ጳውሎስ ኞኞ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby እናመሰግንሃለ » Thu Apr 26, 2012 7:06 pm

-----
Last edited by እናመሰግንሃለ on Tue Sep 03, 2013 4:52 pm, edited 1 time in total.
እናመሰግንሃለ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 824
Joined: Mon Jun 01, 2009 8:07 pm

Postby recho » Thu Apr 26, 2012 7:46 pm

ዲጎኔ wrote:ሰላም ለሁላችን ለግብዞች እምቧይን ብርቱካን ለሚሉት ጭምር

ማፈሪያ ማፈሪያ ነህ .. ባንተቤት በአሽሙር መሳደብህ ነው !

እንዴት መታደል ነው አንድ ዳግማዊ ጴጥሮስ ለሀይማኖቱ ቀናኢ ተገኘ ፕፕፕፕ

በመናገር መብቴ ተጠቅሜ እና በገዛ ጭንቅላተ አስቤ የፈለኩትን ሰው እንደፈልኩ አድርጌ ኮምፕሊመንት ማድረግ መብቴ ነው! ባንተ ጭንቅላት እንዳስብ አትጠብቅ አይደረግም! አንተን ያናገረህ የለም ! የጋበዘህም ጭምር ... እስቲ እንደ ክርስቲያን ሲነኩህ ማሳለፍን እና ከቻልክ ሳይነኩህ መንካትን ተው ! አንተ የምትለው አይነት ክርስክቲያን ከሆንክ አያቅትህም

ተረታችሁ ምን ይላል የአይጥ ምስክር ድንቢት ..ምን ከምን አብረህ አዝግም

አይዞህ ጨርሰው .. ግም ለግም አብረህ አዝግም ነው ተረቱ! ማፈሪያ ነህ አሁንም ! እንደ እድሜህ አስብ አባባ ማሙሽ ... ማንነቴን የምታውቅ አልመሰለኝም! በሀይማኖት ነጻነት አምናለሁ .. ማስታወሻ ካለህ እሳት ሲወርድ እልል ሲል መጀመሪያ የተጣላው ከኔጋር ነው .. ዽንጤ ምናም እያለ ሲያብጠለጥለኝ ነበር .. አልተቀየምኩትም .. ለሀይማኖቱና ለቤተክርስቲያኑ ካለው ቀናኢነት የተነሳ ያለውን ብልዋል ..
በጣም ይከብድሀል እንጂ ከቻልክ ዱ ሚ ኤ ፌቨር አንድ ጸሎት ጸልይ ... የክርስቶስን ልብ ይስጠህ... ለሚሰድቡህ የምትጸልይበትና የምትመርቅበት, ሲበድሉህ ይቅር የምትልበት.

ጨረስኩ .. ምልስልስ ስለምትወድ እየመጣህ እንደምትንዛዛ አልጠራጠርም !
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Thu Apr 26, 2012 7:55 pm

recho

እኔን አትሳደብ እያልሽ እየመከርሽ እዚህ ትዘላለፊያለሽ አይደል :D የሰይፉን ጭውውት ላገኘው አልቻልኩም.....ምንአልባት ጉዳዩ የሚስብ ስላልሆነ በደንብ አልፈለኩት ይሆናል.....ይቅርታ :wink:

ሌላ ደህና ጉዳይ ፈልጊና አዛው አንቺው ቤት ወጋችንን እንቀጥል.....አንቺ ልጅ በቀኝ አውለኝ በይ :lol:

ሠላም

recho wrote:

"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Postby recho » Thu Apr 26, 2012 8:02 pm

ቅቅቅ መች ተሳደብኩ .. ማፈሪያ ያልኩት ስለሆነ ነው .. ያልሆነው አላልኩትም .. ግን የምርን አንድ ነገር የታዘብኩት ምን መሰለህ ..ኦርቶዶክስ ኤክስትሪም ሲሄድ ተዎ እናንተ እግዜሩ አይወደውም ካልክ ዽንጤ ነህ ... ዽንጤዎቹ ደግሞ ሲተረተሩ እረ ጉድ ካልክ ግም ለግም አብረህ አዝግም ትባላለህ .. ቴዲን ከጠላህ ወያኔ ትባላለህ.... ኤርትራዊያን ብላቹ ህዝቡን አትሳደቡ ከመንግስት ጋር ያላቹን ጭግር እዛው ጨርሱ ካልክ ደግሞ ሻቢያ ትባላለህ .. ለምን ስም ሳንሰጣጥ ጉዳዩ ዙሪያ እንደማንወያይ አይገባኝም :twisted: ይሄ ሽማግሌው ግን ሳይጠራ ጥልቅ ብሎ ነው ተሳድቦ የሄደው .. :lol: ሰሞኑን ሽማግሌዎቹ ምን ነካቸው ??? ቅቅቅ ዞረብኛል ባክህ ! ለነገሩ ዲጎኔን እንኩዋን አውቀዋለሁ ... የሚያሳዝነው .. ባለው ሀይማኖታዊ አቁዋም ከ እናመሰግንሀለን ጋር እኩል የማደንቀው ሰው ነው .. አሁንም አደንቀዋለሁ .. ለሀይማኖቱ ካለው ቀናኢነት የተነሳ ዛረ ሪቾን ስለተሳደበ መንግስተ ሰማያትን ሴኢውር አርግዋል ...ቅቅቅቅ በማቃጠር የሚገባበት ቤት ቢሆን አልቆልን ነበር :lol: :lol:

የሰይፉን ጉዳይማ ዝም ስትል እንዳሸነፍኩ ቆጥሬ እኮ አለፍኩት ቅቅቅ ሌላ ጉዳይ አምጣ ... ምን ጭር ኢንተሌክችዋሊ እኔ ወይ አንተ እስክናምን ሳንሰዳደብ እንወያይና እስቲ ዋርካዊያንን እንደዚህም አለ እናስብላቸው :lol:ዳግማዊ ዋለልኝ wrote:recho

እኔን አትሳደብ እያልሽ እየመከርሽ እዚህ ትዘላለፊያለሽ አይደል :D የሰይፉን ጭውውት ላገኘው አልቻልኩም.....ምንአልባት ጉዳዩ የሚስብ ስላልሆነ በደንብ አልፈለኩት ይሆናል.....ይቅርታ :wink:

ሌላ ደህና ጉዳይ ፈልጊና አዛው አንቺው ቤት ወጋችንን እንቀጥል.....አንቺ ልጅ በቀኝ አውለኝ በይ :lol:

ሠላም

recho wrote:
ዲጎኔ wrote:ሰላም ለሁላችን ለግብዞች እምቧይን ብርቱካን ለሚሉት ጭምር

ማፈሪያ ማፈሪያ ነህ .. ባንተቤት በአሽሙር መሳደብህ ነው !

እንዴት መታደል ነው አንድ ዳግማዊ ጴጥሮስ ለሀይማኖቱ ቀናኢ ተገኘ ፕፕፕፕ

በመናገር መብቴ ተጠቅሜ እና በገዛ ጭንቅላተ አስቤ የፈለኩትን ሰው እንደፈልኩ አድርጌ ኮምፕሊመንት ማድረግ መብቴ ነው! ባንተ ጭንቅላት እንዳስብ አትጠብቅ አይደረግም! አንተን ያናገረህ የለም ! የጋበዘህም ጭምር ... እስቲ እንደ ክርስቲያን ሲነኩህ ማሳለፍን እና ከቻልክ ሳይነኩህ መንካትን ተው ! አንተ የምትለው አይነት ክርስክቲያን ከሆንክ አያቅትህም

ተረታችሁ ምን ይላል የአይጥ ምስክር ድንቢት ..ምን ከምን አብረህ አዝግም

አይዞህ ጨርሰው .. ግም ለግም አብረህ አዝግም ነው ተረቱ! ማፈሪያ ነህ አሁንም ! እንደ እድሜህ አስብ አባባ ማሙሽ ... ማንነቴን የምታውቅ አልመሰለኝም! በሀይማኖት ነጻነት አምናለሁ .. ማስታወሻ ካለህ እሳት ሲወርድ እልል ሲል መጀመሪያ የተጣላው ከኔጋር ነው .. ዽንጤ ምናም እያለ ሲያብጠለጥለኝ ነበር .. አልተቀየምኩትም .. ለሀይማኖቱና ለቤተክርስቲያኑ ካለው ቀናኢነት የተነሳ ያለውን ብልዋል ..
በጣም ይከብድሀል እንጂ ከቻልክ ዱ ሚ ኤ ፌቨር አንድ ጸሎት ጸልይ ... የክርስቶስን ልብ ይስጠህ... ለሚሰድቡህ የምትጸልይበትና የምትመርቅበት, ሲበድሉህ ይቅር የምትልበት.

ጨረስኩ .. ምልስልስ ስለምትወድ እየመጣህ እንደምትንዛዛ አልጠራጠርም !
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby ገልብጤ » Thu Apr 26, 2012 8:09 pm

ሪቾ ወያኔ ነሽ ለካስ :roll: :roll:
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1681
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

Postby recho » Thu Apr 26, 2012 8:48 pm

ገልብጤ wrote:ሪቾ ወያኔ ነሽ ለካስ :roll: :roll:
እረ ተወኝ ወዳጄ ! የስድብ ሁሉ የከፋውን ሁሉ ሆንኩ እኮ ዘንድሮ .. ለደግነቱ ዋርካ ብቻ መሆኑ! :lol: :lol:
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby ዲጎኔ » Fri Apr 27, 2012 3:01 am

ሰላም ለሁላችን ይሁን
ወገኖች በተለይ ሪቾ ስለተግሳጸሽ በጣም አመሰግናለሁ የማምነው ጌታዬ ክርስቶስ ቅዱሱ ሲሰድቡት አንዳች ክፉ እንዳልወጣው እኔም ባሪያው ያንን ማድረግ አለብኝ::ነገር ግን ሰው ነኝና አንቺ ወገኞችን ፊትለፊት ስትፋለሚ የማውቅሽ ይህንን የሌላውን በእሳት መቃጠልና ራስን ማጥፋት የሚያበረታታ ጉድ በተባረከው ሐዋርያ ጴጥሮስ ስታመሳስይ መቀበል ስላልቻልኩ ያልኩትን ብያለሁ ይቅርታ!
ከዚህ በተረፈ ሽማግሌነት ጸጋ ነው አይደለሁም ምስሌን የሚያውቅ ጌታን ጠይቂው::
ለማንኛውም በክርስቶስ ፍቅር እወደሻለሁ በላ ለዴጢ!
ዲጎኔ ሞረቴው ከተሀድሶ ሰማእቷ ብዙነሽ ሰፈር አማውቴ ሶዶ
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby እናመሰግንሃለ » Fri Apr 27, 2012 4:01 am

----
Last edited by እናመሰግንሃለ on Tue Sep 03, 2013 4:54 pm, edited 1 time in total.
እናመሰግንሃለ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 824
Joined: Mon Jun 01, 2009 8:07 pm

Postby recho » Fri Apr 27, 2012 1:34 pm

ጥሩ ! አሁን ተግባባም መሰለኝ! :)

ዲጎኔ wrote:ሰላም ለሁላችን ይሁን
ወገኖች በተለይ ሪቾ ስለተግሳጸሽ በጣም አመሰግናለሁ የማምነው ጌታዬ ክርስቶስ ቅዱሱ ሲሰድቡት አንዳች ክፉ እንዳልወጣው እኔም ባሪያው ያንን ማድረግ አለብኝ::ነገር ግን ሰው ነኝና አንቺ ወገኞችን ፊትለፊት ስትፋለሚ የማውቅሽ ይህንን የሌላውን በእሳት መቃጠልና ራስን ማጥፋት የሚያበረታታ ጉድ በተባረከው ሐዋርያ ጴጥሮስ ስታመሳስይ መቀበል ስላልቻልኩ ያልኩትን ብያለሁ ይቅርታ!
ከዚህ በተረፈ ሽማግሌነት ጸጋ ነው አይደለሁም ምስሌን የሚያውቅ ጌታን ጠይቂው::
ለማንኛውም በክርስቶስ ፍቅር እወደሻለሁ በላ ለዴጢ!
ዲጎኔ ሞረቴው ከተሀድሶ ሰማእቷ ብዙነሽ ሰፈር አማውቴ ሶዶ
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby ምክክር » Sat May 05, 2012 7:32 am

ጳውሎስ ኞኞ ልጅ እግር ሳለ አንድ ዓይነ ሥውር ጣልያን ፓስቲ ቤት ባሬስታ ቀጥሮ ያሰራው ነበር:: አዲስ አበባ::ሳንቲቶ ይባላል:: ሳንቲቶ ዓይነ ሥውር ቢሆንም ወደል ያለ ቂጣም ጣልያዊ ነው:: ሳንቲቶ ዓይኑ ስለማያይ ጳውሎስን ይጠረጥረዋል:: ፓስቲውን ከሚሸጠው ይልቅ የሚበላው ይበልጣል በሚል:: እናም ጳውሎስ አራዳው የአለቃውን ጥርጣሬ ለማስታገስ ሲል ፓስቲ ቤት ውስጥ እየባሸረ ሲንጎራደድ ማፏጨት ያበዛል:: አፌ ፍሪ ነው ፓስቲ አልያዘም እመነኝ ሳንቲቶ እንደማለት:: ጳውሎስ ዘንግቶ ፉጨት ካቆመ ጣልያዊው በንዴት ባንኮኒውን እየመታ "ምኖ ጳውሎስ ፉጨት አቆመ ፓስቲ በላ መሰለኝ" ሲለው ጳውሎስ ወዲያው አፉን እየጠራረገ ፉጨቱን ይቀጥላል:: ዘፈን ነው:: ጓደኞቹ ቀኑን ሙሉ ስታፏጭ አይደክምህም ሲሉት ዘፈኗንም ስለምወዳት አይሰለቸኝም ይላቸዋል:: ቂቂቂቂ

የወንፈሌ የወንፈሌ ጥጥ
የሳንቲቶ ቂጥ
የወንፈሌ ጥጥ
የሳንቲቶ ቂጥ
እያለ የሚቀጥል ዘፈን ነበር......በፉጨት
ምክክር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 322
Joined: Thu Jun 26, 2008 10:10 am
Location: Super Earth

Postby ዘርዐይ ደረስ » Wed Aug 15, 2012 10:19 pm

ሀዲስ 1 wrote:ጋሽ ጳውሎስ ኞኞን ለማስታወስ ጊዜያችሁን በመሰዋት እዚህ ብቅ ላላችሁ ሁላ ምስጋና ይድረሳችሁ :: ታዲያ እንደእህታችን ሪቾ አንዳንድ ነገር ጣል ጣል ብታደርጉ መልካም ነው :: ሪቾ በርቺ : አትጥፊ ::

እውቁ ጋዜጠኛና ደራሲ ጳውሎስ ኞኞ በ 11 ህዳር 1926 ዓ.ም ቁልቢ አካባቢ ተወልደው ድሬዳዋ ከተማ አደጉ :: በጣሊያን ወረራ ምክንያት ትምህርታቸውን ከ 4ኛ ክፍል በላይ መቀጠል አልቻሉም ነበረ :: ብሩህ አእምሮና የፈጠራ ችሎታ የነበራቸው ሰው ስለነበሩ : በልጅነታቸው የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ጣሊያንን ሰገድሉ ወይም ሲማርኩ ስዕል በመሳል ያሳዩ ነበረ :: ጳውሎስ ካላቸው የፅሁፍ ጥማት የተነሳ የ ድምፅ ጋዜጣ አዘጋጅ በመሆን የብዕር ድምፃቸውን ያሰሙ ነበረ :: ጋዜጦች ላይ ከፅሁፍ አቅራቢነት እስከ አዘጋጅነት ለበርካታ አመታት ሰርተዋል :: በተለይ አንድ ጥያቄ አለኝበሚለው የአዲስ ዘመን ጋዜጣ አምዳቸው ላይ ብዙ ታዋቂነትን አግኝተዋል :: አቶ ጳውሎስ ኞኞ ከ 1955 ዓ.ም. ጀምሮ ለኢትዮጵያ ስነፅሁፍ እድገት የነበራቸውን ተሰጥኦ በአግባቡ በስራ ላይ ያዋሉ እውቅ ጋዜጠኛና ደራሲ ነበሩ :: እኚህ ታዋቂ ሰው በተወለዱ በ 58 ዓመታቸው ከዚህች አለም በሞት ተለይተዋል ::
አቶ ጳውሎስ
የጌታቸው ሚስቶችበሚል ርዕስ ያሳተሟትን መፅሀፍ " ከታተመችበት ወር አንስቶ ለአንድ አመት የመፅሀፌ መብት የግሌ ነው :: ከአንድ አመት በኃላ መብቱ የማንኛውም ኢትዮጵያዊ ይሁን :: ከወሰንኩት ጊዜ በኃላ አሳትሞ ለመሸጥ የፈለገ ሁሉ ከድርሰቴ ሳይቀንስም ሆነ ሳይጨምር ሊያራባው ይችላል :: ስሜን ሳይሰርዝ አሳታሚውን እገሌ ብሎ ማንም ኢትዮጵያዊ ከፈለገ እንዲያራባት የደራሲነት መብቴን ለቅቄያለሁኝ :: አሳታሚው የግሉን የመግቢያ ሀተታ በስሙ ቢፅፍ እኔም ሆንኩ ወራሼ አንቃወምም " ብለዋል ::

ምንጭ:- ውኪፔዲያ

ሀዲስሰላም ለዚህ ርእስ ከፋች ሀዲስና ሌሎችም ተሳታፊዎች:-

በእርግጥም ጳውሎስ ኞኞ በሁለገብ ችሎታውና ራሱን አስተምሮ ለ ከፍተኛ ዕውቅና መብቃቱ የሚያስደንቅ ስብዕና ያሳያል::

ሀዲስ ከዊኪ ፔድያ የወሰድከው የጳውሎስ የህይወት ታሪክ አንድ ስህተት አለበት::ጳውሎስ ትምህርቱን ያቋረጠው በጣልያን ወረራ ምክንያት ሳይሆን ድህነት ትምህርቱን መከታተል ስላላስቻለው ነው::

መቼም ጳውሎስ እንደዚህ ተጠይቆ እንደዚህ አለ ሲባል ያልሰማን የለንም::እንደ አለቃ ገብረ ሃና ተጨማምሮበት ይሁን ወይስ ሁሉም እሱ ያለው ይሁን እንጃ እንጂ::

አንዳንዴ ግን በቁም ነገር ለሚጠየቀው ጥያቄ የሚሰጠው መልስ ግን ይገርማል::አሁን እስቲ ከዚህ በታች ያለው ባልና ሚስቱን የባሰ የሚያቃቅር መልስ አይደለም?

ጠያቂ:-የቤት እመቤት ነኝ:::ኑሮዬን በደኅና ሁኔታ ለመምራት ስል ለባሌ የሚገባውን ነገር ከመፈጸም አንድም ቀን ቦዝኜ አላውቅም::ይህም ያልኩበት ምክንያት በአሁኑ ጊዜ ወንድ እንደውድ ዕቃ በመቆጠሩ ነው::ነገር ግን ጧት ጧት ለባለቤቴ ቁርስ ሳዘጋጅለት አንድም ቀን ለመብላት ፈቃደኛ ሆኖ አይገኝም::ፈቃደኛ ሆኖ የማይገኘው ለምን ይመስለሃል?

መልስ:-ምናልባት ይጠጡ እንደሆነ ሲጃራ ያጠሱ እንደሆነ::ከሆነም በልኩ ያድርጉ በሏቸው ''በአሁኑ ጊዜ ወንድ እንደ ውድ ዕቃ'' አሉ? ኧረ ዱሮም ውድ ዕቃዎች ነበርን::ከቤት ከወጡ በኋላ በየቡና ቤቱ ኬክና ካፑቺኖ ለምደውም ይሆናል::ጳውሎስ በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ችግር እንደደረሰበትም በዚህ ርእስ ሥር አንብቤአለሁ::ግን ጳውሎስስ በማያውቀው ገብቶ አልዘባረቀም?ለምሳሌ የሚከተለውን እንመልከት::

ከዚህ በታች የቀረበው ጽሑፍ 'ማስረጃ የሌለው መልስ' በሚል ርእስ ከስብከተ ወንጌልና ማስታወቂያ መምርያ ለአቶ ጳውሎስ የተሰጠ መልስ ነው::

ረቡዕ ሐምሌ 4 ቀን 1965 ዓ.ም. 33ኛ ዓመት ቁጥር 163 በወጣው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ አቶ ተክሉ ዋቅጅራ የተባሉ ሰው ''ሙሉ ፍታትና ግማሽ ፍታት የሚሉት አለ ፍታቱም በገንዘብ ይበላለጣል::በሰማይ ቤት ግማሽ ፍታት ከተደረገለት ሰው ይልቅ ሙሉ ፍታት የተደረገለት ሰው ይጸድቃል ማለት ነው?'' ብለው ላቀረቡት ጥያቄ አቶ ጳውሎስ ኞኞ አስረጂ የሌለውና ያልተስተካከለ መልስ ሰጥተዋል::የእሳቸው መልስ ባጭሩ ''ሙሉም ሆነ ጎደሎ በፍታት ጽድቅ የለም የሚል ነው::''

ይህ አነጋገር በመሠረቱ የአቶ ጳውሎስ የግል አስተያየት እንጂ አስረጂ የተጠቀሰለት ምክር የተነገረለት ስላልሆነ ተቀባይነት ሊኖረው አይችልም::አይገባብም::ፍታት ሲባል እንደ አቶ ጳውሎስ አነጋገር ሳይሆን መሠረቱ የታወቀ በአዲስ ኪዳን ህግ የጸደቀ አማናዊ ሥርዓት መሆኑን ቤተ ክርስትያን ያመነችውና የተቀበለችው ነው::ይኸውም በማቴዎስ ወንጌል ም 16 ቁ 19 እንደተጻፈው ጌታ ለቅዱስ ጴጥሮስ የሰጠው ሥልጣን በመጀመርያ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ነው::ቃሉም ''የመንግሥተ ሰማያትን ቁልፍ ሰጥቼሃለሁ::በምድርም ያሠርከው በሰማይ የታሠረ ይሆን ዘንድ በምድርም የፈታኸው በሰማይ የተፈታ ይሆን ዘንድ ይላል::

ይህ ሥልጣን የቅዱስ ጴጥሮስ ብቻ ነው እንዳይባልም ለደቀ መዛሙርቱ ሁሉ የሰጣቸው ለመሆኑ በማተዎስ ወንጌል ም 18 ቁ 18-20 ተጽፎ ይገኛል::ሌላም ተመሳሳይ ማስረጃ በዮሐንስ ወንጌል ም 20 ቁ 18 ላይ ይገኛል::ይህም ሁሉ የሚያስረዳው ካህናት በሰው ነፍስ ላይ ያላቸው የማሠርና የመፍታት ሥልጣን መሠረቱ ከምን ከማንስ እንደሆነ ነው::ቤተክርስትያናችን ይህን የመሰለ የጌታችንን ቃል መሠረት ሳታደረግ የምትሠራውና የምትፈጽመው ወይም ለሌሎች የምታዘው ሥርዓት የለም:.ስለዚህ አንድ ሰው ነፍሱ ከሥጋው ከተለየች በኋላ ጸሎተ ፍትሐት የሚደረግለት ወይም የሚፈታው ከዚህ በላይ እንደተገለጠው ጌታችን ለሐዋርያት በሰጠው ሥልጣን መሠረት ከማዕሠረ ኃጢአት ለመፍታትና ፍጹም የሆነ ሥርየትን ለማሰጠት ነው እንጂ የልማድ ጉዳይ አይደለም::እግዚአብሔር ሰውን የሚምርበትና ይቅር የሚልበት ምክንያት ፈላጊ እንደመሆኑ ካህናት ከላይ በተሰጣቸው ሥልጣን ስለአንድ ሰው ብቻ ሳይሆን በመሰላቸው መንገድ ስለ ሰው ልጆች ሁሉ ደኅንነት ወደ ፈጣሪ ቢጸልዩና ቢማልዱ እግዚአብሔር ጸሎታቸውን ይቀበላቸዋል::እግዚአብሔር ካጸደቀ ደግሞ ጽድቅን የሚከለክል ማንም የለም::

አቶ ጳውሎስ ይህንን ሳይውቁ ቀርተው ይሁን አውቀውም ክደውት ይሁን ምክንያታቸው በግልጥ አልታወቀም::ብቻ ቃሉን በፈቃዳቸው ሽረው ሕዝቡን ያሰናበቱ ይመስላል::ይህም ራሱ የቤተ ክርስትያንን መብት መጋፋት ስለሆነ ወደፊት ቢያስቡበት አይከፋም::አቶ ጳውሎስ በቤተ ክርስትያን ሥርዓትና እምነት ውስጥ እየገቡ ይህን መሰል የስህተት መልእክት ለማስተላለፍ ሲሞክሩ ይህ የመጀመርያ ጊዜያቸው ሳይሆን ተደጋግሞ የታወቀ ነው::ሆኖም(ላም ባልዋለበት----እንደሚባለው ሰዎችን ግራ ከማጋባት እና ራሳቸውን ከማስገመት በቀር በዚህ በኩል መልስ ለመስጠት ባደረጓቸው ሙከራዎች ሁሉ ጥሩ ውጤት አስገኝተዋል ማለት አይቻልም:.ስለዚህ አቶ ጳውሎስ ይህንን ተወት አድርገው የዚህ ዓይነት ጥያቄ ሲያጋጥማቸው አገኝ አጣውን ከመቀባጠር ተቆጥበው ጉዳዩ እኔን ስለማይመለከት ለሚመለከተው ክፍል አስተላልፌዋለሁ መልሱን በዚያ በኩል ተጠባበቁ ቢሉ ኖሮ ሳይመሰገኑ አያልፉም ነበር::ሙሉ ፍታት ግማሽ ፍታት የተባለውም በቤተ ክርስትያን ውስጥ የሌለ የስሕተት አነጋገር ነው::አለ የሚባልም ቢኖር የጉዞ ፍትሐትና በቤተ ክርስትያን የሚፈጸመው ጸሎተ ፍትሐት ነው::ይህም ሙሉና ግማሽነቱን የሚያሳይ ሳይሆን በመንገድ እየሄዱ የሚፈጸምና በአንድ ቦታ ተቁሞ የሚከናወን መሆኑን የሚያመለክት ነው እንጂ ከላይ እንደተባለው መበላለቱን አይደለም አሁንም እንደዚህ የመሳሰሉትን ጉዳዮች ቤተ ክርስትያን መልስ እንድትሰጥባቸው ማድረጉ ለሁሉም የሚበጅ ምክራችንን እንለግሳለን::

ምንጭ:-አዲስ ዘመን ሐምሌ 14 ቀን 1965 ዓ.ም.

:arrow: እንግዲህ በአቶ ጳውሎስና በቤተ ክርስትያኒቱ መካከል የነበረው ግጭት በጊዜው ነበርን የሚሉ መናፍቃን እንደሚሉት ሳይሆን በዚህ እና በተመሳሳይ መልኩ አቶ ጳውሎስ ይፈጥሩት በነበረው አግባብ ያልሆነ ጣልቃ ገብነት መሆኑን ይህንን የታሪክ ማኅደር አግኝቼ ለማረጋገጥና ይመለከተኛል ለሚል ሁሉ ለማካፈል በመቻሌ ደስ ብሎኛል::
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1159
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Postby ዲጎኔ » Thu Aug 16, 2012 4:41 am

"ይህ ሰው በሽታ ሆኖ በአለም ባሉት አይሁድ ሁሉ ሁከት ሲያስነሳ የመናፍቃን መሪ ሆኖ አግኝተነዋል"የሐዋስራ 24:5(መናፍቃን ሐዋርያን ሲከሱ)

ሰላም ለሁሉ ለዋርካ ግብዝ ፈሪሳዊያን ራሳቸው መናፍቅ ሆነው ኢመናፍቁን መናፍቅ ለሚሉት ጭምር

ደራሲ የኮሪያ ዘማች አስታራቂ አስማሚና ተሀድሶ ወንጌል አማኝ ጳውሎስ ኞኞ ከዘመን የቀደመ የእውነት ጋዜጠኛና የሰውልጆች መብት ተሟጋች ነበር::
አዎ እዚህ እንደተጠቀሰ በግማሽ ይሁን በሙሉ በፍትሀት መዳን እንደሌለ ቀድሞ የገባው ጳውሎስ ኞኞ ለጠያቂው ተገቢ መልስ ሰጥቷል::ተዝካር ዘኬ የለመዱ ቢያወግዙት ጣልቃ ገብ ቢሉት በከንቱ ወጋቸው ለምን ወደእኛ ይህን ጥያቄ አልመራህ ብለው ቢያጣጥሉት ለጳውሎስ ያ ምኑም አልነበር::ሁለት ጊዜ ያውም በዚያ ዘመን 300 ብር መቀጫ ያስቀጡ ምንደኞች ልጅ ዛሬ ሙትወቃሽ ሆኖ ከባህሉ ውጭ ጳውሎስ የሰጠውን ተገቢ መልስ ሊተች ይዳዳል::ጳውሎስ ወደመጨረሻ ላይ አንዱ የጉዋደኛውን እህት ወዶ በየቀኑ መስኮት ላይ ይገተር የነበር ልጆቷን በግምባር አገናኝቶ እንደማትፈልገው ሰውየው ሲረዳ ወደህሊናው መመለሱ ከጳውሎስ ድንቅ ስራዎች አንዱ ነበር::እሱና ባለቤቱ ልጅ ሳይኖራቸው በፍቅር እንደሚኖሩ እየጠቀሰ የወለዱት እንዲፋቀሩ ምክሩና እነአክሊለ ከበደ ያሳደጋቸው የድሀልጆች ለጳውሎስ በጎስራ ምስክሮች ናቸው::
ኢህአዲግ ግፈኛውን ደርግን አስወግዶ ነጻ ጋዜጣ ሲፈቀድ ጋሸ ጳውሎስ ከመጀመሪያ ነጻጋዜጣ አዘጋጆች 1ዱም ነበር::

አዎ ጋሸ ጳውሎስ ሞኖፊስቱን የተፋለመበት የፍትሀት ጉዳይ የአውሮፓ ተሀድሶ መሰረታዊ ጉዳይ ነበር:: በፍትሀት ስም ምእመናን የሚበዘብዙትን ማርቲን ሉተር እንደተፋለመው ፍትሀት አያድንም የሚያድን እንደቅዱስ ቃሉ በክርስቶስ አምኖ የእግዚአብህሄር ልጅነት በጸጋ መቀበል ብቻ ነው::
ዲጎኔ ሞረቴው ከጳውሎስ ኞኞ ኪነጥበባት ማእከል
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby Superego » Fri Aug 17, 2012 2:33 pm

ስለ ጳውሎስ የማስታውሰውን እንዲህ ልበል:

ት/ቤታችን ንግግር እንዲያደርግ ተጋብዞ መጥቶ ነበርና "አሁን ሁልሽም ጭንቅላት ውስጥ የምትመላለስው ነገርን አውቃታለሁ:: ጳውሎስ 4ኛ ክፍል ነው የምትሉት" ብሎ ሁላችንንም አስግርመን:: እውንቱን ነበር ያኔ 11 ከፍል ተማሪ ነበርንና የእሱን 4ኛ ክፍል መሆን እናስብ ነበርና::

ሌላው የማልረሳው "ኦሮሞ ማለት ስድብ አይደለም" ያለንን ነው:; ጳውሎስ የራሱን ገጥመኝ ሲንገረን
"እዚ ማሳታውቂያ ሚኒስቴር ያሉ ካድሬዎች ኦሮሞ ብሎ ሰድበን ብለው ከሰሱኝ:: ተከስሼ አልቃችን ጋ ስቀርብ ኦሮሞ ማለት ስድብ አለመሆኑንና ከ 200 አመት በፊት የአሁኑ ኦሮሞውች ኦሮሞ በመለት ራሳቸውን ይጠሩ እንደነበር የሚያሳይ ማስርጃ አሳየሁና ክሱ ወድቅ ሆነ" ብሎናል::

የአሁኑ ዘመን ፖለቲከኞችና ካድሬውች ከዚ ይማሩ ይሆን?!
Superego
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 149
Joined: Fri Aug 26, 2005 11:37 pm
Location: ethiopia

Postby ሀዲስ 1 » Tue Sep 18, 2012 6:22 pm

ከጳውሎስ ኖኞ ትዝታዎች

ወንድማችን መልከፃዲቅ ካቀረበው ::

ጥያቄ :- ከእድገት በህብረት ዘማች

ከወሊሶ ወደ ቡኢ ስንዘምት አንዲት ቅል ይዤ ነበር የመጣሁት :: ታዲያልህ ይሀውልህ ይቺ ቅል መጋቢት 1 ቀን ተሰበረችብኝ :: አሁን ውሀ የምይዝበት ኮዳ የለኝም :: ባለፈው እትምህ ላይ ልመና አብዝታችኌል ብለህ ወቅሰሀን ነበር :: በርግጥ ሌላውን ማስቸገር ይቀፋል :: ግን ምን ይሻላል ትላለህ ?

የጳውሎስ መልስ :- ለዚህ የሚሻለው መፍትሄ ከዚያው ሌላ ቅል መፈለግ ነው ::

ሀዲስ
what we learn from history is, we do not learn from history.

http://www.isil.org/resources/philosoph ... nglish.swf
ሀዲስ 1
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1643
Joined: Wed Mar 10, 2010 12:23 am

Postby ሀዲስ 1 » Tue Sep 18, 2012 6:56 pm

ሰላም ዘርዐይ ደረስ !!!

ይሄንን መልዕክትህን ገና ዛሬ ማንበቤ ነው ::
ለተሳትፎህ እናመሰግንሀለን ::

ግን ከቶፒኩ ለምን ወጣህ አትበለኝና "ፍትሀትን" በተመለከተ የኔም አስተሳሰብ እንደ "ጳውሎስ ኞኞ" ነው ::

በፍትሀት መፅደቅ ካለ ሲኦል እኮ ባዶ ሊሆን ነው !

ለምሳሌ :--
1. አንዱ እድሜ ልኩን ፈጣሪን ሲፈራ : ሲያከብር : ትዕዛዙን ሲጠብቅ ኖሮ ቀሳውስት የሌሉበት ቦታ ህይወቱ ብታልፍና ማንም ፍትሀት ሊያደርግለት ባይችል ሲኦል ሊገባ ነው ማለት ነው ?

2. ሌላው ግለሰብ የስንቱን ህይወት ያጠፋ : ስንቱን ወላጅ ያለልጅ ያስቀረ : የዘረፈ : ፈጣሪውን የሰደበ በሞቱ ወቅት ባጠገቡ ቀሳውስት አግኝቶ ፍትሀት ስለተደረገለት ከቅን ምዕመናን ጋር ነፍሱ ከገነት ታርፍ ይሆን ?

በቁጥር ሁለት የተጠቀሰው ልክ ከሆነ ..... ታዲያ በዚህች አለም ውጥንቅጥ ውስጥ ለምንስ ራሳችንን እናቅባለን ? ...... ሙልጭ ያለ አለማዊ ኑሮ መኖር : መግደል : መዝረፍ : ማመንዘር : ፈጣሪን ማስቀየም : ወዘተርፈ ፈፅመን በሞታችን ወቅት ለምን ፍትሀት አይደረግልንምና ገነትን አንወርስም ? ለምንስ ይሄንን የመሰለ ወርቃዊና አለማዊ ህይወት ኢግኖር አድርገን ራሳችንን እናስጨንቃለን ? መጨረሻ ላይ ቤተሰቦቻችን ስህተቶቻችንን በፍትሀት ሊያርሙልን ከቻሉ ?

ሪሊ ለዚህ ነገር መልስ እፈልጋለሁኝ :: በበኩሌ በጳውሎስ መልስ ነው የማምነው ::

ሀዲስዘርዐይ ደረስ wrote:
ሀዲስ 1 wrote:ጋሽ ጳውሎስ ኞኞን ለማስታወስ ጊዜያችሁን በመሰዋት እዚህ ብቅ ላላችሁ ሁላ ምስጋና ይድረሳችሁ :: ታዲያ እንደእህታችን ሪቾ አንዳንድ ነገር ጣል ጣል ብታደርጉ መልካም ነው :: ሪቾ በርቺ : አትጥፊ ::

እውቁ ጋዜጠኛና ደራሲ ጳውሎስ ኞኞ በ 11 ህዳር 1926 ዓ.ም ቁልቢ አካባቢ ተወልደው ድሬዳዋ ከተማ አደጉ :: በጣሊያን ወረራ ምክንያት ትምህርታቸውን ከ 4ኛ ክፍል በላይ መቀጠል አልቻሉም ነበረ :: ብሩህ አእምሮና የፈጠራ ችሎታ የነበራቸው ሰው ስለነበሩ : በልጅነታቸው የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ጣሊያንን ሰገድሉ ወይም ሲማርኩ ስዕል በመሳል ያሳዩ ነበረ :: ጳውሎስ ካላቸው የፅሁፍ ጥማት የተነሳ የ ድምፅ ጋዜጣ አዘጋጅ በመሆን የብዕር ድምፃቸውን ያሰሙ ነበረ :: ጋዜጦች ላይ ከፅሁፍ አቅራቢነት እስከ አዘጋጅነት ለበርካታ አመታት ሰርተዋል :: በተለይ አንድ ጥያቄ አለኝበሚለው የአዲስ ዘመን ጋዜጣ አምዳቸው ላይ ብዙ ታዋቂነትን አግኝተዋል :: አቶ ጳውሎስ ኞኞ ከ 1955 ዓ.ም. ጀምሮ ለኢትዮጵያ ስነፅሁፍ እድገት የነበራቸውን ተሰጥኦ በአግባቡ በስራ ላይ ያዋሉ እውቅ ጋዜጠኛና ደራሲ ነበሩ :: እኚህ ታዋቂ ሰው በተወለዱ በ 58 ዓመታቸው ከዚህች አለም በሞት ተለይተዋል ::
አቶ ጳውሎስ
የጌታቸው ሚስቶችበሚል ርዕስ ያሳተሟትን መፅሀፍ " ከታተመችበት ወር አንስቶ ለአንድ አመት የመፅሀፌ መብት የግሌ ነው :: ከአንድ አመት በኃላ መብቱ የማንኛውም ኢትዮጵያዊ ይሁን :: ከወሰንኩት ጊዜ በኃላ አሳትሞ ለመሸጥ የፈለገ ሁሉ ከድርሰቴ ሳይቀንስም ሆነ ሳይጨምር ሊያራባው ይችላል :: ስሜን ሳይሰርዝ አሳታሚውን እገሌ ብሎ ማንም ኢትዮጵያዊ ከፈለገ እንዲያራባት የደራሲነት መብቴን ለቅቄያለሁኝ :: አሳታሚው የግሉን የመግቢያ ሀተታ በስሙ ቢፅፍ እኔም ሆንኩ ወራሼ አንቃወምም " ብለዋል ::

ምንጭ:- ውኪፔዲያ

ሀዲስሰላም ለዚህ ርእስ ከፋች ሀዲስና ሌሎችም ተሳታፊዎች:-

በእርግጥም ጳውሎስ ኞኞ በሁለገብ ችሎታውና ራሱን አስተምሮ ለ ከፍተኛ ዕውቅና መብቃቱ የሚያስደንቅ ስብዕና ያሳያል::

ሀዲስ ከዊኪ ፔድያ የወሰድከው የጳውሎስ የህይወት ታሪክ አንድ ስህተት አለበት::ጳውሎስ ትምህርቱን ያቋረጠው በጣልያን ወረራ ምክንያት ሳይሆን ድህነት ትምህርቱን መከታተል ስላላስቻለው ነው::

መቼም ጳውሎስ እንደዚህ ተጠይቆ እንደዚህ አለ ሲባል ያልሰማን የለንም::እንደ አለቃ ገብረ ሃና ተጨማምሮበት ይሁን ወይስ ሁሉም እሱ ያለው ይሁን እንጃ እንጂ::

አንዳንዴ ግን በቁም ነገር ለሚጠየቀው ጥያቄ የሚሰጠው መልስ ግን ይገርማል::አሁን እስቲ ከዚህ በታች ያለው ባልና ሚስቱን የባሰ የሚያቃቅር መልስ አይደለም?

ጠያቂ:-የቤት እመቤት ነኝ:::ኑሮዬን በደኅና ሁኔታ ለመምራት ስል ለባሌ የሚገባውን ነገር ከመፈጸም አንድም ቀን ቦዝኜ አላውቅም::ይህም ያልኩበት ምክንያት በአሁኑ ጊዜ ወንድ እንደውድ ዕቃ በመቆጠሩ ነው::ነገር ግን ጧት ጧት ለባለቤቴ ቁርስ ሳዘጋጅለት አንድም ቀን ለመብላት ፈቃደኛ ሆኖ አይገኝም::ፈቃደኛ ሆኖ የማይገኘው ለምን ይመስለሃል?

መልስ:-ምናልባት ይጠጡ እንደሆነ ሲጃራ ያጠሱ እንደሆነ::ከሆነም በልኩ ያድርጉ በሏቸው ''በአሁኑ ጊዜ ወንድ እንደ ውድ ዕቃ'' አሉ? ኧረ ዱሮም ውድ ዕቃዎች ነበርን::ከቤት ከወጡ በኋላ በየቡና ቤቱ ኬክና ካፑቺኖ ለምደውም ይሆናል::ጳውሎስ በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ችግር እንደደረሰበትም በዚህ ርእስ ሥር አንብቤአለሁ::ግን ጳውሎስስ በማያውቀው ገብቶ አልዘባረቀም?ለምሳሌ የሚከተለውን እንመልከት::

ከዚህ በታች የቀረበው ጽሑፍ 'ማስረጃ የሌለው መልስ' በሚል ርእስ ከስብከተ ወንጌልና ማስታወቂያ መምርያ ለአቶ ጳውሎስ የተሰጠ መልስ ነው::

ረቡዕ ሐምሌ 4 ቀን 1965 ዓ.ም. 33ኛ ዓመት ቁጥር 163 በወጣው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ አቶ ተክሉ ዋቅጅራ የተባሉ ሰው ''ሙሉ ፍታትና ግማሽ ፍታት የሚሉት አለ ፍታቱም በገንዘብ ይበላለጣል::በሰማይ ቤት ግማሽ ፍታት ከተደረገለት ሰው ይልቅ ሙሉ ፍታት የተደረገለት ሰው ይጸድቃል ማለት ነው?'' ብለው ላቀረቡት ጥያቄ አቶ ጳውሎስ ኞኞ አስረጂ የሌለውና ያልተስተካከለ መልስ ሰጥተዋል::የእሳቸው መልስ ባጭሩ ''ሙሉም ሆነ ጎደሎ በፍታት ጽድቅ የለም የሚል ነው::''

ይህ አነጋገር በመሠረቱ የአቶ ጳውሎስ የግል አስተያየት እንጂ አስረጂ የተጠቀሰለት ምክር የተነገረለት ስላልሆነ ተቀባይነት ሊኖረው አይችልም::አይገባብም::ፍታት ሲባል እንደ አቶ ጳውሎስ አነጋገር ሳይሆን መሠረቱ የታወቀ በአዲስ ኪዳን ህግ የጸደቀ አማናዊ ሥርዓት መሆኑን ቤተ ክርስትያን ያመነችውና የተቀበለችው ነው::ይኸውም በማቴዎስ ወንጌል ም 16 ቁ 19 እንደተጻፈው ጌታ ለቅዱስ ጴጥሮስ የሰጠው ሥልጣን በመጀመርያ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ነው::ቃሉም ''የመንግሥተ ሰማያትን ቁልፍ ሰጥቼሃለሁ::በምድርም ያሠርከው በሰማይ የታሠረ ይሆን ዘንድ በምድርም የፈታኸው በሰማይ የተፈታ ይሆን ዘንድ ይላል::

ይህ ሥልጣን የቅዱስ ጴጥሮስ ብቻ ነው እንዳይባልም ለደቀ መዛሙርቱ ሁሉ የሰጣቸው ለመሆኑ በማተዎስ ወንጌል ም 18 ቁ 18-20 ተጽፎ ይገኛል::ሌላም ተመሳሳይ ማስረጃ በዮሐንስ ወንጌል ም 20 ቁ 18 ላይ ይገኛል::ይህም ሁሉ የሚያስረዳው ካህናት በሰው ነፍስ ላይ ያላቸው የማሠርና የመፍታት ሥልጣን መሠረቱ ከምን ከማንስ እንደሆነ ነው::ቤተክርስትያናችን ይህን የመሰለ የጌታችንን ቃል መሠረት ሳታደረግ የምትሠራውና የምትፈጽመው ወይም ለሌሎች የምታዘው ሥርዓት የለም:.ስለዚህ አንድ ሰው ነፍሱ ከሥጋው ከተለየች በኋላ ጸሎተ ፍትሐት የሚደረግለት ወይም የሚፈታው ከዚህ በላይ እንደተገለጠው ጌታችን ለሐዋርያት በሰጠው ሥልጣን መሠረት ከማዕሠረ ኃጢአት ለመፍታትና ፍጹም የሆነ ሥርየትን ለማሰጠት ነው እንጂ የልማድ ጉዳይ አይደለም::እግዚአብሔር ሰውን የሚምርበትና ይቅር የሚልበት ምክንያት ፈላጊ እንደመሆኑ ካህናት ከላይ በተሰጣቸው ሥልጣን ስለአንድ ሰው ብቻ ሳይሆን በመሰላቸው መንገድ ስለ ሰው ልጆች ሁሉ ደኅንነት ወደ ፈጣሪ ቢጸልዩና ቢማልዱ እግዚአብሔር ጸሎታቸውን ይቀበላቸዋል::እግዚአብሔር ካጸደቀ ደግሞ ጽድቅን የሚከለክል ማንም የለም::

አቶ ጳውሎስ ይህንን ሳይውቁ ቀርተው ይሁን አውቀውም ክደውት ይሁን ምክንያታቸው በግልጥ አልታወቀም::ብቻ ቃሉን በፈቃዳቸው ሽረው ሕዝቡን ያሰናበቱ ይመስላል::ይህም ራሱ የቤተ ክርስትያንን መብት መጋፋት ስለሆነ ወደፊት ቢያስቡበት አይከፋም::አቶ ጳውሎስ በቤተ ክርስትያን ሥርዓትና እምነት ውስጥ እየገቡ ይህን መሰል የስህተት መልእክት ለማስተላለፍ ሲሞክሩ ይህ የመጀመርያ ጊዜያቸው ሳይሆን ተደጋግሞ የታወቀ ነው::ሆኖም(ላም ባልዋለበት----እንደሚባለው ሰዎችን ግራ ከማጋባት እና ራሳቸውን ከማስገመት በቀር በዚህ በኩል መልስ ለመስጠት ባደረጓቸው ሙከራዎች ሁሉ ጥሩ ውጤት አስገኝተዋል ማለት አይቻልም:.ስለዚህ አቶ ጳውሎስ ይህንን ተወት አድርገው የዚህ ዓይነት ጥያቄ ሲያጋጥማቸው አገኝ አጣውን ከመቀባጠር ተቆጥበው ጉዳዩ እኔን ስለማይመለከት ለሚመለከተው ክፍል አስተላልፌዋለሁ መልሱን በዚያ በኩል ተጠባበቁ ቢሉ ኖሮ ሳይመሰገኑ አያልፉም ነበር::ሙሉ ፍታት ግማሽ ፍታት የተባለውም በቤተ ክርስትያን ውስጥ የሌለ የስሕተት አነጋገር ነው::አለ የሚባልም ቢኖር የጉዞ ፍትሐትና በቤተ ክርስትያን የሚፈጸመው ጸሎተ ፍትሐት ነው::ይህም ሙሉና ግማሽነቱን የሚያሳይ ሳይሆን በመንገድ እየሄዱ የሚፈጸምና በአንድ ቦታ ተቁሞ የሚከናወን መሆኑን የሚያመለክት ነው እንጂ ከላይ እንደተባለው መበላለቱን አይደለም አሁንም እንደዚህ የመሳሰሉትን ጉዳዮች ቤተ ክርስትያን መልስ እንድትሰጥባቸው ማድረጉ ለሁሉም የሚበጅ ምክራችንን እንለግሳለን::

ምንጭ:-አዲስ ዘመን ሐምሌ 14 ቀን 1965 ዓ.ም.

:arrow: እንግዲህ በአቶ ጳውሎስና በቤተ ክርስትያኒቱ መካከል የነበረው ግጭት በጊዜው ነበርን የሚሉ መናፍቃን እንደሚሉት ሳይሆን በዚህ እና በተመሳሳይ መልኩ አቶ ጳውሎስ ይፈጥሩት በነበረው አግባብ ያልሆነ ጣልቃ ገብነት መሆኑን ይህንን የታሪክ ማኅደር አግኝቼ ለማረጋገጥና ይመለከተኛል ለሚል ሁሉ ለማካፈል በመቻሌ ደስ ብሎኛል::
what we learn from history is, we do not learn from history.

http://www.isil.org/resources/philosoph ... nglish.swf
ሀዲስ 1
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1643
Joined: Wed Mar 10, 2010 12:23 am

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 8 guests