ማርቆሶች ተሰብሰቡ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ለማ12 » Fri Aug 10, 2012 7:17 pm

ሰላም ሙ

እኔስ አልተፋሁም ጋሻ አሰፋ ያደረገንን አየህው?

ደግሞ አንድ ቀን ምን አደረገን መሰለህ

የሴት አስተማሪ ነበረችን የከሳት ፈረቃ ስለነበረን ዝናብ ይዘንብ ነበር

አስተማሪያችን ስትመጣ ጥላ ይዛ ነበር የመጣችው ቀይ ሱሪ ታጥቃ ነበርና ከጥላው ተንጠፋጥፎ ብሀላ በኩል እመቀመጫዋ ላይ ትንሽ ውሀ ነገር ነክታለች:
ልትጽፍ ወደ ፕልክ ቦርዱ ስትዞር ሴቶች አሁን ተነጭታ ነው የመጣች ብለው ከመጠን በላይ ሲስቁ ሁላችንም ሳቅን እሳም ፊታን አዙራ በምን ነው የምጽቁ ብላ ብትጠይቀን የሚመልስ ጠፋ እኔን ስትጠይቀኝ ትናገርና ፈርዶብሀል ብለው በአይናቸው ጠቀሱኝ እኔም አላውቅም አልኩ እንደገና ዞራ ልጽፍ ስትል ይስቃሉ አሁን ካላወጣችሁ እሄዳለሁ አልችን እኛም ዝም አልናት ወዲያው ወደ ቢሮ ሄደችና ለጋሽ አሰፋ ስትነግረው እሱም ትልቅ ጥላ ይዞ በጣም ትልቅ የገበሬዎችን ዱላ ይዞ ነጣና አውጡ አለን እኛም ዝም አልነው ካላወጣችሁ ተነሱ ውጡና እዚህ ዝናብ ላይ ተኙ አለን ምቅቅቅቅቅቅቅ
ምንም ማድረግ ስላልቻልን እየሮጥን እዝናቡ ላይ ተኛን እሱም በያዘው ዱል እየደወለ ተንከባለሉ አለን ቅቅቅቅቅቅቅ
ዝናቡ በጣም ይዘንባል ጎርፉ በላያችን ላይ እየዘለለ ይወርዳል በዚያ ላይ እየተከተለ በየዘው ዱላ ይደበድበናል. የለበስነው ዩኒፎርም ነው በጣም ስስ ነው ከሰውነታችን ይጣበቃልቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

ሲያንከባልለን ውሉ ደግሞ በሙሉ ተማሪው እንዲያዬን ሰንደቅ አላማ ተሰልፋችሁ አውርዱ አለን ኤናም ያዘዘንን አደረግን እንደተሰለፍን መሀል ከተማ ድረስ እንድንሄድ ይልማን ጭምሮ አዘዘን እኛም ተሰልፈን ቀጠልን ያ ሁሉ ያይ የነበረ ግን የተወስን ልጆችን ነበር ምክንያቱም በጣም ሰው አይደፍረንም እያልን እንደባደብ ስለነበረ ነው ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅያ ሁሉ አለፈ እረ ስንቱ?ፎቶቤቶችን አንስተሀል
ሁሉንም በደንብ አውቃቸዋለሁ

በተላይ ፎቶ ሀይሌን አዲስ አበባም አገኘው ነበር አንድ ልጅ ነበረችው አገሩን የምታጠፋ

ቤቱ ወደ ድብዛ መሄጃው ላይ ነበር አሁን ሸጦት ሽይ ቤት ሆኖ አይቸዋለሁ:

የሙሉአለም ፎቶ ቤት ልጆች በጣም ግኣደኞቼ ናቸው አሁንም

አንዱ በጣም ሀብታም ሆኗል አዲስ አበባ ሌላም ታሪክ አል ግን እሱን አልናገርም ሰወች ስለሚያውቁኝ ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

በል አትጥፋ
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1105
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby ሙዝ1 » Wed Sep 26, 2012 12:24 pm

ሰላም ጋሽ ለማ1 .... ጋሽ ብልህ ሳይሻል አይቀርም ከአጎቶቼ ጓደኞች አንዱ እንዳትሆን? ለምን መሰለህ ...

የሙሉአለም ፎቶ ቤት ልጆች ጓደኞቼ ናቸዉ ነዉ ያልክ? :wink: ሀብታም የሆነዉን እኔም አዉቀዋለሁ .... ... ሀይሌ መሰለኝ ስሙ? ረሳሁት ... ... አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እያለሁ ልመረቅ አካባቢ ዉጭ ያለ አጎቴ ባጋጣሚ እህቱ ጋ ሲደዉል እኔን ያገኘኝና ስናወራ ልመረቅ እንደሆነ ነገርኩት ... በቃ ብር ከሀይሌ ጋ ዉሰድ ብሎ አድራሻ ሰጠኝ ... .... ሄድኩ ... ቂቂቂ ስንት ትፈልጋለህ አለኝ :wink: ተሳቅቄ ይሄን ያክል አልኩት ... ጥፋ ከፊቴ? አሁን ይሄ የሚጠየቅ ብር ነዉ? ብሎ ከጠየኩት 3 እጥፍ ሰጥቶ አባሮኛል .... አጠር ያለ ወፍራም ... መላጣ ....

ከነሱ ቤት የኔ ጓደኞች እነማ መሰሉህ .... እነ ኤልያስ ደጀኔና እስጢፋኖስ ደጀኔ .... የጀኔራል ቁምላቸዉ ደጀኔ ወንድሞች ናቸዉ መሰለኝ .... ጀኔራል ቁምላቸዉን ስሙ ከ82ቱ መፈንቅለ መንግስት ጋ በተገናኘ ይታወቃል ... ...

እስኪ ስለ መስቀል
መስቀል በደብረ ማርቆስ ከተማ የሚከበረዉ ንጉስ ተክለሀይማኖት አደባባዩ ጋ ሲሆን .... በመስከረም 16 ከ9 ሰአት ጀምሮ የሁሉም ቤተክርስትያን ቄሶችና ህዝቡ በደመራዉ አካባቢ ይሰባሰብና በጳጳሱ ና በመንግስት ተወካይ ምናልባትም ካንቲባዉ አማካኝነት በጋራ ይለኮሳል ... ... ቂቂቂ ይሄማ ምን አዲስ ነገር አለዉ ማለታችሁ አይቀርም ... ... ልክ ነዉ ምንም አዲስ ነገር የለዉም ... ... አዲሱ ነገር የደመራዉን ምሰሶ ስትወድቅ ለመዉሰድ የሚደረገዉ የፍንዳታዎች ግብግብ ነዉ :wink: ...

የሆነ ቦታ የደብረ ማርቆስ ልጆች ጀብደኞች ናቸዉ ካልኩባቸዉ ምክንያቶች አንዱ ይሄ ነዉ .... ደመራዉ ይቀጣጠላል ... .... ይነዳል ... እሳቱን አስቡት ... የከተማ ደመራ እሳት ... እንዲሁም የምሰሶዉን ርዝመት ... ጎረምሶቹ መጨፈር ይጀምራሉ ....ህዝቡ ራቅ ራቅ እያለ መቆም ይጀምራል .... የሁሉም ሰፈር ፍንዳታዎች ወደ እሳቱ በቅርብ ይሰባሰባሉ .... የአብማ ... የፈረስቤት ... የዉሰታ ... ... የሸዋበር .... አሁንም ደመራዉ ይነዳል ... ምሰሶዋ መነቃነቅ ስትጀምር ሁሉም ያሰፈስፋል .... ወደ የትኛዉም አቅጣጫ ስትወድ ምሰሷዋን ለመዉሰድ ያለዉ ድብድብ ,,,, ቂቂቂ .... ያ ምሰሶ እሳት ነዉ .... ሰዉ እሳትን ለመያዝ መጣላት ... .... ቢሆንም ደስ ይላል ... .... ጀግንነት በተለያየ መልኩ ይገለጻል ... ...
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Postby -...- » Wed Sep 26, 2012 5:50 pm

ሙዝ1 wrote:ሰላም ጋሽ ለማ1 .... ጋሽ ብልህ ሳይሻል አይቀርም ከአጎቶቼ ጓደኞች አንዱ እንዳትሆን? ለምን መሰለህ ...

በደንብ አወኩህ አሁን

አንተ ደህና ነህ ለመሆኑ ?

ለሚቾን ዱሮ ገና በጠዋቱ ነው ያወኩት.....አንተ ኩታራ ሙዝ ጋሼ ማለትህም ተገቢ ነው :: እኔንም ጋሼ በለኝ..ምክንያቱም ከለማ ጋር የጠላ ቤት ትውውቆች ነበርን ብዙ ባንቀራረብም
ሞቼ እየተነሳሁ ልሙት እንደገና
አንድ ሞት ላገሬ አይበቃትምና
-...-
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 401
Joined: Thu Feb 09, 2012 8:36 pm

Postby ሙዝ1 » Thu Sep 27, 2012 12:41 pm

ነጠብጣቡ ...
ስላወከኝ ደስ ብሎኛል ... ኩታራ የምትለዋ ቃል ግን በጉብል ትለወጥ ... የዚህ ቤት አማረኛ ስላልመሰለችኝ ነዉ ... ስማንጂ ነጥቦ ... ዘመዶቼ ለአዲስ አመት ጋብዘዉኝ ወደ ማርቆስ ጎራ ብዬ ነበር ከባለቤቴ ጋ እናም ከአጎቶቼ ጋ ሳወጋ ስለ ለማ ሳወጋቸዉ .... ... በርግጠኝነት ይሄ ሰዉ ፋሲል ካሴ ...ዮሀንስ አሰፋ ወይንም ዘላለም ቸርነት መሆን አለበት አሉኝ :wink: የነሱ ዘመን ጉልቤዎች መሰሉኝ .... አገር ቤት ከሆነ ያለዉ ደግሞ አበጀ ምናምን አሉኝ :lol: .... የሆነዉ ይሁን ለማ አሁን የኔ እንጂ የናንተ ጓደኛ አይደለም ብያቸዋለሁ :wink:
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Postby ሙዝ1 » Thu Sep 27, 2012 1:08 pm

ስማንጅ ነጠብጣቡ ...
ስለ ጠላ ቤት ስታወራ .... ማርቆስ የምትታወቀዉ በጠላ ቤት ስሞች ነዉ አይደል? .... እስኪ ከምታስታዉሳቸዉ የጠላ ቤት ስሞች አስታዉሰን ....

የማርቆስ ጠላ ቤት ማህበራዊ ደረጃ እንደ ሀረሩ የጣሳ ጠላ ቤት አልያም እንደ ጅጅጋዉ አርቄ ቤት አይደለም ... ... ማርቆስ ላይ ጠላ ይጠጣል ... ጠላ ይበላል ... ጠላ ያዝናናል .... ጠላ ያስታርቃል ... ጠላ ያስተዛዝናል ... ብቻ ጠላ ብዙ ነገር ነዉ ማለት ይቻላል ... ... ማርቆስ ላይ ጠላ መጠጣት ሀረር ላይ ጠላ እንደመጠጣት አይደለም ... ... ምናልባት ሀረር ላይ ጫት እንደመቃም ሊሆን ይችላል ... ... ሀረርጌ ዉስጥ ጫት መቃም ሳይሆን የሚያስገርመዉ አለመቃም ነዉ .... ሀረርን ከጭሮ (አሰበ ተፈሪ) ጀምሮ ወደ ቀኝ እስከ ምጨታ (አርሲ ጥግ) ... ወደ ፊት እስከ ጅጅጋ ... ወደ ግራም እስከ ድሬዳዋ --- ደወሌ ድረስ ያሉ ማህበረሰቦች እናቶች ለልጆቻቸዉ ምሳ አስቀምጠዉ ለጉዳይ ከቤት ከወጡ ምናልባት ምሳ ሳህኑ ስር የጫት ብር ይቀመጣል ... ... ማርቆስ ብር ዉድ ስለሆነ የጠል ባይተዉልህም እቤት ዉስጥ ካለ ግን እንድትጠጣ ይበረታታል ... አንድ ምሳሌ ላስታዉስህማ ነጠብጣቡ ... ... የዛሬ አመት አካባቢ የሆነ ዘመዴ ሰርግ ስለነበረዉ ሄጄ ነበር ... .. ባለቤቴን ይዤ (በልጅነቷ ከሀገር ወጥታ ዉጭ ያደገች ልጅ ነች :wink: ) ነዉ የሄድኩት ... ቂቂቂ ... ከአክስቶቼ ልጆች አንደኛዋ ልጇ ሲያለቅስ እንደማባበያ ጠላ ስታጠጣዉ አይታ ... ባለቤቴ የጮኸችዉ ጩኸት አትጠይቀኝ :wink: ... ለሷ ጠላ በዛ መልኩ አይገለጽም ...

ማርቆስ ጠላ ቤት የሚታወቀዉ ጠላ በመሸጥ በመግዛት ብቻ አይመስለኝም ... በጣም ዉብ ዉብ የሆኑ ጨዋታዎች የሚፈልቁበት .... ነቆራዎች ... በብዛት የሚፈበረኩበት ቦታ ይመስለኛል ... ለነገሩ ብዙም ልምዱ የለኝም ....

ነጠብጣቡ ለነገሩ አንተ የየቦ ባላገር ስለሆንክ ምናልባት ስለ ጥጃ ጥበቃ ብታወራን ይሻላል መሰለኝ :wink: ... ቂቂቂ ይመችሽ አባ ....

መልካም ጨዋታ
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Postby ለማ12 » Sat Sep 29, 2012 10:57 am

እኔማ አውቄው ውሀው ደፍርሶ አለ ያገሬ ገበሬ!

ይህን ያህል የተጫወታችሁ የት ሄጀ ነው:
እረ በማርቆሱ:
አደራህ ነጠብጣብ አስቀይሜህ ከሆነ ይቅርታ አድርግልኝ:

አንድ ሰው ከአመት በፊት ያለኝን እዚህ ላይ ልንገራችሁ ደህና እንደ እናንተ ስንጫወት እያለ ሲአውቀኝ
አንተንማ ምን ማጫወት ነው ባገኝህ አንገትህን ነበር የምቆርጥህ ያለኝ በጣም ይገርመኛል አሁንም ለዚህ ነው ራቅ ራቅ ያልኩት ቅቅቅቅ

ሙ ጋሼ ልበልህ ነው ያልከኝ እንደፈለክ ከአጎቶችሁ አካባቢ ሳልሆን አልቀርም:
ከጠራሀቸው ሰውች ውስጥ አይደለሁም ግን በጣም ጋደኞቼ ነበሩ:

ዘውዱ ግርማ በመኪና አደጋ አዲስ አበባ ተገደለና ለልቅሶ እንደተቀመጥን
ዘውዱ መንግስቴ እየሮጠ ገባና ምን አለ መስለህ

ዘውዱን የገደለውን እናቱን ልብዳት ብሎ ሊአለቅስ ሞክሮ በጣም ነው ያሳቀኝ
እውነት ልንገራችሁ ያሳለፍነውን ሁሉ ሳስበው እንባየ ይመጣል መልካም ጊዜ ነበር

ሙ አዎ ሀይሌ ሙሉአለምን በደንብ ገልጽህዋል ግን ታናሹ ነው ህብታም የሆነው ተፈሪ ሙሉአለም የሚባለው 4 ያህል ልጆች ወለድኩ ያለኝ መሰለኝ አሁንም በቅርብ ወልዷል አመት የሞላው አይመስለኝም
ሀይሌ በጣም ወጣት ልጅ አግብቶ ሚስቴናት ብሎ አስተውውቁኛል

የቁምላቸው ደጀነ ልጆች ሳያሆኑ ቁምላቸውን ያሳደገው የእኛ አባት ነው የሚሉ ይመስለኛል በትክክል ማወቅ አልችልም
የቁምላቸው ደጀኔ አንድ እህት ነበረችው ጦቢይው ደጀኔ የምትባል ሻይ ቤት ነበራት አንድ ቀንን ሻይ ልጠጣ ገብቼ መቸም አፌ አይቆኣ`ጥርም ስለፈልፍ ሻይ የምትቀዳዋ ልጅ እኔን አፉአን ከፍታ እየሰማች ያለማቆአረጥ ስካር ስትጨምር ጦቢያው አይታ አንቺ ወንበር አፈ ምንድን ነው የምሰሪ ብላ የተቆጣቻትና ያሳቀችኝ ትዝ ይለኛል:

በጣም ጉልበታም ነኝ ከሚሉት ነበርኩ አሁን ግን በጣም አስተዋይ ከሚባሉትና ከትሻናፊዎች መንደር ትስልፌያለሁ በጣም ለማስተዋል እየሞከርኩ ነው:

ሙ ደመራ ብዙ ትዝ ይለኛል አጫውተኝ ካልክ አጫውትህ አለሁ

በሉ ሰላም ዋሉ ወይም እደሩ::
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1105
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby ሙዝ1 » Sat Nov 24, 2012 3:17 pm

ሀይ ለሚቾ ... እንዴት ነህ? ይህቺን ቤታችንን ችላ አልናት'ኮ ...
ስማንጂ .... እኔማ ከአንዳንድ ጀለሶች ጋ ... በሀበሻ 16 ... 21 ... 50 እየተሰባሰብን አዲስ አበባዉ ቢር ጋርደን እንከትማለን ... እናም እነዚህ ቀናት ለኛ በጣም ልዩ ናቸዉ ... ብዙ ብዙ የማርቆስ ትዝታዎቻችንን የምንጫወትባቸዉ ጊዚያት ናቸዉ ....

ባለፈዉ .... አባ አይቸዉን አንስተን ብዙ ብዙ አወጋን ... ሳቅን .... አይቸዉ ጋቢና መነን ወደ ሗላ ... አሉ አሉ ቀዳማዊ ሀይለስላሴ ደብረ ማርቆስ መጥተዉ ... ሌላ ደግሞ አየለ ጀምብ እግርንም እንዲሁ በድርበቡ ነካክተነዉ አለፍን . .... ... ቆምጨ አምባዉ እንዲሁ ... ከዘመኑ ደግሞ በቄ ባሪያዉን ... ቆይ አንተ ግን በቄ ባሪያዉ ነህ :lol: :lol: እየዉ ሲያዉቀኝ እንደማትለኝ ነዉ .... ፖለቲካ ቤት ስለ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮነን ስታወራ የሰማሁህ መሰለኝ ... ... እናም በቄ ባሪያ ትዝ አለኝ ... ይሄ ዲፕሎማ!!! በቄን ስሰድበዉ ማለት ነዉ ...

ትንሽ ስለ አየለ ጀምብ እግር ...
አየለ ጀምብ እግር መናኸሪያ አካባቢ የሚሸከም ተሸክሞ አዳሪ ነዉ ... እናም ከእለታት አንድ ቀን ... አንድ የተረገመ ቀን አንዱ አየለ ወሸላ ብሎ ሰደበዉ አሉ ሲፈርድበት ...
አዩም ነቃ ብላ .... አይይይይይ እንደዉ ያቺ እናትህ ሚስጥር አትችል ይሄንንም ወሬ ብላ ነገረችህ? አለ አሉ ... .... እንግዲህ በዘመንኛዉ እናትክን እንትን ብየልሀለሁ ማለቱ መሆኑ ነዉ መሰለኝ ...

እስኪ ትንሽ ስለ አባ አይቸዉ የምታስታዉሰዉን ቀደድ ቀደድ አድርግልን ... :lol:
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Postby ለማ12 » Sun Nov 25, 2012 3:37 pm

ሙ አልየሁትም ነበረ ወደዚህ ቤት መምጣትህን እውነትም አሁን ጠጋ ጠጋ አልክ:

እኔ ባሪያው አይደልሁም:

ዘመዶችህን ፍሬህይወት ቸርነትን ያንገላታት የነበር ማነው ብከህ ጠይቃቸው : ከዝያ ማንነቴን ይነግሩሀል:

ቆምጬ አምባውና እኔ በደንብ እንቀራረባለን በጣም ነው የማከብረው:

ደመቀ መኮነ ይቀርበኛል አሁንም
ቢርጋርደን አልጠፋም እዚያ ወጣቶችን ሳይ በጣም እቀርባለሁ ማርቆሶች ከሁኑ

ታገኘኛለህ ያነን ባለ 3 ሊትሩን እጋብዛችሁ አለሁ : መኪኖች እቀያይራለሁ ዘበኞቹ በደንብ ያውቁኛል ሰላምታ የሚስጣቸውና የሚሳደበው ሰውዬ የቱ ነው በላቸው ::
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1105
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby ወፌ » Mon Nov 26, 2012 8:10 pm

ለማ12 wrote:ሙ አልየሁትም ነበረ ወደዚህ ቤት መምጣትህን እውነትም አሁን ጠጋ ጠጋ አልክ:

እኔ ባሪያው አይደልሁም:

ዘመዶችህን ፍሬህይወት ቸርነትን ያንገላታት የነበር ማነው ብከህ ጠይቃቸው : ከዝያ ማንነቴን ይነግሩሀል:

ቆምጬ አምባውና እኔ በደንብ እንቀራረባለን በጣም ነው የማከብረው:

ደመቀ መኮነ ይቀርበኛል አሁንም
ቢርጋርደን አልጠፋም እዚያ ወጣቶችን ሳይ በጣም እቀርባለሁ ማርቆሶች ከሁኑ

ታገኘኛለህ ያነን ባለ 3 ሊትሩን እጋብዛችሁ አለሁ : መኪኖች እቀያይራለሁ ዘበኞቹ በደንብ ያውቁኛል ሰላምታ የሚስጣቸውና የሚሳደበው ሰውዬ የቱ ነው በላቸው ::

አንዳድ ሰዎች ስለ ቆምጨ አምባው ሲያወሩ ሰማለው ለመሆኑ ይሄ ሰው ማነው?
ወፌ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 77
Joined: Fri Aug 24, 2007 4:27 pm

Postby ለማ12 » Mon Nov 26, 2012 8:46 pm

የአስር አለቃ ቆምጬ አምባው:

የደብረ ማርቆስ ውህኒ ቤት ጠባቂ የነበሩ ሲሆን እስረኛ ተቀምጦ መዋል የለበትም በማለት እስረኞቹ ስራ እንዲሰሩ በማድረግ ለመጀመሪያ ጊዜ ደብረ ማርቆስ ወህን ቤት ውስጥ የዋሻው ሚካአኤል የሚባል ቤተክርስቲያን ያሰሩ
ለዚህም ታማኝነታቸው የወረዳ: ያውራጃ አስተዳዳሪ በመሆን የሰሩና በምተጨማሪም የ ኢሰፓ ማእከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩ ሲሆን
በስልጣን ዘመናቸው ጎጃም ውስጥ ለአስተዳደር አስቸጋሪ የነበሩትን ቦታዎች ያስተዳደሩ ሲሆን ሲአስተዳድሩም በጸባይ ህዝቡን በማባበል በማስተማር በተለይም በሀማኖት በማስፈራራት የሰሩ እሳቸውም በቤተክርስቲያን ትምህርት መጥነኛ እውቀትን ያካበቱ የልጆች አባት ናቸው
ወያኔ ሲገባ ለአጭር ጊዜ ታስረው በህዝቡ ጫና በአጭር ጊዜ የተፈቱ እድሜልካቸውን ባካባቢው ወይም በመንደራቸው ህዝቡን በቅን በማገልገል የታወቁ ተውዳጅ ሰው ናቸው::
ብዙ ጊዜ እሳቸውን በቀልድ ወይም በተረት የሚአንሱ ብዙ ቢሆኑም ቀልዱ ግን የሚበልጠው የእሳቸው ያለሆነ ነው [/u] የህዝብን በደል በማናቸውም ግዜ የማይቀበሉ

ለምሳሌ በአንድ ወቅት ደብረ ማርቆስ ከተማ የኩአስ ሜዳ ሊሰራ ውሀ በትቃረጠበት ጊዜ ለረፍት መጥተው የህዝቡን ችግር ባዩ ጊዜ ሁኔታውን ከክፍለ ሀገሩ አስተዳደር በላይ በመሆን ለህዝቡ ውሀ እንዲቀርብ አድርገዋል:

ያደርጉት ነገር ብዙ ቢሆንም ለረፍት ወደ ደብረ ማርቆስ ማለትም ወደ ቤተሰባቸው ሲመጡ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ቤተ መጽህፍት ቤት በመዘዋወር ተማሪወችን እንዲያጠኑ ያስገድዱ የንበሩ:
በአሁኑ ወቅትም በደብረ ማርቆስ እየኖሩ ለተውሰኑ ድሀወች የውክልና ወይም የጥብቅና ስራ በመስራት ላይ የሚገኙ ታላቅ ሰው ናቸው ::
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1105
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby TAዛBI » Tue Nov 27, 2012 9:02 am

ለማ12 wrote:የአስር አለቃ ቆምጬ አምባው:

ሰላም ለማ

እኔ ቲን ኤጀር ነገር እያለው ቆምጫምባው ፖፑላር ነገር ነበሩ ብዙ ቀልዶች ነበሩ በቆምጫምባው

ከሰማሁት አንዱ

ቆምጫምባው አንድ ግዜ እግር ኳስ ጨዋታ ላይ በክብር እንግድነት እንዲገኙ ተጋብዘው ጨዋታውን ከተከታተሉ በኋላ ባሰሙት ንግግር ላይ በጫወታው መደሰታቸውን ገልጸው ሆኖም 22 ተጫዋቾች አንድ ኳስ ላይ መረባረባቸው አግባብ እንዳልሆነ በቅርቡ ፓርቲ እና አብዮታዊው መንግስት ለያንዳንዱ ተጫዋች አንድ አንድ ኳስ የሚያልድበትና ጨዋታው በ22 ኳሶች የሚካሄድበት መንገድ እንደሚያመቻቹገልጸው ነበር ይባላል

እንዲሁም በደርጉ የሶሻሊስት ዘመን የፖለቲካ ትምርት ሲሰጣቸው "ማርክስ እንዳለው" ሌኒን እንዳለው"እንግልስ እንዳለው" እየተባለ በተደጋጋሚ ስለሚወራ በኒህ ሰዎች ተገርመው እነዚህ የአያ እንዳለው ልጆች እንዴት የተባረኩ ናቸው ማለታቸው ይወራል

ሁሉም ቀልድ ነው መቸም እሳቸው እንዳላሉት ግልጽ ነው :: እኔ ግን እንደሌሉቹ ደርጎች ገዳይ አድርጌ አስባቸው ነበር ነገር ግን በወቅቱ ግን ምንም መጥፎ ስራ ያልሰሩ ቢሆን ነው አሁንም በወገናቸው መሀል በሰላም አገራቸው በራቦር ጸሀፊንትና በአቦካቶተንት እየሰሩ ያሉት

ሰላም
TAዛBI
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 145
Joined: Mon Dec 22, 2008 8:42 am

Postby ለማ12 » Tue Nov 27, 2012 10:36 am

TAዛ BI ሰላም ነው ?

ቆምጬ በጣም ቀልደኛ ነው ጨዋታ ሲችል ሰው አይወዳደረውም ሰወችን በጨዋታ ነው ወደ ቁምነገር የሚመራቸው:
ቅቅ 22 ኩአስ ይሰጣቸው ያለ እሱ አይደለም እውነተኛ ቀልድ ግን ልንገርህ

በጎጃም ክፍለ ሀገር 7 አውራጃዎች ይገኛሉ ታዲያ እሱ የነበርው ቢቸና ስልነበረ አውራጃዎቹ የእግረ ኩአስ ሜዳ እንዲያሰሩና ጨዋት እንዲካሄድ ታቅዶ መጀመሪያ የጨዋታ ሜዳ የሰራና የጨረሰ ይሸለማል ተባለ ይህን ለማሰራት በቅን አላልቅ ስላለ ማታ እንዲሰራ አዘዘ ታዲያ ማታ ጨለማው አላሰራ ስለአለ በዚያ የሚአልፉት መኪኖች ቆመው እንዲያበሩ አዝዞ አሰርቱአል በጣም ይስቃል ይህን አሁን ሲአስበው:

ደግሞ አንድ ጊዜ ደግሞ ማርቆስ መጥቶ ሰወች ውሀ ለመቅዳት ተሰልፈው ሲጠብቁ አየና ምንድን ነው አለ ውሀ የምትቀዳው ሰራተኛ ሰርግ ሄዳ ነው እስክትመጣ ተሰልፈው ነው አሉት:
በል ባስቸኩአይ ጥራት አለና ተጠርታ መጣች አንቺ ሰርግ እስክትበይ ሰው እዚህ ጸሀይ መብላት አለበት በይ እይስከ ምሽቱ 2 ሳት ተቀምጠሽ እንድታስተናግጅ ብሎ አዝዞ እስከ 2 ሳት ተቀምጣ ለብቻዋ ስትንቀጠቀጥ ማምሸቱአ ትዝ ይለኛል በመሰረቱ መስራት ያለባት እስክ 8 ስአት ከቀኑ ነበር:

እስከ 2 ሳት መስራቱአን በደንብ ሲቆጣጠራት ነው ያመሸውበስራው ላይ ቀልድ ቢአበዛም ቀልዱ ግን ከስራው ጋር የተዛመደ ከሆነ ብቻ ነው:
በተለይ እንዳይላልን በጣም ይቆጣው ነበር ሰው አትበድል እያለ

ሰው እንዲበደል አይፈቅድም በጣም ይቆጣል አሁንም የሚሰራው ለህብርተ ሰቡ በጣም ከፍተኛ ነው:
ሽፍቶችን በጣም ነበር የሚያባብልና ወደ ሰላም የሚመልሳቸው
ሌቦችን ስልጣን ይስጣቸው ነበር ለምንድን ነው ሲሉት በጨለማ የሚሰርቀውን በጽሀ ስታምጣው ራሱን ይፈራዋል በጣም ራሱን ይፈራዋል ዝም ብለህ ከተውከው ግን ተደብቆ መስረቁን ይቀጥላል ይል ነበር:

ጎቦ እንዳይበሉ በጣም ይከታተላቸው ነበር:
ልጆቹ ጠንክረው እንዲማሩ ቢለፋም ለከፍተኛ ትምህርት ግን አልበቁለትም:

ከሱ ይልቅ ወንድ ልጁ ሞኛ ሞኝ በጡንቻው የሚአስብ ነገር ነው : ጠፍ ነገር

ቆምጬ በጣም ታላቅ ሰው ነው ::
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1105
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby ወፌ » Tue Nov 27, 2012 10:44 am

ዋው ለማ በጣም ምስጋናዬ ይድረስህ ጥያቄዬን በሚጥም ጨዋታና ለዛ ስለመለስክልኝ:: ልጆቹ ግን ለከፍተኛ መአረግ አለመብቃታቸው ትንሽ ያሳዝናል:: በሱ ቢወጡ ምናልባት ከትምህርት ጋር ለአገር የሚጠቅም ስራ ይሰሩ ነበር::
ወፌ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 77
Joined: Fri Aug 24, 2007 4:27 pm

Postby እምቢ ለሀገር » Fri Nov 30, 2012 5:03 pm

የአያ ለማ እና የአያ ሙዝ ትዝታ-ዘማርቆስ ለዛ ባለው አንደበት ሲፈስ እየሰማሁ አላስችል ቢልኝ ነው አመጣጤ...ደግሞስ በሞጣው መንገድ ካልተሄደ በስተቀር ምድረ የኔ ቢጤ ጐንደሬ ማርቆስን ረግጦም አይደል ወደ አዲስ አበባ በየቀኑ ሚተመው...
እስኪ ከዚህ ጋር የተያያዘ ትዝታ ካላችሁ አውጉን...

ያ ባልጀራዬ ሞንሟናው ጐጃሜስ የት ሄደ??...በሉ እስኪ ሞቅ ሞቅ አድርጉት...
ሙዝነት...የሲኒማ ቤቷ ትዝታ ትመቻለች :lol: :lol: በአዲስ አበባው አማረኛሽስ ሙድ አልያዙብሽም??...እዛ ጋ..ጋ..ጋ ምናም ስትይ...ማርቆሶች ምንም አይሉሽም ነበር??

ይመቻችሁ ደርቢዎቸ :lol: :lol:
ETHIOPIA ETHIOPIA ETHIOPIA
እምቢ ለሀገር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 262
Joined: Mon Feb 13, 2012 5:08 pm

Postby *ማህደረ* » Sat Dec 01, 2012 1:08 pm

እንደ ፈራሁት ሙዝነትን እዚህ ቤት አገኘሁት :lol: አንተየዋ እንደው ደህና ነህ? :D ጨዋታ ማበላሸት አልፈለኩም ያው አንተን ሰላም ለማለት ነው የገባሁት እዚህ ....ያንን ሀሪከንን የት እንደማገኘው እስኪ ጠቁመኝ? መቸም ይህንን ሁሉ ገጽ ሳገላብጥ አልውል :( ሀሪኩ ይንን ካነበብክ ሰላም ብያለሁ

ይቅርታ ማርቆሶች :wink:
ማህደረ
*ማህደረ*
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 419
Joined: Fri Aug 05, 2005 12:56 am
Location: ethiopia

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests