገር ጀግኖች ባላቅራራን ነበር። የፊደላችንን አፈጣጠር፣ ትርጉምና እሴት... ፊደሎቹን ስንቆጥር ጀምሮ ብንማር፣ አፍሪካ ውስጥ የራሳችን ፊደል ያለን ህዝብ መሆናችን ያኔ ቢነገረን ኖሮ፣ ዛሬ ያን ክብር የሚሽጥ ዜጋ በልተፈጠረብን ነበር። ሃይማኖታችንም ያው ነው። ዘመን አመጣሽ እምነቶችን በቀላሉ ተቀብለን የራሳችንን የምናኩዋስሰው የራሳችን ጥንታዊ ሃይማኖቶች ለህዝቡ አልኝታና ተስፋ ሆነው የሳለፉትን ታሪክ ስለማናውቅ ነው። የአለማወቃችን መዘዝ ብዙ ነው፣ በክብር፣ በንብረት፣ በጊዜና በህይወት አስከፍሎናል። አሁን ድረስም እየከፈልንበት ነው። ካላወቅን ወደፊትም መክፈላችን እንቀጥላለል።

ይህን ሁኔታ የምንቀይረው በእውቀት ብቻ ነው። እውቀት ትክክለኛውን ግንዛቤ እንድንይዝ፣ የችግሮቻችን መንስኤ እንድናውቅና ትክክለኛ መፍትሄ እንድናገኝ ይረዳናል። ውሽትን ከእውነት፣ ያለተደረገውን ከተደረገው የምንለየው ስናውቅ ነው። ፖለቲክኞች ለራሳቸው አላማ የፈጠሩትን ታሪክ ከእውነተኛው ታሪክ መለየት የምንችለው እውነተኛውን ታሪክ ስናውቅ ብቻ ነው። አልያ አሉባልታን እንደ ታሪክ ወስደን ያልሆነ መደመደሚያ ላይ ከማረፍ አልፈን የማያስፈልግ መስዋእትነት እስከመክፈል እንደርሳለን።

ይቀጥላል---
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 330
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Postby password » Sat Feb 26, 2011 2:50 pm

ታዲያ ታሪክን በትምህርት ቤት ካልተማርን ከየት መማር እንችላለን ?

ስለሃገራችን ታሪክ በቋንቋችንም ሆነ በውጭ ቋንቋ የተጻፉ መጻህፍትን በመመርመር ታሪክ ማወቅ ይቻላል። ዳሩግን እንዲህ ያሉ መጻህፍትን አሳድዶ የማንበቡ ተነሳሽነት የሚታየው በአብዛኛው በሙያው ሰዎች ወይም በጉዳዩ ልዩ ጥናት በሚያደርጉ ሰዎች እንጂ... ሌላው ደረቅ ታሪክን ቁጭ ብሎ የማንበብ ትእግስት ሆነ ፍላጎት የለውም። የደረቅ ታሪክ አጻጻፍ ስልት አጓጊና መሳጭ ስላልሆነ ልዩ ዝንባሌ የሌለውን ሰው የመያዝ ሃይሉ ዝቅ ያለ ነው። በትምህርት ቤትም ብዙዎቻችን የታሪክ መጻህፍት የምናጠናው ፈተናውን ለማለፍ እንጂ ታሪኩን የማወቅ ፍላጎት ወጥሮ ስለሚይዘን አይደለም።

አንባቢን ቴሌቪዥንና ፊልም ከመሳሰሉ አዝናኝ የጥበብ ዘርፎች ስቦ የታሪክ መጽሃፍ እንዲያነብ ለማድረግ ጽሁፉ በእጅጉ መሳጭና ስሜት ኮርኩዋሪ በሆነ ስልት መጻፍ ይኖርበታል። የልቦለድ አጻጻፍ ስልት እይታ ውስጥ የሚገባው እዚህ ላይ ነው። ታሪክ በልቦለድ አጻጻፍ ስልት ሲጻፍ ታሪካዊ ልቦለድ ይባላል። የታሪካዊ ልቦለድ አጻጻፍ ስልት መቸቱን፣ ገጸባህሪያትን፣ የታሪኩን መንስኤ፣ ሂደቱንና ፍጻሜውን የሚያቀርብበት ልዩ ዘዴ ስላለው ደራሲው እነዚህን ዘዴዎች በመጠቀም ማሳወቅ የፈለገውን እውነተኛ ታሪክ በልቦለድ አለባብሶ ያስተላልፋል። የሚጎመዝዝ መድሃኒት በማር ጠቅልለው እንደሚያስውጡን፣ አሰልቺውን ደርቅ ታሪክ በልቦለድ አጣፍጠው ያስነብቡናል።

ዘርዓይ ደረስ የፋሽስቶችን አንገት በጎራዴ መቅላቱን በቀር ውስጠ ጉዳዩን ጠልቄ የተረዳሁት ታሪካዊ ልቦለድ መጽሀፍ በማንበብ ነው። ስለ አምስቱ ዐመት የጠላት ወረራ ዘመን ያለኝን ግንዛቤ በሰፊው ያገኘሁት ታሪክ ቀመስ ከሆኑ ልቦለድ መጻህፍት ነው። የእስራኤልና የፍልስጤምን መሰረታዊ ችግር የተረዳሁት "ኤክሶደስ " ከተሰኘው ታሪከዊ ልቦለድ ነው። ታሪካዊ ልቦለድ ታሪክ የማስተማሪያ አንዱ መንገድ ሊሆን እንዲችል አያጠያይቅም። እዚህ የምንወያይበት ምርኮኛ የተሰኘው ታሪካዊ ልቦለድ መጽሃፍ ካነሳው ጭብጥ የምንማረው ብዙ ነገር እንዳለ እምነቴ ነው .......እና እናንብብ!!!!

ዋርካ ታንብብ!!!!

ፓስ
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 330
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Postby password » Sat Feb 26, 2011 4:30 pm

እባካችሁን wrote:password- አዲስ መጽህፍ ስላስተዋወከን አመሰግናለሁ:: ሆኖም በአማርኛ ባይተረጎምም በመዓዛ መንግስቴ ለንባብ የቀረበው ባለአራት ክፍል የመጀመሪያ መጽሀፍ Beneath the Lion's Gaze ግሩም ታሪካው ልብ ወለድ ይመስለኛል:: ታሪኩ ኢትዮጵያን መሰረት ያደረገ ቢሆንም እስካሁን ወደአማርኛ አልተተረጎመም። ወደሌሎች የውጪ ቋንቋዎች መተርጎሙን ግን አንብቤያለሁ።
እባክህ እርስዋንም ከሚመሰገኑት ተርታ አስገባልኝ:: ምክንያቱም ካልተሳሳትኩ የዚያን ወቅት ታሪክ በልብወለድ መልክ በእንግሊዘኛ ያቀረበች የመጀመሪያው ጸሀፊ ትመስለኛለች::

ሰላም እባካችሁን

የመዓዛን BENEATH THE LION'S GAZE አግኝቼ እያነበብኩት ነው። አንዳልከ(ሺ)ው የዚያን ዘመን ታሪክ መሰረት ያደረገ ነው። መጽሀፉ አለም አቀፍ አድናቆት ሲያገኝ በኛ በባለጉዳዮቹ አካባቢ ሲወራለት አልሰማሁም። አሁንም አንቺ ባትነግሪን ኖሮ ሳናውቀው ብዙ እንቆይ ነበር።

ሙስናና አፍቅሮተ ነዋይ በአገራችን ሰችዎ የጥበብ ስራ ላይ የሚሰሩት ስራ ያሳዝናል። ሃቀኛ የጥበብ ሰዎች ለገንዘብና ለዝና ደንታ የላቸውም። ስለሆነም ስራቸውን ለማስተዋወቅ ሆነ ለማሻሻጥ አይንቀሳቀሱም። ለሬክለምና ለፕሮሞሽን አይጨነቁም። ቢፈልጉም የሚከፍሉት ገንዘብ ያላቸው ብዙ አይደሉም። ለዚህ ነው ለአርባ አምሳ አመታት በጥበብ ስራ ላይ የቆዩና ለስነጥበብና ባህል ዳብሮት ከፍተኛ አስተዋጸኦ ያደረጉ ቁጭ ብለው፣ የይድረስ ይድረስ ስነፅሁፉ፣ ትያትርና ፊልም እንደ ቃሪያና ሽንኩርት የጉሊት ገበያ ያወጡት ነጋዴዎች ጥበበኞችና አርቲስቶች ተብለው ለህዝብ እይታ ብሎም እውቅና የሚዲያ ሽፋን ሲገፍፉ የምናየው። በፕሮግራም አዘጋጁና በነጋዴው መሃል የሚደረገውን ግንኙነት የሚያውቁት ሁለቱ ብቻ ናቸው። እሱን ወደፊት እንመለስበታልን። አሁን ይህን ያስባለኝ የመዓዛ መጽሃፍ ነው። እንዲህ አለም አቀፍ እውቅና ያገኘን የኢትዮጵያዊት ስራ የሚዲያው ሰዎች እንዴት ሳያውቁና ሳያሳውቁን ቀሩ?

A finalist for THE 2010 FLAHERTY-DUNNAN FIRST NOVEL PRIZE

MAAZA MENGISTE was named "New Literary Idol" by New York magazine.

ለማንኛውም ስዊድን የምትኖሩ መጽሃፉን ከ
BOKUS
kundservice@bokus.com
phone: 040-35 21 00
pris: 110kr inclusive porto

ማዘዝ ትችላላችሁ......

ፓስ ....... ዋርካ ታንብብ !!!!!
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 330
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Postby Tጂ » Sat Feb 26, 2011 4:44 pm

password wrote:
እባካችሁን wrote:password- አዲስ መጽህፍ ስላስተዋወከን አመሰግናለሁ:: ሆኖም በአማርኛ ባይተረጎምም በመዓዛ መንግስቴ ለንባብ የቀረበው ባለአራት ክፍል የመጀመሪያ መጽሀፍ Beneath the Lion's Gaze ግሩም ታሪካው ልብ ወለድ ይመስለኛል:: ታሪኩ ኢትዮጵያን መሰረት ያደረገ ቢሆንም እስካሁን ወደአማርኛ አልተተረጎመም። ወደሌሎች የውጪ ቋንቋዎች መተርጎሙን ግን አንብቤያለሁ።
እባክህ እርስዋንም ከሚመሰገኑት ተርታ አስገባልኝ:: ምክንያቱም ካልተሳሳትኩ የዚያን ወቅት ታሪክ በልብወለድ መልክ በእንግሊዘኛ ያቀረበች የመጀመሪያው ጸሀፊ ትመስለኛለች::

ሰላም እባካችሁን

የመዓዛን BENEATH THE LION'S GAZE አግኝቼ እያነበብኩት ነው። አንዳልከው የዚያን ዘመን ታሪክ መሰረት ያደረገ ነው። መጽሀፉ አለም አቀፍ አድናቆት ሲያገኝ በኛ በባለጉዳዮቹ አካባቢ ሲወራለት አልሰማሁም። አሁንም አንተ ባትገረን ኖሮ ሳናውቀው ብዙ እንቆይ ነበር።

ሙስናና አፍቅሮተ ነዋይ በአገራችን ሰችዎ የጥበብ ስራ ላይ የሚሰሩት ስራ ያሳዝናል። ሃቀኛ የጥበብ ሰዎች ለገንዘብና ለዝና ደንታ የላቸውም። ስለሆነም ስራቸውን ለማስተዋወቅ ሆነ ለማሻሻጥ አይንቀሳቀሱም። ለሬክለምና ለፕሮሞሽን አይጨነቁም። ቢፈልጉም የሚከፍሉት ገንዘብ ያላቸው ብዙ አይደሉም። ለዚህ ነው ለአርባ አምሳ አመታት በጥበብ ስራ ላይ የቆዩና ለስነጥበብና ባህል ዳብሮት ከፍተኛ አስተዋጸኦ ያደረጉ ቁጭ ብለው፣ ስነፅሁፉን፣ ትያትርንና ፊልሙን እንደ ቃሪያና ሽንኩርት የጉሊት ገበያ ያወጡት ነጋዴዎች ጥበበኞችና አርቲስቶች ተብለው ለህዝብ እይታ ብሎም እውቅና የሚዲያ ሽፋን ሲገፍፉ የምናየው። በፕሮግራም አዘጋጁና በነጋዴው መሃል የሚደረገውን ግንኙነት የሚያውቁት ሁለቱ ብቻ ናቸው።
ወደፊት እንመለስበታልን። አሁን ይህን ያስባለኝ የመዓዛ መጽሃፍ ነው። እንዲህ አለም አቀፍ እውቅና ያገኘን የኢትዮጵያዊት ስራ የሚዲያው ሰዎች እንዴት ሳያሳውቁን ቀሩ?

A finalist for THE 2010 FLAHERTY-DUNNAN FIRST NOVEL PRIZE

MAAZA MENGISTE was named "New Literary Idol" by New York magazine.ለማንኛውም ስዊድን የምትኖሩ መጽሃፉን ከ
BOKUS
kundservice@bokus.com
phone: 040-35 21 00
pris: 110kr inclusive porto

ማዘዝ ትችላላችሁ......

ስለ BENEATH THE LION’S GAZE ሲወራ አይቼ ማለፍ ስላልቻልኩኝ ነው:: በጣም መነበብ ያለበት ልብ የምያንጠለጥል ድርሰት ነው:: እዛ መጻፍ ውስጥ ያላለቀስኩለት ገጸ ባህሪ የለም:: ለደራሲዋ ትልቅ ምስጋና ከ አክብሮት ጋር:: የ እንግሊዘኛውን መጻፍ ኦንላይን መግዛት ይቻላል::
“Love is like the wind, you can't see it but you can feel it."
Tጂ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 301
Joined: Sat Aug 11, 2007 3:59 am

Postby password » Sun Feb 27, 2011 5:34 pm

የትረካ ዐይነት፣
ምርኮኛ ሁለት ጭብጦች የያዘ የፈጠራ ድርስት ሲሆን የመጀመሪያው ጭብጥ ታሪካዊ ልቦለድ ከሚባለው የስነጽሁፍ ዘርፍ የሚመደብ ነው። ይህ ክፍል በዘመነ ደርግ የመጀመሪያዎቹ አመታት የነበረው የማህበረ-ፖለቲካዊ ቀውስ በህብረተሰቡ ላይ ያደረሰውን ግፍና መከራ በዋናዋ ገጸባህሪ ህይወት ዙሪያ እያጠነጠነ ይተርካል። የሚጀምረው ዋናዋ ገጸባህሪ፣ ፍሬህይወት ለእደገት በህብረት የእውቀትና የስራ ዘመቻ ስትነሳ ነው። በዚህ ዘመቻ በእስራ ሺዎች የሚቆጠሩ የዩንቨርስቲና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ወደ ገጣሪቱ ኢትዮጵያ በመዝመት የገበሬ ማህበራት ከማቁዋቁም እስከ ጥርጊያ መንገድ መዘርጋት ያለውን ስራ ሲስሩ፣ የወቅቱን የተቃወሚ ሀይል ፖለቲካ ሲያጠኑ፣ በህቡእ ሲደራጁ ያወሳልንና፣ አያይዞ ዘማቾች ወደየመጡበት ተመልሰው በሃገሪቱ አስተዳድራዊ ለውጥ ለማምጣት በህቡእ ሲንቀሰቀሱ ይተርክልናል። ፍሬህይወት ለትግሉ እስከ ህይወት መስዋእተነት ለመክፈል ከሚንቀሳቀሱት ወጣቶች አንድዋ ነች።

አገዛዙ በህቡዕ የሚደረገውን እንቅስቃሴ ለመደምሰስ በሚወስደው ኢሰብዓዊ እርምጃ በርካታ ወጣቶች ይታሳራሉ፣ ብዙዎች ይሰደዳሉ፣ ይገደላሉ። ተቃውሞውም በዚያው ልክ እያየል ሲሄድ አሰሳ፣ ነጻ እርምጃና ቀይሽብር የወቅቱ ሃቅ ይሆናሉ። ህብረተሰቡ ይታመሳል፣ ወጣቶች መግቢያ መውጫ ያጣሉ። የፍሬህይወት ወንድም ይገደላል። እህትዋ ትጠፋለች፣ እናትዋ ይታመማሉ። በመጨረሻ ፍሬህይወት የምትታገልለት ፓርቲ፣ ኢህአፓ መከፋፈሉ ሁዋላም ክፉኛ ተመትቶ መፍረሱ ሲታወቅ ወጣቶች እጅ መስጠትና የትግል ጉዋዶቻቸውን ማጋለጥና ማስያዝ ይጀምራሉ። ፍሬህይወት ትታሰራለች። ከተወስነ ጊዜ በሁዋላ ሰላም ብጤ በመስፈኑ ትፈታና ሰላማዊ ኑሮ ትቀጥላለች። ይህ ክፍል በወቅቱ በነበረው እውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ስለሆነ ታሪካዊ ልቦለድ ወስጥ ሊመደብ ይችላል። ኤች አይ ቪንና መዘዙን የሚተርከው ሁለተኛው ክፍል ግን በዋናዋ ገጸባህሪ ህይወት ዙሪያ ያጠነጠነ ቢሆንም ራሱን የቻለ ጭብጥ ይዞ የቆመ መደበኛ ልቦለድ ነው። በእንድ ጥራዝ መጽሃፍ ውስጥ በመስፈሩ ምክንያት እንጂ እንደ ሌላ መጽሃፍም ሊቆጠር ይችላል።

የትረካ ስልት
የምርኮኛን ተነባቢ ካደረጉት ነጥቦች አንዱ የትረካ ስልቱ ነው። የገለጻ ለዛና የጭውውቱ ጣዕም። ከባድ የአማርኛ ቃላትና እንደ ጥቅስ የረቀቁ አረፍተ ነገሮች ያልበዙበት መሆኑም ለተነባቢነቱ አስተዋጽኦ ያደረገ ይመስለኛል። በአማርኛ ልቦለድ ተደጋግመው በመመምጣት አንባቢ ያሰለቹ ብሂሎች ተወንፍተው የወጡ ወይም እንደይገቡ በጥንቃቄ የታሰበበት ይመስል አንድ ክልቼ ለአመል እንኩዋ አላየሁበትም።

ምርኮኛን ተነባቢ ያደረገው የገልጻ ስልት ለምሳሌ እንመልከት፣ ከገጽ 276

...አንዳንዴ የማታውቀውን የአሲምባ ተራራ በምናብዋ ትቃኛዋለች። አሲምባ የኢህአፓ ሰራዊት የትቅ ትግል ማዕከል መሆኑን ከመስማት ሌላ ስለቦታው የምታውቀው ባይኖርም በሀሳቡዋ ታየዋለች። በፊልም እንዳየቻቸው የጦር ምሽጎች ሁሉ የአሲምባ ህይወት ከባድ እንደሚሆን ታስባለች። የተጎሳቆሉ፣ ግን ለምንም የማይበገሩ የሰራዊቱ አባላት ይታዩዋታል። ሚሚ (ታናሽ እህትዋ) ጸጉራን አሳጥራ፣ ቁምጣ ለብሳ፣ ዝናርዋን ታጥቃ፣ በረባሶ ተጫምታ በተራራው ላይ ታች ስትል፣ ስትታኮስ ... ላብዋ በግንባርዋ ሲንቆሮቆር... ሌሎቹ ሲያበረታትዋት... ድንገት ደግሞ ሌላው ትዝ ይላታል። "እዚያም መከፋፈል ተፈጥሮ ይሆን? " ብላ ራስዋን ትጠይቃለች። ልክ እንደ አዲስ አበባው እነርሱም ዘንድ ክፍፍል ሲፈጠር፣ አንዱ በሌላው ላይ መሳሪያ ሲያዞር ... አይኖችዋን ትጨፍናለች። ከዚያ በሁዋላ ያለውን ላለማሰብ አእምሮዋን ለመግታት ትሞክራለች። ግን አይሆንላትም እንደገናም ታስበዋለች።

ይህ ስልት፣ ይህ የሰው አእምሮ ውስጥ የሚብሰለሰልን ሃሳብ የመግለጽ ስልት በደንብ ከተሰራበት አንባቢን ከገሃዱ አለም ወደ ፈጣራው የማስጉዋዝ ችሎታ ያለው ሃይለኛ ዘዴ መሆኑ ይታመናል። አንባቢን በገለጣ እንዲያዝን፣ እንዲጨነ ከማድረግ አልፎ ህመሙ፣ ጉዳቱ፣ ናፍቆቱ፣ ቀቢጸ ተስፋው እንዲሰማው ከተፈለገ ገጸባህሪው ጭንቅላት ውስጥ የሚብሰለሰልውን ሃሳብ መግለጽ ያስፈልጋል። ቆንጂት ይህን ዜዴ ብዙ ቦታ ተጠቅማበታልች። ለዚም ነው ትረካዋ እጅግ ስሜት ኮርኩዋሪና መሳጭ የሆነው የሚል እምነት አለኝ።

ይቀጥላል .......
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 330
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: Google Adsense [Bot] and 5 guests