ቤተ- ሞንሟናው

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ክቡራን » Wed Nov 21, 2012 2:01 pm

ማነህ አድሚን ለመነኝ ብለህ ራስህን በራስህን ማርኬት የምታደርገው የክብርነታችን ንብረት :lol: :lol:

ግጥሞችህን ገረፍረፍ አደረኩት ጥረት አለህ ገጣሚ የመሆን ፍላጎት አለህ....ቃላት ላይ ችግር የለብህም:: ጽንሰ-ሀሳብ ግን ለማፍለቅ ትጨነቃለህ:: ግጥሞችህ በቃላት ጮማ ሰብተው በንጥረ ነገር ግን ደክርተዋል:: የቦርጫም ሰው ግጥም አይነቶች ናቸው:: ስብ ብቻ ነው:: ቀይ ስጋ የለውም:: ቡዙ ጊዜ ሰው ራሱን ነው የሚጽፈው ይላሉ ጽሀፍት:: ቃላት ብቻ መድርደር ገጣሚ አያሰኝም:: ግጥም በሰብስታንስ ይለካል...ይዞት በሚመጣው ጠጣር መልክት ይመዘናል:: ያንተው የቃላት ቱማታ ብቻ ነው::
ሰርቃ....አብረቅርቃ..ደምቃ...ፈልቃ...ወድቃ...ብቻ ነው:: የቃላት አደራደሮችህን ስመለከት የደመቁ ቤት የጠላ ብርጭቆዎች በሀሳቤ ይመጣሉ:: ምክሬ በግጥም አትጫወት ነው:: :lol: :roll:
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7990
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby የተሞናሞነው » Wed Nov 21, 2012 4:08 pm

እንዴት ነህ ክቡ :)
አይ ያንተ ነገር...ብዙ ጊዜ ሰዎችን የሾተል ንብረት በማድረግ 'የክብርነታችን' ስትል ተደጋጋሚ ስህተት ስትሰራ እያነበብሁ መቸም እኔ አንተን ማስተካከል ነውና ስራዬ እንዲሁ ከማልፍህ ላስተካክልህና መጠቀሙን ከፈለግህው እንኳን 'የክቡርነታቸው ወይም የክብርነታቸው' ነው ማለት ያለብህ እንጅ 'የክብርነታችን' ካልህ ባለቤቱ ራስህን እያደረግህ ነው...'የክብርነታችን' የሚለው ራሱ ክቡርነቱ ሾተል ነው እንጂ አንተ አይደለህም:: ሞንሟናው ግን እንኳን እንደሱ አይነት ቅል ራስ ፍልጥ መሃይም ይቅርና በሌላውም ስር ስለማያድር....ነገር ግን ደግሞ ይህንን አንተ ከሱ ተራ የሆንከው ብትለው አይገርመኝምና አልፌሃለሁ :wink:

ለአስተያየትህ ግን ምስጋናየን አቅርቤ...እንግዲህ ሰው እንደ እይታው...ባህሉ...የዕውቀቱ ልክ...መረዳት አቅሙ :wink: ...ይለያያልና ይሁን ብያለሁ:: አንዳንዱ በከባድ ቃላት የተሰነኙ ግጥሞችን ...አንዳንዱ ቀለል ያሉና ለዛ ያላቸውን....ሌላው የመልዕክቱን ክብደት...ወዘተ...ያያል:: እኔ ራሴን ገጣሚ ነኝ ብዬ ማዕረግ ባልሰጠውም ግን ግጥም ከሚያውቁ ፌስ ቡክም ላይ ፖስት ከማደርጋቸውና ሌላም ጋር ለግሌ ከደበቅኍቸው መሃል :wink: በግል ካካፈልኳቸው የስነጥበብ ቤተሰቦች ከሰጡኝ አስተያየት...ግጥሞችህ ለዛ ያላቸውና ቀልጠፍ ያሉ ናቸው የሚሉኝ ይበዛሉ...በተለይ ለዛ የምትለዋ ተደጋግማብኛለች....ለዛ የሚለው እንግዲህ ጣዕም መሰለኝ...አይ ዶን ኖ....ግን ደግሞ እራሴም እንደ ግጥም ወዳጂነቴና ጥሩ አንባቢነቴ የራሴን ሳነባቸው አንድ ነገር ማለት እችላለሁ....ያልተዝረከረኩ ፍስስ ብለው እየጣፈጡ የሚዋጡ ናቸው....በእውቀቱ ስዩም እንዳለውም...ግጥም ያልተዝረከረከ ፍልስፍና ነው:: እዚህ ላይ ያካፈልኳቸው የፍቅር ግጥሞችም ውብ ናቸው....ለመጽሃፍም ብቁ የሚሆኑ ናቸው....ፍልስፍናም ለዛም አላቸው...እንግዲህ እንደመረዳታችን መጠን ይለያያል ብያለሁ :wink: አስተያየትህ 'ባለፈው ፍቅር ምንድን ነው' ብለህ ከጠይቀህው የመነጨ ነው:: ፍቅርን በደንብ የሚኖርበት የሚያውቀው እነዚህን ግጥሞች እንዳንተ አያያቸውም :lol: ታላቁ የግሪክ ፈላስፋ ፕላቶ ከዚህ ጋር በተያያዘም ‘at the touch of love everyone becomes a poet’ ብሏልና እኔም በስሜት ሆኜ ነው የምጽፋቸው...በዚህ ስሜት ውስጥ ካልሆንክ ላይገቡህ ይችላሉ :wink:

ኤኒወይስ እንዲሁ ቤቴ ገብተህ በስድ ንባብ ከምሰድህ ባለፈው ባስ ውስጥ አንዷ ችክ ፈረንጅ አጠገቤ ቁጭ ብላ አየት አየት ማድረግ ስታበዛ እዚያው ላይ ሳልወርድ በማስታወሻየ የከተብኳትን እምብዛም ባትሆንም ቀላል የስንኝ ቋጠሮ ላካፍልህ :roll:


ቆዳው የጠቆረ

ቁመቱ ያጠረ

ምን ይመስላል ኧረ'

ያለችኝ መሰለኝ

አንድ ፈረንጅ በልቧ

ጎን ለጎን ቁጭ ብለን

ሆኜ ካጠገቧ


እኔም ዛዲያ

የጸጉሯን ንጣት

የቆዳዋን ግርጣት

የፊትዋን ወዝ ማጣት

በደንብ አስተውዬ

በልቤ ሰደብኳት

'ሰይጣን የመሰለች

ነጫጭባ!' ብዬ :evil:


:)
/ልጅ ሞንሟናው/
የተሞናሞነው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1129
Joined: Wed May 11, 2011 5:39 pm

Postby ክቡራን » Wed Nov 21, 2012 6:02 pm

ዌል ጥሩ ነው ልብ የገዛህ ትመስላለህ:: ምን ያህል እንደምትሄድ እናያለን:: :) ተረጋግተህ ነው መልስ የሰጠሀው ጥሩ ነው:: ለማወቅ ለመስተካከል ፍላጎት እንዳለህ ያሳያል:: ያ ከሆነ ቅቤ መቀባባት ሳይሆን እርስ በርስ እየተራረምን ሁለት ስለት ያለው ገጣሚ እንድትሆን እናደርግሀለን:: 8) እመለሳለሁ:: በተረፈ እኔ ክብርነታችን የምለው ክብርነታችንን ሾተልን እንጂ ራሤን ኢንኩሊሲቭ አድርጌ ዐይደለም:: እኔ ንብረትና ሰፊ የሆነ የተንጣለለ ሜዳ የለኝም:: ግን የክብርነታችንን ንብረቶች ከዳር ሆኘ አያለሁ:: አንዳንዶቹም መሻሻል እያደረጉ ከንብረትነት ራሳቸውን አውጥተው ለማየትም በቅቻለሁ:: :D
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7990
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ሾተል » Sat Nov 24, 2012 12:48 pm

የተሞናሞነው
ታላቁ የግሪክ ፈላስፋ ፕላቶ ከዚህ ጋር በተያያዘም ‘at the touch of love everyone becomes a poet’ ብሏልና እኔም በስሜት ሆኜ ነው የምጽፋቸው...በዚህ ስሜት ውስጥ ካልሆንክ ላይገቡህ ይችላሉ :wink:

ኤኒወይስ እንዲሁ ቤቴ ገብተህ በስድ ንባብ ከምሰድህ ባለፈው ባስ ውስጥ አንዷ ችክ ፈረንጅ አጠገቤ ቁጭ ብላ አየት አየት ማድረግ ስታበዛ እዚያው ላይ ሳልወርድ በማስታወሻየ የከተብኳትን እምብዛም ባትሆንም ቀላል የስንኝ ቋጠሮ ላካፍልህ :roll:


ቆዳው የጠቆረ

ቁመቱ ያጠረ

ምን ይመስላል ኧረ'

ያለችኝ መሰለኝ

አንድ ፈረንጅ በልቧ

ጎን ለጎን ቁጭ ብለን

ሆኜ ካጠገቧ


እኔም ዛዲያ

የጸጉሯን ንጣት

የቆዳዋን ግርጣት

የፊትዋን ወዝ ማጣት

በደንብ አስተውዬ

በልቤ ሰደብኳት

'ሰይጣን የመሰለች

ነጫጭባ!' ብዬ :evil:


:)
/ልጅ ሞንሟናው/


ሙናዬ እንግዲኽ ታላቁ ፈላስፋ ሁሉም ገጣሚ ይሆናል ባለው መሰረት እኛም ስነጽሁፍ ስለነካን ሁላችንም ሀያሲ ስለሆንን በስሜት ሆነኽ እራስኽን የተሰማህን ስለጻፍከው ግጥም ትንሽ አስተያየት ብሰጥ ...

በርግጥ ከዚህም በፊት በጽሁፎችኽ አንተን ብቻ አይደለም አገር ቤት ያለችው እናትህንም አውቃታለሁ ብል የተሳሳትኩ አይደለሁም ::ማለት ያው በሀሜት ወልዳ በሀሜት አሳድጋ አንተኑ ሀሜተኛ ስላደረገችኽ ማለት ነው ::

ያ ይሁን ...ግን ወደ ግጥሙ ስንመጣ ባህሪህን በግጥሙ ውስጥ አገኘሁትና ስለዛ ልል ወደድኩ ::

እንደ ግጥሙ ከሆነ በራስኽ የማትተማመን ....ሁልጊዜ ሰው ስላንተ የሚያወራብኽ ወይም ያወራብህ የሚመስልኽ ....ያየኽ ሁሉ የሚያናንቅህ የሚያንጉዋጥጥኽ ከሰው በታች አድርጎ የሚያይኽ ይመስልኻል ....በውስጥህ ከየትኛውም ማህበረሰብ ጋር ነጻ ሆነኽ የምትገናኝ ...ነጻ ሆነኽ የምትወያይ ,,,ነጻ ሆነኽ የምትጫወት ሰው አይደለኽም ......የሆነ የግጥም ምሽት አዳራሽ ውስጥ ከመሰል ታዳሚዎች ጋር ታድመኽ እነሱ ግጥሙን እያነበቡ ስለግጥሙ ሲወያዩ ወይኔ ይኼኔ ታዳሚዎቹ ጠቁዋራው መልኬን እያዩ እየተነጋገሩብኝ ይሆናል ....ወይኔ ምነው አጭር ሆኘ ባልተፈጠርኩ ....ምናለ ከሀሜተኛ እናት ተፈጥሬ ሳበቃ ሀሜተኝነት ከእሷ ባልተማርኩ .....ወይኔ ይኼኔ ጥሩ ልብስ አልለበሰም ብለው እያሙኝ ይሆናል .....ውይ ግጥሙ ውስጥ ስለ ገንዘብ ተወርቷል ....እኔ ገንዘብ የለኝም ....ታድያ ገጣሚው እኔን መንካቱ ይሆናል እኮ ....ደግሞ ስለ አስጠሊታ ዝንጀሮ ግጥሙ ውስጥ ከቶዋል ....ይኼኔ እኮ እኔን መንካቱ ነው ወዘተ እያልክ በሲኮፍሮኒያ የምትሰቃይ ሰው ሆነው ነው ያገኘውህ .....በራስ መተማመን የሚባል ነገር ከቶም የለኽም ....ሰውን የምታምን ሰው አይደለኽም ......

ካልሆነ ሰው እንዴት በሰላም የራሷ ችግር እየመዘመዘዛት ወደ ራስዋ ቢዝነስ የምትሄድን አንድ የትራንስፖርት መገልገያ ላይ አጠገብህ የተቀመጠችንና ምንም በዚች አለም ኑር አትኑር መፈጠርኽን እንኩዋን ያላወቀችን ፈረንጅ ሴት እንዴት አይምሮህ ውስጥ እራስኽን አጨናንቀኽ ያለሀጥያቷ ሴትየዋን ሀጥያት ውስጥ ከተህ እራስህን አውርደኽ ይኼኔ ጥቁር ስለሆንኩ ሰድባኝ ይሆናል አጭር ስለሆንኩ አሾፋብኝ ይሆናል ብለኽ እሷን በልብህ በመስደብ ሀጥያት ትገባለኽ ?

ይኼ ትልቅ የስነልቦና ችግር ስለሆነ አደራ እራስኽን ከመግደልህ በፊትና ድምጽ ሰማሁ ሰው ሊገድለኝ ነው እንትና ስለእኔ አወራ ምናምን እያልክ የሚበር ባቡር ውስጥ ገብተኽ እንዳትገላገል ኢንሹራንስ ካለኽ ሂድና ያንጎል ዶክተር ጎብኝ ከሌለኽም እዚህ ዋርካ ያለን ከቀረቀርናት አዋጥተን ልንደርስልህ እንችላለን ::

ይኼ ሲይርየስ ነገር ነው ::አንድ አንድ ጊዜ ከውስጣችን ያለን ነገር ስለሆነ የምንጽፈው ያንተ ደግሞ ብዙ ጊዜ ጽሁፎችኽን ያየ ከዛ ጋር የሚያገናኝና ሰው ሳይነካኽ ሰድቦኝ ይሆን ሾተል ይኸንን ጽሁፍ የጻፈው እኔን ለመንካት መሆን አለበት...ክቡራን በምሳሌ የጻፈው እኔኑ ለመንካት ነው....ዳግማዊ እንትናን በጽሁፉ የተናገረው እሷን ሳይሆን እኔን ነው ወዘተ ነው ብለኽ ከእኔ ጭምር ሰዎችን ሳይነኩህ መፈጠርኽን ረስተውት ሲያበቁ ስትላከፍ አይኻለሁ ::

እንደገና የዚህ ቤት ርእስ እራሱ ስላንተ ሊመሰክር ይችላል ::በራስኽ ጊዜ ምን ያኽል ኢምፖርታንት እንደሆንክ ለመገመት ከሳይበር ዋርካ ለተወሰነ ጊዜ እራስኽን ብታገል እንዳንተው ከብት ጉዋደኞችኽ ስትጠፋ እንኩዋን አልሆኑህም ...ረሱኽ ....ማንም ሩም ከፍቶ ሙናየ ጠፋ ያለም የለም ....ከዛ ነፍሱን ይማረውና ታላቁ መሪ መለስ ሲሞት ብቅ አልክና መልሰኽ ማንም የት ጠፋኽ ስላላለኽ በዛው ጠፋኽና መልሰኽ እንኩዋን አንተ ጠፋኽ ብለው በፌስ ቡክ ሊፈልጉህ አይደለምእዚህ ያላችሁት ከብቶችንና ምድረ ዘረኛ የሰው ዘርና ሀይማኖት እየጠራ ሲሳደብ የሚውሉትን ባጠቃላይ መቆጣጠሩን ትተው የራሳቸውን ሌላ ቢዝነስ ሲሰሩ የሚውሉትን የሳይበር አድሚኖች ለምነው ምን ብለው አመጡኝ አልክና በራስኽ ፈጠራ ደስታ ውስጥ ገብተኽ ህጻን ያሞኘኽ መስሎህ እራስኽን አታለኽ ከች አልክ ::

አትጠቅምም እንጂ መኖርኽ ለዋርካ ጥሩ ነው ::ለምን ብትል እንዳንተ ያለ ከብቱን ታከን ነው መልክት ማስተላለፍ ስንፈልግ የምናስተላልፈው ::አንተና መሰሎችኽ ከዚህ ዋርካ ብትጠፉ የማንን ጽሁፍ ተደግፈን ወይም ከምን የተዝረከረከ ቶፒክ ተነስተን እውነትን እየጻፍን እናንተ ዝርክርክ ከብቶችን እናስተምር ?

እና ምንም ከብት ብትሆንም በከብት ሰውነትህ ያው ወገኔ ስለሆንክ የምመክርህ ነገር ቢኖር የጭንቅላት በሽተኛነት እየጀማመረኽ ስለሆነና በራስ መተማመንህን ስላጠፋው ሂድና ሳይካትሪስት እይ ::ግድ የለኽም ቀልዱን ለጊዜው እናቁምና ሂድና ታይ ::አንጎልኽ የተበለሻሸና የማይጠቅም ከሆነ እሱን አውጥተው ጭድ ሞልተው ይልኩህና ደህና ትሆናለኽ ...

ዛሬ አጠገቤ የተቀመጠች ሴትዮ ጥቁር ነኽ ...አጭር ነኽ ብላ ሰድባኝ ይሆናል ብለኽ አላፊ አግዳሚን ሳይቀር መሳደብ የጀመርክ ነገ አንድ ትልቅ ድንጋይን እሱ ድንጋይ ሆኖ ሲያበቃ ይኼኔ ድንጋይ ብሎ ሰድቦኝ ይሆናል ብለኽ ከድንጋይ ጋር ስትደባደብ የድንጋዩ ባለቤት እንዳያስቀፈድድኽ ...

በል ሰሞኑን ግጥሙችኽን ለመተቸት ካንተ ጋር ልሆንም እችላለሁ ::ምልህ አንድም የሚረባ ግጥም ባይኖርኽም አንተነትህን ስለሚያሳዩ ከግጥሞችኽ አንተነትህን እያወጣን እንደዚህ እንጠቁምኻለን ::

ግን የገረመን ዋርካ ፍቅር ከፍተኻት አሳፍረን አሸማቀን ያስተውንህን ሩም ለምን ርእሱን ነጥብ አድርገኽ ረሳታት ?ማለት እናትህና አንተ ሀሜተኛ መሆናችሁን የነገርከንን ሩም ::

ጻፍ

አለን

ሾተል ነን ......ፕሉቶ ፍቅር የነካካው ሁሉ ገጣሚ መሆን ይችላል እንዳለው ስነጽሁፍ የነካካው ሁሉ ሀያሲ ነው ማለቱ ስለሆነ ይኼው ገመገምንኽ .....ቅቅቅቅቅቅቅ ....ዋርካ ለዘላለም ኑሪ .....
_________________
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9645
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby የተሞናሞነው » Sat Nov 24, 2012 2:16 pm

ስማ እስኪ ሾተል

ከላይ ክቡራንን አንተ ከባለቤትነቱ ከሌለህበት 'የክብርነታችን' ሳይሆን 'የክብርነታቸው' ነው ማለት ያለብህ ብዬ አስረድቸውም አልገባውም :wink: እንዴው ስምንተኛ ክፍልንም ሳታጠናቅቁ ትመጡና ማስረዳቱ ደከመነ :roll: ሰለቸነ :lol: ታከተነ :lol: እዳ ገባን እኮ :lol: :lol: እንግዲህ ጊዜው ደርሶ የአቡነ ጳውሎስ ሀውልትንም መንቅለን ስንጥለው ክቡየ 'የቅዱስነታችን ሀውልት ፈረሰ' ብላ ዜና መስራቷ ነው :) ክቡራን አይዞነ አስተካክል ተሳስተሀል ደግመህ አሰላስለው :roll:

ሾተል እንጂ... አቡጊዳ ምን ማለት ነው :roll: ቅቅቅ አንድ ሀገር ጽፈህ ጽፈህ እኮ ነው ጋሽ ለማ ይህንን ጥያቄ ጠይቆ አፈር ያበላህ :lol: :lol: ግን ቆይ የደረሰ ሁሉ ያንተን አለመማር መሀይምነትህን ያወጋል :roll: አይ ሚን ሰው መማር አለመማር...ማወቅ አለማወቅ.... መደደብ አለመደድብ.... መደነዝ አለመደነዝ.... መብቱ መሰለኝ :roll: እዚያ ለስድብ ከተከፈተ ቤትም አንዱ ታዛቢ 'የወርቃለማሁ ዶንኪይ ጋር አመሳስሎሀል ቅቅቅቅቅቅ አንተ ግን ይህም አይገባህም....ፑር :lol:
የተሞናሞነው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1129
Joined: Wed May 11, 2011 5:39 pm

Postby ሾተል » Sat Nov 24, 2012 2:41 pm

የተሞናሞነው wrote:ስማ እስኪ ሾተል

ከላይ ክቡራንን አንተ ከባለቤትነቱ ከሌለህበት 'የክብርነታችን' ሳይሆን 'የክብርነታቸው' ነው ማለት ያለብህ ብዬ አስረድቸውም አልገባውም :wink: እንዴው ስምንተኛ ክፍልንም ሳታጠናቅቁ ትመጡና ማስረዳቱ ደከመነ :roll: ሰለቸነ :lol: ታከተነ :lol: እዳ ገባን እኮ :lol: :lol: እንግዲህ ጊዜው ደርሶ የአቡነ ጳውሎስ ሀውልትንም መንቅለን ስንጥለው ክቡየ 'የቅዱስነታችን ሀውልት ፈረሰ' ብላ ዜና መስራቷ ነው :) ክቡራን አይዞነ አስተካክል ተሳስተሀል ደግመህ አሰላስለው :roll:

ሾተል እንጂ... አቡጊዳ ምን ማለት ነው :roll: ቅቅቅ አንድ ሀገር ጽፈህ ጽፈህ እኮ ነው ጋሽ ለማ ይህንን ጥያቄ ጠይቆ አፈር ያበላህ :lol: :lol: ግን ቆይ የደረሰ ሁሉ ያንተን አለመማር መሀይምነትህን ያወጋል :roll: አይ ሚን ሰው መማር አለመማር...ማወቅ አለማወቅ.... መደደብ አለመደድብ.... መደነዝ አለመደነዝ.... መብቱ መሰለኝ :roll: እዚያ ለስድብ ከተከፈተ ቤትም አንዱ ታዛቢ 'የወርቃለማሁ ዶንኪይ ጋር አመሳስሎሀል ቅቅቅቅቅቅ አንተ ግን ይህም አይገባህም....ፑር :lol:


ሙናዬ የቢሆን አለም ጭፈራውንና እንደ እያረረ እንደሚስቀው ማሽላ የውሸት ሳቁን ተወውና እንዲሁም ግጥም ብለኽ የግጥምን ውበት ማበላሸቱን ለጊዜው ተወውና የአንጎል ችግር አለብህ...ያ ደግሞ ከምትጽፋቸው እራስኽ እንዳልከው እኔነቴን ይገልጹልኛል ብለኽ ከጻፍካቸው ጽሁፎች አንተነትህን እንዳጠናነው የአንጎል ችግር አለብህና ሂደኽ ታከም ወይም የተበላሸውን አንጎልኽን በቀዶ ጥገና መንግለኽ አስወጣውና ጭድ አስጠቅጥቀኽበት ናና ግጥም ከመጻፍኽ በፊት ግጥም ምን እንደሆነ ከጻፉት አንብበኽ ተምረኽ ጻፍልን::

በእውቀቱ ስዩም እንዲህ አለ ፕሉቶ እንዲህ አለ እንትና እንዲህ አለ እያልክ ከምትዘባርቅ ሙናዬ እንዲህ አለ እንዲባልልህ እራስኽ ያልከውንና ሰው ሊያጣቅስልህ የሚችሉትን ነገሮች ጻፍ....ምክር ነው::በውቀቱ ስዩም አለ በቀልቱ ለራሱ ነው ያለው...ሰዎች እንዲሉለት....ስለዚህ እራስኽን ዲፔንድ ሆነኽ ጻፍ...ማለቴ ከሰው አትማር ማለት አይደለም...ግን እንትና እያልክ እንትና ባለው አትክረም......እራስኽ ለመፍጠር ጣር......በውቀቱ የታየውንና ያመነበትን የራሱን ነው የጻፈው....አንተም ያመንክበትን የራስኽን ጻፍ.....ያለዛ ያጣቢ ልጅ አለቅላቂ እንደሆንከው ሁሉ በዛው ትከርማለኽ.....ለማም የራሱን ነው ያለው....እሱ ለሾተል ያለውን ተራ ነገር አንተ ጭንቅላት ቢኖርህ ለምን ከለማ በፊት ቀድመኽ አልጻፍክም?

ምንን አስታወስከኝ መሰለኽ.....የአረቡ ስፕሪንግ ሰሞን ቱኒዚያኖቹ ቤን አሊን በህዝባዊ አመጽ ጣሉት....ከዛ ግብጾች ሙባረክን....ከዛ የሊቢያውን ሞማር ጋዳፊን ሊብያዎች. በህዝባዊ አመጽ ጣሉ....ከዛ የእኛ ተቃዋሚ ተብይዎች ያንተ ግሩፖች ከብቶቹ እነ ብርሀኑ ነጋ እንደ አረቦቹ በድፍረትና በጀግንነት አንድ ተሁኖ በግንባር ሄደው ማስወገድ የሚፈልጉትን መንግስት ወይ ማስወገድ ወይ መሞከር ሲገባቸው እዛው የተሸጎጡበት አሜሪካ ሆነው በቃ በሶሻል ሜድያ ለካስ መንግስት ይወድቃል ብለው ለ 6 ወር ያክል በየደቂቃው ሶሻል ሜድያ....ትዊተር....ፌስ ቡክ....ስካይፕ ወዘተ ሲሉና እንትና እንዳለው.....እንትና እንደተናገረው.....እነ እንትና በትዊተር እንደጻፉት ወዘተ እንዳሉ እራሳቸውን አልነበሩምና በሶሻል ሜድያ መንግስት መጣል አይደለም ማነቃነቅ እንዲሁም ህዝብን ማነሳሳት ቀርቶ የማይሞከር ነገር መሆኑን ሲያዩ በቀን ሰላሳ ሺኽ ጊዜ ትዊተር ፌስ ቡክ ይሉ ከነበረው አሰልቺ ነገር እራሳቸውን አግለው እኛም አንድ አይነት ነገር ከመስማት ተገላገልን እልሀለሁ....አባባ ታምራት በኢመልሽ ጦር መርፌ ሰክቼብሻለሁ እያለ ህዝቡን ያታልል እንደነበረው እነ ብሬ ሊያታልሉ ሞክረው ደጋፊ አጥተው እራሳቸውን አታለው ሁሉንም ነገር ረሱት::ትዝ ይለኛል የኢኮኖሚ ትምህርቱን ትቶ ስለ ሶሻል ሜድያ እንደ አንድ የ አይቲ ሊቅ እራሱን ሊቅ አድርጎ ብርሀኑ በዛ ዘጊ አነጋገሩ እ እ እ እ እ እ በትዊተር ወያኔን ልንጥል የቀረን ጊዜ ጥቂት ነው ሲል......ቅቅቅቅ

አንተም እንትና እንዲህ አለ....እንትና ግጥሙን ሰብስቡት አለ....እንትና ግጥም መፍሰስ መደፋት አለበት አለ እያልክ ሰውን እየተከተልክ እንጂ እራስኽን እየረሳኽና የራስህ አቁዋም እንደሌለህ አንድ ቀን ስታውቅ ለእኛም ለከብቶቹ አስተዳዳሪዎችና ባለሀብቶች ታከስረን ዘንድ ለዘለአለም ከጽሁፍና ከዋርካ ድራሽኽ እንዳይጠፋ እራስኽን ሁን......ሙናዬ እንደተናገረችው የሚያስብል ነገር ጻፍ....ወይም አትጻፍ...

ስለ ክቡራንና እኔ ምንም የሚያገባኽ ነገር የለም......እንደፈለገውን ማለት ይችላል::ከመቶ በላይ ፐርሰንት መብት አለው....ዲሞክራሲ መብቱ ሲሆን የወንድሙን ነገር ካልተጠቀመ እኔም የወንድሜን ነገር ካልተጠቀምኩ ምኑን ወንድማማቾች ሆንን?ዝም ብለኽ ታለቀልቃለኽ እንጂ ዲሞክራሲ ወንድማዊ መብቱን ተጠቅሞ ነው እንደ ፈለገ ሳይሰጋ ከብቶቼን እያገዘኝ እያስተማረልኝ ያለው......ዋ ብቻዬን እያገድኩዋችሁ ያለሁትን ልወንድምና እህቶቼ አከፋፍይያችሁ ወይ ከእኔ የተሻለ አድርገው ይመግቧችሁዋል ወይም አራቁተውና አስርበው አጠውልገው ገለው ይገላግሉኛል::

ለማንኛውም የአንጎል ዶክተርህን ነገ ዛሬ ሳትል ጎብኝ....

አጠገቤ ቁጭ ብላ በልቧ አማችኝ ብሎ ነገር.....ቅቅቅቅቅ.....ከዚህ በላይ ምን በጭንቅላት መታመም አለ?እንኩዋን በአይኑዋ ስላየችኽ አይደለም በቋንቋዋ ብጸድብህም የማይገባህ ደነዝ እንዴት ፈረንጅን የሚያክል ነገር ባይኑ አየኝ ብለኽ ስለ እይታ ስነልቦና አንባቢ ሆነኽ አንብበኽ ልትነግረን ቋመጥክ?ቆይ አንተ ልብና ኩላሊትን እንዲሁም ሰው ያሰበውን አይደለም ሊያስብ ያለውን የሚያውቀው አምላክ ነኽ?ገና ለገና አጠገቤ ተቀምጣለች ብለኽ አምታኝ ይሆናል....በጡሩራ መልኬ እየተሳሳቀችበት ይሆናል....በአጭርነቴ ይኼ የሞተ ቁላ የሚያክል ቁመት ያለው ምስኪን ብላኝ ይሆናል ወዘተ እያልክ እራስኽን እይጨናነቅክ ውልፊጥ ውልፊጥ ያልከው ለቴናም አይደለምና ሂድና ታከም.....በራስ መተማመን ይኑርህ....እንትና አለ ሳይሆን እኔ አልኩ ማለትን ልመድ....

ከብት


ሾተል ነን.......አሁንም ምክራችን በብላሽ ነው
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9645
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Thu Nov 29, 2012 10:05 am

ሙናዬ....እርግጠኛ ነኝ ሰሞኑን የጠፋኸው በክብርነታችን ሆነን ባመላከትንኽ መሰረት የአንጎል ዶክተር ልታይ ሄደኽ ጭድ ጠፍቶ ሳር አስገጥመኽ ለመምጣት እንደሆነ እናትህ ስታማኽ ሰማሁ::እና ምን ያኽል እውነት ነው?ጭድ ቢሆን ጥሩ ነበር....ሳር ከሆነ አንጎልኽ ውስጥ ያስጠቀጠቅከው ማመንዠግ ሁሉ ልትጀምር ስለሆነ ድድህ ይርገፍና ለድድህ ጥሩ አይደለም::

ሾተል ነን........
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9645
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Fri Nov 30, 2012 8:53 am

ሙናዬ

ነፍሴ በፍለጋ ተንከራታ ኳትና

አንችን የሚተካ አላገኘሁኝም አላገኝምና

ጥሪኝ እናቴ ና በይኝ ቶሎ ና

ቁጭ ብለን እናውጋ ...

ሰፈሩን እንማው እንዳምና ታች -አምና ::ይኽ ግጥም ምንን ያመላክታል ?ቸክቻኪው የስድ ንባቡ ባለቤት ሙናዬ በሀሜት ሱስ ናላው ስለዞረና ሀሜተኛ እናቱን ተለይቶ በሚኖርበት አገር አብሮት ሰውን የሚያማ ሁዋላቀር ግለሰብም ሆነ ማህበረሰብ ስላላገኘ ኑሮው በያዘው ሱስ መሰረት ተናግቶ ሌት ተቀን ምኞቱ እናቱ ስትጠራው ስራውን እንበለው ትምህርቱን አቁዋርጦ ሄዶ ወደ ገጠር እናቱ ጋር ቀሚስ ለብሶ አጎዛ አንጥፎ ምስኪኑን ገጠሬ እንትና አባበሉ ከየት አምጥቶ እንደሆን እንጃ አዲስ ጋቢ ለብሶ አየሁ ብላ እናቱ ተመቅኝታ የሀሜት ሪፖርት ስታቀርብለት ....እሱማ ድሮም ገንዘብ አለው እኮ ....ከየት አባቱ አምጥቶ እንደገዛውማ የታወቀ ነው ....አዋቂ (ጠንቋይ ቤት )ስለሚሄድ እኮ ነው ....እና ለምን 2 ብር አለኝ ልስጥሽና እዛ ቆላ ያለው አዋቂ ቤት ሄደሽ ምናምኑን አሰርተሽ አንደፋውም ?ልክ ነኽ ልጄ ስጠኝና በማለዳው ተነስቼ ልሂድና ሰርቼለት ልምጣ ...እንቺ እማዬ ....

ደግሞ ባይገርምህ የእከሌ አባበሉ ያቺ ሴቷ ልጅ አዲሳባ ለትምህርት ሄዳ ስታበቃ እንዴት የመሰለ ሸማ ለናቷ ላባቷ ካቦርታ ገዝታ ብትልክላቸው የዛሬ ወር ሞንሟናው ሞቶ ለቀብር ወጥተን ሳለ የተላከላቸውን ልብስ ቢለብሱት ካካባቢው ሁሉ ደምቀው ላያቸው እንዴት ያናድዳል መሰለኽ ?እኔማ ንዴቱ ሲያብከነክነኝ ቢያድር ይኼው እስከ ትላንትናዋ ሰአት እራስ ምታቱ ቢጫወትብኝ ከጉዋሮ መተሪ ጨቅጭቄ ብታጠነው ተሻለኝ ......ውይ እማዬ እኔን እምም ያድርገኝ ግን ይቺ አዲሳባ ያለችው ልጃቸው ያንቺን ሞራል አትጠብቅም እንዴ ....ቆይ ከየት አምጥታ ነው ?ተማሪም አልነበረች ?ከአሁኑ ተማሪ እያለች እንደዚህ ቤተሰቦችዋን ማስጌጥ ከጀመረች ነገ ደግሞ የተንጣለለ ቤት ልትሰራላቸውም አይደል ?በይ ሌላ የደበቅኩዋት 2 ብር አለች እሷን ይዘሽ ሽባ ሆና ተሰቃይታ እንድትሞት ኮረሪማ አሰክተሽባት ነይ ::

እንደገና ይኽ ግጥም የሚያሳየው ጸሀፊው ወይም ታሪኩን የሚተርክልን ከብት ብዙ ሀሜተኞችን በአለም እግሩ እስኪነቃ በሄደበት አይቷል ነገር ግን እናቱን የሚያክል ሀሜተኛ ሸረኛ አይቶ እንደማያውቅ እራሱ ሲነግረን ይኽንን ሀሜት የሚሉትን ክፉ የስጋና የአንጎል ደዌ በሽታ እሱም እናቱም ከተጠናወታቸው እራሳቸውን ካወቁበት ጊዜ ጀምሮ ሲሆን ሀሜትን አምናም ካቻምናም እንዲሁ እንደ ሪቹዋል ፕራክቲስ በማድረግና በጥንቆላ የአንድ አካባቢ ሰውን በሀሜትና በመሰሪነት የፈጁ መሆናቸውን ከግጥሙ ልንረዳ ስለቻልን እነዚህ ሁለት ኢትዮዽያዊ ግለሰቦች ቢቻል በመንግስት ታድነው ተይዘው ዘብጥያ ወርደው ህብረተሰቡ ከሀሜትና ጥንቆላ እንዲሁም ክፉ ስራ ሰራተኞች ይገላገል ዘንድ የነዚህ ሰዎች በህግ ፊት መቅረብ የማያጠያይቅ ጉዳይ ስለሆነ መንግስት ቢያስብበት ጥሩ ነው እንላለን ::

ሰው እንዴት ሰውን ያማል ?እንዴትስ የሚወራ ስንት ነገር ኖሮ ሲያበቃ ስለ ሰው ወንድ ልጅ ከሀሜተኛ እናቱ ጋር ስለ ሰው ያወራል ?

መጣን

ሾተል ነን .........
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9645
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby እንሰት » Fri Nov 30, 2012 8:27 pm

የተሞናሞነው ከክቡራን ጋር በቁም ነገር ወግ ጀምራች ሁዋል:: ይበል የሚያሰኝ ነው:: ግጥምህን አነበብኩዋትና እንዲህ ቢያደርጋትስ ኖሮ አልኩ::

[quote="የተሞናሞነው"]እንዴት ነህ ክቡ :)
...

[color=indigo][i]
ጎን ለጎን ቁጭ ብለን

ሆኜ ካጠገቧ

ቆዳው የጠቆረ

ቁመቱ ያጠረ

ምን ይመስላል ኧረ'

ያለችኝ መሰለኝ

ፈረንጁዋ በልቧ

ዛዲያ እኔም

የጸጉሯን ንጣት

የቆዳዋን ግርጣት

የፊትዋን ወዝ ማጣት

በደንብ አስተውዬ

በልቤ ሰደብኳት

'ሰይጣን የመሰለች

ነጫ ጭባ!' ብዬ :evil:


ምን ትላለህ?
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby የተሞናሞነው » Fri Nov 30, 2012 10:31 pm

ሰላም ወንድም እንሰት... እንዴት ነህ?

ያው ክቡ ምንም እንዲሁ እዚህ በምንነታረከው ጠበኛ ብንመስልም የኒክ እንጂ ምናልባትም በአካል ብንተዋወቅ ጥሩ ወንድሞች እንሆናለን...ከሀገር ልጅ በላይነቱም:: እናልህ ቤቴ የገባው ለመተንኮስ ቢሆንም በግጥሞቼ ላይ አስተያየት ቢጤ ጣል ሲያደርግ ቤቴ የገባውን ሰው ማክበር አለብኝ ብዬ ስሜቴን ደቆስ አድርጌ :) ለመመለስ ሞክሬያለሁ:: መተናኮሱም ይሁን....መለስ ሲሞት እንኳን እንዲያ ስለው እንዳልከረምሁ ' ወይኔ የኢትዮጵያ መሪ ፈረንጅ ሀገር እንደሄደ ሞተ' በሚል ስሜት በሚገርመኝ መልኩ በጣም ነበር ያዘንኩት:: የሚገርመኝና ሊገርምህ የሚችለው እዚያ ላይ ፖለቲካውም ምኑንም ረሳሁት.... አንድ ጓደኛየ ደግሞ 'እልልልልል' እያለ ነበርና 'አንተ አስመሳይ ወያኔ ነህ' ያለኝ አይረሳኝም :lol: እኔ እንግዲህ ሌላ መሪ አላውቅም ቢያናድደኝም ብቃወመውም ብጠላውም ግን ለካስ ከመሌ ጋር እድሜየን ሙሉ ተላምደን ኖሯልና ሞቶ ከቦሌ ሲገባ ላይቭ እየተከታተልኩኝ ሳይ ሁሉንም ረስቼ ከምር አዘንኩኝ:: እና ልልህ የፈለግሁት ዞሮ ዞሮ እዚህ ብንተራኮስም ይህ ሀገር የሚትና ሀበሻነት ከዚያም አልፎ ሰብዐዊነት ስሜቱ ላለው...እነዚህ ያገናኙናል:: ከሁሉም በላይ እኔን በተለይ ሰብዓዊ ስሜት ያለው ቅን ሰው ይገዛኛል:: እንግዲህ ክቡራን የወያኔ ደጋፊ ነው...ግልጽ ነው...ግን ቢሆንም ቢሆንም ብለህ ያው አንዳንዴ ሰላም የምትለው አይነት ሰው ነው :) ሲያስፈልግም በዱላ እንለዋለን ታዲያ :roll:

እችን ግጥሜን ጥሩ አስተካክለሀታል እስማማለሁ:: እንዲሁ ነው ዝም ብዬ የጫርኳትን ክቡን ሰድበህኝም ቢሆን ቤቴ መጥተህ ባዶ ቤት በስድ ንባብ አልሰድህም በሚል የጋበዝኩት:: እንሰት አንድ ጥያቄ እስኪ ልጠይቅህ....ግጥም አንዴ ከተጻፈ በኍላ ላስተካክልህ ስለው ለምንድን ነው የማይመጣልኝ...ወይም ለማስተካከል የማልፈልገው? ካሁን በፊት በግል የጻፍኳቸው አሉኝ....ግን የሆነ የሚቀራቸው ነገር እንዳለ እያየሁ....ልሄድባቸው አልቻልኩም::

እስኪ ከቻልኩኝ እዚህ ላወጣቸው ያልፈለግኍቸው በግል የምልክልህም ይኖሩኛል::

ምስጋና ከወንድማዊ አክብሮት ጋር


እንሰት wrote:የተሞናሞነው ከክቡራን ጋር በቁም ነገር ወግ ጀምራች ሁዋል:: ይበል የሚያሰኝ ነው:: ግጥምህን አነበብኩዋትና እንዲህ ቢያደርጋትስ ኖሮ አልኩ::

የተሞናሞነው wrote:እንዴት ነህ ክቡ :)
...

[color=indigo][i]
ጎን ለጎን ቁጭ ብለን

ሆኜ ካጠገቧ

ቆዳው የጠቆረ

ቁመቱ ያጠረ

ምን ይመስላል ኧረ'

ያለችኝ መሰለኝ

ፈረንጁዋ በልቧ

ዛዲያ እኔም

የጸጉሯን ንጣት

የቆዳዋን ግርጣት

የፊትዋን ወዝ ማጣት

በደንብ አስተውዬ

በልቤ ሰደብኳት

'ሰይጣን የመሰለች

ነጫ ጭባ!' ብዬ :evil:


ምን ትላለህ?
የተሞናሞነው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1129
Joined: Wed May 11, 2011 5:39 pm

Postby እንሰት » Fri Nov 30, 2012 10:45 pm

ወንድም አለም
መቸም በደግም በክፉም ከተነጋገርከው ሰው ጋር የምትጋራው ነገር ይኖራል:: ከክቡ ጋርም ስለ ግጥም ስታወሩ ባነብ ሁለቱ ተደማመጡ አልኩ::

ግጥም ስትጽፍ እና ስታነብ ልዩነት አለው:: ለምሳሌ ያንተን ግጥም እኔና ሾተል አነበብነው እሱ ወደ ጭብጡ ሄደ በራስ መተማመን ስለጎደለህ ነው እንዲህ የምትጽፈው አለ እኔ ደግሞ እሱ አልታየኝም የግጥምህ መልክቱ ሳይንዛዛ ውብ በሆነ ቃላት መተላለፉን አየሁና ጮክ ብዬ ነበብ ሳደርገው አልፎ አልፎ ያዝ ያዝ አደረገኝ ያለምንም የቃላት ለውጥ እንኩዋን እንዲህ ቢያደርገው አልኩ ያንን ሳነበው ትክልክል ያለ መሰለኝ:: ያንን ስሜቴን ላኩልህ ማለት ነው::

በምክር ደረጃ ከሆነ አርትኦት ከጀመርክ ሀሳብ እንደመጣልህ አንድ ህሊናህን ያጫረውን ነገር እንዳየህ አትጽፍም ስለዚህ እንዳትጽፍ ያግድሀል ማለት ነው:: እንደ እኔ ከሆነ የተጻፉት ማረሚያ ጊዜ ይኖራቸዋል እንድመጣልህ ስንኙን መቀዋጠሩ ስዱንም መክተቡ ይሻላል ባይ ነኝ::

በጉዋዳ የ'ምየላ" አድራሻዬን ልልክልህ እችላለሁ ከዋርካ የዘለለ ሀሳብ መለወዋጥ ካስፈለገ::
አክባሪህ

የተሞናሞነው wrote:ሰላም ወንድም እንሰት... እንዴት ነህ?

ያው ክቡ ምንም እንዲሁ እዚህ በምንነታረከው ጠበኛ ብንመስልም የኒክ እንጂ ምናልባትም በአካል ብንተዋወቅ ጥሩ ወንድሞች እንሆናለን...ከሀገር ልጅ በላይነቱም:: እናልህ ቤቴ የገባው ለመተንኮስ ቢሆንም በግጥሞቼ ላይ አስተያየት ቢጤ ጣል ሲያደርግ ቤቴ የገባውን ሰው ማክበር አለብኝ ብዬ ስሜቴን ደቆስ አድርጌ :) ለመመለስ ሞክሬያለሁ:: መተናኮሱም ይሁን....መለስ ሲሞት እንኳን እንዲያ ስለው እንዳልከረምሁ ' ወይኔ የኢትዮጵያ መሪ ፈረንጅ ሀገር እንደሄደ ሞተ' በሚል ስሜት በሚገርመኝ መልኩ በጣም ነበር ያዘንኩት:: የሚገርመኝና ሊገርምህ የሚችለው እዚያ ላይ ፖለቲካውም ምኑንም ረሳሁት.... አንድ ጓደኛየ ደግሞ 'እልልልልል' እያለ ነበርና 'አንተ አስመሳይ ወያኔ ነህ' ያለኝ አይረሳኝም :lol: እኔ እንግዲህ ሌላ መሪ አላውቅም ቢያናድደኝም ብቃወመውም ብጠላውም ግን ለካስ ከመሌ ጋር እድሜየን ሙሉ ተላምደን ኖሯልና ሞቶ ከቦሌ ሲገባ ላይቭ እየተከታተልኩኝ ሳይ ሁሉንም ረስቼ ከምር አዘንኩኝ:: እና ልልህ የፈለግሁት ዞሮ ዞሮ እዚህ ብንተራኮስም ይህ ሀገር የሚትና ሀበሻነት ከዚያም አልፎ ሰብዐዊነት ስሜቱ ላለው...እነዚህ ያገናኙናል:: ከሁሉም በላይ እኔን በተለይ ሰብዓዊ ስሜት ያለው ቅን ሰው ይገዛኛል:: እንግዲህ ክቡራን የወያኔ ደጋፊ ነው...ግልጽ ነው...ግን ቢሆንም ቢሆንም ብለህ ያው አንዳንዴ ሰላም የምትለው አይነት ሰው ነው :) ሲያስፈልግም በዱላ እንለዋለን ታዲያ :roll:

እችን ግጥሜን ጥሩ አስተካክለሀታል እስማማለሁ:: እንዲሁ ነው ዝም ብዬ የጫርኳትን ክቡን ሰድበህኝም ቢሆን ቤቴ መጥተህ ባዶ ቤት በስድ ንባብ አልሰድህም በሚል የጋበዝኩት:: እንሰት አንድ ጥያቄ እስኪ ልጠይቅህ....ግጥም አንዴ ከተጻፈ በኍላ ላስተካክልህ ስለው ለምንድን ነው የማይመጣልኝ...ወይም ለማስተካከል የማልፈልገው? ካሁን በፊት በግል የጻፍኳቸው አሉኝ....ግን የሆነ የሚቀራቸው ነገር እንዳለ እያየሁ....ልሄድባቸው አልቻልኩም::

እስኪ ከቻልኩኝ እዚህ ላወጣቸው ያልፈለግኍቸው በግል የምልክልህም ይኖሩኛል::

ምስጋና ከወንድማዊ አክብሮት ጋር


እንሰት wrote:የተሞናሞነው ከክቡራን ጋር በቁም ነገር ወግ ጀምራች ሁዋል:: ይበል የሚያሰኝ ነው:: ግጥምህን አነበብኩዋትና እንዲህ ቢያደርጋትስ ኖሮ አልኩ::

የተሞናሞነው wrote:እንዴት ነህ ክቡ :)
...

[color=indigo][i]
ጎን ለጎን ቁጭ ብለን

ሆኜ ካጠገቧ

ቆዳው የጠቆረ

ቁመቱ ያጠረ

ምን ይመስላል ኧረ'

ያለችኝ መሰለኝ

ፈረንጁዋ በልቧ

ዛዲያ እኔም

የጸጉሯን ንጣት

የቆዳዋን ግርጣት

የፊትዋን ወዝ ማጣት

በደንብ አስተውዬ

በልቤ ሰደብኳት

'ሰይጣን የመሰለች

ነጫ ጭባ!' ብዬ :evil:


ምን ትላለህ?
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby ሾተል » Sat Dec 01, 2012 12:34 am

የተሞናሞነው

..መለስ ሲሞት እንኳን እንዲያ ስለው እንዳልከረምሁ ' ወይኔ የኢትዮጵያ መሪ ፈረንጅ ሀገር እንደሄደ ሞተ' በሚል ስሜት በሚገርመኝ መልኩ በጣም ነበር ያዘንኩት:: የሚገርመኝና ሊገርምህ የሚችለው እዚያ ላይ ፖለቲካውም ምኑንም ረሳሁት.... አንድ ጓደኛየ ደግሞ 'እልልልልል' እያለ ነበርና 'አንተ አስመሳይ ወያኔ ነህ' ያለኝ አይረሳኝም :lol: እኔ እንግዲህ ሌላ መሪ አላውቅም ቢያናድደኝም ብቃወመውም ብጠላውም ግን ለካስ ከመሌ ጋር እድሜየን ሙሉ ተላምደን ኖሯልና ሞቶ ከቦሌ ሲገባ ላይቭ እየተከታተልኩኝ ሳይ ሁሉንም ረስቼ ከምር አዘንኩኝ:: እና ልልህ የፈለግሁት ዞሮ ዞሮ እዚህ ብንተራኮስም ይህ ሀገር የሚትና ሀበሻነት ከዚያም አልፎ ሰብዐዊነት ስሜቱ ላለው...እነዚህ ያገናኙናል:: ከሁሉም በላይ እኔን በተለይ ሰብዓዊ ስሜት ያለው ቅን ሰው ይገዛኛል::


አቤት ውሸት....እዝጎ ማርነ ክርስቶስ.....ምነው ለዚች አጭር ህይወት ሀይማኖት ካለን ለክራችን ወይም ሀይማኖት ከለለን ለህሊናችን እውነት ብናወራ ምን አለበት?

ሙናየ ፖለቲካ ሩም የሚገባ ሰው እዚህ የሚገባ አልመስልኽ ብሎ ይሆን እንደ ጣቃ ጨርቅ የምትቀደደው?

በል በመለስ ሞት ፖለቲካ ሩም ያላገጥከውን ከዚህ ጋር አስተያየውና እራስኽን ታዘብ::

ውሸታም ከብት::

የተሞናሞነው

ፖሰት የተደረገ: ማክሰ Jul 31, 2012 12:13 pm ርዕስ ፖሰት ያድርጉ:
ታጋይ ስልኪ አለህ እንዴ በማሪያም የመለስ ድራሽ መጥፋት አንተንም ድራሽህን አጥፍቶህ ሳፈላልግ ....እንኳን ባይሆን ሁለት መስመርም ብትሆን እችን ጣፍክልን አይዞህ ....'ምንም ቢሆን የአድዋ ስላሴ ልጅ ነህ ' አለ ሁሌም ፈገግ የሚያደርገኝ አባ ጦቢያ ቀብር መቸ ነው ግን ? ታየኝ እኮ እነ ኮሎኔል ማራኪ ተሰብስባችሁ ዋይ ዋይ ስትሉ ....ወግ አደል መቸስ እኔ እንኳን የመለስን ሞት ከዕቁብም አልቆጥረው .....በፊትም ህወሃቶችን ስለምንቃችሁ


ሌላም አለ ገና ይወጣል::

እና ከብታችን አትዋሽ....ለህሊናው ኑር አንተ የሀሜተኛ ልጅ ሀሜተኛና ውሸተኛ::ለካስ እናትህ ውሸትንም አስተምራኽ ኖሯል?

ሾተል ነን.......ዋሾዎችን እጅ ከፍንጅ የምንጋምመው አስካሪ
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9645
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ቁምቢ » Sat Dec 01, 2012 12:51 am

:lol: :lol: :lol: ናይስ በሳቅ ነው የሞትኩት ሰው በማስረጃ እንደዚ ሲጋለጥ አይቼ አላውቅም...........እጅ ከፉ ይባላል ይሄ አያያዝ............መልስ እንጠብቃለን.......የተሞናሞነው........ጠበቃዎችንም ቢሆን አናግረህ መልስ ይዘህ ና እዚሁ እየተንጓዳጎድን እንጠብቅሃለን............
የሰው ልጅ
መውደድ ሲችል መጥላቱ
መምከር ሲችል ማማቱ
መስራት ሲችል መቅናቱ
ማስታረቅ ሲችል ማጣላቱ
ያሳዝናል የሰው ፍጥረት በሕይወቱ፥፥
ቁምቢ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 83
Joined: Mon Nov 26, 2012 3:55 am

Postby ሾተል » Sat Dec 01, 2012 1:04 am

ቁምቢ wrote::lol: :lol: :lol: ናይስ በሳቅ ነው የሞትኩት ሰው በማስረጃ እንደዚ ሲጋለጥ አይቼ አላውቅም...........እጅ ከፉ ይባላል ይሄ አያያዝ............መልስ እንጠብቃለን.......የተሞናሞነው........ጠበቃዎችንም ቢሆን አናግረህ መልስ ይዘህ ና እዚሁ እየተንጓዳጎድን እንጠብቅሃለን............


ቁምቢ እስቲ ለሙናየ ምነው ባይዋሽ በልልኝ.....

እስቲ አንድ ልጨምርና ይኼንን ውሸታም ላዋርደው::

የተሞናሞነው


እረ ስልኪ ዉዉዉዉ ...ውውው ቅቅቅቅቅ የት ገባህ ግን እኔ 'ኮ ደስ የሚለኝ መለስን የተባለችው ገጣባ ራስ መሞቷ አይደለም የናንተ በውሸት ትንሽ ዘረኛ ትምክህት (ሐየት ል ..ቁን ጨምሮ ) የተገነባችው ሞራል ኩሽሽሽሽሽሽ ስትል ማየት ነው


ምነው ባይዋሽ ግን?

ግን ሙናዬ የ ስጦታው ልጅ መሰለኝ::ቅቅቅቅ....እውነተኛ ስሙን እራሱ ይናገር..

ሾተል ነን........ከወታደራዊ ደህንነት ጥበቃ ቢሮ
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9645
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Tue Dec 04, 2012 2:31 pm

ሙናዬ.....በመለስ ሞት ሀዘን ላይ ቁጭ ብለኽ ሰዎች ወያነ አሉህ አይደል?....

ወይ ዘንድሮ.......

እንደ ሙናዬ አታጋልጠኝ ማለት ነው...

ምናለ ግን አቁዋም ቢኖርህ አንተ ከብት?

የሆንክ የሀሜተኛ ልጅ

አፈር ብላና ትን ይበልኽ

ሾተል ነን.........
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9645
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: Bing [Bot], Google [Bot] and 2 guests