ማርቆሶች ተሰብሰቡ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ገልብጤ » Mon Dec 24, 2012 3:14 pm

ዳግማዊ ስታሳዝን ዋርካ ለይ በጣም ትበሳጫለህ መስለኝ :?:

ዋርካ ፖለቲካ ቤት ነው እንዴ ይህ ..እዚህ መጥተህ ከምትዘበዝብ ለምን እዛው የመልስ ምት አጸጠውም ነበር :?:
አንድ ሰው ዋርካ ፖለቲካ ቤት ስለተናገረህ ብቻ ..ዋርካ መደበሪያችንን እየዞርክ ታበክታለህ :?:
እባክህ አደብ ግዛና ስትበሳጭም በልኩ አድርገው
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1680
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Mon Dec 24, 2012 3:21 pm

ሠላም ገልቤው

እኔማ የእሱን ውሸታምነት ስላጋለጥኩኝ ደስ ብሎኛል እንጂ ምን ያበሳጨኛል :wink: ......ይልቅ አንተ ለመለሰልህ መልስ የምትለው አጥተህ ተበሳጭተህ ይሆን ይሆናል :D የአብዬን ወደእምዬ :lol: :lol: ይኸውልህ ደፈር ብለህ መልስለት

ለማ12 wrote:ቀልቀሎ ስልቻ
አቁማዳ ይህ ሁሉ አንድ አይነት ነው


ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ


አኩአ ሴፍ የሚባል ውሀ የሚወጣው ደብረ ብርሀን ነው
ገልቡቃላት አት
ሰንጥቅ እንጂ


:lol: :lol: :lol: :lol:
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Postby ገልብጤ » Mon Dec 24, 2012 3:31 pm

ይልቅ አንተ ለመለሰልህ መልስ የምትለው አጥተህ ተበሳጭተህ ይሆን ይሆናል


ቅቅቅቅ..ብበሳጭ እንኳን መልስ የሰጠኝ ቦታ ነው መመለስ ያለብኝ አይደለም እንዴ .....
አንተ እኮ ጎተራን አልፈህ መሳለሚያ መጥተህ አልነበረም መልስ ወይም ማጋለጥ የነበረበህ ..እዛው ጃስ ያለበብት ቦታ ነበር መመለስ የነበረብህ
እናም ገልብጤ ዋርካ ለይ በኒክ ኔም አይበሳጭም ...ይልቅስ ፈገግ ያደረገኝ ...
ውሀ ፋፍሪካ ..ያለት ነገር ናት
ውሀ የተፈጥሮ ነገር ሆኖ እያለ
እናም ልልህ የፈለኩት እዛው ብትመላለሱ ጥሩ ነበር ነው
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1680
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Mon Dec 24, 2012 3:37 pm

ገልብጤ wrote:ቅቅቅቅ..ብበሳጭ እንኳን መልስ የሰጠኝ ቦታ ነው መመለስ ያለብኝ አይደለም እንዴ .....
አንተ እኮ ጎተራን አልፈህ መሳለሚያ መጥተህ አልነበረም መልስ ወይም ማጋለጥ የነበረበህ ..እዛው ጃስ ያለበብት ቦታ ነበር መመለስ የነበረብህ


ገልቤው....ሌባ ተይዞ ዱላና ቦታ ይጠየቃል እንዴ :?: :lol: በተገኘበት በማንኛውም ቦታ እርምጃ ይወሰድበታል.......አይደለም እንዴ :?: ቅቅቅቅቅቅቅቅ

እናም ገልብጤ ዋርካ ለይ በኒክ ኔም አይበሳጭም ...ይልቅስ ፈገግ ያደረገኝ ...
ውሀ ፋፍሪካ ..ያለት ነገር ናት
ውሀ የተፈጥሮ ነገር ሆኖ እያለ
እናም ልልህ የፈለኩት እዛው ብትመላለሱ ጥሩ ነበር ነው


ውሀ የተፈጥሮ ቢሆንም እርሱ ሊል የፈለገው ውሀ በቦትል ማሸጊያ ፋብሪካዎችን ነው :D :D :D

መልካም የፈረንጆች ገና :!:
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Postby ለማ12 » Mon Dec 24, 2012 4:45 pm

ግልቡ አትፍረድበት:
አንድ ትዝታ ር ላጫውትህ በጣም ጊዜው የሄደ ቢሆንም

አባቴ ገብያ ሄደው ብዙ ሸቀጦች አምጥተው ማታ ማህበር ነበራቸውና ወድ ማህበራቸው ሄዱ
ይህን የተረዱ ጎረቤቶች ማታ ገብተው ሊዘርፉ እቆጥ እንደትኛን መጥተው እቆጥ እንደተኛን አንዱ ወደቀብን እናታቸን እመሀል ተኛታ ብትጮህ ሊአፍናት ሞከረ
እር ልጆችንስ አትግደል ብላ ብትግፋው እመሬት ተፈጠፈጠ አንዱ ወደ ማጀት ገብቶ ኖሮ ተንስቶ ሊሮጥ ሲል የቆመው እንጨት ግንባሩን ሲለው እር አያቦጋለ መውጫው በት ነው ያለው ትዝ አለኝና አሳቀኝ
አሁንም እዚህ መጥቶ የሚለፈው የሚሄድበት ጠፍቶት ነው ደግሞ እንደዚህ ያለውን ደንቆሮ እኤልክትሪክ ሳይጨብጥ አለቀውም:

ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ


ገልብጤ wrote:ዳግማዊ ስታሳዝን ዋርካ ለይ በጣም ትበሳጫለህ መስለኝ :?:

ዋርካ ፖለቲካ ቤት ነው እንዴ ይህ ..እዚህ መጥተህ ከምትዘበዝብ ለምን እዛው የመልስ ምት አጸጠውም ነበር :?:
አንድ ሰው ዋርካ ፖለቲካ ቤት ስለተናገረህ ብቻ ..ዋርካ መደበሪያችንን እየዞርክ ታበክታለህ :?:
እባክህ አደብ ግዛና ስትበሳጭም በልኩ አድርገው
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1103
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby ሙዝ1 » Tue Dec 25, 2012 11:02 am

ሰላም ሰላም ጎበዝ እንዴት ናችሁልኝ? ይሄ የገና ዝግጅት እንዴት እያደረጋችሁ ነዉ?
ከሀገር ዉጭ ያላችሁ ወገኖቼ መልካም የፈረንጆችና የናንተ ገና በዐል ይሁንላችሁ .... ...

ዳጊና ለሚቾ .... ኸረ ሰላም እንፍጠር .... ልዩነታችንን እንደ ኦፖርቹኒቲ እንዬዉ ... ... እንማማር ጥሩ ነዉ:: በነጻ አስተማሪ ወይንም አስተካካይ አራሚ ወንድም ተግኝቶ ነዉ:: አንዳችን ላንዳችን'ኮ ትልቅ ሀብት ነን:: ዳግማዊ ለለማ ... ለማ ለዳግማዊ ችግሮችን ማሳየትና ማስተካከል ካልቻሉ ጆርዳን ወይንም ለማቪች አሊያም ዳጊቪች ሊመጡልን አይችሉም:: ችግር የለዉም::

ወደ ቤቱ እንሂድ እስኪ ...
ለሚቾ ... ስለነ ፋሲል ካሴ ... ዘላለም ቸርነት ና ዮሀንስ አሰፋ ስጠይቅህ ጓደኞቼ ነበሩ ብለኸኛል መሰለኝ .. ... የዛ የጉልቤዉ ዘመን ከሆንክ ሰለሞን ደምሴን ታዉቀዋለህ -- -- ዘፋኝ ነገር የነበረ? የሆነ ቀን አምባሳደር አካባቢ አየሁትና የሆነ ጭፈራ ቤት ይዘፍናል የሚል ነገር ሰምቼ ነበረና እስኪ Youtube ልፈልገዉና ለለማ ልለጥፍለት ብዬ ስፈልግ .... ሌላ ሰለሞን ደምሴ የሚባል ዘፋኝ ሰማሁኝ ....

ነይማ የኔ አለም ነይማ
ነይማ ላሳይሽ ነይማ
ነይማ በረሽ አገር ላሳይሽ

የሚል አሪፍ ዘፋኝ እያዳመጥኩ ነዉ ሰምቼዉ አላዉቅም ... ... ዋዉ በጣም አሪፍ ዘፈን:: የምጠቀምበት url መለጠፍ ስላልፈቀደልኝ ነዉ ያለጠፍኩልህ ... አዳምጠዉ ደስ የሚል ዘፈን ነዉ:: "እኔ ነኝ ያለ" ከሚለዉ የአሸብር በላይ ዘፈን ቀጥሎ የወደኩት የዘመኑ ጎጃምኛ ዘፈን ነዉ::

ቆይ ግን ሁሌም ግራ የሚገባኝ የናንተ ዘመን ፍንዳታዎች ለምንድን ነዉ የማታረጁት? :wink: I know, u r early 40s ..... አጎቶቼን ጨምሮ ብዙዎቻችሁ ሁሌም የሚገርመኝ ብዙም የሚያሳጣ የእድሜ ለዉጥ ፊታችሁ ላይ አይነበብም .... ... ቂቂቂ እኛ ብዙዎቻችን መሸበትና መመላለጥ ጀምረናል:: ቀድመናችሁም ወደ ትዳር ገብተናል:: ይሄን የምልህ ለምን መሰለህ? ሰለሞንን ከረጅም ጊዜ በሗላ ነዉ ያየሁት (አንተም ሰለሞን ልትሆን ትችላለህ?) ... ምንም አይነት ለዉጥ አላየሁትም .... ድሮ የማቀዉ ልጅ ነዉ አሁንም ያየሁት:: አሁንም ሽክ ብትን ብሎ:: :lol: :lol:

ለሚቾ ሁሌም እየረሳሁት ነዉ ... እስኪ ስለ ቀለብ ልጆች አዉጋኝ ያንተ ነገር ከነዛ ጉደኛ ቆንጃጅት ልጆች አንዷ ቺኬ ነበረች እንደማትለኝ ነዉ ... በለጡ በጣም የምወዳት ዉብ ልጅ ነበረች --- የዛሬ 15 አመት ታሪክ ነዉ ማወራህ ... .. ምናልባትም ዛሬ አንቱ የተባለች ባለትዳር ልትሆን ትችላለች .... በአካል ላገኛቸዉ ከምመኛቸዉ የልጅነት አይኑካዬ ምናልባትም ቀዳሚዋ ልትሆን ትችላለች ... ታላቅ እህቷ ከሸኩ ጋ ትቀራረባለች ሲባል ሰምቻለሁ? :lol: ... አማኑኤልስ የት ይሆን ያለዉ? አማኑኤልን ሳስታዉስ ምን ትዝ ይለኛል መሰለህ .. ቦሌ አካባቢ ካሉ ምሽት ቤቶች (አይ ቲንክ ድሪምናይት ኦር ሉክ እነሱ ቤቶች አዘወትር ነበር) ... እናም ከሙዚቃዉ በላይ ዳሊጋዉ የሚል ድምጽ ይሰማኛል ... .. ይሄንን ስም በደንብ አዉቀዋለሁ .... ዳሊጋዉ ... በጣም የምወደዉ ቦታና ሚዳቋና ብሆር አደን የምንወጣበት ... ጥሩ ጥሩ የልጅነት ጨዋታዎችን የምንጫወትበት .... ፈርስ ግልቢያ የምንለማመድበት ብዙ ብዙ ከልጅነቴ ጋ የተሳሰሩ የአይምሮም .... የሰዉነት ለምጥም ትዝታዎች አሉኝና እንዴት መሀል ቦሌ ላይ ሰማሁት ብዬ ድምጹ ወዳለበት አካባቢ ስሄድ አማኑኤልና 2 በአይን የማዉቃቸዉ ሰዎች .... .... የሚገርም ገጠመኝ አወጉኝ ... ተገባብዘን ተለያየን ...:: [/url]
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Postby ሙዝ1 » Tue Dec 25, 2012 11:09 am

ለማ12 wrote:ደግሞ ደብረ ብርሀን ምን ትሰሩ ሄዳችሁ ?

ለሚቾ ስለ ደብረ ብርሀን ከተማዉ አይደለም ያወራነዉ .... ደብረ ብርሀን ስላሴ --- ጎንደር ከተማ ቀበሌ 3 ከአንገረብ ወንዝ ፊት ለፊት ተራራ ላይ ጉብ ያለ እጅግ በጣም የሚማርክ ተፈጥሯዊ ዉበት ያለዉ ቤተክርስቲያን ነዉ:: በጣም ታሪካዊም ነዉ:: ስለሱ ሰፈር ነዉ ያወራን::
በደንብ ባውቀውም
በተለይ ከ2 አመት በፊት ይመስለኛል
የገብያውን ውሀ ፋፍሪካ ለመጎብኘት ሄጃልሁ:
አውሩ ስለጎንደር ያለኝን ለማቅርብ ዝግጁ ነኝ::


ገበያዉ የሚባል ሰዉ ነዉ ባለቤቱ? ገበያዉ የሚለዉን ስም አዉቀዋለሁ .... አልመጣልኝም ...
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Postby ለማ12 » Tue Dec 25, 2012 12:11 pm

ሙ ሰላም ነው ?
አሁን የደረስክብኝ ይመስለኛል:
ጎንደር ጥሩና ታሪካዊ ሀገር ነው ደስ ይለኛል ብዙ ጊዜ እመላለሳለሁ ጎሀ ሆቴል ነው የማርፈው በጣም ደስ ይለኛል


ደብረ ብርሀን ስላሴንም በደንብ ነው የማውቃት ብዙ ደስ የሚሉ ነገሮች አሳልፌአለህ:

እኘ ደብረ ብርሀን ስትሉ ሰሜን ሸዋ መስሎኝ
አኩአአ ሴፍ ውሀ የሚወጣው እዚያ ነው ባለቤቱም
አቶ ገብያው ታከለ ይባላል በጣም እነቀራረባልን
ያነን ላይ ባልፈው ሄጅ ነበር
አሁን ግን ሸጦታል
በተረፈ የሚስቱ እህት እና እኔ ጥምቀትን ልንውል ጎንደር ተያይዘን ሄደን ነበር የያዘ ጋኔል ሳያጠምቅ አይለቅም ነው የሚሉት ጥሎብኝ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ይህን ጎረምሳ ይዘፍናል አልከኝ እሱን በደንብ ባውቀውም በጣም ስለሚፈራኝ ነው መሰል ብዙም የሚወደኝ አይመስለኝም
ከሚዘፍኑት የሚቀርበኝ ጌቴ አንለይ ነው በእኛ ጊዜ በጣም ያስቸግሩት ስለነበር እኔ አትንኩት እያልኩ እቆጣ ስለነበር ዛሬም በጣም ነው የሚቀርበኝ
ማነው ቢሉት በቀጥታ ያለማመንታት እኔን ብቻ ነው የሚናገረው:
:roll: :roll:
አሁን የልጆች አባት ሆኗል:

የጋሽ ቀልብን ልጆች አነሳህ?
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

እረ አትስጋ ምንም የለም እናታቸው ብዙ ግራና ቀኝ ትመለከት ነበር ደግሞ ወጣት ልትሆን ትሞክር ነበር::
እስኪ አገሪቱ ዋለ ሆቴል ጎን የነበርች ጎረምሳ አስብና ምን አይነትና የማን እንደነበርች ለማውቅ ሞክር:


ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

ዘላለም ቸርነት ጎረምሳ ሆኖ እኔን ግን ብዙም የማይገላምጥ ነበር ምን አልባት የህቱ ---- ስልሆንኩ ይሆናል
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ዛኣሬ ያነሳሀቸው ነገሮች ሁሉ የነበርኩባቸውና ያለሁባቸው ናቸው:
ዳሌጋው በጣም ደስ የሚል አካባቢ ሲሆን አባ አስራት ገዳም ዘወትር እሄድ ነበር:
ጫካውን ታውቀው የለ?
ለምሳም ይሁን ለመሳም አላውቅም ::

ቅቅቅቅቅ
ብዙ ነገሮች ላወራህ እሞክርና በጣም እፈራለሁ:
ቅቅቅ
በጣም ረባሽ ነበርኩ መሰለኝ:
ትንስ አርጅቼአለሁ መመልጡን የጀመርኩት ገና ድሮ ነው:


ላዛሬው በዚህ ላብቃ አትጣል ላልከው ካልነኩኝ አልነካም ከነኩኝ ግን አሁንም ወኔው እንዳለ ነው መሰለኝ አልችልም
ቅቅቅቅቅቅቅ
ሙዝ1 wrote:
ለማ12 wrote:ደግሞ ደብረ ብርሀን ምን ትሰሩ ሄዳችሁ ?

ለሚቾ ስለ ደብረ ብርሀን ከተማዉ አይደለም ያወራነዉ .... ደብረ ብርሀን ስላሴ --- ጎንደር ከተማ ቀበሌ 3 ከአንገረብ ወንዝ ፊት ለፊት ተራራ ላይ ጉብ ያለ እጅግ በጣም የሚማርክ ተፈጥሯዊ ዉበት ያለዉ ቤተክርስቲያን ነዉ:: በጣም ታሪካዊም ነዉ:: ስለሱ ሰፈር ነዉ ያወራን::
በደንብ ባውቀውም
በተለይ ከ2 አመት በፊት ይመስለኛል
የገብያውን ውሀ ፋፍሪካ ለመጎብኘት ሄጃልሁ:
አውሩ ስለጎንደር ያለኝን ለማቅርብ ዝግጁ ነኝ::


ገበያዉ የሚባል ሰዉ ነዉ ባለቤቱ? ገበያዉ የሚለዉን ስም አዉቀዋለሁ .... አልመጣልኝም ...
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1103
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby ሙዝ1 » Tue Dec 25, 2012 3:18 pm

ለማ12 wrote:ሙ ሰላም ነው ?
አሁን የደረስክብኝ ይመስለኛል:
ጎንደር ጥሩና ታሪካዊ ሀገር ነው ደስ ይለኛል ብዙ ጊዜ እመላለሳለሁ ጎሀ ሆቴል ነው የማርፈው በጣም ደስ ይለኛል


ዋዉ ምርጥ ቦታ .... ከታች ከብልኮ ጫፍ ጀምሬ ምንም አይነት ትራንስፖርት ተጠቅሜ አላዉቅም ወደ ጎሀ ሆቴል ስሄድ:: ጠመዝማዛዉን ዳገት የሚጥመዉን ነፋሻማ አየር እየተመገብኩ ነዉ ጫፍ ተራራዉ ላይ የምደርሰዉ::

በተረፈ የሚስቱ እህት እና እኔ ጥምቀትን ልንውል ጎንደር ተያይዘን ሄደን ነበር የያዘ ጋኔል ሳያጠምቅ አይለቅም ነው የሚሉት ጥሎብኝ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

ቀላል ተለክፈሀል ... ቅቅቅቅ ... በል መጥኔዉን ይስጥህ ...
ገበያዉ ያልከዉ ..... መኖሪያ ቤቱ እንቁላል ፋብሪካ አካባቢ ነዉ?

ከሚዘፍኑት የሚቀርበኝ ጌቴ አንለይ ነው በእኛ ጊዜ በጣም ያስቸግሩት ስለነበር እኔ አትንኩት እያልኩ እቆጣ ስለነበር ዛሬም በጣም ነው የሚቀርበኝ
ማነው ቢሉት በቀጥታ ያለማመንታት እኔን ብቻ ነው የሚናገረው:
:roll: :roll:
አሁን የልጆች አባት ሆኗል:


ኖ ያኛዉ ሰለሞን አይደለም የዘፈነዉ .... ሌላ ሰለሞን ደምሴ ነዉ:: ሞክሼዉ ነዉ::
ሀሀሀሀ ጌቴ አንለይን የማዉቀዉ ወንቃ ያስተምር ነበር:: እሱን ስናዬዉ አቤት ደስታችን ... ጌቴ ... የሆነ ወቅት ወደ ችግር ጎዳና እያመራ ነበር .... አምላክ ረድቶት ጥረቱም ተሳክቶለት አሁን መስመር ይዟል:: የግጥምና ዜማ ደራሲ ጓደኛዉ ማን ነበር? የኔው አካሉ? እሱን ደብረ ማርቆስ በአካል አላዉቀዉም .... አሁንም ድረስ አላዉቀዉም ... ... ግን የነ ይጥና አበራ (እስከ አዲስ አበባ የዘለቀ ጓደኛዬ ነዉ) እህት ጽጌረዳ የምትባል ጓደኛዉ ነበረች አሉ .... እናም የሆነ ዘፈን አለ ... ለሷ የዘፈነላት .... የኔ ጽጌረዳ አበራ የሚል .... ታዲያ አባ አበራ

የጋሽ ቀልብን ልጆች አነሳህ?
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

እረ አትስጋ ምንም የለም እናታቸው ብዙ ግራና ቀኝ ትመለከት ነበር ደግሞ ወጣት ልትሆን ትሞክር ነበር::

አዎ አስታወስኳት .... በጣም የሚገርመዉ በእሷ እድሜ ሞተር ባይስክል የሚነዳ ሴት አላዉቅም ነበር:: በጣም ትገርመኝ ነበር:: ቂቂቂቂ ወጣት ልሁን ማለቷን አላዉቅም .... በልጆቿ ግን እቀና ነበር::

እስኪ አገሪቱ ዋለ ሆቴል ጎን የነበርች ጎረምሳ አስብና ምን አይነትና የማን እንደነበርች ለማውቅ ሞክር:
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

ጉድ መጺሁ አለ ጉራጌ ,,,, ... ,,,
ቆይ ቆይ ጋሽ ለማ .... እዛ አካባቢ ብዙ ጎረዶች በተለያዬ ጊዜ ነበሩ:: አንተ የምትለዉ ማንን ይሆን? በነገርህ ላይ እነ ዳዊት, ወዳጄና እንዳሌ (የአገሪቱ ዋለ ልጆች) በደንብ አዉቃቸዋለሁ:: ተደባዳቢ ነገር ነበሩ:: ከእንዳሌ ጋ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ እያለ እኔ ፍሬሽ ሆኜ ተገናኝተናል::
እሽሽሽሽሽሽሽ ጎረቤት? ሀሀሀህ ጉዳይ ታዬ ቡና ቤት? ቂቂቂ ... የነ ይታያልና ሰሌ ታላቅ እህት ትሆን? :lol: :lol: እየዉ ሲያዉቀዉ .... አሁን በህይወት የለችም መሰለኝ ... ነዉ ወይንስ ትንሽ ከፍ ብሎ ያሉ ሆቴሎች እነ ትነበብ .... ወሰን የለሽ .... ምናምን ልጆች? ማን እንደሆነች አላወኩም እስኪ ጥቆማ ስጠኝ :lol: :lol:

ሀሀሀሀ የሽወርቅ ሞገስ ሆቴል ትዝ አለኝ .... አልጋ አዳር በ3 ብር ነበር .... ቀን ላይ 2 ብር .... አቤት አቤት ቂቂቂ ... ታዬ ኬክ ቤት ዘቢብ ኬክ ከወተት ጋ 1 ብር አይሞላም ነበር::


ዘላለም ቸርነት ጎረምሳ ሆኖ እኔን ግን ብዙም የማይገላምጥ ነበር ምን አልባት የህቱ ---- ስልሆንኩ ይሆናል
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

ቂቂቂ ምንድን ነዉ እንገር ጋሽ ለማ? ቂቂቂ የከተማዉ ሴቶች ያንተ ነበሩ እንዴ? :lol: ከነሱ ቤተሰብ ሚጢጢ የምትባለዋ ልጅ አዉቃታለሁ .... ቂቂቂ ልጅቷ የሰማይ ስባሪ የምትክል ስሟ ሚጢጢ ቂቂቂ .... ኦ ... ከነሱ ቤተሰብ በጣም አሪፍ የዘላለም የእህት ልጅ ማህሌት ..... አሪፍ ነበረች .... አዲስ አበባ አልፎ አልፎ ሻይ ቡና እንል ነበር::

ዛኣሬ ያነሳሀቸው ነገሮች ሁሉ የነበርኩባቸውና ያለሁባቸው ናቸው:
ዳሌጋው በጣም ደስ የሚል አካባቢ ሲሆን አባ አስራት ገዳም ዘወትር እሄድ ነበር:
ጫካውን ታውቀው የለ?
ለምሳም ይሁን ለመሳም አላውቅም ::

አባ አስራት ገዳም? ህምምም በጣም አዉቀዋለሁ ... መሰለች መልካሙን ታዉቃታለህ? :lol: :lol: አሁን ታዋቂ ሯጭ ነች .... ሀገራችንን ወክላ ብዙ ጊዜ ሩጣለች ... እናም አባ አስራት ገዳም አካባቢን ሳስብ እሷ ልጅ ትዝ ትለኛለች ...
ሆ ሆ ገዳም ሄደህም ጽም ነበር? በል በል ወንድሜ አንተ ግፍህ ብዙ ነዉ ... ዋርካን በመብረቅ እንዳታስመታት ...
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Postby ለማ12 » Tue Dec 25, 2012 4:51 pm

ሙ ከየት ልጀምርና የት ልጨራልህ?
አዎ በዚያ ሰፈር ነው እዚያ ሰፈር ወረድ ብሎ በጣም ረባሽ ልጅ ነበር አለባቸው ዉዱ ነው የሚባል ይሆን? የወታደር ልጅ ነው
ሰው አይደፍረኝም ብሎ የሰፈሩን ልጅ በሙሉ ለራሱ አድርጎ ሲታገል ወምድምህ ተው እንጂ እንካፈል ብዬ የመሪነቱን ሚና ተረከብኩ:
አባ ጎባው የሚባሉ ሰውዬ ነበሩ
ልጆቻቸው ፋናዬ ጎባው ትንሽቱ ረሳሁ ስሙአን
ደርጀ ጎባው የሚባል ወንድም ነበራቸው ረባሽ
እረ ሰንቱ ስንቱ ጉድ እኮ ነው


ያልከውን ሰፈር ደግሞ ከውሮ ትነበብ መቅድም ጋር በጣም እንተዋወቃለን ያሳደገቻቸው ሴት ልጆች ነበሩ
ሙሉጎጃም
አጀቡስ ነው የሚሉአት
መርከቤ የሚባል ወንድ ልጅም አለ አሁን አዲስ አበባ ነው ያለው ብዙ ቀን ይደውልልኛል ወይም ይመጣል
ተሰማ ዳቦ ቤት አልክ ስለዚህ አልናገርም አስደናቂና አሳዋቂ ትዝታ ስለአልኝ


ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ


የዘላለም እህት ፍረህይወት ቸርነት የምትባለው ትልቅ እህታቸው ማለቴ ነው አሁን አሜሪካ ያልች ይመስለኛል አግብታ በጣም ከምወዳቸው ሴቶች አንደኝዋ ምናልባትም የመጀመርዋ ሳትሆን ትቀራልች?
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

መሰለሽች? አንተ ልጅ እረ ተው ልረፍበት:
ቅቅቅቅቅቅቅቅ

ቀበሌ 06ና 07 መካከል ፖሊስ ጣቢያው ፊት ለፊት አንድ ጉአደኝ አለቻት ይመስለኛል

ሙሉጎጃም ትባላለች:

ታዲያ ምን ሆነ መሰለህ አሁን ጉምሩክ ትሰራለች የሆነ ነገር እርዳታ የሚሆን ነገር ሰጥተን እርዳታው ለፊስቱላ ሆስፒታል የሚሰጥ ነበር ታዲያ እባካች ሁ በንጻ ልቀቁትና ስጡአቸው ብዬ ብለምን ውጣውረዳቸውን አበዙ
ታዲያ ውረሱት ልል እዚያ ስሄድ እስዋ አወቀችኝና ሀገርህ የት ነው አለችኝ እኔም ወሎ አልኩአት.
እህ ብዙ ከአናዘዘችኝ በሀላ ለመሆኑ የራባ ጫካ ያደረከው ትዝ ይልሀል ስትለኝ የምገባበት ኣጣሁ
አሁን አንተ ለዝበህ ሰው ሆንክ ብላ ያሳፈችኝ አሁንም ያስቀኛል ግን የዚያን ጊዜውን ጥፋቴን ባይመልሰውም ለመካስ ሞከርኩ


ቅቅቅቅቅ

የሆተል ዋጋው በኛ ጊዜ ትንሽ ቢሆንም እንሄድ የነበረው
እናት አለም ዋሴ ሻይ ቤት ነበር
ዋጋውን አልናገርም ያስቃል
ቅቅቅቅ

እዚያ ገብታ የምታለቅስ ልጅ ከእናት አለም የሚደርስባት ስድብ ትዝ ይለኛል


ምን ታደርጊ መጣሽ ትላት አለች:


ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1103
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby ለማ12 » Sat Apr 06, 2013 5:17 pm

ሙ ሰላም ነው?
መግባት አልቻልክ?
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1103
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby ሙዝ1 » Fri May 17, 2013 10:38 am

ሄይ ለሚቾ ...
እንዴት ነህ ባያሌዉ?

መርከቤን ታዉቀዋለሃ? ሀሀሀ መርከቤ የኮምፒዉትር አፕሊኬሽኝ መምህር ሆኗል ... አያስቅም? ያዉ መርከቤን በደንብ ካወከዉ ማለቴ ነዉ:: ሀሀሀ .... ታናሽ ወንድሙን ታዉቀዋለህ ይሆን? :lol: :lol: ቴዲ ... ሀሀሀ የሆነ ወቅት ዋርካ ላይ የነበረ ይመስለኛል:: በጣም ደፋር የቢዝነስ ሰዉ ነዉ:: እኔና ቴዲ በጣም የሚገራርሙ ታሪኮች አሉን:: ቴዲ ቀድሞኝ ዩኒቨርሲቲ ቢገባም .... ጨርሶ ለመዉጣት አልቻለም ... የቀንም የማታም ሞከረ አልሆነለትም .... ... አምላክም እባክህ ትምህርቱን ተወዉና ማምታታቱን ሞክር ብሎ ሹክ አለዉ መሰለኝ ... በዛ መንገድ ተሳካለት ... ... በዚህ የወጣትነት እድሜዉ ባለ ብዙ ቢዝነስ ሆኗል:: የመጨረሻ ያየሁት ቦሌ የከፈተዉን ዉስኪ ቤት ለመመረቅ ሄጄ ነዉ:: ፊቱን ወደ ቻይና በማዞር እየበረታ እንደሆነ ... ቤጂንግ ቢሮ እንደተከራዬ ምናምን አይነት ቀደዳ ስንቀድ ነበር .... ያቺ ቀዥቃዣ ስዊድናዊት ናት ጀርመናዊት ሚስቱ አስሬ ጣልቃ እየገባች ብትበጠብጠንም ... ደስ የሚል ጊዚ አሳልፈናል::

አቦ ዋርካ ላይ ለመጻፍ በጣም እየተቸገርኩ ነዉ:: ፊደሉ ሁሉ ጠፍቶብኛል .... ለቀማዉ ይሰለቻል
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Postby ለማ12 » Sat May 18, 2013 9:25 am

ሙ ሰላም ነኝ:
አዎ ገብቶኛል መግባት አልችል ብለህ እንደሆነ ደግሞ የኮምፑተር ባለሙያዎች ቁቅቅቅቅቅቅ

ሰሙኑን ደግሞ የመኪና ማስተማሪያ ሰራን ብለው እየው ብለው ሰጥተውኛል:


ያው ታገሉት ምን ይደረግ የሚገርመኝ በየቀዳዳው እየገባችሁ የምጸሩት ስራ ደስ ይላል:

አቶ መርከብን ሰላም በለው ወይስ እኔ ልበለው ለሁሉም ምልክት እሰጥልህ አለሁ ማንነቴን እንዲነግርህ:
ሰሞኑን ደግሞ ድሮ ደጅ ታስጠናኝ የነበረች ወደእሱአ ዞሩ እይታገልኩ ነው ርጅናው ተጫነኝ መሰል በየቀኑ መገኘትን ቀንሻለሁ:

ቁቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ያው ትግሉ ግን ይቀጥላል ቢሆንስ ምን ይደረግ:
ካልሆነ ዝም ብሎ አይን አይኑን ማየት ነው :

ቁቅቅቅቅቅቅቅ
ሰላም ሁን አትጥፋሙዝ1 wrote:ሄይ ለሚቾ ...
እንዴት ነህ ባያሌዉ?

መርከቤን ታዉቀዋለሃ? ሀሀሀ መርከቤ የኮምፒዉትር አፕሊኬሽኝ መምህር ሆኗል ... አያስቅም? ያዉ መርከቤን በደንብ ካወከዉ ማለቴ ነዉ:: ሀሀሀ .... ታናሽ ወንድሙን ታዉቀዋለህ ይሆን? :lol: :lol: ቴዲ ... ሀሀሀ የሆነ ወቅት ዋርካ ላይ የነበረ ይመስለኛል:: በጣም ደፋር የቢዝነስ ሰዉ ነዉ:: እኔና ቴዲ በጣም የሚገራርሙ ታሪኮች አሉን:: ቴዲ ቀድሞኝ ዩኒቨርሲቲ ቢገባም .... ጨርሶ ለመዉጣት አልቻለም ... የቀንም የማታም ሞከረ አልሆነለትም .... ... አምላክም እባክህ ትምህርቱን ተወዉና ማምታታቱን ሞክር ብሎ ሹክ አለዉ መሰለኝ ... በዛ መንገድ ተሳካለት ... ... በዚህ የወጣትነት እድሜዉ ባለ ብዙ ቢዝነስ ሆኗል:: የመጨረሻ ያየሁት ቦሌ የከፈተዉን ዉስኪ ቤት ለመመረቅ ሄጄ ነዉ:: ፊቱን ወደ ቻይና በማዞር እየበረታ እንደሆነ ... ቤጂንግ ቢሮ እንደተከራዬ ምናምን አይነት ቀደዳ ስንቀድ ነበር .... ያቺ ቀዥቃዣ ስዊድናዊት ናት ጀርመናዊት ሚስቱ አስሬ ጣልቃ እየገባች ብትበጠብጠንም ... ደስ የሚል ጊዚ አሳልፈናል::

አቦ ዋርካ ላይ ለመጻፍ በጣም እየተቸገርኩ ነዉ:: ፊደሉ ሁሉ ጠፍቶብኛል .... ለቀማዉ ይሰለቻል
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1103
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby ሙዝ1 » Wed Jun 05, 2013 10:18 am

‘ሰማይ አይታረስ፣ ንጉስ አይከሰስ’ በሚተረትባት፣ ‘እናውቃለን፣ ብንናገር እናልቃለን’ በሚል የሹማምንትን በደል እያወቁ ዝምታን የመረጡ ብዙዎች በሚኖሩባት አገር ከሰሞኑ አዲስ ነገር ተሰማ፡፡ የሚፈሩ ባለስልጣናት፣ ሹማምንትና ባለጠጐች ተከሰሱ፡፡ ይሄን ተከትሎም “…ብንናገር እናልቃለን’ በሚል ስጋት የውስጣቸውን በውስጣቸው ይዘው ሲብሰለሰሉ የኖሩ ብዙዎች ‘ጥቆማ’ ለመስጠት ወደ ስነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን መጉረፍ መጀመራቸውም በየጋዜጣውና በቴሌቪዥኑ ተነገረ፡፡ ስለ ሙስና፣ ስለ ሙሰኞችና ከወትሮው በተለየ ሙስናን ለማጋለጥ መጉረፍ ስለጀመረው “ተበዳይ ህዝብ” ብዙዎች ብዙ ብለዋል፡፡ ብዙዎች ያሉትን ለመድገም አይደለም አነሳሴ፡፡ መንግስት ‘ንጉስም ይከሰሳል’ ብሎ ከማወጁና ሹማምንትን ማሰር ከመጀመሩ፤ ህዝብም አፍኖ የያዘውን የሹማምንት በደል አፍ አውጥቶ በድፍረት ማጋለጥ መናገር ከመጀመሩ በፊት ስለነበረ፣ ስላልተዘገበ፣ ስላልተነገረ ‘አየለ ጀምብ እግር’ የሚባል ሰው ነው የማወጋችሁ፡፡

የሹማምንትንና የባለጠጐችን በደል አፍ አውጥቶ ይተነፍስበት ሁኔታ የተመቻቸለት፣ አቤቱታውን ሰምቶ ፍትህ ይሰጠው አካል የተቋቋመለት፣ ‘የሚያውቀውን’ በመናገሩ አጉል ነገር እንይደርስበት ከለላ የተደረገለት … ይሄ ሁሉ የሆነለት፣ ይሄኛው ትውልድ ስለማያውቀው አየለ እናገራለሁ፡፡ አጭር፣ ወፈር ያለ፣ ፀጉሮቹ የከረደዱ፣ ደማቅ ጠይም ጐልማሳ፤ ሁለቱም እግሮቹ በዝሆኔ ያባበጡ ከሰል ተሸካሚ፡፡ የሚሰማ እንጂ የማይነበብ የሆነ የተለየ ድምጽ ያለው ተረበኛ ሰው ነበር - አየለ። መቼና የት እንደተወለደ ባላውቅም የከሰል ተሸካሚነት ኑሮ ሲገፋ በኖረበት የደብረማርቆስ ጐዳና ላይ ሞቶ እንደተገኘ መረጃ አለኝ፡፡ አየለ ከሞተ ሃያ ያህል አመታት አልፈዋል፡፡ ከእነዚህ አመታት በኋላም ግን የደብረ ማርቆስ ህዝብ አየለን አልረሳውም፡፡ ይሄም ሆኖ ግን ህዝቡ ተሸካሚውን አየለን ዛሬም ድረስ የሚያስታውሰው በጉልበቱ ሳይሆን በአንደበቱ ነው።
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Postby ሙዝ1 » Wed Jun 05, 2013 10:24 am

ለሚቾ ሰላም ነዉ? እዚህ ቤት የሆነ ወቅት ስለ አየለ ጀምብ እግር አዉርተን ነበር:: ያለፈዉ ቅዳሜ አዲስ አድማስ እትም ላይ ስለ አየለ ጀምብ እግር .... የአገር ሳቅ .... የአገር ሀቅ በሚል ፊያሜታ የሚባል ሰዉ የጻፈዉን ነዉ ፖስት ያደረኩት ....

ይቀጥላል
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests