ማርቆሶች ተሰብሰቡ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ሙዝ1 » Wed Jul 10, 2013 3:45 pm

ቀጠለ

የሌባ ጣትዋን ወደ እኛ እያሾለች ብትለውስ ‹‹እንካ ስላንትያ ጨዋታው›› ግልጽ ሆነልኝ፡፡ በልጅቷ እጅግ ተገረምኩ፡፡ ‹‹እንዴት ያለችው ጨዋታ አዋቂ ናት›› አልኩኝ፡፡ ግን ደም ፍላቴን አመጣችው፡፡
‹በእጅ ከመጣች ጥሩ› አልኳቸው፡፡ መቼም ገላጋይ አላጣም ብዬ፡፡
‹እጅ በእጅን ምን አመጣው፣ እህ እንግዲህ አገርሽ ግቢ እንጂ›
‹‹እንዴት?››
‹‹የሀገርሽ ሰዎች ዱላ ተማዘዙ፤ ተቀበል በይና አንቺም ተሰናኝው፡፡
‹እህና ለእኔ ነው ብዬ ልበለው›
‹‹ዋ! ያልተወችሽን፤ ደሞ ገብቶሻል፡፡›› ብለው እርግጠኛ ሆኑ፡፡
‹ከጀመርኩኝ ተቀምጬ አይደለም› አልኳቸው፡፡
‹‹እህ! ሽመል እናቀብልሽ፣ ትንጎራደጅ?›› የጓደኞቼ ልግጥም አበሳጨኝ፡፡ በአኳያውና በአንጣሩ ያልሆነው የልጅትዋ ወግ፤ ባላገርነቴን አነሳሳው እንጂ፣ አላቄምኩባትም፡፡ የመጣው ይምጣ...ጀመርኩ...
እኛም እናውቃለን፤ ሰዋ ሰው ጨወታ፣
ዘልቀን መጣን ʼንጂ፤ ማን አገሩን ፈታ፡፡ ብዬ አዝማሪውን- ወደ እኛ በጥቅሻ ጠርሁት፡፡
አባይ ገራገሩ፤ ፈሰስክ እንዳመልህ፣
አባይ ገራገሩ፤ ፋለልክ እንደልብህ፣
ዛሬም ጎንበስ ቀና ምንስ ታነሳለህ
የማንን ልብ ይዘህ ትጎማለላለህ፡፡
ፈረስ ተፈናጦ ነበር ጨወታችን፣
ግባልኝ ግቢልኝ ነበር ምሳሊያችን፣
ታላቅና ታናሽ ነበር ማዕዳችን፣
አስደፈርከን እንጂ ያለ አመላችን፡፡
ትዝታ ብቻ ነህ ስትፈስ ያለጓሮህ
ቆረቆረን መሬት አንተ ባገር ሳለህ፡፡
ከሰው ባዳ ገብተህ ትቀላውጣለህ
ውጣ ትወጣ እንደሁ እንደ ዘመዶችህ
ዘመቻ ከዘር ነው፣ ይታይ ወንድነትህ፡፡
እኛን እኛን ጥለህ ከቋራ መዝለቅህ
እኛን እኛን ንቀህ ጎረቤት መሄድህ
ተይዘህ ነው እንጂ ኩራቱ ከጅሎህ
ሞያ ከልብ ነው፣ ወግ ወጉን ላሳይህ
ግባልኝ ከጎጤ አለኝ የማዋይህ፡፡
መሳ ለመሳ ነው ጎጃምና ጎንደር
ሲያርስም ተከባብሮ፣ ሲዘራም ሲከምር
ተወስቶም አያውቅም፣ ሲጣላ በድንበር፡፡
ተአልጋ!! ካልሽኝማ የበላይ ይለያል
የየቅል ነው ማለት እቴ ያስነውራል፡፡
ሽልማት በሽልማት ሆኜ ስበቃ፤ ከእኛ ወገን ጭብጨባ፣ ከዚያ ወገን የሽንፈት ስሜትን አይተን ዝም አላልንም፡፡ እንዴውም ወኒያችን መጣ፡፡ ከተመልካችም ይቀጥል የሚያስብል ጭብጨባ ናኘ፡፡ እናም ጀመርኩ

ይቀጥላል
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Postby ሙዝ1 » Wed Jul 10, 2013 3:51 pm

እንኳንም ሳላየው፤ ባየውም አያምረኝ
የሰው ትራፊ አልወድ፤ እረ ሽም አይለኝ፡፡
በእርግጥ ከነካሽኝ ከደነጎርሽኝ
ልቅመሰው ምን አለ አስተርፊልኝ፡፡
እንኳንም ለአገር ልጅ ነገር ለሚገባው
እንኳን ለባላገር ፍቅሩ ለሚገለው
ይሰጠው የለም ወይ ለሚተላለፈው፡፡
ከተስፋይቱ ምድር ለመጣ እንግዳ
አሮጌውን ትቶ አዲስ ይሰናዳ
ምን ያረግልሻል ዞሮ የእኔ እዳ፡፡
‹‹እንዲያበል አንተ አለ›› ጓደኛዬ በሞራል፡፡ ‹‹በይ እንጂ፣ በይ እንጂ!!›› አሉኝ ጓደኞቼ፡፡ ‹‹ተዋት ይበቃታል›› ብል በፍጹም አላስቀምጠኝ አሉ፡፡ አዝማሪው ከዚህና ከዚያ ማዋጋቱ ስለተመቸው፤ ሽልማቱም ይዥጎደጎድለት ጀምርዋል፡፡ ታዳሚው በጨዋታችን ተደስትዋል፡፡ እቴ ንገረኛይቱ ግን በስሱ ጨለም ጨለም ያለ ፈገግታዋን ታሳያለች፡፡ ሆድ ለሆድ፣ እጅግ ዘልቀናል እኔ እና እስዋ፡፡
ያላሳቡ ነዋሪ፣ ስጦ ይጠብቃል፤
ያላሳቡ ገፊ፣ ዘመዱን ይገላል፤
‹‹ተʼቆላው ነኝ›› ብሎሽ ተቤቴ ሰንብቷል፡፡
ቅልውጥ አይደለም፣ ልማዱን ያድርስ፤
‹‹ጦሜን ሰንብቼልሽ!›› በግድፍቱ ልርከስ፡፡
የሰው ቤት እንጀራ ያጠግባል ከራስ
የለመዱት እህል አይጥም እንደ አዲስ
አየሁን አያውቅም በቃኝ አይል ከርስ፡፡
ያʼባልሽ ታማሚ፣ ታንቺ ሲያደርሰው፣
ከራርሞ ሲመጣ፣ ወገቤን ሚለው፤
አይደለም ህመሙ፣ አይደለም ውጋቱ፤
‹አላርስም!!› የሚልሽ፣ ደክሞ ጉልበቱ፡፡
እህሌን ሳስፈጨው መጅን የገፋበት፤
‹‹ባለ ብዙ ሞያ፣ ባለ ብዙ ስራ›› ሲል የከረመበት፡፡
ህሙም እኔው ነኝ፤ ህመምም የለበት
ምሴን ስጭኝና ከቤትሽ ልውጣለት፡፡
...ተሰናኘሁት ይደረፋው!! ከተስፋይቱ ምድር እንግዶች አባላት መልክቱ በትክክል ግልጽ ያልሆነ የጭብጨባ ስሜት ተደመጠ፡፡ ሴቲቱ በተንቀለቀለ አስተያየትና ፍጥነት ወደ እኔ መጣች፡፡ ጓደኞቼ የሚመጣውን ስለሚያውቁ አመጣጥዋን አይተው ገለል አሉላት፡፡ እኔም ብድግ አልኩኝ፡፡ እጅዋን ከፍ ከፍ አድርጋ፤ በወኔና በስሜት.......‹‹ባላገር›› አለችኝ፡፡ ‹‹ባላገር›› አልኳት፡፡ ከት ብላ ስቃ እኔንም አሳቀችኝ፡፡ ተቃቅፈን... ግብዣው ጦፈ፣ ጨዋታው ደመቀ፣ ጎጃም እና ጎንደር(መሳ ለመሳ) የነበረው አቀማመጣችንን ትተን፤ ቅልቅል ሆነና ሌቱን ግጥም ስንሰጥ፤ ግጥም ስንቀበል ነጋ፡፡ ባላገር እንዲህ ነው፡፡ (ወደ አዝማሪው ቤት ከገባን ሰዓት ጀምሮ በደረት ኪሴ በያዝኳት የመቅረጸ ድምፄ ያስቀረሁት የአዝማሪ ቤት ጨዋታ ነው)
ምስጋና፡- ‹‹የገጠር ወግ ፍለጋ›› አዝማሪ ቤት
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Postby ፓን ሪዚኮ » Thu Jul 11, 2013 12:14 am

ሠላም ሰላም መንቆረሮች ....ቤታቹህ : ፉከራቹህ እና ሽለላቹህ ሁሉም በጣም ደስ ይላል :: በሉ እንግዲህ በርቱ እኔም "አሻ በል ገዳዬ !" እያልኩ እቀበላቹሀለሁ ::ፓኑ አባ ፈርዳ
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ለማ12 » Sun Jul 21, 2013 12:40 pm

ሙ ሰላም ነው?


ወይ ትዳሪቱ አለ ያገሬ ጎበዝ በየአዝማሪ ቤቱ ሆነ አዳሩ?
ቻይ ምድር ነው ያለው በል እስቲ ታገለው

በርበሬ ዱቄት አይሆንም ቂጣ

ፍቅር እንዴት ነሽ ጠብ እስኪመጣ
ትብሏል እኔ የለሁበትም ትዳሩ ትዳር እንዲሆን በሳቱ መሰብሰቡ የሚከፋ አይመስለኝም


ሪዚኮ አንተ የእኛን ፍከራ ከምትገመግም አንተም ፈክር እንጂቁቅቅቅቅቅቅቅ

ሰላም ሁኑልኝ::
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1105
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby ለማ12 » Tue Aug 06, 2013 4:54 pm

ሙ ሰላም ነው?

አዳሩበአዝማሪ ቤቱ ሆኖ ነው የጥፋችሁት?


በሉ አትጥፉ::
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1105
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby ሙዝ1 » Sat Aug 10, 2013 10:16 am

ለማ12 wrote:ሙ ሰላም ነው?

አዳሩበአዝማሪ ቤቱ ሆኖ ነው የጥፋችሁት?


በሉ አትጥፉ::


ሰላም ለሚቾ .... እንዴት ነህ ወዳጄ? ምን አሁን አሁንማ እርጅና መጣና ጉድ ሆንኩልህ እኮ .... እንደያኔዉ ቢሆን ኖሮ አርብ ምሽት ከዳትሰን እስከ ካሳንቺስ ስናካልል ነበር የሚነጋዉ ... አሁንማ ልጆች ወለድንና ጫወታዉም ... መዝናናቱም ከነሱዉ ጋ ሆነ ... ርግጥ ነዉ አልፎ አልፎ ጎራ ማለቱም አልቀረም ... ቢሆንም ግን በድሮዉ ፓሽኝ መሄድ ቀርቷል .... ያኔ እናቴ አንተ ጨፍረን ሸልመን ... ትርፍ ተዝናኝ ሴቶችንም ጠልፈን ነበር የምንገባዉ .... ,,, ... አዝማሪዎቹም ሲያዩን ገና የነገ እቁባችን ሞላች ይሉ እንደነበረ ሰምቻለሁ ... ...

ከቅድሙ አሁን ትንሽ ደስ አለኝ
ሙዘይድ አካሌ መጣ መሰለኝ ....

ሙዘይድ አንበሳዉ ይመጣል ብለሽ
የሰራሽዉ ዶሮ እንዳይበላሽ ...

ሙዘይድ ሙዙካ
ትወዳለህ አሉ ማታ ነካ ነካ ..

እስኪ ጎራ እያልን እንጨዋወር አትጥፋ ...
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Postby ሙዝ1 » Sat Aug 10, 2013 10:30 am

ፓን ሪዚኮ wrote:ሠላም ሰላም መንቆረሮች ....ቤታቹህ : ፉከራቹህ እና ሽለላቹህ ሁሉም በጣም ደስ ይላል :: በሉ እንግዲህ በርቱ እኔም "አሻ በል ገዳዬ !" እያልኩ እቀበላቹሀለሁ ::ፓኑ አባ ፈርዳ


ፓኑ አሄሄ .... አሁን አንተ ነህ የምትቀበል ... ዳርክን ይዘህ ታየን እንደሆነ እንጂ ቂቂቂ ...
ለሚቾ ፓኑ አባ ፈርዳ ማለት ወረ ጃርሶ .. ... የጎሀ ጽዮን አነበሳ ነዉ .... ፍልቅልቅ ላይ ከሚመሽጉት ሽፍቶችም አንዱ ነዉ:: .... ያገሬን ነጋዴ የያዛትን ጥሪት ከሚዘርፉት ባለ ነፍጦች ጎራ የሚመደብ ታሪካዉ ጠላታችን ነዉ ቂቂቂ ቆይ ብቻ እንገናኝ ... አንዴ ክረምት ከርሜ ወደ አዲስ አበባ ስመለስ የተሳፈርኩባት የአያቴ ኢነትሬ ኳትሮ መኪና ላይ አስወርደዉ የዘረፉን .... በመዝረፍ ቢያበቁስ? ዘፈን ዝፈኑ ተብለን .... እኔ (ያኔ 15 አካባቢ ነኝ እድሜዬ) ሹፌሩና ረዳቱ እየተቀባበልን በዛች ዉብ ጨረቃ ያዘፈኑንን አልረሳዉ .... ለነገሩ ፈሪ ናቸዉ .... ፊታችሁን ወደ ጋራዉ ዙራችሁ ዝፈኑ ብለዉን እኛም እየተቀባበልን አንዴ አሸበል ገዳዬን ... አንዴ እምቡ በይ እምቡ በይን ... አንዴ ሻሻረፈረፈን .... ከነ እስክስታዉ እያስነካን ስንል ቆየንና ደከም ሲለን የእስክስታዉ አካል አስመስለን ... በርከክ አልንና ወደ ሗላ ተለጥጠን ስንዘፍን እነ አጅሬ የሉም .... እኛም ዝፈኑ የተባልነዉ የማምለጫ መንገዳቸዉን እንዳናየዉ እንደሆነ ገባን እየተሳሳቅን .... የተመታነዉን ቦታ እያሻሻን ... ጎሀ ጽዮን ገባን ...

ፓኑ ላዉራ ካለ ስለ አምራቾች .... ከነ ግብጦዉ ሊያወጋህ ይችላል ... ተዉ አትቀስቅሰዉ የአብቹን ታሪክ ከጉጉት ከሚጠብቁት መካከል ነኝና ያንን ይጻፍልን ... እዚህ ስራ ስንፈታ ብንመጣ መች አነሰንና ...

መልካም ጊዜ
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Postby ለማ12 » Sat Aug 10, 2013 5:33 pm

አይ ሙ:

ምኑን ትዝ አሰኘህኝ ያቺን በርሀ በግራቸው ከቆረጡት ጎበዞች አንዱ መሆኔንስ ታውቅ ነበር?


የሚገርምህ ያገሬ ገበሬ ሰዎቹን ሁሉ ግልገሊቱን ሱሪ ሳይቀር ሲአስወልቃቸው እኔ ውንድምህ ያቺን ውሀ ተሻግሬ ስለነበር እየአቅራራሁ ከነጠቅላላ ሱሪዬ እነ ሪዚኮ ሰፈር ገባሁ:

የሪዚኮን ወገኖች ወንድ ወንድ ስምስልባቸው ከሁአላዬ እነ ጋሽ ዮሴፍ ርቃናቸውን መጥተው አይ ጎጃም አሰኙኝ:


ቁቅቅቅቅቅቅቅቅ

እር ስንቱ አለፈ እድሜም እንደዚሁ ይሄዳልመሞትሽ ነው አለ ያ ጎበዝ ነገም ይሞታል:ናእስኪ አጫውቱኝ:


ሰላም ሁኑልኝ!
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1105
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby ሙዝ1 » Mon Aug 12, 2013 2:54 pm

ለማ12 wrote:
ምኑን ትዝ አሰኘህኝ ያቺን በርሀ በግራቸው ከቆረጡት ጎበዞች አንዱ መሆኔንስ ታውቅ ነበር?


መቸም እንደነ ፍቅር እስከመቃብሮቹ ሰብለና በዛብህ የአባይ ድልድይ ከመገንባቱ በፊት የሲኦል ግርማ ያለዉን የአባይ በርሀ እንዳላቋረጥክ ርግጠኛ ነኝ :lol: .... አዎ በዚያ ወቅት ደብረ ማርቆስ አልነበርኩምና ከዝና ያለፈ አላዉቀዉም ... ... የካቲት / 83 ....

የሚገርምህ ያገሬ ገበሬ ሰዎቹን ሁሉ ግልገሊቱን ሱሪ ሳይቀር ሲአስወልቃቸው እኔ ውንድምህ ያቺን ውሀ ተሻግሬ ስለነበር እየአቅራራሁ ከነጠቅላላ ሱሪዬ እነ ሪዚኮ ሰፈር ገባሁ:

የሪዚኮን ወገኖች ወንድ ወንድ ስምስልባቸው ከሁአላዬ እነ ጋሽ ዮሴፍ ርቃናቸውን መጥተው አይ ጎጃም አሰኙኝ:


ቁቅቅቅቅቅቅቅቅ

እር ስንቱ አለፈ እድሜም እንደዚሁ ይሄዳል

መሞትሽ ነው አለ ያ ጎበዝ ነገም ይሞታል:

ናእስኪ አጫውቱኝ:


ሰላም ሁኑልኝ!


ዘርዘር አድርገዉና እናዉጋንጅ የምን ጥግ ጥጉን መሄድ ነዉ አለ ያ ሰዉዬ :lol: :lol: :lol:
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Postby ፓን ሪዚኮ » Sat Aug 17, 2013 9:25 am

ሰላም መንቆረሮች ! ምንም እንኳን ከከተማችሁ ወጣ ብትልም : እስቲ ስለ "አዴት "ከተማ የምታውቁትን አውጉኝ ...:: እዚህ በእት የሚያስቸግር ከሆነ በግል መልክት ላኩልኝ ::ስለ ትብብራቹህ በቅድሚያ ከፍ ያለ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ::
ፓኑ አባ ፈርዳ
ጎሀጺዮን
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ሙዝ1 » Sun Aug 18, 2013 8:17 am

ፓን ሪዚኮ wrote:ሰላም መንቆረሮች ! ምንም እንኳን ከከተማችሁ ወጣ ብትልም : እስቲ ስለ "አዴት "ከተማ የምታውቁትን አውጉኝ ...:: እዚህ በእት የሚያስቸግር ከሆነ በግል መልክት ላኩልኝ ::ስለ ትብብራቹህ በቅድሚያ ከፍ ያለ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ::
ፓኑ አባ ፈርዳ
ጎሀጺዮን


ፓኑ ታላቅ ሰዉ .... እንዴት ነህ ወገኔ? መጽሀፉ ምን እየደረሰ ይሆን? መቸም አብቹ ወደ አዴት መሰረት አለዉ እንዳትለኝ ቂቂቂ

አዴት ከደብረ ማርቆስ ይልቅ ለባህርዳር ነዉ የምትቀርበዉ ምናልባት የባህርዳር ልጆች ካሉ ሊያወጉን ይችላሉ ... ... ከስም ያለፈ በጭራሽ አላዉቃትም .... ለስራህ የሚጠቅምህ ከሆነ ግን ... ... የፍላጎትህን ትኩረት ንገረኝና መረጃዎችን አሰባስቤ ልልክልህ እችላለሁ .. ...
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Postby ፓን ሪዚኮ » Mon Aug 19, 2013 11:47 am

ሙዝ1 wrote:
ፓን ሪዚኮ wrote:ሰላም መንቆረሮች ! ምንም እንኳን ከከተማችሁ ወጣ ብትልም : እስቲ ስለ "አዴት "ከተማ የምታውቁትን አውጉኝ ...:: እዚህ በእት የሚያስቸግር ከሆነ በግል መልክት ላኩልኝ ::ስለ ትብብራቹህ በቅድሚያ ከፍ ያለ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ::
ፓኑ አባ ፈርዳ
ጎሀጺዮን


ፓኑ ታላቅ ሰዉ .... እንዴት ነህ ወገኔ? መጽሀፉ ምን እየደረሰ ይሆን? መቸም አብቹ ወደ አዴት መሰረት አለዉ እንዳትለኝ ቂቂቂ

አዴት ከደብረ ማርቆስ ይልቅ ለባህርዳር ነዉ የምትቀርበዉ ምናልባት የባህርዳር ልጆች ካሉ ሊያወጉን ይችላሉ ... ... ከስም ያለፈ በጭራሽ አላዉቃትም .... ለስራህ የሚጠቅምህ ከሆነ ግን ... ... የፍላጎትህን ትኩረት ንገረኝና መረጃዎችን አሰባስቤ ልልክልህ እችላለሁ .. ...
ሰላም ሙዛችን...የአቢቹን መጨረሻ ሳፈላልግ ..በአዴት ከተማ መሰነባበቱን የሚጠቁም መረጃ አገኘሁ ...ለነገሩ ወደ "አመዳሚት" ሲያልፉ ነው መሰለኝ ...ብቻ ከዚህ በፊት "አዴት' የምትባል ከተማ በጎጃም ምድር መኖሯን እንኳን ሳልሰማ ፈረንጆች ክበው ጽፈዋት ሳይ ገረመኝ:: የማወቅ ጉጉቴም ጨምሮ ሳጣራ "የራስ ሀይሉ ተ/ሀይማኖት ተወዳጅ ከተማ እንደነበረች ..ፈረንጆችን ከደብረ ማርቆሱ ቤተመንግስታቸው ይልቅ በአዴት መቀበልና ማስተናገድ ይወዱ እንደነበር ሌላ ያገኘሁት ነገር የለም ...ታውቂ ደራሲዎቻችን እንኳን ስለዚች ድንቅ ከተማ አንድም ነገር ጽፈው አያውቁም ...እስቲ የምትችሉትን ስለ "አዴት "በአዴት ከተማ አድባርና አምላክ ስም አጫውቱኝ :;
ከማክበር ጋር
ፓኑ አባ ፈርዳ
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ለማ12 » Mon Aug 19, 2013 4:49 pm

ሙ ሰላም ነው?


ዳር ዳር አልክ ነው የምትለኝ ታዲያ ዳር ዳሩን ነው እንጂ መሀሉማ ይውጣል:ቁቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

ሙ በጣም ነው ይምፈራው በጣም ረብሽ ነበር መሰለኝ:


አሁን ግን በጣም ጨዋና ሽማግሌ ሆኜ በጣም ጨዋ ሰው ሆኛለሁ ግን አያምኑኝም ባለፈው ሰለከንቲባው ስናንሳ ምኑን ያህል እንዳሳቀኝ ታውቃለህ?
እንደአልኩህ አማኑኤል ተገናኝተን ስናወራ ለመሆኑ አንተ እንደዚህ ትለዝብና ሰው ትሆናልህ ብሎ ያሰበ ሰው ነበር አለኝ እኔም በጣም አዝኜ በጣም ተሰማኝ አሁን እዚያ አካባቢ ስሄድ ትላልቅ ሰወችን እየፈለኩ እጫወታለሁ:
በጣም ደስ ይለኛል:
ክ3 አመት በፊት ይመስለኛል ማርቆስ ተቀምጬ ስጫወት

ዶክተር ስንታየሁ ነው አሉ የሚሉት የትምህርት ሚንስተር የነበረ ነው አሉ ካፍ የወደቀ ጥሬ ነው የሚሀል ሰወች ሊአከብሩት ሸር ጉድ ሲሉ ወንድምህ ምን አልኩት መሰለህ በል እባክህ ብዙ የምንጫወተው ስላለ ፈቅ ብለህ ተቀመጥ ብዬው ቁጭ አልኩ ሰወችም ደንግጠው አንተ ይህ ጥጋብህ አሁንም አለቀቀህም ብለው ተቆጡኝ:

ስለዚህ ሳወራ በጣም ነው የምጠንቀቀው ሰው እንዳላስቀይም ደግሞ አስቀይሜ ይሆናል በሚል እፈራለሁ::ለዚህ ነው ጎን ለጎን የምሄደው?
እንዴት እስከአሁን አጎቶችህ አላወቁኝም??


ተመሰገን ነው::


ርዚኮ አዴት ደግሞ ምን ፈለክ ከአንድ አመት በፊት አዴት የሄድኩት ሰከላ የሚሉት ሀገር አባይ የሚመንጭበትን ለመጎብኘት ነው:
አዴት የድሮ ከትማ ናት ከጎጃም ውስጥ ደንበኛው ነገር የሚገኘውም እዚያ ነው:


ቁቅቅቅቅሰላም ሁኑልኝ::
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1105
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby ለማ12 » Wed Aug 28, 2013 3:55 pm

በወቅቱ የጉርምስና ወቅት ነበር ታዲያ በዚያን ወቅት ሴቶቹ ሁሉ ቀሚሳቸውን በስትሁአላቸው ቀደው ነበር የሚመጡት ታዲያ አንድ ቀን አስተማሪያችን ሲአይ በጣም ቅር አለውና የሚከተለውን ትዛዝ አስተላለፈ:


አሁን በእረፍት ሳት አንድም ሴት ልጅ የተቀደደ ቀሚስ ለብሳ ባያት የመጨረሻው ነው ብሎ አዎጀ ታዲያ እረፍቱ እስኪደርስ ድረስ ሴቶቹ ቀሚሳቸውን ለመስፋት መድፌ ለመዋስ ትምህርት ቤቱ ቀውጢ ሆነ :
በመጨርሻም
አንዲቱን ኮረዳ ከተማሪው ፊት አውጥቶ ቀሚሱአን ከሁአላ ገለጠ አድርጎ እስት እግዚያብሄር ያሳይሽ ይህ ጎረምሳ ትምህርቱን ይማር ወይስ ያንቺን ነገር ይመልከት አለና በሳቅ ገደለን
ይህን ያደረገ ማን ነበር የትስ ትምህርት ቤት ነበር ?

ደብረማርቆስ ውስጥ?
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1105
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby ለማ12 » Tue Sep 10, 2013 4:39 pm

ለሁላችሁም 2006 መልካም ዘመን ይሁንላችሁ !
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1105
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests