የሃበሻ ጀብዱ (አስተያየት መስጫ)

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

የሃበሻ ጀብዱ (አስተያየት መስጫ)

Postby ዘርዐይ ደረስ » Sat Jun 18, 2011 10:33 pm

ሰላም ለሁላችሁም እያልኩ:-


ከወር በፊት ፓን ሪዚኮ የ'ሃበሻ ጀብዱ' እንደታተመለት ሲያሳውቅና የዋርካ ታዳሚዎችም የእንኳን ደስ ያለህ መግለጫቸውን ሲያቀርቡለት እውነት ስላልመሰለኝ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቤ ነበር::እንድጠራጠር ካደረጉኝ ምክንያቶች አንዱ እዚህ ዋርካ ላይ ለሚረባው ለማይረባው አዲስ ርእስ ስንከፍት ይህን መፅሐፍ ለማስተዋወቅ ግን ራሱን የቻለ ርእስ ባለመከፈቱ ነው::

ያም ሆነ ይህ ሰሞኑን ባልጠበቅኩት አጋጣሚ ይህ መፅሐፍ እጄ ሊገባ በመቻሉ ለማንበብ በቅቻለሁ::እንደ ታሪክ መጽሐፍ ሳይሆን እንደ ልብወለድ (ልቦለድ) የማይሰለች ሆኖ ነው ያገኘሁት::ምነው ግን ሌሎቻችሁ እስካሁን ዝም አላችሁ? በነገራችን ላይ ይህን መፅሐፍ የጨረስኩት በ 6 ጊዜ ሲሆን በጠቅላላው ከ 14 እስከ 15 ሠዓታት ፈጅቶብኛል::

ለጊዜው ይህንን ካልኩ በኋላ ሰፋ ያለ አስተያየት ለመስጠት እሞክራለሁ::
Last edited by ዘርዐይ ደረስ on Wed Jun 22, 2011 9:10 pm, edited 1 time in total.
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1380
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: የሀበሻ ጀብዱ (አስተያየት መስጫ)

Postby ፓን ሪዚኮ » Sun Jun 19, 2011 12:19 am

ዘርዐይ ደረስ wrote:ሰላም ለሁላችሁም እያልኩ:-


ከወር በፊት ፓን ሪዚኮ የ'ሀበሻ ጀብዱ' እንደታተመለት ሲያሳውቅና የዋርካ ታዳሚዎችም የእንኳን ደስ ያለህ መግለጫቸውን ሲያቀርቡለት እውነት ስላልመሰለኝ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቤ ነበር::እንድጠራጠር ካደረጉኝ ምክንያቶች አንዱ እዚህ ዋርካ ላይ ለሚረባው ለማይረባው አዲስ ርእስ ስንከፍት ይህን መፅሐፍ ለማስተዋወቅ ግን ራሱን የቻለ ርዕስ ባለመከፈቱ ነው::

ያም ሆነ ይህ ሰሞኑን ባልጠበቅኩት አጋጣሚ ይህ መፅሐፍ እጄ ሊገባ በመቻሉ ለማንበብ በቅቻለሁ::እንደ ታሪክ መጽሐፍ ሳይሆን እንደ ልብወለድ (ልቦለድ) የማይሰለች ሆኖ ነው ያገኘሁት::ምነው ግን ሌሎቻችሁ እስካሁን ምነው ዝም አላችሁ? በነገራችን ላይ ይህን መፅሐፍ የጨረስኩት በ 6 ጊዜ ሲሆን በጠቅላላው ከ 14 እስከ 15 ሠዓታት ፈጅቶብኛል::

ለጊዜው ይህንን ካልኩ በኋላ ሰፋ ያለ አስተያየት ለመስጠት እሞክራለሁ::
ውድ ዘራይ ይቺን ቤት ስልከፈትክልኝ ከምር ከልቤ ላመሰግንህ እወዳለሁ....እጅጉን በጣም አመሰግናለሁ
ፓን
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ዘርዐይ ደረስ » Sun Jun 19, 2011 5:29 pm

ሰላም ፓን ሪዚኮ:-

ምስጋናህን ተቀብያለሁ::ቃል በገባሁት መሠረትም ስለ መፅሐፉ ያለኝን አስተያየትና አንዳንድ ጥያቄዎች አቀርባለሁ::በመጀመርያ ጥያቄዎቼን አስቀድማለሁ::


1)ገፅ 20:-እዚህ ላይ አዲስ አበባ በ1889G.C. እንደተቆረቆረች ተጠቅሷል::በይፋ እንደሚታወቀው ግን አዲስ አበባ የተቆረቆረችው በኅዳር ወር 1879(በኛ አቆጣጠር) ነው::በ1979ዓ.ም. የዋና ከተማችን መቶኛ ዓመትም በድምቀት እንደተከበረ አስታውሳለሁ::ታዲያ መፅሐፉ ላይ የተጠቀሰው በህትመት ስህተት ነው ወይስ ደራሲው እንደዚያ ነው የፃፉት?

2)እዚሁ ገጽ ላይ አዲሱ ንጉሥ ሬጀንት ራስ ተፈሪ....ይላል::ዘውዲቱ ንግሥተ ነገሥታት በነበሩበት ወቅት ተፈሪ ንጉሥ ሬጀንት እንደነበሩ አንብቤ ስለማላውቅ ግራ ገብቶኛል::

3)ገፅ32:-ንጉሡ ፈረንሳይኛና እንግሊዝኛ አቀላጥፈው ይናገሩ እንደነበር ተጠቅሷል::ፈረንሳይኛ ይችሉ እንደነበር ብዙዎች የመሰከሩት ሲሁን እንግሊዘኛ አቀላትፈው መናገራቸውን አልሰማሁም አላነበብኩም::እንዲያውም አንድ ጊዜ በእንግሊዝኛ የመግቢያ ንግግር እንዲያደርጉ ተፈልጎ ብላቴን ጌታ ኤፍሬም ተወልደ መድኅን እንግሊዝኛውን በአማርኛ ፊደል ጽፈውላቸው እንዳነበቡ 'የኤርትራ ጉዳይ' የሚለው መጽሐፍ ላይ ተጠቅሷል::

4)ገፅ 115:-ራስ ሥዩም መንገሻ የአፄ ዮሀንስ የልጅ ልጅ እንደሆኑ ተጠቅሷል::ብዙዎች የታሪክ ፀሀፊዎች እንደሚሉት ግን የራስ ሥዩም አባት ራስ መንገሻ የአጼ ዮሐንስ የወንድም ልጅ እንደ ነበሩ ነው::

5)ገፅ 57:-እንግሊዝና ፈረንሣይ በእርግጥ ኢትዮጵያ በጣሊያን በመወረሯ ደስተኞች ነበሩ?

6)ገፅ 67:- ...ሆን ብለው ደጃች ኃይለሥላሴ ጉግሳን ከሞተው አባቱ ከራስ ጉግሳ....ጋር በማለዋወጥ የሚለው በትክክል አልገባኝም::

7)ገፅ 114:-የጣልያን....ሠፈርም ለመቃኘት ከሠፈር ወጣሁ..... እዚህ ላይ ያለገባኝ ነገር ከሰፈር ነው የወጡት ወይስ ካደሩበት ቤት?

8)ገፅ94:-በዚያን ወቅት አንዲት ኢትዮጵያዊት ባጋጣሚ የተዋወቀችውን ሰው(ያውም ፈረንጅ) እንዲያገባት መጠየቋ ገርሞኛል::

9) ገፅ 109 የገፁ መጀመርያ ላይ አስራ አምስት አስራ አምስት አለንጋ ተገረፉ ይልና ወደ መጨረሻ አካባቢ ደግሞ በጣም ጥቂቶች ናቸው 50 አለንጋ የሚችሉት ይላል:.ይህም አልገባኝም::

10) ገፅ157:- የድሮ ፖስተኞች ፖስታውን የሚሰኩት በእንጨት ባላ ላይ እንደሆነ ተገልጿል::የታሪክ መፃሕፍት ፎቶ ላይ እንዳየሁት ግን እንጨቱ ባላ አይደለም::

11)ገጽ 210:- እዚህና ለሎችም ቦታዎች ላይ ኪዳነ ምህረት ያልከው ምን እንደሆነ አልገባኝም::

12)አንዳንድ ቦታዎች ላይ በቅንፍ የተቀመጡ ቃላቶች አሉ::ያንተ ናቸው ወይስ የደራሲው?

13)ደራሲው ኦሮሞ እያሉ ነው የጻፉት ወይስ አንተ ነህ የቀየርከው?

14)የሀበሻ ጀብዱ የሚለው ርዕስም ትንሽ ግር ብሎኛል::ደራሲው በኢትዮጵያ ያደረጉትን ጀብዱ ወይስ የኢትዮጵያውያንን ጀብዱ ለመግለጽ ነው?

በተረፈ ለመፅሐፉ ያለኝን አድናቆት በድጋሚ እየገለጽኩ ለጊዜው እዚህ ላይ ይበቃኛል::

P.S. መፅሐፉ የደራሲውን ሙሉ ማስታወሻ ያካተተ ነው?ወይስ ወደፊት ለማሳተም ያዘጋጀኸው አለ?ለማንኛውም በነካ እጅህ ተመሳሳይ ታሪኮችን ፈልገህ እንደምታስነብበን ተስፋ አደርጋለሁ::
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1380
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Postby ፓን ሪዚኮ » Mon Jun 20, 2011 8:10 am

ውድ ዘርዐይ...እስቲ ጥያቄዎችህን ለመመለስ ልሞክር

1: በዚህ መፅሀፍ ውስጥ የተጠቀሱስ ቀኖችና አመተ ምህረቶች በሙሉ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ሲሆኑ ...ከ 1889 ላይ 7 እንኳን ብንቀንስ 1882 ይሆናል እና እርግጠኛ ሆኖ ለመናገር ይከብድ ይሆናል ...እንዳልከው ኢትዮጲያውያን የሚያምኑበትን ቀን እኔም ወደማመኑ እቃረባለሁ ...ችግሩ ታዲያ አዲስ አበባ የኢትዮጲያ ዋና ከተማ መሆኗን የሚያውጅ ምንም አይነት አዋጅ በአጼ ሚኒሊክ ያለመነገሩ ነው ...

2:አዲሱ ንጉስ...ንጉሰ ነገስት ሀይለስላሴን ለመግለጽ ሲሆን ሬጀንት ራስ ተፈሪ መኮንነን ባለሙሉ ስልጣን እንደራሴ የነበሩበትን ጊዜ የሚያመላክት ሲሆ ...አዲሱ ንጉስ ብሎ ነጠላ ሰረዝ ይጎለዋል ...ኢዲት ስህተት ነው
3: እንግሊዘኛ ይናገሩ እንደነበረ በምስራቅ አውሮፓ በሰፊው ይነገራል ...ማስረጃ ግን የለም ...ጃንሆይ በጃቸው አንዲትም ነገር ጽፈው ስለማያውቁ ማስረጃ ለማቅረብ እጅጉን በጣም ይከብዳል
አዶልፍ ፓርለሳክ ግን እንግሊዘኛ እንደሚችሉ ጽፏል

4: በትክክል ራስ መንገሻ የአጼ ዮሀንስ የወንድም ልጅ ናቸው ...ነገር ግን በ መተማው ጥርነት አጼ ዮሀንስ ቆስለው በሞት አልጋ ላይ እንዳሉ ..ልጄን መንገሻን ጥሩልኝ ብለው አልጋውንም ለማውረስ ሞክረው ስለነበር ..ከዚያን ግዜ ጀምሮ ራስ መንገሻ እንደ አጼ ዮሀንስ ልጅና አልጋ ወራሽ መቆጠር ጀመሩ ...እውነታው ይሄው ነው

5: በትክክል

6 :ወጣቱ ደጃዝማች ሀይለስላሴ ጉግሳ በአውሮፓ ውስጥ ስለማይታወቅ ...ጣልያኖች ሆን ብለው በአውሮፓ ጥቂት ሀገሮ ጣልያንን ጨምሮ ታላቅ ወዳጅነትና ዝና የነበራቸውን የአመጸኛውን አባቱን የራስ ጉግሳን ስም ይጠቀሙ ነበር
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Mon Jun 20, 2011 8:33 am

7 : የጣልያን አውሮፕላኖች ሰሞኑን ብቅም ስላላሉ እና ሰፈርም ለመቃኘትህዳር 13 ቀን እረፋዱ ላይ ከሰፈር ወጣሁ ...ይላል .....በቀላሉ የጣልያን አውሮፕላኖች ፋታ ስለሰጡን እግረ መንገዴን የጦር ሰፈሬንና የደጃዝማች አበራን የጦር ሰፈር ለመጎብኘት ከጦር ሰፈሬ ወጣሁ ..ለማለት ነው

8 : ለኛ ትውልድ አስደናቂ ቢሆንም በዛ ጀግና ትውልድ ግዜ ሴቶችም በጦርሜዳ ይውሉ ነበር ...ያበስላሉ ቁስለኛ ያክማሉ የሞተ ይቀብራሉ ...ያቺ ጉብል ግን በጥቂቱም ቢሆን ፈረንጁ ያለ ሚስት ገረድ ወደ ጦር ሜዳ መሄዱ ያሳዘናትም ይመስላል
9 : ...15 አለንጋ አስከፊ ቢሆንም ለሞት አይዳርግም ...50 አለን ነኝ የቀየርኩት ...አለንጋ እንዲገረፉ ከሚፈረድባቸው ሶዎ ጥቂቶቹ ብቻ በህይወት ይተርፋሉ ለማለት ነው

10 : ባላ ስንጥር ብዙም የሚያጣላ አይመስለኝም

11 : ኪዳነ ምህረቱ የነዛ ብዙ ዋሻዎች የበዙባት ቆላማ ቀበሌ ስም ነው

12 : የኔ ናቸው
13 : እኔ ነኝ የቀየርኩት ለማስረጃ ካርታውን ይመልከቱ ...ራያ ኦሮሞ አዘቦ ኦሮሞ

14 : መግቢያው ላይ ወይም የጀርባው ሽፋን ላይ ተገልጿል
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ሾተል » Mon Jun 20, 2011 8:40 am

የአበሻ ጀብዱ መጽሀፍ እጃችን ገብቶ ስላላነበብን ስለመጽሀፉ የምንለው ምንም ነገር ባይኖርም ንጉስ ሀይለስላሴ እንግሊዘኛ ይናገሩ ወይም አይናገሩም ነበር ለሚለው በቂ መልስ ባይሆንም ፓላሳቸው ጋርደን ውስጥ ሆነው በጥቂቱ በእንግሊዘኛ ሲናገሩ ከዚህ በፊት ዩ ትዩብ ላይ የተመለከትኩትን ጀባ ልበላችሁ ::የፓኑንና የዘርአይ ደረስን ውይይት ባያግዝም በጥቂቱ ሳያግዝ ያግዛልም ብለን ነው ታድያ ::

http://www.youtube.com/watch?v=_fiDDOs60ew

መልካም ውይይት

* ፓኑ እናንተ ጋር ይመጣል ብዬ የነበረው ልጅ ከቺኩ ጋር ጫጉላ ጊዜውን ፕራግ ያሳልፋል ብለን ስንጠብቅ እዚሁ ፍቅር መስራቱን ጀምረው ያንን ያኽል መንገድ አቁዋርጠን የምንሄድበትን ጊዜ እዚሁ ሌት ተቀን ፍቅራችንን እንወጣ ብለው ይኸው ጉዋደኛዬ ምን ከመሰለ ሰውነቱ ከስቶ ከስቶ ብታየው ለካስ ፑናኒ አሲድም አላት እስክንል ድረስ ሆነናል ::ልጅቱ ታድያ አምሮባት አበባ መስላለች ... ጉዋደኛዬን መጣ መጠመጠችው::አክስታ ከስፓጌቲ ተራ ከተተችው::እንግዲህ ገንፎ ጉዋደኛዬን መቀለብ አለብኝ እንጂ አንድ ቀን ንፋስ ይዞት ዳንዩብ ወንዝ ውስጥ እንዳይከትብኝ::

ብሮ ልል የፈለኩት ገብቶሀል አይደል ?

መልካም ቀን

ሾተል ነን
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9658
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ዘርዐይ ደረስ » Thu Jun 23, 2011 1:00 am

ፓን ሪዚኮ በድጋሚ ሰላም እያልኩ:-


ለሰጠኸኝ ፈጣንና አጥጋቢ መልሶች ምሥጋናዬ ከፍ ያለው ነው::በነገራችን ላይ ከሦስት ቀን በኋላ ወደ ዋርካ ስመለስ በዚህ ርእስ ላይ በርካታ ታዳሚዎች አስተያየት ይሰጣሉ የሚል ግምት ነበረኝ::እንግዲህ የማላሰለችህ ከሆነ ሌሎቹ እስኪሳተፉ ጥያቄዎቼን ልቀጥል::በህይወቴ አንድ መፅሐፍ ካነበብኩ በኋላ ከደራሲው(ተርጓሚው) ጋር ስወያይ የመጀመርያ ጊዜዬ መሆኑንም ሳልጠቅስ አላልፍም::


15) ገፅ 303 አንቀፅ 5: አንዲት ደረቅ ጥይት ጮኸች ስትል ምን ማለትህ ነው?

16)ገፅ 327 አንቀፅ 1:-ደነቆረ የምንለው ለሚሰማ ነው እንጂ ለሚናገር ነው እንዴ?

17) ገፅ 41 እና ገፅ 191 ያሉትን የፈረንሣይኛና የጣልያንኛ ፅሑፎች ለምን አላስተረጎምካቸውም?

18) የሶሉና ሰው ያልከውስ ምንድን ነው?

19) መፅሐፉን ሳነብ ያናደደኝ ነገር ቢኖር ከገጽ 275 እስከ 278 ያለው ያለመኖሩ ነው::እዚያ ቦታ ላይ ከገፅ 271 እስከ 274 ያለው ተደግሟል::ይህ ስህተት ሁሉም መፅሐፍት ላይ ነው ያለው ወይስ እንደ ዕድል ሆኖ ነው እኔን ያጋጠመኝ?

20)ባለፈው መጨረሻ ላይ ለጠየቅኩህ ጥያቄ መልስ ስላልሰጠኸኝ በድጋሚ ላስታውስህ::
ሰላም ሾተል:-

ለውይይቱ ላደርተግከው አስተዋፅኦ አመስግናለሁ::ዐፄው እንግሊዝኛም ይናገሩ ነበር ማለት ነው::
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1380
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Postby ፓን ሪዚኮ » Thu Jun 23, 2011 6:06 am

ሰላም ውድ ዘርዐይ
በቅድሚያ እስቲ ባለፈው የጠየከኝን የመጨረሻ ጥያቄ ልመልስ

ደራሲው በ 1948 ዐ.ም ያሳተሙት መጽሀፍ በኔ የትርጉም ስራ ውስጥ ተጠናቆ ግበቷል ::
ደራሲው በዚሁ መጽሀፋቸው ላይ ጥቂት ስለ 5 አመት የአርበኝነቱ ጦርነትም ጥቂት ብለዋል ...ይሄ ደሞ ከውጪ ሆነው የጻፉት ከመሆኑም በላይ በጣም ትንሽ በመሆኑ ሙሉ የትርጉም ስራ ይወጣዋል ብዬ አላምንም ቢሆንም እኔ አሁን በማዘጋጀት ላይ ላለሁት የዚህ መጽሀፍ ቀጣይ ታሪክ ቀመስ ልቦለድ መጽሀፍ ላይ መንደርደሪያና ማጣፈጫ አድርጌ ልጠቀምበት አስቤአለሁ
እስቲ ወደ ሽቀላ ልሂድና ከሽቀላ መልስ ሌሎችን ጥያቄዎችህን ለመመለስ እሞክራለሁ
እስከዛው ቸር ይግጠመን
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby እንሰት » Thu Jun 23, 2011 3:59 pm

ሰላማት አባ ፈርዳ
አሀ ቀጣይም አለው ማለት ነው? ደግ ደግ እስኪ በርታ:: አንድ ጥያቄ ነበረኝ::

ስለ ቺኮዝ ጠብመንጃ ወደ ኢትዮጵያ አገባብ እስኪ የምታውቀው ነገር ካለ አጫውተን::


ፓን ሪዚኮ wrote:ሰላም ውድ ዘርዐይ
በቅድሚያ እስቲ ባለፈው የጠየከኝን የመጨረሻ ጥያቄ ልመልስ

ደራሲው በ 1948 ዐ.ም ያሳተሙት መጽሀፍ በኔ የትርጉም ስራ ውስጥ ተጠናቆ ግበቷል ::
ደራሲው በዚሁ መጽሀፋቸው ላይ ጥቂት ስለ 5 አመት የአርበኝነቱ ጦርነትም ጥቂት ብለዋል ...ይሄ ደሞ ከውጪ ሆነው የጻፉት ከመሆኑም በላይ በጣም ትንሽ በመሆኑ ሙሉ የትርጉም ስራ ይወጣዋል ብዬ አላምንም ቢሆንም እኔ አሁን በማዘጋጀት ላይ ላለሁት የዚህ መጽሀፍ ቀጣይ ታሪክ ቀመስ ልቦለድ መጽሀፍ ላይ መንደርደሪያና ማጣፈጫ አድርጌ ልጠቀምበት አስቤአለሁ
እስቲ ወደ ሽቀላ ልሂድና ከሽቀላ መልስ ሌሎችን ጥያቄዎችህን ለመመለስ እሞክራለሁ
እስከዛው ቸር ይግጠመን
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby ፓን ሪዚኮ » Sat Jun 25, 2011 7:13 am

ውድ ዘርዐይ ...መጽሀፌ ዐገር ቤት እንደ አብዮታዊው ሰራዊት እየመራ መሆኑን ትናንት ቢራ ቤት ሰማሁ ...ደስ አለኝ ...እስቲ ስለሁሉም ፋታ ልውሰድና እንጫወታለን ...መልካም ሰንበት
ፓኑ አባ ፈርዳ
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ዘርዐይ ደረስ » Sun Jun 26, 2011 7:39 pm

ፓን ሪዚኮ wrote:ውድ ዘርዐይ ...መጽሀፌ ዐገር ቤት እንደ አብዮታዊው ሰራዊት እየመራ መሆኑን ትናንት ቢራ ቤት ሰማሁ ...ደስ አለኝ ...እስቲ ስለሁሉም ፋታ ልውሰድና እንጫወታለን ...መልካም ሰንበት
ፓኑ አባ ፈርዳ


ሰላም ብላቴን ጌታ ፓን ሪዝኮ:-


የሃበሻ ጀብዱ ኢትዮጵያ Bestseller ሆኗል እያልከኝ
ነው? እንደዚያ ከሆነ እንኳን ደስ ያለህ(ን)! እስራኤል አገር ግን ሳይከለከል ይቀራል? :cry:

በተረፈ ለጥያቄዎቼ እንዳለፈው አፋጣኝ መልስ አገኛለሁ ብዬ ነበር::ከሁለት ሳምንት በኋላ ዋርካ ተመልሼ ስገባ ያንተ መልሶችና የሌሎቹም ታዳሚዎች አስተያየቶች እንደሚጠብቁኝ ተስፋ በማድረግ ለዛሬ ከአጎትህ ያመለጡ የፊደል ግድፈቶች ስላገኘሁ ምናልባት ለሁለተኛው እትም ሊጠቅሙ ይችላሉ በማለት በከፊል እንደሚከተለው ደርድሬአቸዋለሁ:-


ገፅ-- አንቀፅ---- ግድፈት---- ሲስተካከል
-----------------------------------------------------

89 ዲንቄም (ድንቄም )

90 ስርጥ (ሰርጥ)

92 ማሀል (መሐል )

107 በራስ ካሳ ፊት ( ራስ ካሣ ፊት)
109- 4 አልንጋ (አለንጋ)

114- 5 ጩኽት (ጩኸት)

136- 4 መኰንንኖች (መኰንኖች)

141- 5 ከሚሰንዝርባቸው (ከሚሰነዘርባቸው)

161- 4 ጩኽታቸው (ጩኸታቸው)

168- 1 ፋሽት (ፋሽስት(ፋሺስት))

194- 6 አውሮላኖች (አውሮፕላኖች)

204- 4 ጭላሸት (ጥላሸት)

226 ርቅት ( ርቀት)

230 ወተን (ወጥተን)

247- 1 እየተመላልሱ (እየተመላለሱ)

250- 3 አደልም (አይደለም)

250- 3 ያውቀሉ (ያውቃሉ)

254- 3 አላንቀስቅስ (አላንቀሳቅስ)

256- መሰለ (መሰለኝ)

257- 4 ትግዕስት ( ትዕግሥት)

257- 5 በተራራራው (በተራራው)

257- 7 ከከዚህ (ከዚህ)

258- 4 ጩከት (ጩኸት)

259- 1 ካዛስ ( ከዚያስ)

269- 5 እየጥፉብኝ (እየጠፉብኝ)

270- 3 ጉዙ (ጉዞ)

271- 2 መውረደ (መውረድ)

271- 3 በማሰፈለጉ--- (በማስፈለጉ)

272- 4 እያንቦጫረቅን (እያንቦራጨቅን)

284- 2 ስናፈጭ (ስናፋጭ)

285- ኃይሌ ከበደ (ኃይሉ ከበደ)

289- 1 የምትንጎራጎረውን (የምታንጎራጉረውን)

291- 3 ፍታውራሪ (ፊታውራሪ)

291- 4 ለእያንዳዱ (ለእያንዳንዱ)

292- 1 ፈቃዶ (ፈቃድዎ)

296- 3 ጉሮው (ጉሮሮ)

308- 3 ሰምብተዋል (ሰንብተዋል)

308- 3 ድኳኑ (ድንኳን)

309- 2 መልክት (መልእክት)

312- 2 ኤንባሲ (ኤምባሲ)

318- 3 የተተጠቀለለውን (የተጠቀለለውን)

323- 1 በተዘጋጅ ( በተዘጋጀ)

324 - 3 ኢትዮጵያውያ (ኢትዮጵያውያን)

324- 4 ኢትዮጵያውን (ኢትዮጵያውያን)
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1380
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Postby ፓን ሪዚኮ » Sun Jun 26, 2011 8:23 pm

ሰላም ዘርሽ....በሁሉም ነጥቦቺህ እስማማለሁ ...የ ኢድሽን ችግር አለ....የማልስማማው ግን የዋጎች ወራስ በሆነው በደጃዝማች ሀይሌ ከበደ ብቻ ነው ...ደራሲው አንዳንድ ግዜ ሀይሉ ..............ሌላ ግዜ ......ሀይሌ ይለዋል ...በነገራችን ላ የቅርበት ወዳጅነትም ነበራቸው .....አበራና ሀይሌ ወዳጆቹ እንደነበሩ በቀጣይ ታሪኩ ላይ ደጋግሞ ያነሳል
ለዛሬ ይብቃና እስቲ ቀደም ብለው ለተነሱ ጥያቄዎች መልስ ላፈላግ...
ፓን
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Wed Jun 29, 2011 10:54 pm

የዋርካ ልጆች የተመሰገኑበት የትርጉም ስራ እንዲህ እደዋዛ የሚታይ አለመሰለኝም ነበር ...ሆነ ቀረ ሰው ማመን ቀብሮ ነው ያለቺው ...ጦጣ ነች ቀበሮ????
ሶሻሊስቱ ፓኑ አባ ፈርዳ
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby password » Mon Aug 01, 2011 10:19 pm

ሰላም ፓን

ከዋርካ ራቅ ብየ ስለነበር ከ 4 ወሮች በፊት የላክልኝን መልክት አላየሁትም .. መልሱን ዛሬ በመጣበት በር ልኬአለሁ.... በመዘግዬቴ አዝኛለሁ....

ካክብሮት ሰላምታ ጋር

ፓስወርድ
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 330
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Postby ፓን ሪዚኮ » Mon Aug 08, 2011 10:16 am

password wrote:ሰላም ፓን

ከዋርካ ራቅ ብየ ስለነበር ከ 4 ወሮች በፊት የላክልኝን መልክት አላየሁትም .. መልሱን ዛሬ በመጣበት በር ልኬአለሁ.... በመዘግዬቴ አዝኛለሁ....

ካክብሮት ሰላምታ ጋር

ፓስወርድ
ሰላም ፓስ እንኳን ደህና መጣህ እያልኩ እኔም ወደ ዋርካ እንደ ጥንቱ መሮጡን አላበዛውም ...እርጅና መጣሁ እያለ ነው መሰል ...ሆነ ቀረ እስቲ እንደገና ሰብሰብ ለማለት እንሞክር ...ዋንሽ ጥሪ ቢያስተላልፍ ችላ ተብሎ ቀረ ...እስቲ እኔም ትግሉን ከራሴ ልጀምር እሞክራለሁ እስከዛው አባይ ቢቀር ጎጆዬን ልገንባ ...ፓን
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Next

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest