ማርቆሶች ተሰብሰቡ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ሙዝ1 » Mon Dec 03, 2012 9:19 am

እምቢ ለሀገር wrote:የአያ ለማ እና የአያ ሙዝ ትዝታ-ዘማርቆስ ለዛ ባለው አንደበት ሲፈስ እየሰማሁ አላስችል ቢልኝ ነው አመጣጤ...ደግሞስ በሞጣው መንገድ ካልተሄደ በስተቀር ምድረ የኔ ቢጤ ጐንደሬ ማርቆስን ረግጦም አይደል ወደ አዲስ አበባ በየቀኑ ሚተመው...
እስኪ ከዚህ ጋር የተያያዘ ትዝታ ካላችሁ አውጉን...

ያ ባልጀራዬ ሞንሟናው ጐጃሜስ የት ሄደ??...በሉ እስኪ ሞቅ ሞቅ አድርጉት...
ሙዝነት...የሲኒማ ቤቷ ትዝታ ትመቻለች :lol: :lol: በአዲስ አበባው አማረኛሽስ ሙድ አልያዙብሽም??...እዛ ጋ..ጋ..ጋ ምናም ስትይ...ማርቆሶች ምንም አይሉሽም ነበር??

ይመቻችሁ ደርቢዎቸ :lol: :lol:


ቂቂቂ ደርቢዎች :lol: :lol: ስማ ስለ ጎንደርም የሆነ ቤት ክፈትና እንቀዳለን ... .. ከቆብ አስጥል.. እስከ ብሉኮ ... ከዞብል መዝናኛ እስከ አዘዞ ... ዞብል ስል ፋሲለደስና ቆነጃጅቶችም ሳይረሱ :wink: ..... እንደዉ የሆነ ቦታ ስለ ደብረ ብርሀን ስላሴ ስታወራ የሰማሁህ መሰለኝ :wink: ... ... አሪፍ አሪፍ ትዝታዎች አሉኝ .... ከነ ሂሩት ... አልማዝ አሁን ፈረንሳይ መሰለችኝ .... ጊዜዎርቅ (ዘፋኝ ሁና በቴሌቪዥን አይቻታለሁ) .... አስቴር ነቃጥበብ (የፍቅር አዲስ እህት አሁን አሜሪካ ነዉ ያለችዉ ....) .... እያለ ይቀጥላል ... ... ምነዉ ሴቶችን ብዛ ዘረዘርክ እንደማትለኝ ተስፋ አደርጋለሁ ...

እስኪ ደግሞ ወደ ማርቆስ ልመለስ .....

ለሚቾ ስለ ጋሽ ቆምጬ ጀምረሀል ,,,, ... ,,,, ሰዉዬዉ እጅግ የሚገርም ሰዉ ነዉ ... እንዳልከዉ ህዝብ የሚለዉ እሳቤ ልቡ ዉስጥ የገባ ነዉ .... እድሮችን ከነበሩበት ባህላዊ አሰራር ወደ ልማት ያመጣ ጎበዝ ሰዉ ነው ....

ሁሌ የማይገባኝ ግን ቆምጨ የሚለዉ ስም ትርጉሙን አለማወቄ ነዉ .... ልጁን አክሊሉ መሰለኝ የሚባለዉ ስጠይቀዉ ያሯሩጠኝ ነበረ እንጂ ቆምጬ ማለት ብሎ ገልጾልኝ አያዉቅም ... ... አምባዉ ያዉ አምባ ከሚለዉ የመጣ ይመስለኛል ... ...

ቂቂቂ በቄ ባሪያዉ ያልኩህ ያዉ እሱ ቤት የብአዴን ከፍተኛ አባላትም አልፎ አልፎ ይገኛሉ ተብሎ ስለሚታማ ነዉ ... .. ...
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Postby ለማ12 » Mon Dec 03, 2012 1:55 pm

ደግሞ አንተ ማነኝ አልክ?

በታሪኩ ወቅት ነበርክ ወይስ አጋጣሚ ነው ይህን ቃል ያልከው ?
ምን ሆነ መሰለህ የስም ጠሪያችን ነበር ስሙን ልተውና አንዲቱን ልጅ ልቡ ያስባል ግን እድሜው ገፋ ያለነበር አሁን በህይወት የለም

ሁሉ ቀን በየቤሬዱ ማብቂያ ላይ እየመጣ ይክታተላታል 1 ቁጥር ስልነበርች 1 ቁጥር ይላል ከዚያም አረጋግጦ ይሄዳል
አንድ የርሻ አስተማሪያችን ነበር ወጣት ነው ደሞ ሞደርን ነኝ ይል ነበር እሱም ይቺን ልጅ ያስባታል ሁለቱም አስተማሪወች ነቄ ብለዋል ማን እንደሚቀድም ነበር ትግሉ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

አንድ ቀን ያው ስም ጠሪያችን መጣና 1 ቁጥር ሲል የለችም የለችም አልነው የት ሄደች ሲለን የእርሻ መምህሩ ወሰዳት አልነውእሱም ሳያስበው የት እንዳለ ሳያውቅ
አየ እንደፈራሁት ! አለና ሳቅ በሳቅ አደረገንይህን ቃል ነው የተጠቀምክበት ?

*ማህደረ* wrote:እንደ ፈራሁት [ሙዝነትን እዚህ ቤት አገኘሁት :lol: አንተየዋ እንደው ደህና ነህ? :D ጨዋታ ማበላሸት አልፈለኩም ያው አንተን ሰላም ለማለት ነው የገባሁት እዚህ ....ያንን ሀሪከንን የት እንደማገኘው እስኪ ጠቁመኝ? መቸም ይህንን ሁሉ ገጽ ሳገላብጥ አልውል :( ሀሪኩ ይንን ካነበብክ ሰላም ብያለሁ

ይቅርታ ማርቆሶች :wink:
ማህደረ
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1107
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby ለማ12 » Mon Dec 03, 2012 2:32 pm

ሰላም ነው ሙ ?


ቆምጬ በጣም ከማከብራቸውና ከመውዳቸው ሰወች አንዱ ነው
ትርጉሙን አላውቀውም ግን ቆፍጣና ማለት ይመስለኛል
ትልቁ ልጁ ግዛቸው ነው ይሚባል ህዝቡ በጣም ያከብረውል ይወደዋልም


ባሪይውን አውቃለሁ ገብቶኛል ግን አይደለሁም የጶለቲካ አባላቸው አይደለሁም
ደመቅን ባህር ዳር የክልሉ ምክትል ሆኖ ነው ያስተዋወቁኝ
እኔ ብዙም ፖለትካቸውን ባልወድም እነሱ አይጤሉኝም
ከባሪያው ጋር የተገናኘነው ያያሌው የጅግሳው) አባት ሞቶ ልቅሶ ላይ ነው በጣም ነው የመቆጣው አንድ ወቅት የከፍያለው እናት አስጠርተውኝ ሄጀ እሱንም እዝያ ነበር ያገኘሁት ብዙ ነገሮችን ነግሮኝ ልጆች በጣም እንደጠሉት ነግሮኝ እኔም ተው ብዬ ነበር::


አየለን አንስተሀል በጣም ነው የሚአስቅ

አንድ ጊዜ አንድ ሰው ባላገር ነው አዉቶቢስ ተራ ሌቦች ያልችውን ገንዘብ ሰርቀውት ድንጋጩ ወግቶ ጣለውና ወየው እናቴ እያለ ሲአልቅስ በል ተው ብለን ስናባብለው ፋርፋ ይመስለኛል ጋቢውን ከሰውየው ላይ አዉልቆ መሬት አነጠፍና እርዳት ሲጠይቅ ሰው እንደ ጉድ ገንዘብ አወረደለት ታዲያ አዩ ቁጭ ብሎ ይልቅም ጀመር ምን እያደረክ ነው ተንስ አልኩት ልቁጠርለት ብየ ነው ብሎ ይሰበስባል በኪሱ ሲከት ጣለው አልኩና በረግጫ ስመታው እሱ ዛሬ ብቻ ነው ገንዘብ ያጣው እኔ እድሜልኬን ስቸገር ነው የምኖረው ታዲያ ያረቂ መጠጭ ልካፈለው እንጂ ብሎ ያሳቀን እስከ አሁን ከአእምሮየ አይጠፋም

በጣም ቀልደኛ ነበረ

ጋሽ ድልሳ ዘውዴን ታውቅዋለህ ሙ ??
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1107
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby ሙዝ1 » Mon Dec 03, 2012 4:03 pm

ለማ12 wrote:ደግሞ አንተ ማነኝ አልክ?

በታሪኩ ወቅት ነበርክ ወይስ አጋጣሚ ነው ይህን ቃል ያልከው ?
ምን ሆነ መሰለህ የስም ጠሪያችን ነበር ስሙን ልተውና አንዲቱን ልጅ ልቡ ያስባል ግን እድሜው ገፋ ያለነበር አሁን በህይወት የለም

ሁሉ ቀን በየቤሬዱ ማብቂያ ላይ እየመጣ ይክታተላታል 1 ቁጥር ስልነበርች 1 ቁጥር ይላል ከዚያም አረጋግጦ ይሄዳል
አንድ የርሻ አስተማሪያችን ነበር ወጣት ነው ደሞ ሞደርን ነኝ ይል ነበር እሱም ይቺን ልጅ ያስባታል ሁለቱም አስተማሪወች ነቄ ብለዋል ማን እንደሚቀድም ነበር ትግሉ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

አንድ ቀን ያው ስም ጠሪያችን መጣና 1 ቁጥር ሲል የለችም የለችም አልነው የት ሄደች ሲለን የእርሻ መምህሩ ወሰዳት አልነውእሱም ሳያስበው የት እንዳለ ሳያውቅ
አየ እንደፈራሁት ! አለና ሳቅ በሳቅ አደረገንይህን ቃል ነው የተጠቀምክበት ?

*ማህደረ* wrote:እንደ ፈራሁት [ሙዝነትን እዚህ ቤት አገኘሁት :lol: አንተየዋ እንደው ደህና ነህ? :D ጨዋታ ማበላሸት አልፈለኩም ያው አንተን ሰላም ለማለት ነው የገባሁት እዚህ ....ያንን ሀሪከንን የት እንደማገኘው እስኪ ጠቁመኝ? መቸም ይህንን ሁሉ ገጽ ሳገላብጥ አልውል :( ሀሪኩ ይንን ካነበብክ ሰላም ብያለሁ

ይቅርታ ማርቆሶች :wink:
ማህደረ


ለሚቾ .... ማህዲ ... ሴት ነች .... እንዳሁኑ ሳይሆን ያኔ ኮረዳ እያለች ዋርካ ላይ ስንቱን ጎረምሳ ለሀጩን አዝረብርባዋለች መሰለህ ... .... ዋዉ ማህዲና አትጥፊ በናትሽ ...


ሄይ ለሚቾ ... የአየለ ጀምብ እግር ያስቃል .... በአካልም ስለማስታዉሰዉ አሰራረቁና በርግጫ ስትመታዉ አመላለሱ ታየኝ'ኮ ....

ጋሽ ድልነሳ ዘዉዴን አዉቀዋለሁ .... ሳዉቀዉ ግን ...
1ኛ. ተስፋ ድልነሳ የምትባል ልጅ ነበረችዉ -- ምናልባት ታላቅ እህቷ ደግሞ በእምነት ድልነሳ .... ከላይ መቼ ማርቆስ እንደነበርኩ አዉርቸኻለሁ አይደል? ... ቂቂቂ ያ ወቅት እነ ተስፋም ለከተማዉ አዲስ ነበሩ .... ትንሽ ጽድት ... ዝንጥ ያሉ ስለነበሩ አይን ይስቡ ነበረ .... እንቀራረብ ነበር .... ቂቂቂ በጣም እንዳትስቅብኝ .... አስቴር ከበደን ስሰማት ተስፋ ነች ትዝ የምትለኝ .... ማታ በህበረ ትርኢት ቀርባ ነበረና ... በጠሗት ስናወራ አዳምጣት ብዬ ልደዉልልህ አስቤ ነበር ግን ባባ ሳሎን አብሮን ስለነበረ አልቻልኩም አይነት ነገር ስትለኝ ... ማማማማ ምን አይነት ኩራት እንደተሰማኝ አትጠይቀኝ ..... ማለቷ ብቻ አይደለም ... ... በአየለ ፊት ማለቷ ነዉ .... አየለ ከት/ሚኒስትሩ ፊት ለፊት ጎሚስታ ያላቸዉ እና ናፖል ሽፈራዉ የተክለሀይማኖት ቡና ቤት ልጅ በጣም ተቀናቃኜ ነበሩ ... ስለዚህ ጋሽ ድልነሳዉ ዘዉዴን ያነ በአካል ሳላዉቀዉ በልጁ አዉቀዉ ነበር ....

2ኛ. አሁን በቅርቡ ከ4 አመት በፊት ግን በስራ አጋጣሚ ተገናኘን .... ... የሆነች በሸር የተከፈተች ማይክሮ ፋይናንስና በተመሳሳይ ስም ትምህርት ቤት አለች ... ትንሽዬ ሼር ስላለችኝ ጋሽ ድልነሳዉን በመጠኑ አዉቀዋለሁ ... ....

ስለ ጋሽ ድልነሳዉ ያሰብከዉን ተናገርና በነካ እጅህ ስለ አባ አይቸዉም አዉጋን :lol: :lol: በተለይ አይቼዉ ጋቢና መነን ወደ ሗላ የምትለዉ የቀዳማዊ ሀይለስላሴ ንግግር ለምን እንደተጠቀሰችም እንዲሁ :wink:
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Postby ለማ12 » Mon Dec 03, 2012 4:33 pm

አየ እኔማ አውቄው ውሀው ደፍርሶ ነው ያለው:


የጋሽ ድልሳን ማይክሮ ፋናንስ አውቃታልሁ ብዙ ለመርዳት የሞከርኩ መሰለኝ
ዉዱ ነው የሚባል ልጅ አብሮ እንዳለ የሰማሁ መሰለኝ ምናልባት የጀን ልጅ ነው መሰለኝላወራህ የፈለኩት አሁን ስለ ጋሽ ድለሳ ነው ወንድ ልጅ አለው ያደገው ግን በጋሽ ድለሳ ሳይሆን በጋሽ ድለሳ አባት ቤት ነው ታዲያ ምን አደረገው መሰለህ በጣም ረባሽ ነበር ደግሞ መደብደብ አይችልም ጋሽ ድለሳ አባቱን በጣም ይፈራውና ያከብረዋል ታዲያ የሚአደርገው ሲጠፋው ወላጅ አምጣ ብሎ አባረረው ጋሽ ድልሳ የጠበቀው አባቴን ያመጣል ብሎ ነው ልጁ ግን ምን ሰራው መሰለህ ወደ ድብዛ መጃው ድልድዩ ስር ተቀምጣ የምትለምን ድሀ 50 ሳንቲም ሰጥቶ ይዞለት መጣ

ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

ምንዎ ነው ሲላት ጋሽ ድለሳ ልጄ ነው እየለመንኩ ነው የማስተምረው አለችው
በጣም አዝኖ ብዙ ከአለ በሀላ
ባያድለኝ ነው እንጅ ልጁስ የኔ ነው አለ

ይህ ልጅ ጋሽ ድለሳን ያልሰራው ነገር የለም በጣም ረባሽ ነበር
ስለ ጋሻ አይቸው ግን ብዙም ትዝታ የለኝም


አሁን እርገጠኛ ነኝ ታውቀኛለህ:
አጅ
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1107
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby እምቢ ለሀገር » Mon Dec 03, 2012 9:25 pm

ኧረ ሙዝነት...ደብረብርሀን ስላሴንም ታውቅልኛለህ...በል በል የማርቆስ ትዝታ ይለቅ እና የጐንደሩን ደግሞ እንቀዳለና!!
አልማዝ ያልካት ማናት? አልማዝ በርሄ ትሆን..ሂሩት ደግሞ ሂሩት ተወልደ ሳትሆን አትቀርም ቤታቸው ወደ ላሊበላ መታጠፊያ...
ግዜሽወርቅ ተስፋዬ...ልክ ነህ አንድ ካሴት ሰርታለች::ስጠው ነበርች :አንድ ራስታ አግብታ አሁን አሜሪካ ነች...(ስጠው ነበርች :wink: )...ወይ ሙዝነት! ቆባስጥልን እንዲህ እንደዋዛ...

በል ከሰሞኑ ያልከኝን ቤት እከፍታለሁ...ጋሽ ለማም ቢሆን የጐንደር ትዝታ አያጣም :lol: ...ኧር በስላሶች...አንተ ሙዝ!..ቆባስጥል?..ሆሆሆሆ...


እምቢተኛው :!:
ቆብ-አስጥል....
ETHIOPIA ETHIOPIA ETHIOPIA
እምቢ ለሀገር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 262
Joined: Mon Feb 13, 2012 5:08 pm

Postby ሙዝ1 » Tue Dec 04, 2012 1:59 pm

ለማ12 wrote:አየ እኔማ አውቄው ውሀው ደፍርሶ ነው ያለው:


ቂቂቂ ይህቺ ነገር ምን ማለት ነች? ትደጋግማታለህ :lol: ... ታሪካዊ ማእጣጧን ማለቴ ነዉ እንጂ ሀሳቡ ገብቶኛል ... አሁን አወከኝ መሰለኝ :wink:
የጋሽ ድልሳን ማይክሮ ፋናንስ አውቃታልሁ ብዙ ለመርዳት የሞከርኩ መሰለኝ
ዉዱ ነው የሚባል ልጅ አብሮ እንዳለ የሰማሁ መሰለኝ ምናልባት የጀን ልጅ ነው መሰለኝ

ያቺ ጉደኛ ማይክሮ ፋይናንስ ስትመሰረት ዳር ዳር አካባቢ ነበርኩ ... በሗላ ላይ አንድ የተጨበጨበለት የባንክ ባለሙያ ጓደኛዬ ... ... ይሄማ ምኑን ማይክሮ ፋይናንስ ሆነ .... ህጋዊ ማጅራት መቺ እንጂ ... ብሎ ሲያብራራልኝ በብላክ ኤንድ ሗይት የተጻፈዉ ሲተረተር እስከ 36% የሚደርስ ወለድ ያስከፍላል ---- ነዉ እንዴ ብዬ በጊዜዉ የነበረኝን የአክሲዎን ድርሻ አስተላልፌ ትቸዋለሁ --- ህዝቤን ጠቅሜ ካልተጠቀምኩማ ይቅር ብዬ ነዉ .... አሁን አሁን ሳስበዉ ግን እጅግ ብዙ ህዝብ ተጠቃሚ እየሆነ እንደሆነ አስባለሁ ...

ዉዱ አደገ የማይክሮ ፋይናንሷ አድራጊ ፈጣሪ ነበር .... የቦርድ ሰብሳቢም ነበር ... ... አሳዛኙ ዜና ከስራዉ ጋ በተገናኘ በተሰራ ወንጀል 6 አመት ተፈርዶበት እስር ቤት ይገኛል ... ... ልክ ነህ የደጀን ልጅና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኮምፒዉተር ሳይንስ የተመረቀ በጣም ፈጣን የቢዝነስ ሰዉ ነዉ .... ከምትገምተዉ በላይ ሀብት አካብቷል ...
አሁን እርገጠኛ ነኝ ታውቀኛለህ:
አጅ

በፍጹም አላስታወስኩህም ... ቂቂቂ

BTW, የጋሽ ድልነሳዉ ልጅ የሰራዉ ስራ በጣም ነዉ ያሳቀኝ .... ... [/quote]
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Postby ሙዝ1 » Tue Dec 04, 2012 2:09 pm

እምቢ ለሀገር wrote:ኧረ ሙዝነት...ደብረብርሀን ስላሴንም ታውቅልኛለህ...


ቀላል አዉቀዋለሁ ወዳጄ ... ደብረ ብርሀን ስላሴ ጀርባዉ እጅግ የሚወደድ የምግብ ያክል የምበላዉ አየር ነበረዉ ... ... ፊት ለፊት የአንገረብን ግድብ እያየህ .... ከጀርባህ ደግሞ የአብነት ተማሪዎች ሲማሩ የሚያወጡት ጣፋጭ ዜማ .... የራሱ ህብረ ዜማ ይፈጥራል ... ምናልባትም ከጎንህ አንዷን የጎንደር መለሎ ... ህምምም እስኪ ተወኝ ወዳጄ ... ብዙ ብዙ ማለት ይቻላል ሆድ ባዶ ይቀራል እንጂ ...
!
አልማዝ ያልካት ማናት? አልማዝ በርሄ ትሆን..ሂሩት ደግሞ ሂሩት ተወልደ ሳትሆን አትቀርም ቤታቸው ወደ ላሊበላ መታጠፊያ...

አንተ 2 ሂሩቶችን አስታወስከኝ ... አንዷ ... ወደ ድብረ ብርሀን ስላሴ ስትሄድ ዳገቱ ላይ .... አቤት አቤት ስንቱን ስንቱን ዳገት ወጥቻለሁ ጃል ... ቀይዋ እንዳልልህ ሁለቱም ብስል ያሉ ቀዮች ... ረዘም ደልደል ያሉ ... ብቸኛዉ ልዩነታቸዉ ጥርሳቸዉ አንዷ ፍንጭት አንዷ ግን ድርድር ያለ :wink: ...
ግዜሽወርቅ ተስፋዬ...ልክ ነህ አንድ ካሴት ሰርታለች::ስጠው ነበርች :አንድ ራስታ አግብታ አሁን አሜሪካ ነች...(ስጠው ነበርች :wink: )...ወይ ሙዝነት! ቆባስጥልን እንዲህ እንደዋዛ...

ቂቂቂ ስጠዉ? ከምር አሳከኝ ... ኤኒዌይ አሪፍ ልጅ ነበረች .... ማግባቷን አላቅም ነበር ... በእድሜም ካልኩህ ልጆች ትንሽ ከፍ ትላለች ...
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Postby ለማ12 » Wed Dec 05, 2012 1:29 pm

ሰላም ለሁላችሁም:

ደግሞ ደብረ ብርሀን ምን ትሰሩ ሄዳችሁ ?
በደንብ ባውቀውም
በተለይ ከ2 አመት በፊት ይመስለኛል
የገብያውን ውሀ ፋፍሪካ ለመጎብኘት ሄጃልሁ:
አውሩ ስለጎንደር ያለኝን ለማቅርብ ዝግጁ ነኝ::
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1107
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby ለማ12 » Sun Dec 23, 2012 6:12 pm

የት ጠፋችሁ ?
ወይስ በሌላ በኩል ወሬ ጀመራችሁ??ለማ12 wrote:ሰላም ለሁላችሁም:

ደግሞ ደብረ ብርሀን ምን ትሰሩ ሄዳችሁ ?
በደንብ ባውቀውም
በተለይ ከ2 አመት በፊት ይመስለኛል
የገብያውን ውሀ ፋፍሪካ ለመጎብኘት ሄጃልሁ:
አውሩ ስለጎንደር ያለኝን ለማቅርብ ዝግጁ ነኝ::
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1107
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby ገልብጤ » Sun Dec 23, 2012 6:31 pm

ውሀ ፋፍሪካ

ትርጉም
ውሀ ፋብሪካ........ :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol:
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1680
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

Postby ለማ12 » Mon Dec 24, 2012 11:16 am

ቀልቀሎ ስልቻ
አቁማዳ ይህ ሁሉ አንድ አይነት ነው


ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ


አኩአ ሴፍ የሚባል ውሀ የሚወጣው ደብረ ብርሀን ነው
ገልቡቃላት አት
ሰንጥቅ እንጂ


ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ


ገልብጤ wrote:
ውሀ ፋፍሪካ

ትርጉም
ውሀ ፋብሪካ........ :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol:
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1107
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Mon Dec 24, 2012 11:34 am

ለማ......አንድ ሰሞን የፖለቲካ አዋቂ መምሰል አምሮህ ታስራ እንደተፈታች ጊደር እምቡር እምቡር እያልህ መዘላበድህ ቀረና "የት ይደርሳል የተባለው ጥጃ ልኳንዳ ተገኘ" እንደሚባለው ባጣ ቆየኝ ሆነህ ቀረህሳ :?: :lol: :lol: ይሁና..አይዞህ :D

በል አሁን አርፈህ የሚያምርብህንና የምታውቀውን የማርቆስ ጨዋታህን ከታላቁ ሰው ሙዝ1 ጋር እዚሁ ቤት ቀጥል :D

አትጥፋ ለማለት ያህል ነው :wink: :lol:

ለማ12 wrote:ቀልቀሎ ስልቻ
አቁማዳ ይህ ሁሉ አንድ አይነት ነው


ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ


አኩአ ሴፍ የሚባል ውሀ የሚወጣው ደብረ ብርሀን ነው
ገልቡቃላት አት
ሰንጥቅ እንጂ


ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ


ገልብጤ wrote:
ውሀ ፋፍሪካ

ትርጉም
ውሀ ፋብሪካ........ :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol:
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Mon Dec 24, 2012 12:41 pm

ከሁሉም አስቀድሜ ሙዝ1ን ይቅርታ እጠይቃለሁ......ለማ የሚባለው የማያውቀውን አውቃለሁ እያለ የሚዘላብድ ውሸታም ቀላማጅ ሰው መጋለጥ ስላለበት ነው :D

ቀላማጁ ለማ12 እጅ ከፍንጅ ሲያዝ

1. ስለ ዶ/ር እሌኒ ገብረመድህን የተናገረው

ለማ12 wrote:እሳ ምንም የምትረባ ሰው አልነበርችም በርግጥ ወንዶች የበታቾቻ ምናልባት ከሳ ይሻላሉ የሚል ግምት አለኝ


በጣም ባልየ ሰው ነበረች ለሹፌሮቻ ሳይቀር በጣም ባልየ ሰው ናት አባታ ድህና ሰው ይመስልስሉ ኑሯቸውም ተራ ኑሮ ነው ነገር ግን ስለልጃቸው ሲነግሩኝ በጣም አስቀውኛል


:lol: :lol: :lol:

http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?p=466847&highlight=#466847

2. ስለምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተናገረው

በመጀመሪያ

ለማ12 wrote:ይህ ልጅ በ 1777 ርሀብ ከወሎ ከተፈናቀሉት ወገኖቻችን ከዚይም ወደ ፓዊ ከሰፈሩት ሰወች ውስጥ ነው :
ታሪኩ ይህ ነው ከወሎ ከየትኛ አካባቢ እንደሆነ አይታወቅም ከራሱ በስተቀር ::ለጥቆም

ለማ12 wrote:አንድ ነገር ትዝ አሰኘህእኝ

ተፈራ ዋልዋ ራሱን ሲክብ ያለ ዳሽን ቢራ አይጠጣም ታዲያ ምን ሆነ መሰለህ አንድ ቀን

ያንተው የ 4 ኪሎው ምሩቅ ደመቀ ቀደም ብሎ ሆዱን እንደአንተ አይወዳትም ጊወርጊስ ቢራ አስመጥቶ ሲጠጣ በድንገት ተፈራ ከመሀላችን ገባና ምን ይምጣልህ ሲባል
ያለዳሻን አልጠጣም አለ
ወዳጅህ ደመቀም የጀመረውን ቢራ ትቶ ለእኔም ዳሸን አምጣልኝ ብሎ ያሳቀኝ ትዝ አለኝ ::


:lol: :lol: :lol:

http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?p=476892&highlight=#476892

3. በተባበሩት መንግስታት የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለሆኑት ዶ/ር ተቀዳ አለሙ የተናገረው

ለማ12 wrote:ሰው ጥራ ቢሉት ራሱ መጣ ነው የሚሉት አሁን ተቀዳ ሰው መሆኑ ነው የሚቀባጥር ?
በል እዚያው ይለፍልፍ ተወው እዚህ ማምጣቱ ጥቅም የለውም ::

:lol: :lol: :lol:

http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=50049&postdays=0&postorder=asc&start=0

4. ስለቀድሞው ሚኒስትር ጁነዲን ሳዶ......ሙዝ ይሔ አንተም ትዝ ይልሀል :lol:

ለማ12 wrote:ጁነዲን አይን ውስጥ ከገባ አመታት ተቆጥሯል ግን እንዴት እንደሚገፉት መንገዱ ቸግሯቸው ነበር በነገራችን ላይ እሱም 5 ኪሎ ተመርቄአለሁ በማለት ይንቃቸዋል .: በጣምም ያከራል ብዝርዝር ስለእሱ ወደሀላ የምለው ይኖረኛል ግን ይህን ቀውስ የሚያልፈው አይመስለኝም :
መስሪያ ቤቱም በውድ ነው የተከራየው የሚል ጉቦኝነትም ስም ከሀላው የተጠነሰሰ ነገር አለበት
መልካሙን ሁሉ ::


http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?p=477791&highlight=#477791
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Postby የተሞናሞነው » Mon Dec 24, 2012 2:34 pm

ቆይ ይህ ስለ አካባቢያቸው ስለ ራሳቸው የሚጫወቱበት ቦታ ነው....እንዴው ወያኔዎች ስትባሉ....ምናለ አንድ ቦታ ብትጸዳዱ :roll: እና ቆዳው ምነው ሙዝና ጋሽ ለማ ስለተጫወቱ እንዲህ አንገበገብህና መጥተህ ተጸዳዳህ :lol: :lol: ምን አይነት ብሽቅ ነህ እንዴው .... ወራዳ የወረድ :roll: :P

ጋሽ ለማ ይህንን አህያ አትመልስለት....የማርቆስ ጨዋታህን ቀጥል :roll:
የተሞናሞነው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1129
Joined: Wed May 11, 2011 5:39 pm

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests