ጳውሎስ ኞኞ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ዘርዐይ ደረስ » Thu Oct 04, 2012 10:29 pm

ሀዲስ 1 wrote:ሰላም ዘርዐይ ደረስ !!!

ይሄንን መልዕክትህን ገና ዛሬ ማንበቤ ነው ::
ለተሳትፎህ እናመሰግንሀለን ::

ግን ከቶፒኩ ለምን ወጣህ አትበለኝና "ፍትሀትን" በተመለከተ የኔም አስተሳሰብ እንደ "ጳውሎስ ኞኞ" ነው ::

በፍትሀት መፅደቅ ካለ ሲኦል እኮ ባዶ ሊሆን ነው !

ለምሳሌ :--
1. አንዱ እድሜ ልኩን ፈጣሪን ሲፈራ : ሲያከብር : ትዕዛዙን ሲጠብቅ ኖሮ ቀሳውስት የሌሉበት ቦታ ህይወቱ ብታልፍና ማንም ፍትሀት ሊያደርግለት ባይችል ሲኦል ሊገባ ነው ማለት ነው ?

2. ሌላው ግለሰብ የስንቱን ህይወት ያጠፋ : ስንቱን ወላጅ ያለልጅ ያስቀረ : የዘረፈ : ፈጣሪውን የሰደበ በሞቱ ወቅት ባጠገቡ ቀሳውስት አግኝቶ ፍትሀት ስለተደረገለት ከቅን ምዕመናን ጋር ነፍሱ ከገነት ታርፍ ይሆን ?

በቁጥር ሁለት የተጠቀሰው ልክ ከሆነ ..... ታዲያ በዚህች አለም ውጥንቅጥ ውስጥ ለምንስ ራሳችንን እናቅባለን ? ...... ሙልጭ ያለ አለማዊ ኑሮ መኖር : መግደል : መዝረፍ : ማመንዘር : ፈጣሪን ማስቀየም : ወዘተርፈ ፈፅመን በሞታችን ወቅት ለምን ፍትሀት አይደረግልንምና ገነትን አንወርስም ? ለምንስ ይሄንን የመሰለ ወርቃዊና አለማዊ ህይወት ኢግኖር አድርገን ራሳችንን እናስጨንቃለን ? መጨረሻ ላይ ቤተሰቦቻችን ስህተቶቻችንን በፍትሀት ሊያርሙልን ከቻሉ ?

ሪሊ ለዚህ ነገር መልስ እፈልጋለሁኝ :: በበኩሌ በጳውሎስ መልስ ነው የማምነው ::

ሀዲስ


ሰላም ሀዲስ:-

መቼም ስለ ጳውሎስ ኞኞ ሲወራ ትዝ የሚለን ቀልዱ የታሪክ አዋቂነቱና ታዋቂ ጋዜጠኝነቱ ወዘተ እንጂ ሃይማኖት አይደለም::እኔም በዚህ ርእስ መሳተፍ የፈለግኩት ሃይማኖትን ሳልነካ ነበር::ተገድጄ ነው የገባሁበት::ያንን ጽሑፍም ያቀረብኩት ፍትሐት ያድናል ወይስ አያድንም የሚል ክርክር ለመክፈት ሳይሆን ጳውሎስ የሰጠው መልስ አግባብ አለመሆኑን ለማሳየት ነው::

:arrow: እሱ የኦርቶዶክስ አማኝ ካልሆነ መጀመርያ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ፍትሕት ለምን እንደሚደረግና የፍትሕት ዓይነቶቹን ማብራራት ነበረበት::ጠያቂው ጳውሎስ ስለ ፍትሐት ያለውን አቋም አወቁ እንጂ የስብከተ ወንጌል መምርያ ከላይ ያቀረብኩትን መልስ እስኪሰጥ ድረስ ለጥያቂያቸው አጥጋቢ መልስ ያገኙ አይመስለኝም::እንደ መምርያው አባባል ጳውሎስ ተደጋጋሚ ምክር ተሰጥቶት በዚህ በኩል ማሻሻያ እንዳላሳየ ነው::በሚልዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የሚቀበሉትን ነገር እንደዚህ ማጣጣሉ ላይ ነው የማልስማማው እንጂ በሥርዓቱ የቤተ ክርስቲያኒቱን እምነት ካስቀደመ በኋላ የራሱን አስተያየት ቢጨምርበት እንደዚህ ተቃውሞ አይገጥመውም ነበር::

:arrow: ፍትሕትን በተመለከተ የመልስ ጽሑፉ ላይ የተሰጠው ማብራርያ ካላረካህ እኔ የምጨምረው ነገር የለኝም::አንድ ማለት የምፈልገው ነገር ግን ፍትሕት ያልተደረገለት ሰው ሁሉ አይድንም ወይም ፍትሐት የተደረገለት ሰው ሁሉ ይድናል ብዬ እኔም አላምንም::
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1159
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Postby ዘርዐይ ደረስ » Sat Oct 13, 2012 6:44 pm

ጠያቂ:-እሻሻላለሁ ብዬ ቡናቤት ብቀጠር ሰለቸኝ::አንዱ በጥፊ ሲያጠናፍረኝ አንዱ ደግሞ በካልቾ ያወልቀኛል::በቡሀ ላይ ቆረቆር እንደሚባለው ሁሉ አንዱ ደግሞ በነፃ ጠጥቶብኝ አጭበርብሮኝ ይሔዳል::ፊቴም ማድያት አወጣ::ምን እንደሚሻለኝ ግለጥልኝ?


ወይዘሮ እናኑ ሽፈራው ከመሿለኪያ

ጳውሎስ ኞኞ:-አዝናለሁ እምይ ምን እንደምልሽ ግራ ነው የገባኝ::እግዚአብሔር ከዚያ ቦታ እህል ውሃሽን እስቲጨርሰው ድረስ እንዲያው እየቻልሽ ኑሪ::አንድ ቀን ቀን ይወጣልሽ ይሆናል::ቀኑ ግን መቼ እንደሆነ አላውቀውም::

* * *

ጠያቂ:-በአዲስ አበባ ከተማ በሦስት ቁጥር አውቶቡስ የምንመላለስ ነን::ግን በዚያ አውቶቡስ ላይ አብዛኛውን ጊዜ የሚመላለሱበት ቆማጦች ናቸው::ታድያ የነኝያ ሰዎች በሽታ በጤነኞቹ ላይ አይጋባም?
በ-ለ-

ጳውሎስ ኞኞ:-ይጋባል::ባጭሩ ቆማጣን ለማበርከት ካልሆነ በስተቀር ለእነሱ አንድ የተለየ አውቶቡስ ማቋቋም ይቻል ነበር::ለነገሩማ ከመንደርስ ቢሆን አብረውን አይደል የሚውሉት?ይኽ ነገር በእውነት ሊታሰብበት የሚገባ ነው::

* * *

ጠያቂ:-ባለፈው አምድህ ጡት የሚያሳድግ ነገር እንዳለ ንገረኝ ተብለህ ተጠይቀህ ነበር::ለዚህ ጥያቄ መልስ ያገኘህለት አይመስለኝም::እኔ ከዚህ በፊት ተጠቅሜ ውጤት ያገኘሁበት መሣርያ ስላለ ይህንኑ መሣርያ ፎቶግራፉንና ጥቅሙን የሚገልጥ ወረቀት ልኬልሃለሁና አንብበህ ለጠያቄዎችህ አስረዳ::

ብዙነሽ ተፈራ

ጳውሎስ ኞኞ:- ከጽሑፉ ይልቅ አንቺ ልክ መሥራቱን ማለት ጡትሽን ማሳደጉን ሞክረሽው መልካም ውጤት ካሳየ ያንቺው ምስክርነት በቂ ሊሆን ይችላል::የዚያን ጉዳይ ዝርዝር ማውጣት ደግሞ ገንዘብ ያልተከፈለበት ማስታወቂያ ስለሚሆን ታሪኩን አላወራም::

* * *


ጠያቂ:-በቀደም በወጣው አምድህ ላይ የመታወቂያ ወረቀቱን መልሰህ የሰጠኸው ሰውዬ የነገረኸን ቃል ጽፈኸው አንብበነዋል::እሱ የሚለው ሌቦች ደበደቡኝ ገንዘብም ወሰዱብኝ ነው::እኛ ለራሳችን እንዲህ ያለውን ነገር የምናደርግ አይደለንም::እርግጥ ነገር ቢፈልገን ትንሽ ዠላልጠን ለቀነዋል::በኋላም የተዝረከረከ ዕቃ አግኝተን ስንለቅም ያንንም የመታወቂያ ወረቀት አግኝተን በአንተ በኩል እንዲደርሰው ላክን::ያገኘናትም ገንዘብ ብትሆን ትንሽ ናት::ለምንም አትበቃ::አንተ እንዲህ የምትረዳን ከሆነ ለወደፊቱ የምናገኘውን የማይጠቅመንን ዕቃ እንልክልህና ለየባለቤቱ ትሰጣለህ::በዚህ ትስማማለህ?

እነ-----

ጳውሎስ ኞኞ:-እነማን ናችሁ?መቼም ለመስማማት ከሆነ ባትሰርቁ ደህና ነበር::ደግሞም የምትሰርቁ ከሆነ የማይጠቅማችሁን ዕቃ ከምትጥሉት ለተሰራቂው ይጠቅመዋልና እንደፈረደብኝ አቀባባይ ሆኜ ልኑር::እግረመንገዳችሁን ታድያ እኔን አደራ::


* * *

ጠያቂ:-በሲጃራ ውስጥ የሚገኘው ግንድ አስቸገረን::የጭሱ አንሶ የከሰሉ ተጨማሪ ምን ይባላል?

ጭሰኛው

ጳውሎስ ኞኞ:-ቢሆን ቢሆን ተጣጥሮ ከጭሰኝነት መገላገል ነበር::ያለዚያ እነሱ በነገሩ ላያስቡበት እኔንም የትንባሆ ቁራጭ ማከማቻ አታድርጉኝ::ሁሉም ሰው ፍልጡን እየላከ እይልኝ ይለኛል::አይቸዋለሁና አውቄዋለሁና እዚያው ሜትር ኩባችሁን እያወጣችሁ ጣሉት::ምን ላድርግ?

* * * *
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1159
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Previous

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: Google Adsense [Bot] and 4 guests