የሃበሻ ጀብዱ (አስተያየት መስጫ)

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ጌታ » Mon Aug 08, 2011 2:23 pm

ውድ ፓኑ

መጽሀፏ እንደወጣች ባካባቢዬ ባለመግኘቴ ትዕግስት በማጣት ይፈጥናል ብዬ ካገር ቤት አስልኬ በብርሃን ፍጥነት አሁን ገና እጄ ገባች (በመርከብ ቢመጣ እንኳን ይህን ያህል አይቆይም :lol: ):: አዶልፍ ፓርስላክ ከጦራችን መሃል ሆኖ የዘገበው ታሪክ እጅጉን ልብ የሚነካ ነው:: አባቶቻችን በጦር በጎራዴ ጣልያንን እንዴት እንዳርበደበዱ በስዕላዊ መልኩ አስቀምጦታል:: ሀበሻን ጀግንነቱን ከነደካማ ጎኑም ጭምር (ጉልበት ሥራ አለመውደድ ) ቁጭ አድርጎታል:: በጀግኖቹ መላው ኢትዮጵያውያን ስኮራ ከፋሽስት ወግነው ወንድሞቻቸውን በወጉት ባንዳዎች አዝኛለሁ.....በግኛለሁም::

መጽሀፉን ገና ባልጨርሰውም ቀጣዩ ዕቅዴ በዚያ ጦርነት ዙሪያ የተጻፉ ፅሁፎችን እያፈላለጉ ማንበብ ነው:: ፓኑ መጽሀፏ እንዴት ፍቅር እንዳስያዘችህ አሁን በደንብ ገባኝ:: ስለተረጎምክልን ታላቅ ምስጋናዬን እነሆ::
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3042
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby ፓን ሪዚኮ » Mon Aug 08, 2011 9:47 pm

መሪጌታ ስለ ምስጋናው እኔም ከፍ ያለ ምስጋናዬን እያቀረብኩ ...ስትጨርስ ይበልጥ በሰፊው እናወጋለን ብዬ አስባለሁ...መርከብ አልከው ....እረ በግር የሚሄድ ሰው ቢኖር ኖሮ ቀድሞ ይደርስ ነበር ...ለሰው ሁሉ ቃል ገብቼ ዋሾ ሆኔ ቀቼብሀለሁ ...ለነገሩ በገዛ ዳቦዬ ልብ ልቡን አጣሁት ያለቺው አሮጊት ብጤ ነው ...በል ሌላ ነገር ሳላመጣ ላምልጥ ...
ፓኑ አባ ፈርዳ
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ጌታ » Tue Aug 09, 2011 12:20 am

ፓን ሪዚኮ wrote:መሪጌታ ስለ ምስጋናው እኔም ከፍ ያለ ምስጋናዬን እያቀረብኩ ...ስትጨርስ ይበልጥ በሰፊው እናወጋለን ብዬ አስባለሁ...መርከብ አልከው ....እረ በግር የሚሄድ ሰው ቢኖር ኖሮ ቀድሞ ይደርስ ነበር ...ለሰው ሁሉ ቃል ገብቼ ዋሾ ሆኔ ቀቼብሀለሁ ...ለነገሩ በገዛ ዳቦዬ ልብ ልቡን አጣሁት ያለቺው አሮጊት ብጤ ነው ...በል ሌላ ነገር ሳላመጣ ላምልጥ ...
ፓኑ አባ ፈርዳ

የመርከቡ ነገር እንዴት መሰለህ:: እንዳልኩህ ይፈጥናል ብዬ ካገር ቤት በሚመጣ ሰው ነበር የላኩት:: መልዕክተኛው ቆይታውን አራዝሞ ከርሞ መጣልህ እንጂ:: እኔማ ቀረ ብዬ ነበር::
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3042
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby እንሰት » Mon Aug 15, 2011 5:38 am

አባ ፈርዳ
መጣፍህ ተነባ [ጀንዲ ማከሉን በስላቅ ለመናገር ነው] ምስክር አግኝታለች::ያው እንግዲህ ምስክርነት በፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም::

ስለአድዋው ጦርነት ምስክርነት የሚሰጠን ገለልተኛ ታዛቢ እስክናገኝ ስለማይጨው ጦርነት የነበረ የዓይን ምክስር አንድ በቅርቡ ያነበብሁት መጽሐፍ ትዝ አለኝ፤ አንድ የቼኮዝላቫኪያ ጎበዝ የጻፈውን የሃበሻ ጀብዱ የሚል መጽሐፍ ተጫነ ጆብሬ መኮንን የተባለ ሰው የተረጎመውን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አሳትሞታል፤ አቶ ስብሓት ብቻ ሳይሆን ማንበብ የሚችል ሁሉ ሊያነብበው የሚገባ መጽሐፍ ነው፤ እኔ ፈረንጅ ስለኢትዮጵያ የፃፈውን ማንበብ ከተውሁ ብዙ ዓመታት ሆኖኛል፡፡ ይህንን ግን በአንድ ቀን ተኩል ጨረስሁት፤ የኢትዮጵያን ዘማቾች ከኋላ እያጠቁ ስለነበሩት ..የትግራይ ሽፍቶች.. ማን ይናገር? የነበረ፤ ነውና እንዲህ ይላል፡-

….የትግራይ ሽፍቶች) ለምን ወንድሞቻቸውን ይገድላሉ?… ከመሀል አገር ስድስትና ሰባት ወር ሙሉ ፍዳውን እያየ ሲጓዝ ከርሞ እዚህ የደረሰው ወንድማቸው፣ የነዚህን ምስኪኖች ህይወትና ንብረት ከጠላት ለመከላከል የገዛ ህይወቱን አልጋ ላይ ጥሎ፣ ቤት ንብረቱን በትኖ መከራውን ባየ ለምን ይገድሉታል?..
እነዚህ ሽፍቶች ወንድሙን የገደሉበት አብቹ የሚባል የአስራ ስድስት ዓመት የሰላሌ ዘማች በጣም ተናዶ የራሱን የግል ቡድን አቋቁሞ ያሳድዳቸው ነበር፡፡

ከዚያም በላይ እህል ውሃ ለዘማቹ እንዳይሸጡ ኢጣልያኖች በመከልከላቸው ዘማቾቹ ችግር ነበረባቸው፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ከዚህ በላይ ለመናገር አልፈልግም፤ ነገር ግን ይህንን እውነት ለመሸፈን በመሞከር የመሀል አገሩን ሰው መወንጀል ትክክል አይደለም፤ እውነት ተደብቆ አይቀርም፡፡

እንነጋገር ማለት አንድም ሆነ ሁለት የጋራ ችግር አለን ማለት ነው፡፡ እንነጋገር ማለት የጋረ አገር፣ የጋራ ወገን፣ የጋራ ሀብት፣ የጋራ ታሪክ፣ የጋራ ራዕይ አለን ብለን ማመን ነው፡፡ እንነጋገር ማለት እውነትን በማስረጃ አስደግፎ ነው፤ እንነጋገር ማለት እንግባባ ማለት ነው፤ እንግባባ ማለት ባንስማማም እንፋቀር፣ አንሸዋወድ፣ አናስሸብር ማለት አይደለም፡፡

http://www.ecadforum.com/Amharic/amharic-articles/597/
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby ጌታ » Wed Aug 17, 2011 5:16 pm

የሀበሻ ጀብዱን አጣጥሜ ከጨረስኳት ሰነባበትኩ:: እንሰት ከላይ የጠቀሰው የፕሮፌሰር መስፍን አስተያየት ዋርካ ፖለቲካ ላይ ሰዉን እያከራከረው ነው::
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3042
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby እንሰት » Sat Aug 20, 2011 7:42 am

ጌታ wrote:የሀበሻ ጀብዱን አጣጥሜ ከጨረስኳት ሰነባበትኩ:: እንሰት ከላይ የጠቀሰው የፕሮፌሰር መስፍን አስተያየት ዋርካ ፖለቲካ ላይ ሰዉን እያከራከረው ነው::

ወንድም ጌታ
አንብቦ ዝም አለ እንዴ? እስኪ ለማንበብ አቅም ላጣን የሚሆን ነገር ጣል ጣል አርግብን እንጂ?
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby ጌታ » Sun Aug 21, 2011 1:10 pm

እንሰት wrote:
ጌታ wrote:የሀበሻ ጀብዱን አጣጥሜ ከጨረስኳት ሰነባበትኩ:: እንሰት ከላይ የጠቀሰው የፕሮፌሰር መስፍን አስተያየት ዋርካ ፖለቲካ ላይ ሰዉን እያከራከረው ነው::

ወንድም ጌታ
አንብቦ ዝም አለ እንዴ? እስኪ ለማንበብ አቅም ላጣን የሚሆን ነገር ጣል ጣል አርግብን እንጂ?

ወዳጄ እንሰት

ጊዜ ኖሮኝ ስለመጽሐፉ ወይም ስለታሪኩ ብዙ ብል ደስ ባለኝ:: ባጭሩ ከልጅነቴ ጀምሮ ስሰማው ያደኩትን የአርበኞቻችንን ጀግንነት ከባዕድ አፍ በመስማቴ ደስ ብሎኛል:: በጣም ያሳዘነኝና ያንገበገበኝ ነገር ጥልያን ያንን ባዶ እጁን ሊዋጋ የወጣ ጀግና ሕዝብ ከመፍራቱ ብዛት በምንም ደረጃ በማይመጣጠን ዘመናዊ መሳሪያ መግጠሙ አንሶት የራሱን ወንድሞች ደልሎና አስታጥቆ በየአቅጣጫው ጨፈጨፈው አስጨፈጨፈው:: ጣልያኖች በዚህ የፈሪ ዱላቸው ዘለዓለም ሊያፍሩበት ይገባል:: ይህን ጉዳቸውን ግን ምን ያህል ሕዝባቸው እንደሚያውቀው በበኩሌ አላውቅም:: ይቺንም ታሪክ አዶልፍ ፓርልሳክ ማውጣቱ ጥሩ ነገር ነው:: (በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ ካምስት ዓመት በኋላም ቢሆን ተባረዋል - የታባታቸው!)

ሌላ ደግሞ በደርግ ዘመን የፖለቲካ ይሁን የታሪክ አስተማሪዎቼ ኃይለስላሴ ከማንኛውም የኢትዮጵያ ነገስታት በተለየ መልኩ ጦራቸውን ሳይመሩ በጅቡቲ በኩል ወደ አውሮፓ ፈርጥጠው በኋላ ድል ሲገኝ ተመለሱ ብለው እንደነገሩኝ አስታውሳለሁ:: ይህን መጽሐፍ ካነበብኩ በኋላ ግን እውነታውን ተረድቻለሁ:: ኃይልዬ ካገር የወጡት ጦራቸው ከተፈታ በኋላ ነው:: ከመጀመሪያውም ጀምሮ በዲፕሎማሲ እንደማመናቸው ሲሸነፉ ለተጨማሪ ጥረት ወደ ኃያላን አገሮች መሄዳቸው ብልህነትን እንጂ ፍርሃትን አያመለክትም:: እርግጥ ነው እዚህ መጽሐፍ ላይ ደራሲው ንጉሱ ከመጀመሪያው ጀምሮ ከጦርነት ይልቅ በዲፕሎማሲ መፍትሄ ይመጣል ብለው የራስ ካሳን ጦር ጥሩ አጋጣሚዎች ሲገኙ ከማጥቃት ይልቅ እንዲከላከሉ ብቻ በማዘዛቸው የአድዋው ዓይነት ድል እንደቀረብን ያስባል::

-----------------------------

የማንበብ አቅም አጣን ላልከው አጋጣሚ አንድ አካባቢ ከሆንን እንዳውስህ ካልሆነም በሌላ መልኩ እንድታነብ እንድሞክር በግል መልዕክቴ ሹክ በለኝ::
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3042
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby እንሰት » Thu Aug 25, 2011 6:30 am

እጅ ነስቻለሁ ለሀሳብህ:: አቅምን በጥሬው በውሰትም በ ሌላም በኩል (አባ ፈርዳ እንዳይሰማ) ማጠናከር ይቻላል አይደል:: የሚመቸኝን በግል መልክት አሳውቄሀለሁ::

በነካ እጅህ ትንሽ ከመጽሀፉ አንዳንድ በለን::
አክባሪህ
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby ሾተል » Thu Aug 25, 2011 1:43 pm

በመጀመርያ ደረጃ ለተከበረው ወንድማችንለፕራጉ ፈረሰኛ ለአባ ፈርዳ የከበረ ሰላምታየን ሳቀርብ አውቶግራሙን አክሎ የስራው ውጤት የሆነውን ስራውን በስጦታ በራሱ ገንዘብ መላክያውን ከፍሎ ባድራሻዬ ይኼንን የአበሻ ጀብዱ የሚሉትን ድንቅ የታሪክ መጽሀፍ ስለላከልኛ በስጦታ ለክብርነታችን ስላበረከተልን እጅግ የላቀ ወንድማዊ በፍቅር የተለወሰ ምስጋናዬን ለአባፈርዳ በዚህ አጋጣሚ ሳቀርብ በኩራት ነው::

አባ ፈርዳ ይኼንን ድንቅ መጽሀፍ በስጦታ መልክ ስለሰጠኸኝ እግዚአብሄር ይስጥልኝ::መቼም እንደተጫወትነው ይኽንን መጽሀፍ ለመተርጎም ምን አልባት ከደራሲው ከሚስተር አዶልፍ ፓርለስካ የበለጠ እንጂ ያልተናነሰ ጉልበት እንዳወጣኽ ነው:.ምን አልባት ይኸንን የታሪክ መጽሀፍ አንባቢዎች ሲያነቡ እንደወረደ የተረጎምከው ይመስላቸው ይሆናል.....መቼም በስልክ እንደተጫወትነውና ተይቄኽ እንደነገርከኝ ደራሲው በራሳቸው ቋንቋና ባህላዊ ዘይቤ የጻፉትን መጽሀፍ አንተ ደግሞ በዛን ወቅት በኢትዮዽያዊያን ባህልና የአነጋገር ዘይቤ ቀይረኽ ለመጻፍ ስትል ብዙ ጉልበቶችን እንዳወጣኽ ነው::እውነቴን ነው የምልው ድካምህ ከሚገርም ውጤት ጋር ተሳክቶለታል ነው የምልኽ::ፈረንጅ የጻፈው መጽሀፍ ሳይሆን አበሻ እዛው ሆኖ ለዛውም አንተው እራስኽ እዛው ሆነኽ የጻፍከው ነው የሚመስለው::ታድያ በዚህ ልትኮራ ይገባሀል::

መጽሀፉ መቼም ምንም የማይወጣለት ሰላዊ መግለጫው የትየለሌ የሆነና ያንን ወቅት በአይነ ህሊናችን እንድናይ የሚረዳ መጽሀፍ ስለሆነ ለደራሲውና ላንተ ለተርጎአሚው ከፍተኛ አድናቆቴን አቀርባለሁ::

በመቀጠል ጌታና እንሰት ይኸንን መጽሀፍ አግኝተው ለማንበብ በጣም መጉዋጉዋታቸውን ስላየሁ ባለፈው ሰሞን እዚህ በሳምንት አንዴ እንደ ባግዳድ የምቆጣጠረው ራድዮ ጣብያችን ላይ ከመጽሀፉ ውስጥ አንድ ምእራፍ ነቅሼ አንብቤ ነበርና ጌታና እንሰት መጽሀፉ እጃችሁ እስኪገባ ድረስ ያለውን የወረወረ ....እንደሚባለው ያለኝን አካፍያችሁዋለሁና በሉ ከታች የምለጥፈው ሊንክ ጋር ተጠነቋቁላችሁ አድምጡ::

በዚህ አጋጣሚ ከቴርቶጋዳ ቀጥሎ ኢትዮድያ ውስጥ ትልቅ ቦታ ተሰጥቶት ስለ ድንቅነቱ የሚወራው መጽሀፍ ይኼ የአዶልፍ ፓርለስካና የ አባ ፈርዳ መጽሀፍ መሆኑንና ከህጻን እስከ ትልቁ አንብብ ብሎ የሚመክርህ መጽሀፍ የአበሻ ጀብዱን እንደሆነ በምስክርነት እናገራለሁ:.(ፕሮፌሰር መስፍን ይኼንን መጽሀፍ በሚገባ ማድነቃቸውን ያስታውሷል)

የሀበሻ ጀብዱን ለማዳመጥ ይኸንን ተጭነው ከዛ Audio 1ንድ የሚለውን ይጫኑ ይጫኑ

መልካም ጊዜ ይሁንላችሁ::

ሾተል ነን
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9653
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ጌታ » Thu Aug 25, 2011 2:32 pm

ሾተል ወንድማችን እንሰት የጠየቀኝን ጥያቄ በአግባቡ ስለመለስክልኝ አመሰግናለሁ:: የኔና የእንሰትን ውይይት ከላይ አይተኸው እንደሆነ እኔ መጽሀፏን አጣጣሜ አንብቤያታለሁ:: ጊዜና ሁኔታ ከፈቀደልኝ ያንተንም ኦዲዮ ለማዳመጥ እሞክራለሁ::
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3042
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby ሾተል » Thu Aug 25, 2011 2:34 pm

ጌታ wrote:ሾተል ወንድማችን እንሰት የጠየቀኝን ጥያቄ በአግባቡ ስለመለስክልኝ አመሰግናለሁ:: የኔና የእንሰትን ውይይት ከላይ አይተኸው እንደሆነ እኔ መጽሀፏን አጣጣሜ አንብቤያታለሁ:: ጊዜና ሁኔታ ከፈቀደልኝ ያንተንም ኦዲዮ ለማዳመጥ እሞክራለሁ::

ሰላም ጌታ....ልፋቴ ከንቱ ሆነ በለኝ....ሰሞኑን አላነበብኩም....ባለፈው መጽሀፉን ማንበብ እንደምትፈልግ ጽፈው አንብቤ ስለነበር ባለፈ ክረምት ቤት ልሰራ ብዬ ነው.....በል እንሰት ብቻውን ይኮምኩም::

አንተ ግን ደህና ነኽ?እስቲ ያወጋችሁትን ወደላይ ወጥቼ ላንብበው::

ሾተል ነን
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9653
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ጌታ » Thu Aug 25, 2011 2:45 pm

ሾተል wrote:
ጌታ wrote:ሾተል ወንድማችን እንሰት የጠየቀኝን ጥያቄ በአግባቡ ስለመለስክልኝ አመሰግናለሁ:: የኔና የእንሰትን ውይይት ከላይ አይተኸው እንደሆነ እኔ መጽሀፏን አጣጣሜ አንብቤያታለሁ:: ጊዜና ሁኔታ ከፈቀደልኝ ያንተንም ኦዲዮ ለማዳመጥ እሞክራለሁ::

ሰላም ጌታ....ልፋቴ ከንቱ ሆነ በለኝ....ሰሞኑን አላነበብኩም....ባለፈው መጽሀፉን ማንበብ እንደምትፈልግ ጽፈው አንብቤ ስለነበር ባለፈ ክረምት ቤት ልሰራ ብዬ ነው.....በል እንሰት ብቻውን ይኮምኩም::

አንተ ግን ደህና ነኽ?እስቲ ያወጋችሁትን ወደላይ ወጥቼ ላንብበው::

ሾተል ነን

ልፋትህ በጭራሽ ከንቱ አልሆነም:: እኔ በጠየቅሁት ብዙ እህቶቻችን የማዳመጥ ዕድሉን ስለሚያገኙ በዛ ይካካሳል (ስለወንዶቹ አያገባንም ብዬ ነው :lol: :lol: )

እኔ እጅጉን ደህና ነኝ:: አገሩን ቀዬውን ሰላም አገኘኸው? ልጆቹ ከብቶቹ ሁሉ ደህና?
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3042
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby ሾተል » Thu Aug 25, 2011 2:54 pm

ጌታ wrote:
ሾተል wrote:
ጌታ wrote:ሾተል ወንድማችን እንሰት የጠየቀኝን ጥያቄ በአግባቡ ስለመለስክልኝ አመሰግናለሁ:: የኔና የእንሰትን ውይይት ከላይ አይተኸው እንደሆነ እኔ መጽሀፏን አጣጣሜ አንብቤያታለሁ:: ጊዜና ሁኔታ ከፈቀደልኝ ያንተንም ኦዲዮ ለማዳመጥ እሞክራለሁ::

ሰላም ጌታ....ልፋቴ ከንቱ ሆነ በለኝ....ሰሞኑን አላነበብኩም....ባለፈው መጽሀፉን ማንበብ እንደምትፈልግ ጽፈው አንብቤ ስለነበር ባለፈ ክረምት ቤት ልሰራ ብዬ ነው.....በል እንሰት ብቻውን ይኮምኩም::

አንተ ግን ደህና ነኽ?እስቲ ያወጋችሁትን ወደላይ ወጥቼ ላንብበው::

ሾተል ነን

ልፋትህ በጭራሽ ከንቱ አልሆነም:: እኔ በጠየቅሁት ብዙ እህቶቻችን የማዳመጥ ዕድሉን ስለሚያገኙ በዛ ይካካሳል (ስለወንዶቹ አያገባንም ብዬ ነው :lol: :lol: )

እኔ እጅጉን ደህና ነኝ:: አገሩን ቀዬውን ሰላም አገኘኸው? ልጆቹ ከብቶቹ ሁሉ ደህና?

ወንድማችን ጌታ......ከአበሻ ጀብዱ ትረካ ቀጥሎ አነስ ያለች ውይይት ነገር ስላለች እሷን አዳምጣት::አገሩ ሁሉም ጥሩ ነው::ደስም ብሎናል::ደስታን የሰጠን አምላክ ክብሩ ይስፋና::

በነገራችን ላይ እነዚህ የእኛን መረዋ ድምጽ ያዳምጡታል ያልከን እህቶቻችን አግብተዋል?የወንድ ጉዋደኛስ አላቸው?ካላገቡና ከሌላቸው ስልክ ቁጥራችንን ስጥልን::ማን ያውቃል ከእህትነት ወደ እንትንነት እንቀይራቸውና ጽጌሬዳ አበባ ይዘን የተነሳነውን ፎቶ ልብ መሀል አድርገን ኢዲት አድርገነው ከድሮ እህቶቻችን ከአሁንዋ እንትናችን ጋር እንልክልህ ይሆናል::ቅቅቅቅቅቅ::

ድሮ ድሮ አተረማመሰው እያልን እንዘፍን ነበር::

ሾተል ነን
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9653
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

ያደለው

Postby እንሰት » Sat Aug 27, 2011 1:15 am

ያደለው እንዲህ ከቢራ በተረፈ ጊዜ አንድ መጽሀፍ ተርጉሞ እንዲህ የጎምቱ ምሁራን መነጋገሪያ ይሆናል::

<<ሶስተኛ፣ እኔ ያላነበብኩትን መጽሐፍ አንብበዋል፡፡ በእርስዎ ትጋት ስደነቅ በራሴ ስንፍና አፈርሁ፡፡ የሆነ ሆኖ የቼኮዝላቫኪያው “ጐበዝ” በማይጨው ጦርነት “የትግራይ ሽፍቶች” በሀገር ወገኖቻቸው ስለፈፀሙት ግፍ የጻፈውን አስነብበውናል፡፡ መልካም፡፡ ይህንን መጥቀስዎ በሽፍቶቹ አሳብበው መላውን ትግራይ ለመፈረጅ ነው የሚል እሳቤ የለኝም፡፡ ምናልባት ወንጀለኞቹ ከራያና አዘቦ ሳይሆኑ አይቀርም የሚል ግምት አለኝ፤ ግምቴ ትክክል ከሆነ ስለድርጊቱ እኮ ብዙ ተጽፏል፤ ለምን አዲስ እንደሆነብዎት አስገርሞኛል፡፡ ለመሆኑ አመፁን ለመፈጸም የገፏፏቸው ታሪካዊና ማህበራዊ ምክንያቶች ይኖሩ ይሆን ብለው ራስዎን ጠይቀዋልን? በትክክል ጠቅሰውት ከሆነ “ጐበዙ”፣ ግን አላዋቂው ፈረንጅ ያልጠየቀው? ይህንን ስል ድርጊቱን የደገፍኩ መስሎ እንደማይታይብኝ እተማመናለሁ፡፡ ለመሆኑ ፈረንጅ የጻፈውን ማንበብ ካቆሙ ዓመታት ከሆነዎት፣ ይኸኛውን ለምን መረጡት? ወደዱትስ? ከኢትዮጵያ ታሪክ የሚያነቡት በመረጣ መሆኑን አስገንዝበውኛል፡፡ የሆነ ሆኖ ስለድርጊቱ እኔም በመጠኑ ጽፍያለሁና፣ ለየት ያለ ግንዛቤ ያገኙበታል ከሚል ግምት የመጀመሪያው መጽሐፌን፣ በተለይም አራተኛውን ምዕራፍ እንዲያነቡልኝ በትህትና እጋብዝዎታለሁ፡፡>>

http://www.fetehe.com/?q=node/7
ገብሩ ታረቀ (ፕሮፌሰር ኤመሪተስ)
Email: tareke@hws.edu
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Re: ያደለው

Postby ፓን ሪዚኮ » Sat Aug 27, 2011 6:47 am

እንሰት wrote:ያደለው እንዲህ ከቢራ በተረፈ ጊዜ አንድ መጽሀፍ ተርጉሞ እንዲህ የጎምቱ ምሁራን መነጋገሪያ ይሆናል::

<<ሶስተኛ፣ እኔ ያላነበብኩትን መጽሐፍ አንብበዋል፡፡ በእርስዎ ትጋት ስደነቅ በራሴ ስንፍና አፈርሁ፡፡ የሆነ ሆኖ የቼኮዝላቫኪያው “ጐበዝ” በማይጨው ጦርነት “የትግራይ ሽፍቶች” በሀገር ወገኖቻቸው ስለፈፀሙት ግፍ የጻፈውን አስነብበውናል፡፡ መልካም፡፡ ይህንን መጥቀስዎ በሽፍቶቹ አሳብበው መላውን ትግራይ ለመፈረጅ ነው የሚል እሳቤ የለኝም፡፡ ምናልባት ወንጀለኞቹ ከራያና አዘቦ ሳይሆኑ አይቀርም የሚል ግምት አለኝ፤ ግምቴ ትክክል ከሆነ ስለድርጊቱ እኮ ብዙ ተጽፏል፤ ለምን አዲስ እንደሆነብዎት አስገርሞኛል፡፡ ለመሆኑ አመፁን ለመፈጸም የገፏፏቸው ታሪካዊና ማህበራዊ ምክንያቶች ይኖሩ ይሆን ብለው ራስዎን ጠይቀዋልን? በትክክል ጠቅሰውት ከሆነ “ጐበዙ”፣ ግን አላዋቂው ፈረንጅ ያልጠየቀው? ይህንን ስል ድርጊቱን የደገፍኩ መስሎ እንደማይታይብኝ እተማመናለሁ፡፡ ለመሆኑ ፈረንጅ የጻፈውን ማንበብ ካቆሙ ዓመታት ከሆነዎት፣ ይኸኛውን ለምን መረጡት? ወደዱትስ? ከኢትዮጵያ ታሪክ የሚያነቡት በመረጣ መሆኑን አስገንዝበውኛል፡፡ የሆነ ሆኖ ስለድርጊቱ እኔም በመጠኑ ጽፍያለሁና፣ ለየት ያለ ግንዛቤ ያገኙበታል ከሚል ግምት የመጀመሪያው መጽሐፌን፣ በተለይም አራተኛውን ምዕራፍ እንዲያነቡልኝ በትህትና እጋብዝዎታለሁ፡፡>>

http://www.fetehe.com/?q=node/7
ገብሩ ታረቀ (ፕሮፌሰር ኤመሪተስ)
Email: tareke@hws.edu
አንተ ኮባ ሰላም ነህ? እዛች ፍትህ ቤት እንዴት ነው ማህበርተኛ የሚኮነው? መመዝገቢያ ቦታ ብፈልግ አጣሁ::
በል ሰላም ዋል
ፓኑ
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests