ቤተ- ሞንሟናው

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby የተሞናሞነው » Fri Jun 15, 2012 12:15 pm

የተውኩትን ነገር
ተመክሬ ተነግሬ በሃገር
ምን ጎትቶ አመጣብኝ
ያን ያረጀ ያን የድሮ ፍቅር

ጉድ ፈላ ዘንድሬ አቤት አቤት
_ማን አስተማረብኝ
ማስቲካ ሆኛለሁ ከረሜላ
_ካ'ፉ አሳደረኝ

ይሄው ይሰማኛል ጥሩምባ
ይሄው ይነፋሉ ጥሩምባ
እልልታው ጭፈራው ደመቀ
ፍቅሬ ተመልሶ ገባ
እረ ጉድ እረ ጉድ ፈላ
እፍረት ይሉኝታዬን አሳጣኝ
ልቤ ለፍቅርህ እያደላ

እዩት ልጁን ሲንጎራደድ
ያንን ሽንጡን ሲያውረገርግ
አይኑ ገዳይ ጥርሱ ገዳይ
ስንቴ ልሙት በዚህ ጉዳይ
ወይ ቁመና ወየው ዛላ
ሰው እንደ'ህል አይበላ
አለ ለካ የሰው ሃረግ
ደረት ክንዱ ባለ'ማረግ

እስኪ በጆሮየ ፍቅርን ይድገም ያነብንብልኝ
ከትንፋሹ በልጦ የሚደመጥ
ምን ሙዚቃ አለኝ
በጁ ቢነካካኝ ድምጽ አወጣሁ
እኔም እንደ ጊታር
ጉድ አረገኝ መውደድ
ጉድ አረገኝ የዚህ ሰው ፍቅር

አቤት አቤት አቤት አቤት
አቤት አቤት አቤት አቤት
ፍቅሬን ላንተ ሰጥቻለሁ
አርገኝ የቤትህ እመቤት

.
.
.
እጂጋየሁ ጂጂ---> http://www.youtube.com/watch?v=UAuNVxC8Fz0
የተሞናሞነው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1129
Joined: Wed May 11, 2011 5:39 pm

Postby የተሞናሞነው » Fri Jun 15, 2012 12:47 pm

የሰውን ልጅ የስሜት ላይ መውጣት ታች መውረድ...መደሰት መከፋትን...የኩነኔ ህይወትን...የሰውን ልጅ ግራ አጋቢ ላይ ታች ህይወትን....በውብ ቃላጼ ታንቆረቁራለች...ደስታን ፍቅርንም ስጡኝ ስትልም ትለምናለች....ፈጣሪዋን ትጠይቀዋለች...ትለምነዋለች....

እስኪ ከረብሻ ኳኳታ ዘፈን ወጣ በሉና በተረጋጋ መንፈስ ሆናችሁ አዳምጧት

እውነት ጂጂ ድንቅ አይደለችምን?! :D

http://www.youtube.com/watch?v=7VkrV-iFED4

አባ አለም ለምኔ
አባ አለም ለምኔ
ጀምበር ወጥታ አትገባም
ሳልሰራ ኩነኔ

ሰው ወደድኩ እያልኩ ደ'ሞ እጠላለሁ
ደ'ሞ ይከፋኛል እደሰታለሁ
ዛሬ ቀጭን ኩታ ነገ ራቁቴን
አገኘው ስል ወዳጅ ደ'ሞ ማጣትን

አባ አለም ለምኔ
ለምን ለምን ለምን ለምን
አባ አለም ለምኔ
ደግሞ ለምን ይክፋኝ
ብስጭት ጭንቀት ጤንነት አይሆነኝ

ሰው በአፉ እያነሳ በእጁ ይጥለኛል
የልቡን አላውቅም ግራ ይገባኛል
የልብን ጥያቄ ማን ነው የሚፈታ
ከአንተ በቀር አባት ከአንተ በቀር ጌታ
ዛሬ ጥያቄ አለኝ
ለምን ለምን ለምን
ደግሞ ለምን ይክፋኝ
ብስጭት ጭንቀት
ጤንነት አይሆነኝ

ደስታን ስጠኝ ለህይወቴ
አይሳንህምና አባቴ
አርቅልኝ ክፉውን
እንዳልማር ክፋቱን
በቀኝ አውለህ አሳድረኝ
ክፉ ነገር ሳይወጣኝ

ምን ሊሰራልኝ ጥላቻ ሃሜት
ሀብት አይሆነኝም ቤት አልስራበት
ልብ ያጨልማል ክፉ ነገር
ልቤን አብሩልኝ ስጡኝ ፍቅር

አባ አለም ለምኔ
ጀምበር ወጥታ አትገባም
ሳልሰራ ኩነኔ
የተሞናሞነው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1129
Joined: Wed May 11, 2011 5:39 pm

Postby የተሞናሞነው » Sun Oct 14, 2012 1:34 am

ይሄውላችቹ አንዱ ፌስ ቡክ ላይ ዋርካን ለምን ተውካት ቢያንስ የፍቅር ፎረምን ብሎ በጅንጀና በልመና ብዛት ቃል አስገብቶኝ አሁን ደግሞ እየቀመቀምኩ በምርቃና አመጣኝ :lol: :lol: ...ስጠረጥር የዋርካ አድሚን ሳይሆን አይቀርም :wink: :wink: ...እሱን ደግሞ መጋፋት ዴግ አደለም....ደህና ናችሁ ግን? አቤት እኔ ዋርካን በቃኝ ብዬ ቻው ብዬ ከሄድኩ በኋላ ስንቱ ነገር ግልብጥብጡ ወጣ...መለስ ሞተ....አዜብ እሪ አለች....ሃይለማሪያም መጣ....ጁነዲን ተባረረ...አዜብም አልወጣም አለች...ወዘተ....እኛም አጨንቁረን እያየን ነው :) ፖለቲካ ሰፈርስ እንዴት ናችሁ? ለማንኛውም ፌስ ቡክ ላይ ፖስት የተደረጉ የፍቅር ግጥሞቼን ጄባ ልበላችሁ እስኪ:: እንቢ ለሃገር አለህ? ሰላምታዬ ይድረሳችሁ የሃገር ልጅ በሞላ...ወደ ግጥሞቹ...ድድድድድአየሽ የኔ ዓለም
በዙሪያችን ያሉ ወንዶች የተባሉ
አፋቸውን ከፍተው አንችኑ ያያሉ
ያጉተመትማሉ ያንሾካሹካሉ
ጣፋጭ ከንፈርሽን በአይን ይስማሉ
ንጽህት ገላሽን ነክተው ሊያረክሱት
(ድፍረታቸው አያልቅ)
በሻከረ እጃቸው እንንካም ይላሉ

እናም...ለምለም ቀዘባ ወለላ
ሽፍንፍን በይልኝ በሻሽ በነጠላ
ማንም አይይብኝ አንችን ከእኔ ሌላ
አይተው አያልፉሽም
ማራኪ ነው ገላሽ
ለአይን የሚያስጎመጅ በአይን የሚበላ

ነይልኝ ጠጋ በይ ሽሽግ በይ ከጎኔ
ከሰው ልከልልሽ ልብስ ልሁንሽ እኔ
አንችን እንደደብቅሁ ትፈጸም ዘመኔ

እኔ ብቻ ልይሽ ልያዝሽ ቀርቤ
አንች ጽላት ሆነሽ መቅደስ ትሁን ልቤ
ላሰማሽ ውዳሴ ልጠንሽ በከርቤ

የኔ ማራኪ የዱር ውስጥ እንኮይ
አይተው ከሚያረክሱ ከአይን ተከለይ
እንደ መነኮሳት ከዓለም ተለይ
ልቤ ገዳምሽ ነው ወደ ውስጤ ነይ

የበረሃ ላይ ምንጭ በሩቅ ተፍለቅላቂ
የወርቅ የአልማዝ የዕንቁ ፍልቃቂ
ሰው አንችን አይይሽ ወደ ውስጥ ዝለቂ
ስጋየን ተሻግረሽ ልቤ ውስጥ ጥለቂ
ከልቤ አትውጭብኝ እዚያው ተደበቂ::

(ፍቅር...ናፍቆት...ስስት...ቅናት... በደረቁ ሌሊት :( )

/ልጅ ሞንሟናው/
09-10-12
Last edited by የተሞናሞነው on Sun Oct 14, 2012 2:34 am, edited 3 times in total.
የተሞናሞነው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1129
Joined: Wed May 11, 2011 5:39 pm

Postby የተሞናሞነው » Sun Oct 14, 2012 1:50 am

ወዳ'ንች ስመጣ
ከበረሃ ውሎ
በጸሃይዋ በሃሩሩ ግሎ
በውሃ ጥም ተቃጥሎ
_ወደ ምንጭ ለመድረስ
_እንደሚገሰግስ
ጣድፎና ቸኩሎ

ወዳንች ስመጣ
ጨቅላ ልጇን ትታ
ወደ ገበያ ወጥታ
_ጡቷ ወተት ሲያፈስስ
በናፍቆት ደንዝዛ
_እንደምትመለስ
ቅመሟን ሳትገዛ
እንደምትል ጥድ'ፍ
_እንደ አንጄተ-ስስ
እንደ'ናት እንስፍስፍ

ወዳንች ስመጣ
አቤት መንሰፍሰፌ
አቤት መጣደፌ
አቤት ችኮላዬ
አቤቱ ደስታዬ
አቤቱ ፍጥነቴ
አቤቱ ጉልበቴ
..............
(ወዳንች ስመጣ )

/ልጅ ሞንሟናው/
11.10.12
የተሞናሞነው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1129
Joined: Wed May 11, 2011 5:39 pm

Postby የተሞናሞነው » Sun Oct 14, 2012 1:56 am

በሾለችው ብዕሬ
በነጭ ወረቀት ላይ
ሆሄያትን ደርድሬ
ቃላትን ቀምሬ

'እንኮይ ልስልስ ገላ
የአበቦች ቅምም
የኔ ማር ወለላ...'

እያልኩኝ ላወሳ
ስምሽን ላነሳሳ
ቃል ስጥል ሳነሳ

እነሆ ስጀምር
ብሶት ላንጎራጉር
ፍቅራችን ልዘምር

አልቻልኩም አለሜ
በሆነ በመንፈስ
ወይ በአየር በነፋስ
(ወይም እውነት ይሆን?)

መአዛሽ አወደኝ
እጆችሽ አቀፉኝ
ከንፈሮችሽ ሳሙኝ

ውስጤ ተላወሰ
እንባዬ ፈሰሰ
ወረቀቴም ራሰ

ቃላት ቀልጠው ጠፉ
በእንባዬ ጎረፉ

ነገሬን ተረድታ
ሁኔታዬን አይታ
ብዕሬም አልቻለች
አብራኝ አለቀሰች
በአይኗ ቀለም ተፍታ

(ሁላችንም ለቅሶ)

/ልጅ ሞንሟናው/
የተሞናሞነው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1129
Joined: Wed May 11, 2011 5:39 pm

Postby የተሞናሞነው » Mon Oct 22, 2012 12:54 pm

ድሮ ድሮ ድሮ
ንጋት ያበስር ነበር
ከሰው ቀድሞ ዶሮ

አሁን ተለውጦ
ሌሊቱን ሙሉ
እንቅልፉን ለጥጦ

ከነጋ ይጮሃል
ጸሃይን እያዬ
እየተንጎማለለ
በሰፈር በቀዬ::

/ልጅ ሞንሟናው/
የተሞናሞነው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1129
Joined: Wed May 11, 2011 5:39 pm

Postby የተሞናሞነው » Wed Oct 24, 2012 8:19 pm

ለመለስ ሞትና ለቅሶ ሰሞን የቋጠርኍቸው የሙሾ ስንኞች :wink:

ትናንት ምድር ሆነህ
_ዛሬ በሰማይ
ታስለቅሰኛለህ
_እላለሁ ዋይ ዋይ

_____________________
አደባባይ ብቆም
_ደረቴን ሰጥቼ
ብተክዝ ብቆዝም
_ልማዴን አጥቼ
ይሄው ደበደብኩት
ቤትህ ውስጥ ገብቼ::

_____________________
ምድረ ነፍጠኛ
እነ ትምክህተኛ
ቦዘኔ አደገኛ
ምድረ ፈሪ ሁሉ
እንኳን ተሳካልህ
ልብ አገኘህ አሉ
ከቤቱ ውስጥ ገባህ
ዛሬ እሱ ሲተኛ::

______________________
(እምዬ ሚኒሊክ ለመለስ)

በቤልጅግ ነበረ
_ጠላቴን ገርፌ
ታሪክ የተውኩልህ
_በደም ቀለም ጽፌ
አንተ ግን
ቀየህን ናቅህና
አድዋን ተውካትና
ወደ ቤልጅግ ሄደህ
ተሸንፈህ መጣህ
_በትንሿ መርፌ::/ልጅ ሞንሟናው/
የተሞናሞነው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1129
Joined: Wed May 11, 2011 5:39 pm

Postby ሀዲስ 1 » Thu Oct 25, 2012 5:54 pm

ሰላም ሞንሟናው !!!!


እንኳን በሰላም ተመለስክ !!!
እንግዲህ ዋርካዋ ሞቅ ሞቅ ልትል ነው ::

በርታ ወንድሜ

ሀዲስ
what we learn from history is, we do not learn from history.

http://www.isil.org/resources/philosoph ... nglish.swf
ሀዲስ 1
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1643
Joined: Wed Mar 10, 2010 12:23 am

Postby ሀዲስ 1 » Thu Oct 25, 2012 6:06 pm

ሰላም ሞንሟንሽ

እስኪ ይህችን የቆየች ዘፈን ለቤትህ ማሞቂያ አድርጋት ::

http://www.youtube.com/watch?v=ZezWmE7FjgM

ሀዲስ
what we learn from history is, we do not learn from history.

http://www.isil.org/resources/philosoph ... nglish.swf
ሀዲስ 1
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1643
Joined: Wed Mar 10, 2010 12:23 am

Postby የተሞናሞነው » Wed Oct 31, 2012 8:00 pm

ወንድም ሀዲስ እንደምን አለህልኝ?

ምላሽ ለመስጠት በመዘግየቴ ይቅርታን አስቀድሜ ለሰላምታህና ለሙዚቃ ግብዣህ ከልብ አመሰግናለሁ::
የተሞናሞነው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1129
Joined: Wed May 11, 2011 5:39 pm

Postby የተሞናሞነው » Sun Nov 11, 2012 12:38 pm

(ናፍቆት እስክንድር ነጋ እና ጭራቆቹ)


ስለ ጭራቅ ተረት ትምህርት ቤት ሲወራ

ሁሉም ደንግጠው ውስጣቸው ሲፈራ

እሱ አልተሸበረም እንዲያውም ተኩራራ

እንደሚጥልለት አባቱን ተማምኖ

አስፈሪ ጭራቁን ጥሎ በዝረራ


ተረቱ አለቀና

ጭራቁን በውስጡ እያሰላሰለ

ቦርሳ በጀርባ አዝሎ እየተቻኮለ

ከትምህርት ቤት ወጣ ድክ ድክ እያለ


ገና ከሩቅ አየው ጀግና አባቱን ቆሞ

'አባ ' ብሎ ሮጠ ሳመው ተጠምጥሞ


'አባዬ ' ብሎ በኮልታፋ በልጅ አንደበቱ

ይነግረው ጀመረ ለጀግናው አባቱ

የሰማውን ሁሉ ከትምህርት ቤቱ

ስለ አስፈሪው ጭራቅ ሲወራ ተረቱ


ግና ምን ያደርጋል

አይናቸው ደም ለብሶ የሚያጉረጠርጡ

ደምን የሚያፈሱ አካል የሚቆርጡ

ጥማቸው ማይረካ የሰው ደም ካልጠጡ

ወሬውን ሳይጨርስ ጭራቆቹ መጡ


ከእቅፉ መንጭቀው ልጁን ወረወሩ

ልጅ ያቀፉ እጆቹን በካቴና አሰሩ

በማይገባው ቋንቋ እየተናገሩ

ወደ ጭራቆች ቤት ይዘውት በረሩ


ናፍቆት አለቀሰ 'ዋይ አባዬን ' አለ

ተረቱ እውን ሆኖ

ጭራቆቹን እንባ በሞሉ አይኖች

ፈርቶ እያስተዋለ ::

__________________________

'ጭራቆቹ መጥተው አስረው በካቴና

አባየን ወሰዱት ጭነው በመኪና

ከነበርንበቱ ባለፈው ታች አምና '


እያለ ነገራት ለጀግናዋ እናቱ

በኮልታፋው በልጅ አንደበቱ

ካሁኑ ናፍቆት ያ ጀግናው አባቱ

ፍርሃት ይዞት ባዶ ሲሆን ቤቱ

በጭራቆች ስራ በዝቶበት ቁጭቱ


ባትሆንም እንግዳ ለጭራቆች ስራ

ናፍቆቷን ስታየው እንባውን ሲዘራ

ስታስታውስ

ከውልደት ጀምሮ ያየውን መከራ

የእናትነት ልቧ ... አዝና ተሸብራ

ስቅስቅ ብላ አነባች ከናፍቆቷ ጋራ


ግን ናፍቆቷን አቅፋ ከእንባዋ ባህር

ድንገት አየች ጀግና ቆፍጣና ደፋር

የጭራቅን ስራ ለጭራቅ ሲነግር

ብእር እያሳዬ ጭራቅ ሲያሸብር

'አዎ እሱ ነው ' አለች

'ጀግናዬ እስክንድር '!


ጀግናዋን እንዳየች ውስጧ ጠነከረ

ትንሹን ናፍቆትም ትነግረው ጀመረ


'አባትህ ጀግና ነው እውነት ተናጋሪ

ካንተም ከኔም ተርፎ ለሌሎቹ ኗሪ

ያየውን ሳይፈራ ለአለም መስካሪ

ጭራቅን በድፍረት እንደሰው መካሪ

ብእሩ ስለት ሰያፍ ጭራቅ አሸባሪ


እናም ሆድ አይባስህ አይዞህ ልጄ በርታ

ፍርሃትም አይግባህ በጭራቅ ድንፋታ

በሰው ለሚሸነፍ የማታ የማታ::

________________________
ትንሹ ናፍቆት እስክንድር ነጋ

ስንት ቀን ሆነህ አባብየህን ካየህ

ካጣህው ከሚተኛበት አልጋ ?

ስንት ጊዜስ መሽቶ ስንት ጊዜ ነጋ ?

ስንት ቀንስ በህልምህ አየሀው

ተከቦ በጅቦች መንጋ ?


አይዞህ ናፍቆቴ እስክንድር

በርታ በል ልብህ ትጠንክር

ተማርልን ፊደልን ቁጠር

አንብብ ያባትህን ደብተር

ከትቦልሃል ብዙ ቁም ነገር

ስለ ጦቢያ ስለ እናት ሃገር

ስለ ነጻነት ስለ ሰው ክብር

በመለያየት ስላለ ፍቅር


ፈልግና ርስትህን ያዝ ከደብተሩ

እዚያ ነውና ያባትህ ጋሻና ጦሩ

የተዋጋበት ለናት ሃገሩ

የተገለጸበት ሰብአዊ ፍቅሩ ::


(ለናፍቆት እስክንድር ነጋ መታሰቢያነት ኦክቶበር 2011, የዛሬ አመት በፊት የተከተቡ ስንኞች )

ልጅ ሞንሟናው
የተሞናሞነው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1129
Joined: Wed May 11, 2011 5:39 pm

Postby እንሰት » Mon Nov 12, 2012 1:15 am

ስታናድድ
ምናለ ቤት ከፍቻለሁ ኑና እዩት ብትለን:: በል እስኪ እዚህ ዋርካ የበተንካቸውንም ስራዎችህን በመልክ በመልኩ ሰብስብና እዛኛው ቤትህ
[url]http://yetemonamonew.wordpress.com/[/url]
ተቁዋደሱ በለን::
ከአክብሮት ምስጋና ጋር

የተሞናሞነው wrote:የተውኩትን ነገር
ተመክሬ ተነግሬ በሃገር
ምን ጎትቶ አመጣብኝ
ያን ያረጀ ያን የድሮ ፍቅር

ጉድ ፈላ ዘንድሬ አቤት አቤት
_ማን አስተማረብኝ
ማስቲካ ሆኛለሁ ከረሜላ
_ካ'ፉ አሳደረኝ

ይሄው ይሰማኛል ጥሩምባ
ይሄው ይነፋሉ ጥሩምባ
እልልታው ጭፈራው ደመቀ
ፍቅሬ ተመልሶ ገባ
እረ ጉድ እረ ጉድ ፈላ
እፍረት ይሉኝታዬን አሳጣኝ
ልቤ ለፍቅርህ እያደላ

እዩት ልጁን ሲንጎራደድ
ያንን ሽንጡን ሲያውረገርግ
አይኑ ገዳይ ጥርሱ ገዳይ
ስንቴ ልሙት በዚህ ጉዳይ
ወይ ቁመና ወየው ዛላ
ሰው እንደ'ህል አይበላ
አለ ለካ የሰው ሃረግ
ደረት ክንዱ ባለ'ማረግ

እስኪ በጆሮየ ፍቅርን ይድገም ያነብንብልኝ
ከትንፋሹ በልጦ የሚደመጥ
ምን ሙዚቃ አለኝ
በጁ ቢነካካኝ ድምጽ አወጣሁ
እኔም እንደ ጊታር
ጉድ አረገኝ መውደድ
ጉድ አረገኝ የዚህ ሰው ፍቅር

አቤት አቤት አቤት አቤት
አቤት አቤት አቤት አቤት
ፍቅሬን ላንተ ሰጥቻለሁ
አርገኝ የቤትህ እመቤት

.
.
.
እጂጋየሁ ጂጂ---> http://www.youtube.com/watch?v=UAuNVxC8Fz0
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby የተሞናሞነው » Tue Nov 13, 2012 6:24 am

ሰላም ወንድም እንሰት

የኔ ነገር መቸስ የውልህ እንዲህ ነኝ....ለእንግዶቻችን እንዳታንስ በማለት እስኪ ትንሽ ልጣጥፍ ልለጣጥፍባት ብዬ ነው... አልረሳሁም :)

ካታላቅ አክብሮት ጋር አመሰግናለሁ ወዳጄ!

ዘ ሞርኒንግ ሰን http://www.youtube.com/watch?v=QVJVKr6CCeU
የተሞናሞነው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1129
Joined: Wed May 11, 2011 5:39 pm

Postby እንሰት » Wed Nov 14, 2012 6:28 pm

እጅ ነስቻለሁ::
በነካ እጂህ ያቺን የጀመርካትን ጽሁፍ ብትቀጥላትስ:: አሁንም ዝርዝሩዋ ሁሉ ተረሳኝ::

የተሞናሞነው wrote:ሰላም ወንድም እንሰት

የኔ ነገር መቸስ የውልህ እንዲህ ነኝ....ለእንግዶቻችን እንዳታንስ በማለት እስኪ ትንሽ ልጣጥፍ ልለጣጥፍባት ብዬ ነው... አልረሳሁም :)

ካታላቅ አክብሮት ጋር አመሰግናለሁ ወዳጄ!

ዘ ሞርኒንግ ሰን http://www.youtube.com/watch?v=QVJVKr6CCeU
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby የተሞናሞነው » Wed Nov 21, 2012 12:45 pm

ብዙ ከመሬት ርቃ

ለዘመናት ቀልብን ሰርቃ

በብርማ ቀለም አብረቅርቃ

እንደምትታየው ደምቃ

_ሲደርሱባት ግን ምድረ በዳ

_አባጣ ጎርባጣና ጎድጓዳ

እንደሆነችው እንደ ጨረቃ


ደረቅ...በረሃ...ባዶ...ኦና

እንዳትሆኝብኝ ሰጋሁና

መምጣቱን ትቼዋለሁ

በሩቁ መደመሙን

አቤት ውበቷ እያልኩኝ

መኖርን መርጫለሁ::/ልጅ ሞንሟናው/
የተሞናሞነው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1129
Joined: Wed May 11, 2011 5:39 pm

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests