ጳውሎስ ኞኞ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ጳውሎስ ኞኞ

Postby ሀዲስ 1 » Sat Apr 21, 2012 9:26 pm

ጳውሎስ ዝም ተብሎ የሚታለፍ ሰው አይደለም :: ሲያልፍ ሲያገድም የሚናገረውና የሚሰራው ነገር ሁላ አስገራሚ ኢትዮጵያዊነትን የሚሸት ነበረ ::
ቀልዳቸው ከሚያምር ሰዎች ውስጥ ስም ቢጠራ ጳውሎስ ከአለቃ ገብረሀና ቀጥሎ የመጀመሪያውን ቦታ በኢትዮጵያችን ይይዛል ብል ምናልባትም አልሳሳትም ::

አንዲት ጠያቂ አንዴ :

ልብሱ ነጭ ጫማው ነጭ
መንገድ ላይ ቆሞ የሰው ገንዘብ የሚነጭ

ማነው ? ብትለውና ብትጠይቀው

ሴትየዋ ! ከትራፊኮች ጋራ ልታጣይኝ አስበሻል መሰለኝ ያለውን አልረሳውም ::

ጳውሎስ በእርግጥም እራሱን ያስተማረ አስተዋይ ሰው ነበረ :: ግን የሱን ስራዎች ምናለ እዚህ ብናስቀምጣቸው : ብናስታውሳቸው ?

እስኪ በናታችሁ የጳውሎስ ትዝታና ጥሩ ስራ ትዝ የሚሏችሁ ብቅ በሉና እዚህ አንድ በሉ :: አዲሱ ትውልድም በዚህ አጋጣሚ ምን አይነት ሰዎች ኢትዮጵያችን በአንድ ወቅት ወልዳ እንደነበረ ይወቅ ::

ሀዲስ
what we learn from history is, we do not learn from history.

http://www.isil.org/resources/philosoph ... nglish.swf
ሀዲስ 1
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1643
Joined: Wed Mar 10, 2010 12:23 am

Postby ዉቃው » Sun Apr 22, 2012 1:00 am

በቃ ..አሪፍ ነው አርዕስትህ :: ሰውየውም በጣም ይመቸኛል :: ይቀጥል ብለናል... ይቀጥል ::
ጉዟችን ረጅም : ግባችንም ሩቅ ነው !!!!
ዉቃው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1034
Joined: Sun Jan 07, 2007 2:48 am

Postby recho » Mon Apr 23, 2012 2:40 pm

ዻውሎስ ... ልጅ ሆኜ አባቴ በግድም ቢሆን እንዳነብ ካደረገኝ መጸሀፍቶች አብዛኛው የዻውሎስ ኞኞ አስደናቂ ታሪኮች ነበሩ... ለሰውየው ካለው አድናቆት የተነሳ ንትብብብ ያሉትን አሮጌ መጻህፍቶች ደብቆ አስቀምጦ እውቀትን ለሚቀጥለው ጀነሬሽን አስተላልፍዋል... ምርጥ አባት .. ኤኒሁ ካደኩ ቡሀላም ጋዜጣ ላይ ያወጣቸው የነበሩ እጥር ብለው ግን ብዙ መልክት የሚያስተላልፋቸውን አጋጣሚው ሰጥቶኝ አንብቤ ነበር

ጥያቄ... ዻውሎስ ባጠና ባጠና አልገባኝ አለ ምን ይሻለኛል ?
መልስ ... በስንጥር ሞክሪው ...

:lol:
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby ሀዲስ 1 » Mon Apr 23, 2012 10:56 pm

ጋሽ ጳውሎስ ኞኞን ለማስታወስ ጊዜያችሁን በመሰዋት እዚህ ብቅ ላላችሁ ሁላ ምስጋና ይድረሳችሁ :: ታዲያ እንደእህታችን ሪቾ አንዳንድ ነገር ጣል ጣል ብታደርጉ መልካም ነው :: ሪቾ በርቺ : አትጥፊ ::

እውቁ ጋዜጠኛና ደራሲ ጳውሎስ ኞኞ በ 11 ህዳር 1926 ዓ.ም ቁልቢ አካባቢ ተወልደው ድሬዳዋ ከተማ አደጉ :: በጣሊያን ወረራ ምክንያት ትምህርታቸውን ከ 4ኛ ክፍል በላይ መቀጠል አልቻሉም ነበረ :: ብሩህ አእምሮና የፈጠራ ችሎታ የነበራቸው ሰው ስለነበሩ : በልጅነታቸው የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ጣሊያንን ሰገድሉ ወይም ሲማርኩ ስዕል በመሳል ያሳዩ ነበረ :: ጳውሎስ ካላቸው የፅሁፍ ጥማት የተነሳ የ ድምፅ ጋዜጣ አዘጋጅ በመሆን የብዕር ድምፃቸውን ያሰሙ ነበረ :: ጋዜጦች ላይ ከፅሁፍ አቅራቢነት እስከ አዘጋጅነት ለበርካታ አመታት ሰርተዋል :: በተለይ አንድ ጥያቄ አለኝበሚለው የአዲስ ዘመን ጋዜጣ አምዳቸው ላይ ብዙ ታዋቂነትን አግኝተዋል :: አቶ ጳውሎስ ኞኞ ከ 1955 ዓ.ም. ጀምሮ ለኢትዮጵያ ስነፅሁፍ እድገት የነበራቸውን ተሰጥኦ በአግባቡ በስራ ላይ ያዋሉ እውቅ ጋዜጠኛና ደራሲ ነበሩ :: እኚህ ታዋቂ ሰው በተወለዱ በ 58 ዓመታቸው ከዚህች አለም በሞት ተለይተዋል ::
አቶ ጳውሎስ
የጌታቸው ሚስቶችበሚል ርዕስ ያሳተሟትን መፅሀፍ " ከታተመችበት ወር አንስቶ ለአንድ አመት የመፅሀፌ መብት የግሌ ነው :: ከአንድ አመት በኃላ መብቱ የማንኛውም ኢትዮጵያዊ ይሁን :: ከወሰንኩት ጊዜ በኃላ አሳትሞ ለመሸጥ የፈለገ ሁሉ ከድርሰቴ ሳይቀንስም ሆነ ሳይጨምር ሊያራባው ይችላል :: ስሜን ሳይሰርዝ አሳታሚውን እገሌ ብሎ ማንም ኢትዮጵያዊ ከፈለገ እንዲያራባት የደራሲነት መብቴን ለቅቄያለሁኝ :: አሳታሚው የግሉን የመግቢያ ሀተታ በስሙ ቢፅፍ እኔም ሆንኩ ወራሼ አንቃወምም " ብለዋል ::

ምንጭ:- ውኪፔዲያ

ሀዲስ
what we learn from history is, we do not learn from history.

http://www.isil.org/resources/philosoph ... nglish.swf
ሀዲስ 1
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1643
Joined: Wed Mar 10, 2010 12:23 am

Postby ዲጎኔ » Tue Apr 24, 2012 2:37 pm

ሰላም ለሁላችን ይሁን
ጋሸ ጳውሎስ ኞኞ ከዘመን የቀደመ ሁለገብ ጋዜጠኛና ሀገር ወዳድ ክርስቲያን ነበር:: በቀድሞዋ ብርሀ ንመጽሄት ስለእስቲግማታ የጸፈውን አንብበያለሁ::
በአጼው ዘመን መገባደጃ ላይ ተገቢ ትችት በማቅረቡ በተዋህዶው ሲኖዶስ ተከስሶ መቀጫ የተጣለበት ሲሆን ደርግ ሊወድቅ አካባቢ ባለቤቱ አስቀድማ አባል በሆነችበት ወንጌላዊት ምስጋና በተክርስቲያን ወሎ ሰፈር በመገኘት ምስክርነቱን ሰምቻለሁ::ነጸብራቅ በተሰኘ መንፈሳዊ መጽኄት ቃለምልልሱ ሲቀናበር ዝግግቱና ቅንብሩ ላይ ነበርን::ልጅ ያላቸው ባልና ሚስትን ሲጣሉ ሲመክር እርሱ ያለልጅ ከሚስቱ ጋር ያለውን ልዩ ፍቅር ሲሆን በማደጎ ካሳደጋቸው አኪሊል ጳውሎስ ትልቁዋ ነበረች::
በስጋ ህይወት ባይኖሩም ስራቸው ዘላለማዊ የሆነ አንጋፋ ጸሀፊዎችና ጋዜጠኞች ዮፍታሄ ንጉሴ ጳውሎስ ኞኞ አሳምነው ገብረወልድ ሰለሞን ተሰማ... የማእበል ደራሲ በግሌ ያደረጉልኝ አስተዋጽኦ ሁሌ ይታወሰኛል::
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby እናመሰግንሃለ » Tue Apr 24, 2012 5:27 pm

----
Last edited by እናመሰግንሃለ on Tue Sep 03, 2013 4:46 pm, edited 1 time in total.
እናመሰግንሃለ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 824
Joined: Mon Jun 01, 2009 8:07 pm

Postby ዲጎኔ » Wed Apr 25, 2012 2:48 pm

ሰላም ለሁላችን ለለየለት ዋሾ እናመስግናለን ባይ ጭምር
ይህ አምድ ስለእውቁ ቆራጡ ሀቀኛ ጋዜጠኛ ጳውሎስ ኞኞ የሚዘከር ነው::በተዋህዶ ሲኖዶስ ክስ ግዝት አልደረሰበትም ለማለት ሲኖዶስ አልበረም ሰርጎ ገቦች ተቆጣጠሩት ብለህ ትዋሻላህ ቀጣፊ!እድሜ ልካችሁን የምትባሉ ድሮ ሁለት ልደት ሶስት ልደት ካራ ቅባት ዘንድሮ የጎንደር የቡልጋ የጎጃም ብላችሁ የጳጳሳችሁ አቡነ ገብርኤልን አስከሬን አስቀምጣችሁ የምትፈናከቱ ለነውረኛ ሲኖዶስ ግፍ ማርከሻ ሲኖዶስ አልነበርንም ትላላህ?ዋሾ የዋሾ ዋሾ!
እስከማቀው ሲኖዶሱም ጉባኤውም ጠቅላይ ቤተክህነቱም በነ አለቃ ልሳኑ በነሊቀስልጣናት በነአለቃ አያሌው ወዘተ እየተመራ ነበር ጋሽ ጳውሎስ ሁለት ሶስት ጊዜ ከሰው ፍርድ ቤት ያቆሙት::ለመክሰሰ ማን ብሏችሁ ድሮ የተሀድሶ በኩሩን
ደቅ እስጢፎ በሀሰት ከሳችሁ በዘማዊ ንጉስዘረያቆብ አይኑ ወጥቶ በቁም የቀበሩ እነአለቃ ታዬን ሙትበቃ የፈረዱ ልጆች ዛሬም ከክፋት አላረፋችሁ!ማፈሪያዎች የፍቅርና የምህረት ሀይማኖት የክርስትና አሰዳቢዎች!
ስማ አንተ የደም አፍሳሽ መንፈስ የተጠናወተህ ዲጎኔ ያቺ ኢትዮጲያና ጥንታዊት ቤተክርስቲያኗ ትንሳኤ እንድታገኝ ህይወቱን ለመክፈል ሳይዳዳ የታገለ የታሰረ የተሰደደ ነው አንተ ስላልከኝ ሳይሆን መፍትሄ ቢኖረው ራስን ማጥፋት አልሳሳም ግን ከቃሉ የሚጣረስ ድርጊት ነው::ይቃጠሉ ያልካቸው ወገኖቼን ንስሀ ካልገባህ አንተው ከአፍህ እንደወጣ በልብህ የሞላ ነውና አድርግና ዋርካ ከአጋንታዊ መልክትህ ትረፍ::

እናመሰግንሃለ� wrote:
ዲጎኔ wrote:.....
በአጼው ዘመን መገባደጃ ላይ ተገቢ ትችት በማቅረቡ በተዋህዶው ሲኖዶስ ተከስሶ ....

በአጼው ዘመን መገባደጃ: በደርግ ዘመን እና በኢህአዴግ ዘመን ተዋሕዶ የራሷ ሲኖዶስ ኖሯት አያውቅም!! ደርግ ሲመጣ ቤተክህነት ውስጥ ተሰግስገው የጠበቁት የአድቬንቲስት: የጂሆቫና የካቶሊክ አንደርከቨር ኦርቶዶክስ መሳይ ፖለቲከኞች ነበሩ:: በደርግ ጊዜ ደግሞ ተዋሕዶ ሳይሆን "የተሃድሶ ጉባኤ" ቤተክርስቲያኒቱን ሲያምስ እንደኖረ እናውቃለን:: አሁን ደግሞ ማን እንዳለ አንተ ከሌላው የተሻለ ታውቃለህ- ቤተክህነቱ የናንተ መፈንጫ ስለሆነ::

ስለዚህ: ተዋህዶን አታንሳ!!! አፍህ ግማታም ዘረኛ የወያኔ ካድሬዎች ወዳጅና የመልካም ነገር ሁሉ ጠላት ስለሆነ: ባንተ ስም ይህ ተዋሕዶ የሚለው የሰውና የእግዚአብሔር: የጎሳና የብሔር: የባልና የሚስት: የቤተሰብና የሕብረተሰብን አንድነትን የሚያንጸባርቀው ክቡር ቃል ሲጠራ ማየት ልናገረው ከምችለው በላይ የመንገፍገፍ ስሜት ይፈጥርብኛል::

እባክህ- ዱ አስ አ ፌቨር! ፈንጂ ማምከኛ በማድረግ ራስህን ለኢትዮጵያ አቅርበህም ቢሆን ዕድሜህን አሳጥረው!
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby እናመሰግንሃለ » Wed Apr 25, 2012 4:53 pm

---
Last edited by እናመሰግንሃለ on Tue Sep 03, 2013 4:48 pm, edited 1 time in total.
እናመሰግንሃለ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 824
Joined: Mon Jun 01, 2009 8:07 pm

Postby ክቡራን » Wed Apr 25, 2012 6:45 pm

Code: Select all
አሁንም ልድገምልህና እባክህ - ዱ አስ አ ፌቨር ! ፈንጂ ማምከኛ በማድረግ ራስህን ለኢትዮጵያ አቅርበህም ቢሆን ዕድሜህን አሳጥረው ! የተሻለ ዕድል እያመለከትኩህ ነው -ለመጽደቅ :: በሕይወት እያለህ በኃጢአት ላይ ኃጢአት ከመጨመር በቀር ልብ የመግዛት ምንም ምልክት አይታይብህምና ::

አንተ መናጢ ደብተራ ከገደብህ እያለፍክ መጥተሀል:: እንደማይህ አሸባሪ ነህ እንጂ ሀይማኖተኛ አይደለህም:: :: ተወያዮች በነጻነት የሚያምኑበትን ነገር እንዳይናገሩ ሀሳባቸውን በሀሳብ ከከመመክት ይልቅ በፈንጂ ራሳቸውን እንዲያጠፉ ታበራታለህ....ድማሚት ታቀበልላህ:: እውነተኛ የእጊዚአብሄር ሰው ያንን አያደርግም:; ቢያንስ በእምነት ""አሬና"" ውስጥ ያለ ሰው ከሱ በዲኖሚኔሽን የተለየውን ወንድሙን ራስህን አጥፋ አይለውም:; አንተ በበጎች መኅል የገባህ ቁራ ነህ!! የተዋህዶ ልጅ ነኝ እያልክ አታላግጥ!! አንድ ነገር ተረድቻለሁ...ሰዎች ኢትዮጵያዊ ሆኖ ለመታየትና ለመመስል ብቻ የኦርቶዶክስ እምነትን እንደ ዣንጥላ ይዘው እነደሚዞሩ ባንተ አረጋግጫለሁ:: አንተ ድብን ያልክ አለማዊ እንጂ መንፈሳዊ አይደለህም:: ላንተ ደሞ ምሱ መስቀል ሳይሆን ካራቴ ነው::
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8154
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ሀዲስ 1 » Wed Apr 25, 2012 8:58 pm

በአንድ ወቅት "አንድ ጥያቄ አለኝ" በሚለው የጋሽ ጳውሎስ ኞኞ አምድ ላይ አንድ ጠያቂ :--

ከኢትዮጵያውያን ዘፋኞች ውስጥ አፈ ሰፊው ማን ነው ? ብሎ ጠይቆት ነበረ :: ታዲያ ልክ እንደሁልጊዜውም የጋሽ ጳውሎስ መልስ ያስገርም ነበረ ::

ብላችሁ ብላችሁ ከምወደው ጓደኛዬ ከመሀሙድ አህሙድ ልታጣሉኝ ነው ? ..... ብሎ ነበረ የመለሰው :: :lol:

ሀዲስ
what we learn from history is, we do not learn from history.

http://www.isil.org/resources/philosoph ... nglish.swf
ሀዲስ 1
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1643
Joined: Wed Mar 10, 2010 12:23 am

Postby እናመሰግንሃለ » Wed Apr 25, 2012 10:08 pm

-----
Last edited by እናመሰግንሃለ on Tue Sep 03, 2013 4:49 pm, edited 1 time in total.
እናመሰግንሃለ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 824
Joined: Mon Jun 01, 2009 8:07 pm

Postby ዲጎኔ » Thu Apr 26, 2012 7:23 am

ሰላም ለሁላችን ይሁን
ወገን ክቡራን የማንስማማባቸው ጉዳዮች ቢኖሩም እምነቴን አክብረህ የምወዳቸው ተዋህዶ ቤተሰቦቼ አጸመርስታቸውን ጭምር ለዚያች ቤተክርስቲያን የለገሱት ሳይቀር ያሉበትን ማህበር አሰዳቢን ስለገሰጽህ ተባረክ!ድሮ አባቶቻቸው ከተራበው ህዝብ ላይ አስራት በኩራት እየቀፈፉ በድግምት ህዝቡን ያሳወሩ ያቺን ጥንታዊት ማህበር የአለማዊ መድረክ ያረጉ ምንደኞች ልጆች ናቸው::አቡነተ/ሀይማኖት የመሰሉ ደቡቦች አምነው የላኩዋቸውን መንፈሳዊ አባትን ጭምር ያሉበትን ማህበር የማይወክሉ አሸባሪ ናቸው::ለማንኛውም የነአባሞገሴ/የፍቅር እስከመቃብሩ ልጆችን ሰምቶ ህዝቦች ያገኙትን የሀይማኖትና የብሄርናጾታ እኩልነት የሚሽር ሸንጎ በጦቢያ ምድር አይፈጠርምና ሳይበር ላይና በስደቱ ሀገር ከነፍስአባታቸው ንብረጉድ እርሚያስ ጋር በልፈፋ ይደሰቱ!
ሀቀኛው ጋዜጠኛ ጳውሎስ ኞኞን ድሮ ያሳሰሩ ዛሬ ደግሞ ተሀድሶዎችን የሚያሳድዱ ግን ፍርዱን ከሰማይም ከምድርም ነጉስ ያገኙታል::

ክቡራን wrote:
Code: Select all
አሁንም ልድገምልህና እባክህ - ዱ አስ አ ፌቨር ! ፈንጂ ማምከኛ በማድረግ ራስህን ለኢትዮጵያ አቅርበህም ቢሆን ዕድሜህን አሳጥረው ! የተሻለ ዕድል እያመለከትኩህ ነው -ለመጽደቅ :: በሕይወት እያለህ በኃጢአት ላይ ኃጢአት ከመጨመር በቀር ልብ የመግዛት ምንም ምልክት አይታይብህምና ::

አንተ መናጢ ደብተራ ከገደብህ እያለፍክ መጥተሀል:: እንደማይህ አሸባሪ ነህ እንጂ ሀይማኖተኛ አይደለህም:: :: ተወያዮች በነጻነት የሚያምኑበትን ነገር እንዳይናገሩ ሀሳባቸውን በሀሳብ ከከመመክት ይልቅ በፈንጂ ራሳቸውን እንዲያጠፉ ታበራታለህ....ድማሚት ታቀበልላህ:: እውነተኛ የእጊዚአብሄር ሰው ያንን አያደርግም:; ቢያንስ በእምነት ""አሬና"" ውስጥ ያለ ሰው ከሱ በዲኖሚኔሽን የተለየውን ወንድሙን ራስህን አጥፋ አይለውም:; አንተ በበጎች መኅል የገባህ ቁራ ነህ!! የተዋህዶ ልጅ ነኝ እያልክ አታላግጥ!! አንድ ነገር ተረድቻለሁ...ሰዎች ኢትዮጵያዊ ሆኖ ለመታየትና ለመመስል ብቻ የኦርቶዶክስ እምነትን እንደ ዣንጥላ ይዘው እነደሚዞሩ ባንተ አረጋግጫለሁ:: አንተ ድብን ያልክ አለማዊ እንጂ መንፈሳዊ አይደለህም:: ላንተ ደሞ ምሱ መስቀል ሳይሆን ካራቴ ነው::
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby recho » Thu Apr 26, 2012 2:44 pm

እናመሰግንሃለ� wrote:
ሀዲስ የጀመረውን ጳውሎስ ኞኞን ዝክር ይቀጥልበት:: ዲጎኔና መሰል እስላማዊ-ወያኔያዊ-ተሃድሶአዊ-ፕሮቴስታንታዊ ልክፍታሞች ታሪክ እያዛባችሁ ተዋህዶን አታንሱ!! አለዚያ እስከዶቃ ማሠሪያችሁ ይነገራችኋል!!
በውነቱ እንደዚህ ሀይማኖተኛ እና እምነት በተራራቁበት, ላመኑበት ነገር ዴዲኬሽን በጠፋበት, ሸፍጥና ክህደት በበዛበት በዚህ ዘመን እንደዚህ ላመነበት ነገር እስከሞት የሚከራከር ሰው መገኘቱ አሁንም የሰውልጅ ተስፋ እንዳለው ነው የሚያሳየው ... አንተን ሳስብ ሁሌ ወደጭንቅላቴ የሚመጣው ዼጥሮስ ነው ... ለጌታው የነበረው ቅንአት እንዴት ከፍተኛ እንደነበር... ኖት መጨረሻ ላይ የካደውን ፓርት ደግሞ ሰደበቺኝ እንዳትል :lol: ሊይዙት ሲመጡ አምላክ ወደደውም አልወደደውም ግድ ሳይኖርው ጆሮ በስለት ሸርክቶ መጣሉ .... ግን ያኔ ጌታ መልሶ ጆሮውን ሲገጥም ምን ተሰምቶት ይሆን? ለሁሉም ኮምፕሊመንት ነው ... ሌላ እንዳይመስልህ .. !
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby ዲጎኔ » Thu Apr 26, 2012 6:42 pm

ሰላም ለሁላችን ለግብዞች እምቧይን ብርቱካን ለሚሉት ጭምር
እንዴት መታደል ነው አንድ ዳግማዊ ጴጥሮስ ለሀይማኖቱ ቀናኢ ተገኘ ፕፕፕፕ ሰውን ሱሳይድ አድርግ ራስህን አጥፋ የሚል የሰይጣን ቁራጭ በተባረኩት ሐዋርያት አምሳያ ሲጠራ እንዴት ዝም ልበል? እሳት ከሰማይ ወርዶ ሀዲያን ሲያቃጥል እልል የሚል አጋንንት ብጹእ ወቅዱስ ሆእነላችሁዋ እንዴት ታድላችሁዋል? ተረታችሁ ምን ይላል የአይጥ ምስክር ድንቢት ..ምን ከምን አብረህ አዝግም

...
recho wrote:
እናመሰግንሃለ� wrote:ሀዲስ የጀመረውን ጳውሎስ ኞኞን ዝክር ይቀጥልበት:: ዲጎኔና መሰል እስላማዊ-ወያኔያዊ-ተሃድሶአዊ-ፕሮቴስታንታዊ ልክፍታሞች ታሪክ እያዛባችሁ ተዋህዶን አታንሱ!! አለዚያ እስከዶቃ ማሠሪያችሁ ይነገራችኋል!!
በውነቱ እንደዚህ ሀይማኖተኛ እና እምነት በተራራቁበት, ላመኑበት ነገር ዴዲኬሽን በጠፋበት, ሸፍጥና ክህደት በበዛበት በዚህ ዘመን እንደዚህ ላመነበት ነገር እስከሞት የሚከራከር ሰው መገኘቱ አሁንም የሰውልጅ ተስፋ እንዳለው ነው የሚያሳየው ... አንተን ሳስብ ሁሌ ወደጭንቅላቴ የሚመጣው ዼጥሮስ ነው ... ለጌታው የነበረው ቅንአት እንዴት ከፍተኛ እንደነበር... ኖት መጨረሻ ላይ የካደውን ፓርት ደግሞ ሰደበቺኝ እንዳትል :lol: ሊይዙት ሲመጡ አምላክ ወደደውም አልወደደውም ግድ ሳይኖርው ጆሮ በስለት ሸርክቶ መጣሉ .... ግን ያኔ ጌታ መልሶ ጆሮውን ሲገጥም ምን ተሰምቶት ይሆን? ለሁሉም ኮምፕሊመንት ነው ... ሌላ እንዳይመስልህ .. !
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby ገልብጤ » Thu Apr 26, 2012 6:52 pm

ዲጎኔ wrote:ሰላም ለሁላችን ለግብዞች እምቧይን ብርቱካን ለሚሉት ጭምር
እንዴት መታደል ነው አንድ ዳግማዊ ጴጥሮስ ለሀይማኖቱ ቀናኢ ተገኘ ፕፕፕፕ ሰውን ሱሳይድ አድርግ ራስህን አጥፋ የሚል የሰይጣን ቁራጭ በተባረኩት ሐዋርያት አምሳያ ሲጠራ እንዴት ዝም ልበል? እሳት ከሰማይ ወርዶ ሀዲያን ሲያቃጥል እልል የሚል አጋንንት ብጹእ ወቅዱስ ሆእነላችሁዋ እንዴት ታድላችሁዋል? ተረታችሁ ምን ይላል የአይጥ ምስክር ድንቢት ..ምን ከምን አብረህ አዝግም

...
recho wrote:
እናመሰግንሃለ� wrote:ሀዲስ የጀመረውን ጳውሎስ ኞኞን ዝክር ይቀጥልበት:: ዲጎኔና መሰል እስላማዊ-ወያኔያዊ-ተሃድሶአዊ-ፕሮቴስታንታዊ ልክፍታሞች ታሪክ እያዛባችሁ ተዋህዶን አታንሱ!! አለዚያ እስከዶቃ ማሠሪያችሁ ይነገራችኋል!!
በውነቱ እንደዚህ ሀይማኖተኛ እና እምነት በተራራቁበት, ላመኑበት ነገር ዴዲኬሽን በጠፋበት, ሸፍጥና ክህደት በበዛበት በዚህ ዘመን እንደዚህ ላመነበት ነገር እስከሞት የሚከራከር ሰው መገኘቱ አሁንም የሰውልጅ ተስፋ እንዳለው ነው የሚያሳየው ... አንተን ሳስብ ሁሌ ወደጭንቅላቴ የሚመጣው ዼጥሮስ ነው ... ለጌታው የነበረው ቅንአት እንዴት ከፍተኛ እንደነበር... ኖት መጨረሻ ላይ የካደውን ፓርት ደግሞ ሰደበቺኝ እንዳትል :lol: ሊይዙት ሲመጡ አምላክ ወደደውም አልወደደውም ግድ ሳይኖርው ጆሮ በስለት ሸርክቶ መጣሉ .... ግን ያኔ ጌታ መልሶ ጆሮውን ሲገጥም ምን ተሰምቶት ይሆን? ለሁሉም ኮምፕሊመንት ነው ... ሌላ እንዳይመስልህ .. !

ዲጎኒ ቅድመ አያቴ... እንኳን ደህና መጣክ
ቅድም ልታነቅ ነው ብለክ ደይመህ አልነበር ንዴ :roll: :roll: ገመዱ ተበጠሰ ማለት ነው
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1681
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

Next

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests