የሃበሻ ጀብዱ (አስተያየት መስጫ)

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby BelayTekalign » Wed Jan 18, 2012 6:28 am

እመቤት ሓያት 11
ጥያቄውን ያቀረብኩት እኮ መጽሐፉ በመከልከሉ እርግጠኛ ስላልሆንኩ ነው ። ምናልባት አንች ስለጉዳዩ የተሻለ ዜና ካለሽ ብታወጊኝ ።

ገዛ ሓያት የሜለውን ፊርማሽን ተከተልኩ .
http://hayet11.blogspot.com/

ስለ አንች ለማወቅ ፈልጌ ሳይሆን ሓ እንደዝያ ስትፃፍ አይቻት ስለማላውቅ ነው . በትርፍ ጊዜየ ግዕዝ አጠናለሁ . ሓ የምትባለውን ፊደል ያገኘኋት የቁራን አረብኛ መስጊድ ላይ ከ5 አመት ተማሪዎች ጋር ስቀራ ነው . ሐ . ፀ . ሠ ንም ከነዘመዶቻቸው አገኘኋቸው . እነዜህ ድምጾች በአማርኛው ጠፍተዋል . በትግሬ እና በትግሬ ምናልባትም በብሌን ይኖሩ ይሆናል .

May I switch to English...
Hebrew and Qoranic Arabic languages resemble our Ge'ez in a lot of ways. Some scholars suggest that Ge'ez is the mother tongue to Arabic, Aramaic (Jesus' toungue) and to Hebrew because some of its semantics are close to the west Semantic language like Akadian, Sumerian who had died by the time Hebrew and Arabic became languages. I don't want to crowd your literature forum with trivia but I think that ሓ has a lot to say for itself.
BelayTekalign
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 5
Joined: Sun Feb 11, 2007 9:59 am

Re: የሃበሻ ጀብዱ ተከለከለ ይባላል እውነት ነውን?

Postby ፓን ሪዚኮ » Wed Jan 18, 2012 7:45 am

BelayTekalign wrote:የሃበሻ ጀብዱ ኢትዮጵያ ውስጥ ተከልክሏል ይባላል:: እውነት ነውን? ከሁለት ወር በፊት የሃበሻ ጀብዱን እንድትገዛልኝ አንድ ዘመዴን ጠይቄ ያው በአገራችንን የአሰራር ቅልጥፍና ፍጥነት መልሱ በቅርብ ደረሰኝ:: እንደተነገረኝማ - መጽሐፉን መንግሥት ለቅሞ አቃጥሏል:: ሲያነብ ወይም ሲሸጥ የተገኘም በሕግ ይቀጣል አለችኝ:: እውነት ነውን? Are these people going NUTS?

እውነትስ ከሆነ መጽሐፉ በአሜሪካ ወይም በአውሮፓ ማግኘት ይቻላልን?

ያም ካልሆነ መጽሐፉን በቼክ ቋንቋ በኢንተርኔት ማግኘት ቢቻል በጉግል መተርጎምያ ቀስ በቀስ ለማንበብ ወስኛለሁ - እግረ መንገዴንም አዲስ ቋንቋ እዳስሳለሁ።

እርዳታችሁን እሻለሁ

በላይ ተካልኝ

ተጨማሪ

ለአቶ ፓኑ አባፈርዳ
እንዲት አገኘኸው V Zemi Krale Kralu / "In the land of the king of kings"" የሚለውን መጽሐፍ?
ሰላም በላይ...የሀበሻ ጀብዱ መጽሀፍ አልተከለከለም...ሲሸጥም ሆነ ሲለውጥ ተይዞ የታሰራ አንድም ሰው የለም ...ብቻ መጽሀፉ ተሸጦ ስላለከ ሁለተኛ እትም እየጠበቀ ነው ...ያው የመንግስት ቤት ስለሚታተም ትንሽ መጉላላቱ አይቀርም ...በተረፈ በንጉሰ ነገስቱ አገር የሚለው መጽሀፍ ...የመጨረሻዎቹን የንጉሰ ነገስቱን አገርና አገዛዝ የሚተርክ ማለፊያ መጽሀፍ ነው ...

ልጅ ተድላ ሀይሉ ...ስለ ቴኦ ግ/ስላሴ ...እስቲ ከሰሞኑ ቃርሜ ብቅ እላለሁ
መልካም ቀን
ፓኑ አባ ፈርዳ
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby Ahmed-1 » Wed Jan 18, 2012 9:24 am

ፓኑ ወረ ጃርሶ እንዴት ነህ የወንዜው!
መጻፉን እስካሁን ማግኘት አልቻልኩም....ባንተ መጻፍ ምክንያት ዘመድ አዘማዶቼንም አኩርፊያለሁ:: ሁለተኛውን እትም ግን በርሬም ቢሆን አመጣዋለሁ:: የኩማንዶ ልጆች እንዳለ ገዝተዉታል ይባላል:: የፊቼ ፒስታ መንገድ ላይ አቧራ እያነሳ የሚበር ሎንቺን አሁን የለም አሉ :wink:
Ahmed-1
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 174
Joined: Mon Mar 19, 2007 3:17 pm

Postby ሓየት11 » Wed Jan 18, 2012 6:03 pm

በትንሽ ማስተካከያ ልጀምር:: ስሜ ሓያት ሳይሆን ሓየት ነው::

ለዛ ነው ሴት የመሰልኩህ:: ቃሉ ትግርኛ ነው:: ብዙ ትርጉም አለው:: አንደኛው ትርጉሙ ግን 'አይበገሬ' ለማለት ነው :lol:

ሀያት ራሱ በትግርኛ ሲሆን በትክክል የሚጻፈውና ፕሮናውንስ የሚደረገው ሓያት ሲሆን ነው:: ሐያት, ሀያት, ወይም ሃያት አይባልም:: በአማርኛ ሁሉም ተመሳሳይ ናቸው:: በግዕዝና በትግርኛ ግን ሀ, ሃ, ሐ, ና ሓ የተለያየ አነባበብ ስላላቸው በተለያየ ሁኔታ እንጠቀምባቸዋለን::

በቅርብ ጊዜ ያነበብኩትን አንድ ድረገጽ ልጋብዝህ:: ጠቃሚ ነገሮችን ታገኝበታለህ:: ከዚህ በፊት ካላነበብከው ማለት ነው:: http://www.filepie.us/?title=Ge%27ez_alphabet

ሌላው ይህ መንግስት ስልጣን ከያዘ ብኋላ ባንዴራና የፖለቲካ ስርዓቱን ብቻ አይደለም የቀየረው:: ፊደሎቻችን ላይም መለስተኛ ጣልቃ ገብነት አሳይቷል:: ከትግርኛው የፊደል ገበታል (which was exactly the same as Amharic alphabet) አንዳንድ ፊደሎችን አንስቷል:: ከአማርኛውም እንዲሁ የተነሱ አሉ መሰለኝ:: ከትግርኛ ሠ, ኅ እና ጸ ተነስተዋል:: በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት የተማረ የትግራይ ተወላጅ እነዚህን ፊደላት አያውቃቸውም:: ወይም የጥንት ናቸው ብሎ ያስባል:: ምሳሌ እዚህ ዋርካ ብንወስድ ዳግማዊ ዋለልኝ የሚባለው ውርጋጥ ወያኔ 'ሠ' ን ሲጠቀምባት አታይም:: የሆነ ነጥብ በቅደም ተከተል ለማቅረብ ሲፈልግ ሀ, ለ, ሐ, መ ብሎ ረ ነው የሚለው:: ይህ ሠ ንጉሡ ስለሚባል የንጉሡን ስርዓት እንዳያስታውሳቸው ፈርተው ያነሱት ይመስላል :lol: 'ኅ' ደግሞ በግዕዙ ከእግዚአብኄርና ከኃይሉ ጋር የሚያያዝ ነገር ስላለው ለኤቲስቶች የሚመች አልሆነም:: የመጨረሻው ጸ ከ ፀ ጋር ድግግሞሽ በመሆኑ ምክንያት የተነሳ ይመስለኛል::

(ካልተሳሳትኩ ጸ ን ከትግርኛው ሲያነሱት ፀ ን ደግሞ ከአማርኛው አነሱት:: በዛ ምክንያትም መሰለኝ አንተም ይቺን ፀ እንደተረሳች ያያሀት::
ስለዚህ የፊደል ገበታው ፀ ያለበት ከሆነ ትግርኛ, ጸ ያለበት ከሆነ ደግሞ አማርኛ ነው እንበል እንዴ :?: )

BelayTekalign wrote:እመቤት ሓያት 11
ጥያቄውን ያቀረብኩት እኮ መጽሐፉ በመከልከሉ እርግጠኛ ስላልሆንኩ ነው ። ምናልባት አንች ስለጉዳዩ የተሻለ ዜና ካለሽ ብታወጊኝ ።

ገዛ ሓያት የሜለውን ፊርማሽን ተከተልኩ .
http://hayet11.blogspot.com/

ስለ አንች ለማወቅ ፈልጌ ሳይሆን ሓ እንደዝያ ስትፃፍ አይቻት ስለማላውቅ ነው . በትርፍ ጊዜየ ግዕዝ አጠናለሁ . ሓ የምትባለውን ፊደል ያገኘኋት የቁራን አረብኛ መስጊድ ላይ ከ5 አመት ተማሪዎች ጋር ስቀራ ነው . ሐ . ፀ . ሠ ንም ከነዘመዶቻቸው አገኘኋቸው . እነዜህ ድምጾች በአማርኛው ጠፍተዋል . በትግሬ እና በትግሬ ምናልባትም በብሌን ይኖሩ ይሆናል .

May I switch to English...
Hebrew and Qoranic Arabic languages resemble our Ge'ez in a lot of ways. Some scholars suggest that Ge'ez is the mother tongue to Arabic, Aramaic (Jesus' toungue) and to Hebrew because some of its semantics are close to the west Semantic language like Akadian, Sumerian who had died by the time Hebrew and Arabic became languages. I don't want to crowd your literature forum with trivia but I think that ሓ has a lot to say for itself.
ሓየት11
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2945
Joined: Sun Apr 06, 2008 7:34 pm
Location: ላን'ሊይ

Postby ፓን ሪዚኮ » Wed Jan 18, 2012 8:38 pm

Ahmed-1 wrote:ፓኑ ወረ ጃርሶ እንዴት ነህ የወንዜው!
መጻፉን እስካሁን ማግኘት አልቻልኩም....ባንተ መጻፍ ምክንያት ዘመድ አዘማዶቼንም አኩርፊያለሁ:: ሁለተኛውን እትም ግን በርሬም ቢሆን አመጣዋለሁ:: የኩማንዶ ልጆች እንዳለ ገዝተዉታል ይባላል:: የፊቼ ፒስታ መንገድ ላይ አቧራ እያነሳ የሚበር ሎንቺን አሁን የለም አሉ :wink:
ኩዩ አለስ እንዴ ባገር??? አዝናለሁ ...ለኔ ፕራግ የደረሱኝን ኮፒዎች ለወዳጆቼ እንኳን ሳላዳርስ አለቁብኝ ....በጎሀም ይሁን በሸገር ያሉ ዘመዶቼ ሲፈዙ መጽሀፉ ተሸጦ አለቀ ....አንዲት በቅርቡ አገር ቤ ደርሶ የመጣ ልጅ በ450 ብር ገዝቶ ያመጣልኝን መጽሀፍ ለአንድ ጉጉ ለሆነ የጥንት የቼኮዝሎቫኪያ ተማሪ ሽማግሌ ቃል ስለገባሁ ...ፓኑ አባ ፈርዳ ወረጃርሶ ቃሉን አያጥፍምና ለራሴም ባይኖረኝ ልልክለት ወሰንኩ ...ግን ግን እናንተ ገርበ ጉራቻዎች ሁለም የጎሀጺዮን ነገር አይጥማቹህም አይደል ? አሊያማ ገና ዱሮ ትገዛው ነበር ...ባልነግርህ ኖሮ ይቆጨኝ ነበር ..ግን ነግሬሀለሁ ...
በል ቻዎ
ፓኑ አባ ፈርዳ
ወረጃርሶ
ጎሀጺዮን
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ዲያስፖራ » Fri Jan 20, 2012 7:57 pm

:evil: መጽሀፉ ከብዙ ደካም በሁላ እጀ ቢገባም አንዳንድ የገጽ ጉድለቶች ይታዩበታል የገዛሁበት ዋጋ; በመጠበቅ ያቃጠልኩት ግዜ; ሰዎችን የተለማመጥኩበት ; እረ ስንቱ !! ይህ ሁሉ አልተሰማኝም ግን የተጎዳሁት በጥሩ ስሜት ላይ እያነበብኩ ሳለ ወደ 5ግጽ ተዘሎ በማግኘቴ ያዘንኩት እና የተሰማኝ ንዴት ከዛ በሁላ ለተፈጠሩት ሁሉ ድርጊት ተጠያቂ ማን ይሆን ??
ማንን ልክሰስ ተርጉአሚውን ??? አሳታሚውን ?? አከፋፋዩን ??
አሁን ማድረግ ያለብኝ እንደገና መጽሀፉን ልኬ ለውጡልኝ በህግ አምላክ ማለት ነው ??
ቀይ ባህር ድንበራችን ነው !!!!
I Love Ethiopia !!!
ዲያስፖራ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 781
Joined: Wed Apr 29, 2009 4:39 pm
Location: no

Postby ጌታ » Fri Jan 20, 2012 8:33 pm

ዲያስፖራ wrote::evil: መጽሀፉ ከብዙ ደካም በሁላ እጀ ቢገባም አንዳንድ የገጽ ጉድለቶች ይታዩበታል የገዛሁበት ዋጋ; በመጠበቅ ያቃጠልኩት ግዜ; ሰዎችን የተለማመጥኩበት ; እረ ስንቱ !! ይህ ሁሉ አልተሰማኝም ግን የተጎዳሁት በጥሩ ስሜት ላይ እያነበብኩ ሳለ ወደ 5ግጽ ተዘሎ በማግኘቴ ያዘንኩት እና የተሰማኝ ንዴት ከዛ በሁላ ለተፈጠሩት ሁሉ ድርጊት ተጠያቂ ማን ይሆን ??
ማንን ልክሰስ ተርጉአሚውን ??? አሳታሚውን ?? አከፋፋዩን ??
አሁን ማድረግ ያለብኝ እንደገና መጽሀፉን ልኬ ለውጡልኝ በህግ አምላክ ማለት ነው ??

ተርጓሚውማ የተሟላ መጽሐፍ እንዳስረከበ ያነበብነው ሰዎች ምስክር ነን:: ባይሆን የጎደሉትን ገጾች ለመካስ ያህል ፓኑ በስካይፒ የሚያነብልህን መንገድ እናመቻች :)
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3083
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby ሓየት11 » Fri Jan 20, 2012 9:22 pm

እኔም ተመሳሳይ ችግር ገጥሞኝ ነበር:: መጽሀፉ ስለ አቢቹ ጀብድነት የሚያወራበት ቦታ ላይ 5 ገጾች አልነበሩትም:: ምንም አማራጭ አልነበረኝም ማንበቤን ገፋሁበት::ዲያስፖራ wrote::evil: መጽሀፉ ከብዙ ደካም በሁላ እጀ ቢገባም አንዳንድ የገጽ ጉድለቶች ይታዩበታል የገዛሁበት ዋጋ; በመጠበቅ ያቃጠልኩት ግዜ; ሰዎችን የተለማመጥኩበት ; እረ ስንቱ !! ይህ ሁሉ አልተሰማኝም ግን የተጎዳሁት በጥሩ ስሜት ላይ እያነበብኩ ሳለ ወደ 5ግጽ ተዘሎ በማግኘቴ ያዘንኩት እና የተሰማኝ ንዴት ከዛ በሁላ ለተፈጠሩት ሁሉ ድርጊት ተጠያቂ ማን ይሆን ??
ማንን ልክሰስ ተርጉአሚውን ??? አሳታሚውን ?? አከፋፋዩን ??
አሁን ማድረግ ያለብኝ እንደገና መጽሀፉን ልኬ ለውጡልኝ በህግ አምላክ ማለት ነው ??
ሓየት11
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2945
Joined: Sun Apr 06, 2008 7:34 pm
Location: ላን'ሊይ

Postby ዲያስፖራ » Fri Jan 20, 2012 9:57 pm

ምንም ቢሆን ክሴን አላነሳም :: ወፍራም ጠበቃ እይፈለኩ ነው :: እናተው በጉርሻ (እይተነበበላችሁ) ኑሩ እነ እንደዛ አላደኩም ፍትፍቱን (እያነበብኩ) ነው ያደኩት ስለዚህ በህግ መብቴን አስከበራለሁ ::
የተገመጠ ሳንድዊች (የጎደለ ገጽ) አንብብ(ብላ) የምትሉኝ በፍጹም አልሰማም ::
ያደኩት ሙሉ አሮስቶ ያልተነካካ ከህትመት እንደወጣ በትኩሱ እይበላን ነው ያደግነው ::
በህይወቴ የምጠላው ልክስክስ አመጋገብ ነው ሳንሱር የሚባል ነገር ፈጽሞ አልወድም የተሸራረፈ እና ስርስዝ ድልዝ የተገነጠለ መጽሀፍት ባልጀመረው ደስ ይለኛል :: :evil:
ቀይ ባህር ድንበራችን ነው !!!!
I Love Ethiopia !!!
ዲያስፖራ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 781
Joined: Wed Apr 29, 2009 4:39 pm
Location: no

Postby ፓን ሪዚኮ » Sat Jan 21, 2012 7:33 am

ዲያስፖራ wrote:ምንም ቢሆን ክሴን አላነሳም :: ወፍራም ጠበቃ እይፈለኩ ነው :: እናተው በጉርሻ (እይተነበበላችሁ) ኑሩ እነ እንደዛ አላደኩም ፍትፍቱን (እያነበብኩ) ነው ያደኩት ስለዚህ በህግ መብቴን አስከበራለሁ ::
የተገመጠ ሳንድዊች (የጎደለ ገጽ) አንብብ(ብላ) የምትሉኝ በፍጹም አልሰማም ::
ያደኩት ሙሉ አሮስቶ ያልተነካካ ከህትመት እንደወጣ በትኩሱ እይበላን ነው ያደግነው ::
በህይወቴ የምጠላው ልክስክስ አመጋገብ ነው ሳንሱር የሚባል ነገር ፈጽሞ አልወድም የተሸራረፈ እና ስርስዝ ድልዝ የተገነጠለ መጽሀፍት ባልጀመረው ደስ ይለኛል :: :evil:
ጉረኛ ነገር ነሽ...ይሄን ግዜ እኮ ...በቦቆሎ ቂጣ አድገሽ ይሆናል ...ሆነ ቀረ ...ጎዶሎውንም ቢሆን በወጉ ካነበብከው ላንተ አሩስቶ ነው ...ለማንኛውም ...ለጠበቃ የምታወጣውን ብር የቀን ህልምህን አሩስቶ ያደረም የሰነበተም ቢሆን ብላበት ...መልክም ምግብ እና ንባብ
ፓኑ አባ ፈርዳ
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby Ahmed-1 » Sat Jan 21, 2012 8:47 am

ፓን ሪዚኮ wrote:
Ahmed-1 wrote:ፓኑ ወረ ጃርሶ እንዴት ነህ የወንዜው!
መጻፉን እስካሁን ማግኘት አልቻልኩም....ባንተ መጻፍ ምክንያት ዘመድ አዘማዶቼንም አኩርፊያለሁ:: ሁለተኛውን እትም ግን በርሬም ቢሆን አመጣዋለሁ:: የኩማንዶ ልጆች እንዳለ ገዝተዉታል ይባላል:: የፊቼ ፒስታ መንገድ ላይ አቧራ እያነሳ የሚበር ሎንቺን አሁን የለም አሉ :wink:
ኩዩ አለስ እንዴ ባገር??? አዝናለሁ ...ለኔ ፕራግ የደረሱኝን ኮፒዎች ለወዳጆቼ እንኳን ሳላዳርስ አለቁብኝ ....በጎሀም ይሁን በሸገር ያሉ ዘመዶቼ ሲፈዙ መጽሀፉ ተሸጦ አለቀ ....አንዲት በቅርቡ አገር ቤ ደርሶ የመጣ ልጅ በ450 ብር ገዝቶ ያመጣልኝን መጽሀፍ ለአንድ ጉጉ ለሆነ የጥንት የቼኮዝሎቫኪያ ተማሪ ሽማግሌ ቃል ስለገባሁ ...ፓኑ አባ ፈርዳ ወረጃርሶ ቃሉን አያጥፍምና ለራሴም ባይኖረኝ ልልክለት ወሰንኩ ...ግን ግን እናንተ ገርበ ጉራቻዎች ሁለም የጎሀጺዮን ነገር አይጥማቹህም አይደል ? አሊያማ ገና ዱሮ ትገዛው ነበር ...ባልነግርህ ኖሮ ይቆጨኝ ነበር ..ግን ነግሬሀለሁ ...
በል ቻዎ
ፓኑ አባ ፈርዳ
ወረጃርሶ
ጎሀጺዮን

ፓኑ ጥፋቱ የኔ ነው:: ያሳፈረኝ ደግሞ አስር የሚሆኑ ወዳጆቼን "በኔ ተዉት...ተርጓሚው ባለንጀራዬ ነው.. የጎሐ ልጅ" ብዬ መጻህፍቶቹን በስጦታ መልክ ለማደል ስፎልል- ጉራ የምለማመድባቸው ይመስል... ስለ 2ኛው እትም ሹክ እንልሀለን ያሉኝን ያገርቤት ሾካኮች አላምናቸውምና አደራህን ጎሐው.....
Ahmed-1
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 174
Joined: Mon Mar 19, 2007 3:17 pm

Postby ዘርዐይ ደረስ » Sat Jan 21, 2012 5:03 pm

ፓን ሪዚኮ wrote:
ዲያስፖራ wrote:ምንም ቢሆን ክሴን አላነሳም :: ወፍራም ጠበቃ እይፈለኩ ነው :: እናተው በጉርሻ (እይተነበበላችሁ) ኑሩ እነ እንደዛ አላደኩም ፍትፍቱን (እያነበብኩ) ነው ያደኩት ስለዚህ በህግ መብቴን አስከበራለሁ ::
የተገመጠ ሳንድዊች (የጎደለ ገጽ) አንብብ(ብላ) የምትሉኝ በፍጹም አልሰማም ::
ያደኩት ሙሉ አሮስቶ ያልተነካካ ከህትመት እንደወጣ በትኩሱ እይበላን ነው ያደግነው ::
በህይወቴ የምጠላው ልክስክስ አመጋገብ ነው ሳንሱር የሚባል ነገር ፈጽሞ አልወድም የተሸራረፈ እና ስርስዝ ድልዝ የተገነጠለ መጽሀፍት ባልጀመረው ደስ ይለኛል :: :evil:
ጉረኛ ነገር ነሽ...ይሄን ግዜ እኮ ...በቦቆሎ ቂጣ አድገሽ ይሆናል ...ሆነ ቀረ ...ጎዶሎውንም ቢሆን በወጉ ካነበብከው ላንተ አሩስቶ ነው ...ለማንኛውም ...ለጠበቃ የምታወጣውን ብር የቀን ህልምህን አሩስቶ ያደረም የሰነበተም ቢሆን ብላበት ...መልክም ምግብ እና ንባብ
ፓኑ አባ ፈርዳ

ሰላም ፓን ሪዚኮ:-

እየጠፋህ አስቸገርክ እኮ! ዝናውና ገንዘቡ ነው :lol: ወይስ ሌላ ምክንያት?ለማንኛውም አንባቢዎችህ በርካታ ጥያቄዎች አለንና በቂ ጊዜ ሲኖርህ ብቅ ብለህ አስተናግደን::

በነገራችን ላይ ዲያስፖራ ትንሽ ስላበዛው የሰጠኸው መልስ ቢያስቀኝም ይህን ርእስ ስከፍት እንዳልኩት እኔም ተመሳሳይ ችግር ገጥሞኛል::የጎደሉት ገፆች ላይ ምን ይሆን ያለው እያልክ ስታሰላስል ከመፅሐፉ የምታገኘው እርካታ ላይ በመጠኑም ቢሆን አሉታዊ ተፅዕኖ አለው::እኔ እንኳ መፅሐፉን ያነበብኩት በውሰት ነበር ለመግዛት አስቤ ግን የዕድል ጉዳይ ሆኖ ተመሳሳይ ገፆች የጎደሉት መፅሐፍ ቢያጋጥመኝ የባሰ እንዳልናደድ ብዬ እያመነታሁ ነበር::ሁለተኛው እትም ላይ እንዲህ ዓይነትና ሌሎችም የህትመት ችግሮች እንዳይኖሩ ለጉዳዩ ብቸኛ ሃላፊነት ያለበት ማተሚያ ቤት እንደሚያስብበት ተስፋ አደርጋለሁ::ገዝተው የሚልኩልንን እንዳናመላልስ እትሙ ገበያ ላይ ሲውል እንደምታሳውቀንም እርግጠኛ ነኝ::

በተረፈ ከዋርካ ፈላሾች ጋር እርቅ አወረድክ ወይስ እንደተኳረፋችሁ ነው::መፅሐፉን በጕጕት ሲጠብቁ ቆይተው እንደዚያ ሞራላቸውን የሚነካ ነገር ስትናገር ቢያድሙብህ አይገርምም::

ቆንጂት 09 እንደፃፈችው:-

ቱ ቱ በስመአም እንዲህ ለሚጠላን ሰውየ ነው ያበሻ ጀብዱ ብሎ ያሳተመውን መጽሀፍ መግዛቴ በቃ ነገ በጥዋት ሳይነጋ አየኛን ጎጆ ሳያቃጥል መጽሀፉን አቃጥየ ፒክኒክ አዛጋጀበታልሁ ዋ ገንዘብ ያለቦታው ወጣ ፕስስስስ መሳሳት ወይኔ ብሬ ያለቦታው ወጣሽ እንደ ስሙ ፕን ብለሽ ጠፋሽ

ሻሎም እንግዳ ሀግ ሰሜያህ ልሀ ወንድም ....ለኮል አም እስራእል
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1311
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Postby ዲያስፖራ » Sat Jan 21, 2012 5:38 pm

አውቅሽ አወቅሽ ቢላት የባላን መጽሐፍ አጠበች ትላንት አንድ ትርጉም ተረጎምክና እንዲህ ያቀባረረህ ደራሲ ብትሆን ምን ሊውጠን ነው ? እነ አቤ ጉበኛ ምን ይበሉ ? እነ ሀዲስ አለማየሁ ምን ይበሉ ? በአሉ ግርማ ምን ይበሉ ?? ምን አልፋህ ይህን ሳንሱር ተድረጎ ከማሀክል የውጣ መጽሀፍ አቃጥለዋለሁ እንደ ታሪክ መጻህፍት ልቅበለው አልችልም :: ይፊደል ግድፈት ይሁን ብለን በጸጋ በተቀበልን ሳያንስ በሳፖታጅ በአሻጥር ሆን ተብሎ ይጎደለ ገጽ መጽሐፍ ማሰራጨት ሆን ተብሎ ታሪክን ለማጣመም ይተድረገ ትልቅ ስህእተት ነው :: አልምረውም አቃጥለዋል ::
ቀይ ባህር ድንበራችን ነው !!!!
I Love Ethiopia !!!
ዲያስፖራ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 781
Joined: Wed Apr 29, 2009 4:39 pm
Location: no

Postby ሓየት11 » Sat Jan 21, 2012 8:00 pm

አስተዳደግህ አስቀናኝ በጣም :lol: አፌን ከፍቼ ልሀጬ እየተዝረከረከ ነው :lol: :lol: አሮስቶ :?: አሻሮ ልትል አዳልጦህ እንዳይሆን ቂቂቂቂቂ

ዲያስፖራ wrote:ምንም ቢሆን ክሴን አላነሳም :: ወፍራም ጠበቃ እይፈለኩ ነው :: እናተው በጉርሻ (እይተነበበላችሁ) ኑሩ እነ እንደዛ አላደኩም ፍትፍቱን (እያነበብኩ) ነው ያደኩት ስለዚህ በህግ መብቴን አስከበራለሁ ::
የተገመጠ ሳንድዊች (የጎደለ ገጽ) አንብብ(ብላ) የምትሉኝ በፍጹም አልሰማም ::
ያደኩት ሙሉ አሮስቶ ያልተነካካ ከህትመት እንደወጣ በትኩሱ እይበላን ነው ያደግነው ::
በህይወቴ የምጠላው ልክስክስ አመጋገብ ነው ሳንሱር የሚባል ነገር ፈጽሞ አልወድም የተሸራረፈ እና ስርስዝ ድልዝ የተገነጠለ መጽሀፍት ባልጀመረው ደስ ይለኛል :: :evil:
ሓየት11
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2945
Joined: Sun Apr 06, 2008 7:34 pm
Location: ላን'ሊይ

Postby ፓን ሪዚኮ » Sat Jan 21, 2012 11:18 pm

ሓየት11 wrote:አስተዳደግህ አስቀናኝ በጣም :lol: አፌን ከፍቼ ልሀጬ እየተዝረከረከ ነው :lol: :lol: አሮስቶ :?: አሻሮ ልትል አዳልጦህ እንዳይሆን ቂቂቂቂቂ

ዲያስፖራ wrote:ምንም ቢሆን ክሴን አላነሳም :: ወፍራም ጠበቃ እይፈለኩ ነው :: እናተው በጉርሻ (እይተነበበላችሁ) ኑሩ እነ እንደዛ አላደኩም ፍትፍቱን (እያነበብኩ) ነው ያደኩት ስለዚህ በህግ መብቴን አስከበራለሁ ::
የተገመጠ ሳንድዊች (የጎደለ ገጽ) አንብብ(ብላ) የምትሉኝ በፍጹም አልሰማም ::
ያደኩት ሙሉ አሮስቶ ያልተነካካ ከህትመት እንደወጣ በትኩሱ እይበላን ነው ያደግነው ::
በህይወቴ የምጠላው ልክስክስ አመጋገብ ነው ሳንሱር የሚባል ነገር ፈጽሞ አልወድም የተሸራረፈ እና ስርስዝ ድልዝ የተገነጠለ መጽሀፍት ባልጀመረው ደስ ይለኛል :: :evil:
አዬ ወዳጄ አሻሮዋም እኮ ቢሆን በህልሟ ሳይሆን አይቀርም ....እስቲ ከሰሞኑ በሰፊው እንጫወታለን ...እስከዛው ሰላም
ፓን
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests