ዲጄ ሓዩ :)

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ሓየት11 » Sun Dec 09, 2012 3:10 pm

81. Step Up Revolution - Opening Scene - http://youtu.be/uPsrNiZScco
82. Pitch Perfect - The Way You Are - http://youtu.be/K0MPuAaHVDw
ሓየት11
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2945
Joined: Sun Apr 06, 2008 7:34 pm
Location: ላን'ሊይ

Postby ሓየት11 » Tue Dec 11, 2012 11:56 pm

83. One More Night http://youtu.be/fwK7ggA3-bU
84. RadioActive http://youtu.be/ktvTqknDobU
ሓየት11
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2945
Joined: Sun Apr 06, 2008 7:34 pm
Location: ላን'ሊይ

Postby recho » Tue Dec 18, 2012 8:14 pm

ዲጄ ሓዩ እና ሌሎቻችን ..

ይቺን ዘፈን ዛሬ ሰማሁዋትና የድሮ ዘፈኖች ምን ያክል ረቂቅ እንደነበሩ አይቼ ገረመኝ ... አሁን በዚህ ዘመን ከምንሰማቸው ወደድኩዋት ወደደቺኝ ስጠጋት ከዳቺን ዲሪም ዲሪም ዲሪም ቦሌ ቦሌ አይነት ዘፈኖች አንጻር ሲታይ ምን ያክል ትርጉም የነበራቸው ዘፈኖች ነበሩ ለካ. ባህሩ ቀኜ ልጅ ሆኜ የሚለው ስለማይገባኝ በጣም ይሰለቸኝ እንደነበር አስታውሳለሁ .. አሁን እርጅና ሲጫጫነኝ ገባኝ ማለት ነው :lol: ስሙዋትማ .. እኔ ከምሰማበት ሳይት ላይ ኮፒ አርጌው ይስራ አይስራላቹ ግን ቼክ ማድረግ አልቻልኩም .. የዘፈኑ አርስት ቃሉ መሰለኝ .. ዘፋኝ ባህሩ ቀኜ ... ዩቲዩብ ላይ ማግኘት አልቻልኩም (ወይንም ትግስት አልነበረኝም የመፈለግ ) ሊሪክሱ በከፊል ያውላቹ .. ሪቾ ቬሪ ኢምፕረስድ ... :) ኢንጆይ ...

ማን ወደማን ይሆን የሚገሰግሰው
መቼም ያገናኛል መንገድ ሰው እና ሰው

አበባም አብቦ ሲበቃው ይደርቃል
ይዋል ይደር እንጂ እያደር ይደርቃል
ልብስም ቢያጌጡበት እያጠቡት ያልቃል
ሰውም ይክረም እንጂ ቦታውን ይለቃል

ምሳር ላወቀበት ደን ይመነጥራል
አትቀደም ያለው ባይን ይጠረጥራል

ልቤ እንደጅረት ወንዝ እየደፈረሰ
እንደኔስ በነገር የማን ቤት ፈረሰ

ሰውም እሰው እቤት ሳይቸግረው ያድራል
እህም ያሉት እንደው በስም ያዳድራል ( :lol: አልገቢቶም)

ቢወራ ቢሰማ ቢሰማስ እስከዳር
ሰው አለ ተብሎ ይፈታል ወይ ትዳር ( :lol: በውነት እንደዚህ የሚያደርግ ይኖራል ? ተጋነነ :lol: አይ የድሮ ሰው)

ማንስ አለሁ ብሎ ስንት ዘመን ኖረ
ምነው በቁም መግደል የማይቀር ሞት ሳለ ( :cry: )

http://www.arifzefen.com/?sids=116
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby TAዛBI » Wed Dec 19, 2012 9:04 am

recho wrote:ዲጄ ሓዩ እና ሌሎቻችን ..

ትውልዱ እኮ ነው ሪችዬ ..ርቀት ሳይሆን ድምቀት የሚያደንቅ ትውልድ ነው

አሁን ይህ ዘፈን አሪፍ ቢሆንም ፍንዳታዎቻችን እንዲያጣጥሙት ከተፈለገ ከጀርባው የ JAY-Z ን ራፕ አስገብቶ አድምቆ remix ማድረግና "ባህሩ ቃኜ featuring Jaz-Z "ምናምን ..ተብሎ መቅረብ አለበት :D

በጥሬው ግን እንጃ ...ይህን ትውልድ ብታስመርጪው ቦሌ- ቦሌን ይመርጥብሻል :lol:
TAዛBI
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 152
Joined: Mon Dec 22, 2008 8:42 am

Postby recho » Wed Dec 19, 2012 10:21 pm

TAዛBI wrote:
ትውልዱ እኮ ነው ሪችዬ ..ርቀት ሳይሆን ድምቀት የሚያደንቅ ትውልድ ነው
ሰላም ታዛቢ ...

እውነትህን ነው .. ርቀት ሳይሆን ድምቀት አርተፊሻል ሂወት ነው የዘንድሮው ነገር .. የዘፈን ግጥሞችን ብትመለከት የመጨረሻ ፊደልዋ ብቻ ግጥም መምታትዋ እና ሙዚቃው ኩዋኩዋታ መብዛቱ ነው የሚታየው ... የሰውም ጸባይ እንደዛው ነው .. ልብ ብለህ ካየህው ቁምነገርን እንደቁምነገር ቆጥሮ በጨዋነትና በጥንቃቄ የሚይዝ ስንት ሰው አለ? አንዳንዴ ወይ እኔ አመለካከቴ ተቀይሮ አስቸግሮኛል ካለዛ ደግሞ እውነትም ዘመኑ የሚገርምነው እላለሁ ... ብስል የዘፈን ግጥሞች ቶታሊ የሉም አይደለም ... የቴዲ ዘፈኖች ለኔ ጣእም ያላቸው ግጥሞች አሉት ... ግን ቢሆንም ከድሮው ጋር ስታስተያየው ወደውስጥ ነው እያደግን ያለነው .. ወይ ፌስቡክ ጀነሬሽን ህምም

አሁን ይህ ዘፈን አሪፍ ቢሆንም ፍንዳታዎቻችን እንዲያጣጥሙት ከተፈለገ ከጀርባው የ JAY-Z ን ራፕ አስገብቶ አድምቆ remix ማድረግና "ባህሩ ቃኜ featuring Jaz-Z "ምናምን ..ተብሎ መቅረብ አለበት :D
ቂቂቂቅ ይቺ ተመችታኛለች .. ታየኝ እኮ ባህሩ ቀኜ ከጄዚ ጋር ሪሚክስ ተደርጎ :lol: :lol: :lol: :lol: ክፉ

...ይህን ትውልድ ብታስመርጪው ቦሌ- ቦሌን ይመርጥብሻል :lol:
ቅቅቅ ቦሌ ቦሌ .. ከልቤ ነው የሳቅኩት መጀመሪያ ያየሁት ዘን .. እንዴ ምንድነው ነገሩ ??? ምኑም አልገባኝ በውነቱ .. በዝላይ ወረድ በይ ወረድ ቅቅቅቅ እረ ጉድ ዘንድሮ :lol: :lol: :lol: [/quote]
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby ሓየት11 » Wed Dec 19, 2012 10:34 pm

ሪቾ ወሳኚትዋ ... :D

ስሚ አረጀሽ እንዴ ... ድሮ ቀረ ማለት አበዛሽሳ ... ሰውኮ ሲያረጅና ኋላ ሲቀር ... ከጊዜው ጋር ኢንኮምፓታብል ይሆንና ... ድሮ ቀረ እያለ ራሱን ያጽናናል ... :lol: ... አበሻ ደግሞ ... የሀምሳ ቀን ዕድሉ ሆኖ ...በሁሉም ዘርፍ ... ድሮን ማድነቅ ይወዳል ... ወደ ኋላ መለስ ብለሽ ... ሚዛንሽን ብታስቀምጪ ግን ... ሀቁ ሌላ ሆኖ ታገኚዋለሽ:: ... እና እቱ ... ወይ ምድብሽን ለይና ... እኛም ኮረዳዎችን እናስስበት ... አታደናግሪን :lol: ... ወይም ደግሞ ... እንደ ዊንዶው አስራ አንድ :wink: ... ቢ ኮምፓታብል .ዊዝ ኤቭሪ ቲንግ ... ቅቅቅ.

ግጥሙ ግን ድንቅ ነው:: ... አመስግንነናል :wink: .
ሓየት11
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2945
Joined: Sun Apr 06, 2008 7:34 pm
Location: ላን'ሊይ

Postby TAዛBI » Thu Dec 20, 2012 2:29 pm

recho wrote:
አሁን ይህ ዘፈን አሪፍ ቢሆንም ፍንዳታዎቻችን እንዲያጣጥሙት ከተፈለገ ከጀርባው የ JAY-Z ን ራፕ አስገብቶ አድምቆ remix ማድረግና "ባህሩ ቃኜ featuring Jaz-Z "ምናምን ..ተብሎ መቅረብ አለበት :D
ቂቂቂቅ ይቺ ተመችታኛለች .. ታየኝ እኮ ባህሩ ቀኜ ከጄዚ ጋር ሪሚክስ ተደርጎ :lol: :lol: :lol: :lol: ክፉቀልዴን መሰለሽ አይደል :)
ባህሩ ቀኜ ግን አስገምጋሚ ጎርነን ሻከር ያለ ደስ የሚል ምቹ ድምጽ ስላላቸው ከጄይዚ ጋር ሚክስ ለማድረግ ምቹ ነው
ጄይዚ ራፑን ከሽከሽ ሲያደርግ መሀል ላይ ባህሩ ሰበር አርገው በወርቃማው ድምጻቸው.... ደሴ ደረቅ ወይራ ገራዶ ገራዶ..አለቀልሽ ልቤ ተንዶ ተንዶ ..ብለው ሲያንቆረቁሩት ድሮና ዘንድሮን ማዋሰብ ይሉሻል እንዲህ ነው :D

ፍንዳታዎችን እንዲህ አርገን ባህል እናስተምር እንጂ አይመስልሽም ?
TAዛBI
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 152
Joined: Mon Dec 22, 2008 8:42 am

Postby recho » Thu Dec 20, 2012 3:50 pm

ሓየት11 wrote:ሪቾ ወሳኚትዋ ... :D

ስሚ አረጀሽ እንዴ ...
ሓዩ ወያኔው ... ማርጀት ብቻ ? ቅቅቅ ከናንተ ከልጅ ልጆቼ ጋር ስውል እኮ ልጅ የሆንኩ እየመሰለኝ እንጂ ቆየሁ ካረጀሁማ :lol:

ድሮ ቀረ ማለት አበዛሽሳ ... ሰውኮ ሲያረጅና ኋላ ሲቀር ... ከጊዜው ጋር ኢንኮምፓታብል ይሆንና ... ድሮ ቀረ እያለ ራሱን ያጽናናል
...
ቂቂቂቂ በቃ ነገር ነገር ያለህ ለታ መስማት የምትፈልገውን መርጠህ ነው የምትሰማው አይደል አንተ የሽማግሌ ፍንዳታ ቅቅቅቅ ያልኩትን እስቲ በዛሬ ሙድ ድገምና አንብበው ... :lol: :lol: :lol:
:lol: ... አበሻ ደግሞ ... የሀምሳ ቀን ዕድሉ ሆኖ ...በሁሉም ዘርፍ ... ድሮን ማድነቅ ይወዳል ... ወደ ኋላ መለስ ብለሽ ... ሚዛንሽን ብታስቀምጪ ግን ... ሀቁ ሌላ ሆኖ ታገኚዋለሽ::

እናንተ አበሾች እንዴት እንደምታስቡ እኔ ምን አውቄ .. ሪቾ አበሻ ናት እንዴ? :lol: :lol: :lol: :lol: ሪቾ ሪቾ ናት .. :lol: :lol:

.
.. እና እቱ ... ወይ ምድብሽን ለይና ... እኛም ኮረዳዎችን እናስስበት ... አታደናግሪን :lol: ... ወይም ደግሞ ... እንደ ዊንዶው አስራ አንድ :wink: ... ቢ ኮምፓታብል .ዊዝ ኤቭሪ ቲንግ ... ቅቅቅ.
አይ ኮረዶቹን በል እስቲ ለኔም ካገኘህ ሸጋ ኮበሌ ፈልግልኝ :lol: :lol:

ታዛቢው ቅቅቅ አፈነዳህኝ በሳቅ .. ታየኝ እሺ ቅቅቅቅቅ ለነገሩ ዘንድሮ ስንት ነገር አየን ቅቅቅ አሁን ይቺን አይዲያ ሰጥተናል ሰሞኑን እነ ቦሌ ቦሌ ይዘዋት ከች ይላሉ .. ኮፒ ራይት ራሱ አይጠበቅልንም :lol: :lol: :lol:
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby ሓየት11 » Thu Dec 20, 2012 6:13 pm

recho wrote:
ሓየት11 wrote:ሪቾ ወሳኚትዋ ... :D

ስሚ አረጀሽ እንዴ ...
ሓዩ ወያኔው ... ማርጀት ብቻ ? ቅቅቅ ከናንተ ከልጅ ልጆቼ ጋር ስውል እኮ ልጅ የሆንኩ እየመሰለኝ እንጂ ቆየሁ ካረጀሁማ :lol:

እኔ ደግሞ ማርጀት ብቻ ስትይ ... ያቺን በሻሽ ደብቀሻት የምትሄጂ ... ጢንጥዬ ቀንድሽን ... ይፋ ልታወጣት ነው .. ብዬ ሰግቼ ቆይቼኮ :lol:

ድሮ ቀረ ማለት አበዛሽሳ ... ሰውኮ ሲያረጅና ኋላ ሲቀር ... ከጊዜው ጋር ኢንኮምፓታብል ይሆንና ... ድሮ ቀረ እያለ ራሱን ያጽናናል
...
ቂቂቂቂ በቃ ነገር ነገር ያለህ ለታ መስማት የምትፈልገውን መርጠህ ነው የምትሰማው አይደል አንተ የሽማግሌ ፍንዳታ ቅቅቅቅ ያልኩትን እስቲ በዛሬ ሙድ ድገምና አንብበው ... :lol: :lol: :lol:

እረ ተይኝ እቴ ... ከሙዴ አይደልካ ችግሩ :lol: ... የፌስቡክ ጀነሬሽንን ማናናቁን ባንቺም ሳይ ጊዜ ... ካረጁት ተርታ ብትሆኚ ነው ... የሚል ግምት ... እላዬ ላይ እንደዘንዶ ተጠቅሎ ... አረፈብኝ ... :lol:

:lol: ... አበሻ ደግሞ ... የሀምሳ ቀን ዕድሉ ሆኖ ...በሁሉም ዘርፍ ... ድሮን ማድነቅ ይወዳል ... ወደ ኋላ መለስ ብለሽ ... ሚዛንሽን ብታስቀምጪ ግን ... ሀቁ ሌላ ሆኖ ታገኚዋለሽ::

እናንተ አበሾች እንዴት እንደምታስቡ እኔ ምን አውቄ .. ሪቾ አበሻ ናት እንዴ? :lol: :lol: :lol: :lol: ሪቾ ሪቾ ናት .. :lol: :lol:

ሰው ከቀየው ሲሸሽ ... እኔ እኔ ነኝ እንጂ ቀዬዬ አይደለሁም ይላል ... አሉ ... ሰለምሽ እንዴ? ... :lol:

ሰላም ነው ግን? ...
ክብነሽ ለማ ሙዝ ዳግም ገለብጬ .... ሰላም ናቸው? ... አረፍተ ነገር ሊሰሩ ... ሁለት ይቀሩሻል :lol:
ሓየት11
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2945
Joined: Sun Apr 06, 2008 7:34 pm
Location: ላን'ሊይ

Postby recho » Thu Dec 20, 2012 6:17 pm

ሓየት11 wrote:ሰላም ነው ግን? ...
ክብነሽ ለማ ሙዝ ዳግም ገለብጬ .... ሰላም ናቸው? ... አረፍተ ነገር ሊሰሩ ... ሁለት ይቀሩሻል :lol:
ቅቅቅ ደህና ናቸው .. ሁለቱን አንተ ሙላበት .. አሁን አትጨቅጭቀኝ አይ ሚስ ዩ ቱ ኤንድ ዩ ኖው ዌር ቱ ፋይንድ ሚ አመዳም :lol: :lol:
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby recho » Thu Dec 20, 2012 6:32 pm

http://youtu.be/ruyaKdPfTN4

እሺ እንግዲህ ከናንተ ከጎረምሶቹ ሰፈር ስንመጣ ደግሞ ይሄንን ዘፈን እጅጉን ወድጄዋለሁ ለምወደው ሰው የሚኖረኝ ስሜት ይሄንን ነው ... ያው ለሪቾ መውደድ እና ማፍቅር ማለት ለተፈቃሪው ማሰብ እና ሁልጊዜ ጥሩ ስሜት እንዲኖረው ማደርግ .. ማደርግ ባይቻል እንኩዋን ማሰብ ነው .. ኦፕስ ክብዬ ናት ለካ ፍቅር ምን ማለት ነው እያለች ልባችንን ያወለቀችው ቅቅቅቅ ለሁሉም .. ፍቅርን በሚገባ መግለጽ የቻለን ዘፈን ስለሆነ ወድጄዋለሁ ..
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby recho » Sat Dec 29, 2012 4:39 am

ዲጄው ቤታቸውን ጥለው ከጠፉ ከራርመዋል ... እንዴት ነው ነገሩ ? :roll:
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby varka911 » Sat Dec 21, 2013 11:37 pm

recho wrote:ዲጄው ቤታቸውን ጥለው ከጠፉ ከራርመዋል ... እንዴት ነው ነገሩ ? :roll:

እውነትም ዲጄው ቤታቸውን ጥለው የት ጠፉ? እንደ ዘበት አመት ሞላቸው እኮ:: በደህና ይሆን? ለማንኛውም እኛው እናማሙቅላቸው እስኪመለሱ :wink:
ሰላም ነሽሳ እህታችን?
እስኪ ጠጋ በይና አጫውችን?

Celine Dion - Loved Me Back to Life

Olly Murs - Right place and Right time

David Guetta - Where em girls at
Get your second chance On my First Aid!
varka911
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 101
Joined: Tue Oct 22, 2013 2:30 pm

Previous

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests