ማርቆሶች ተሰብሰቡ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ለማ12 » Mon Oct 14, 2013 4:54 pm

ሰላም ሰላም ሰዎችሰላም ነው ሙ?
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1103
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby ሙዝ1 » Wed Nov 06, 2013 8:29 am

ሰላም ሰላም ለሚቾ ... እንዴት ነህ ወዳጄ? ተጠፋፋን አይደል .... :: ምነዉ ወሬ አለቀብን እንዴ? መቸም የአምራቾችን ጸበል የቀመሰ በለዛ ወጎችን መዳከሙ እሙን ነዉና እስኪ ቀዳዳዉን ረጨት ረጨት አድርገዉ ...

እዚህች ቤት ዉስጥ የሆነ ቀን ስለ አደም ልጆች አንስተህ ነበር ,,, ምናልባትም አንዱ ጓደኛህ ነበር ... ,,, አንሻ ከ2 ሳምንት በፊት በአጋጣሚ ተገናኝተን ልታገባ እንደሆነ አጫዉታኝ መጥሪያ ወረቀትም ሰጥታኝ ነበር ... ያዉ የኔ ነገር እርጅናዉ እየተጫነኝ ነዉ የት እንደጣልኩት አላወኩም ይሄዉ ሰርግና ሞት አንዴ ነዉ ቢባልም ሳልሄድ ቀረሁ ... ... ሰርጉም እዚህ አዲስ አበባ ሂልተን አዲስ ነበር .... የጎጃም ጭፈራ እንዴት አምሮኝ ነበር መሰለህ? አመለጠኝ ... ...

ከምር ግን ሰርግ'ኮ የትም ቢደገስ እንደ ማርቆስ አይደምቅም .... ... ካለምንም ባንድ ሙሉ ሌሊት ጠላችንን እየለጋን ጭፈራዉን ... ሽለላዉን .... ስናስነካዉ ማደር .... በጠሗትም ተነስተን የሆማ አበባዬ እያልን ወደ ሆማ ቆረጣ ... ሀሀሀሀ ድፍድፍ በዋንጫ ተደርጎ የሆማዉን ዛፍ የመምታት ባህልም አለ አይደል? ሁሉም ባገር ላይ ያምራል ባክህ ... ... ባለፈዉ አንድ ወዳጄ እዚሁ አዲስ አበባ ሰርግ ደግሳ ነበር ... ምድረ ጎጃሜ ዉስኪያችንንን እየቀነደልን ስናስነካዉ ነበር ምናልባት ልጅቷንም ልታዉቃት ትችላለህ .... በላይነሽ አቦዴ ትባላለች .... ደብረ ማርቆስ ቀበሌ 10 ... አሁን አፍሪካ ህብረት ነዉ የምትሰራዉ .... ከኔ ጋ እንኳን የምንትዋውቀዉ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ እያለን ንዉ ... ... የሆነዉ ሆኖ ስናስነገርጠዉ ብናመሽም የልባችን አልደርስ ብሎ ጓደኞች ሰብሰብ ብለን ወደ አዝማሪ ቤት ሄደን የቀረዉን እዛዉ ተወጥተን ወደየ ትዳራችን ተበተንን ....
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Postby ለማ12 » Wed Nov 06, 2013 7:14 pm

ሙ ሰላም ነው?

እናንተ ስታረጁ እኛ ምን እንበል ?


የጋሻ አደም ልጅ አገባች ነው የምትለኝ

ማንላታቸው ጠቀለሉአት?

እኔ በዚያን ወቅት ማለትም በወጣትነተ አብዝቸው ነው መሰለኝ አሁን ብዙም መጠጡን አልደፍርም ይህን ጎጃሞች በጠላ ምትክ ውስኪውን ሲአፈሱት እየታዘብኩ ዝም ብየ ነው የማያቸው :
አዎ የጋሻ አደም ልጆች በመጠኑም ቢሆን እንቀራረብ ነበር በተልይም

ዘመንና አብዱ

ግን ሁሉቱም አሁን ያው እንደምታውቀው የሉም:
ትላልቆቹ
እንድሪስና መሀመድ ናቸው ያሉት ከዚች ውሮበላ በተጨማሪ ማለተ ነው:

በጣም የምወደው ዘፈን ሳይሆን ፉከራ ነው በጣም ነው ደስ የሚለኝ:

አሁንማ ጎጃሞች አቶ ገተን ነው በየሰርጋቸው የሚያዘፍኑት
የእሱ ዘፈን ባይጥመኝም:
በነገራችን ላይ እናቱ በጣም ዘፋኝ ናቸው አሁን ዘፍነህእው መሞትህ ነው ይሉታል:

እስኪ አምራቾች ሰፈር ያደረጋችሁትን አምጣና አውራኝ:


በተልቸቼ በጣም ነው ትዝ የምትለኝ በጣም እቀርብ ነበር
ያ የተነከረና የተቀቀለ ባቄላ ትዝ ይልሀል?


ቁቅቅቅቅቅቅ
ቦቀልት ነው የሚባለው?

ሙ ካስተማሪወች ጋር ስንጠጣ የሚቆጣኝና የሚሰድበኝ ማን እንደነበረ ታውቃለህ?ጋሼ አበባ አላምረው ነበትር የጋሽ አእምሮ የልጅ ባል:

አንተ የደረስክበት አይመስለኝ በጣም ሀለኝኣ ደግሞ ጋሽ ምኑዬ(ቁራ) ነበር አሁን እዚህ አዲስ አበባ ነው ያለው: ሰላም አልለውም የኮራሁ ይመስለው ይሆን ?

አቶ ደመቀንስ ታውቀዋለህ?


ያውስትራልያ በግ ነበር የምንለው በጣም አለውደውም አንድ ቀን በሽጉጥ አስፈራርቶኝ በጣም ስቄበታለሁ:
በጣም ባልዬ ነበር:

ያንበሳ የጽፈት መሳሪያ መደበርንስ ታውቀዋለህ?

ቀስ እያልኩ እኔነቴን ልንገርህ እንJ እስከአሁን ልታውቀኝ አልቻልክም:

በረግጥ አንተ በነበርክበት ወቅት አልነበርኩም:
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1103
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby ወሮበላው » Fri Nov 08, 2013 9:17 am

ሰላም ሰላም ማርቆሴዎች እንዴት ናቹሁ ???
ታላቁ ሙዝ እና አቶ ለማ የማርቆስ ወግ አድርታቺሁት የለ እንዴ ... ጠላ ቤት አስመሰላቺሁት እኮ ..... ::
ማርቆስ በቅርቡ አንድ የቤተሰብ ቪዲዮ አይቼ ፎቅ በፎቅ ሆናለች ጥሩ ጥሩ መዝናናኛዎች ተከፍተውባታል አሉ .....
እኔ ያኔ ተማሪ ሆኜ ክረምትዋን ማርቆስን ከ አብማ እስከ ውሰታ ስንፈላሰስባት ነበር የማሳልፈው ... በዋላ በዋላ ግን ጉርምስና ሲመጣ ብዙ አልስበኝ አለ ::
አያቶቼ ውሰታ ወንዝዋን ተሻግሮ ነው ሚኖሩት .. 2 ወር ክረምት ሀይለኛ ጎጄ ሆኜ ነው ምመለሰው ..... በቃ እንደተመስኩ የሰፈር ልጆች ለተወሰኑ ቀናት ሙድ ይይዙብኛል .... ስናገር ... ዋአ ... አበዛለው .... ስምል .... እናትህ ??? ትሙት !! .... ብቻ ምን አለፋቹ በሁለት ወር ውስጥ ሀይለኛ ጎጄ ሆኜ ነው ምመለሰው .... እስኪ ከነ ትዝታዎቼ እመለሳለው
Man United Forever
ወሮበላው
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 841
Joined: Sun Oct 17, 2004 10:52 pm
Location: united states

Postby ለማ12 » Fri Nov 08, 2013 5:17 pm

ደግሞ አንተ ማነኝ አልክ ወሮበላ?


ወሰታ ዘመዶች አሉኝ ነበሩኝ አልክ
ጉድ ሳይሰማ ክረምቱ አይጠባም ነው የሚሉት
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1103
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby ለማ12 » Fri Nov 08, 2013 5:43 pm

ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1103
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby ሙዝ1 » Tue Nov 26, 2013 9:27 am

አያ ለማ12
እንዴት ሰንብተሀል ወዳጄ .... ወሮበላዉ የጥንቱ በላ ወግ አምታና እና ቧልት!!!

ለሚቾ ሰማኸኝ የሚባለዉን ዘፋኝ ብዙም አይስበኝም ... ይልቅ ልጅቷ እንዴት ታምራለች ጃል .... ሀሀሀ ... መቀመጫዋስ ቢሆን? ኸረ ፊቷስ?

በጣም የወደድኩት ዘፈን

http://www.youtube.com/watch?v=DZaWJrAOZ9w

ይሄንን ነዉ ... አሪፍ ፍቅርን በባህላዊ መንገድ የሚገልጥ ዘፈን ...
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Postby -...- » Thu Nov 28, 2013 7:20 am

አንቺዬ ትመጪ እንደሆን ስራው ባል(በአል) ይሁን
አንተዬ ትመጣ እንደሆን ስራው ባል ይሁን
በስራ በስራ ነጠላ ልበሺ
የባል መደረቢያ እኔ አለሁልሽ

ቪዲዮውን በጣም ወደድኩት : ሙዝ እግዜር ይይልህ በትዝታ ሮኬት አበረርከኝ :: የአላሙዲ ሀብት ቢኖረኝ ዛሬዉኑ በፕራይቬት ጄት ማርቆስ ደርሼ ስጨፍርና ሳስጨፍር አድር ነበር :: በርሜል ካቲከላም ይታዘዛል :: አይ ጎጃም አይ እምዬ አይ ጨዋታ አይ እስክስታ ኑሮን ያወቅንበትና ባለን ተደስተን የምንኖር ጎጃሜዎች ነን ብል ስህተት አይሆንም ሌላውን ዝቅ ማድረጌ ሳይሆን የጎጃምን እውነታ መናገሬ ነው

እስኪ ስም ጥሩሉልኝ የኔ አለም
ከጎጃም በላይ ሀገር አለ ወይ
ለማሩ ወለላ የኔ አለም ለጤፉ ማማር
ጎጃም መፈጠር

እዩልኝ አቧራው ሲጨስ
http://www.youtube.com/watch?v=7kfdiQ4-Od8
ሞቼ እየተነሳሁ ልሙት እንደገና
አንድ ሞት ላገሬ አይበቃትምና
-...-
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 401
Joined: Thu Feb 09, 2012 8:36 pm

Postby ለማ12 » Thu Nov 28, 2013 5:34 pm

ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1103
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby ለማ12 » Fri Dec 06, 2013 5:09 pm

ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1103
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby ዲጎኔ » Sun Dec 08, 2013 2:29 pm

ሰላም ለሁላችን
ማርቆሶች/ጎጃሜዎች እንደምን ከረማችሁ?የውቅቱ የሀገራችን የፖለቲካ ትኩሳት እንዴት እየተሰማችሁ ነው::በከተማ/ብሄር በተከፈቱ አምዶች አልፎ አልፎ ስገባ ማርቆስ /ጎጄዎች አምድ ዛሬ ብቅ ብያለሁ::በቅርቡ ወልቃይቶች በአውስትራሊያ ያከሄዱት ስብስባ የዋርካው ወገኔ ተነስ ሲዘግብ የዋርካ ብእረኛ ቦቹ ያልተጠበቀ አባባል:-ወልቃያት ጎንደር ከፋ ሳንል በአንድነት ወደጋራ ጠላታችን ወያኔ እናትኩር ብሏል ድንቅ! የነበላይ ዘለቀ ወኔ ከጎጃም የበቀለ የት ደረሰ? በራሴ በጋብቻ በሞረቴነት በጋራ ከጎጄዎች ጋር የምገፋ ስለሆነ እዚህ ብሳተፍ ተገቢ ነው::ሰሞኑ የኩናማ ኑዌር ከፊቾ ልጆች ናይሎቲክ መነሻ ብለን የህዝቦቻችን ፍልሚያ እንዴት እንደግፍ እያልን ስለሆነ በናይሎቲክነት ልሳተፍ? የወያኔው ርኩስ መሪ መፈክር የአባይ/አክሱም ጉዳይ ለከፊቾ ምኑ ነው ካልያዛኝ::አፍሪካን ሊመግብ ይችላል የተባለለት የአባይ መፍለቂያ ለጦቢያ ህዝቦች የጋራ ትግል የበለጠ እንዲሳተፍ እጃችሁ ከምን እላለሁ?
ዲጎኔ ሞረቴው የግዮን/አባይ መነሻ በማየቱ የሚደሰተው ከባህርዳር ተሀድሶ ማህበር

-...- wrote:አንቺዬ ትመጪ እንደሆን ስራው ባል(በአል) ይሁን
አንተዬ ትመጣ እንደሆን ስራው ባል ይሁን
በስራ በስራ ነጠላ ልበሺ
የባል መደረቢያ እኔ አለሁልሽ

ቪዲዮውን በጣም ወደድኩት : ሙዝ እግዜር ይይልህ በትዝታ ሮኬት አበረርከኝ :: የአላሙዲ ሀብት ቢኖረኝ ዛሬዉኑ በፕራይቬት ጄት ማርቆስ ደርሼ ስጨፍርና ሳስጨፍር አድር ነበር :: በርሜል ካቲከላም ይታዘዛል :: አይ ጎጃም አይ እምዬ አይ ጨዋታ አይ እስክስታ ኑሮን ያወቅንበትና ባለን ተደስተን የምንኖር ጎጃሜዎች ነን ብል ስህተት አይሆንም ሌላውን ዝቅ ማድረጌ ሳይሆን የጎጃምን እውነታ መናገሬ ነው

እስኪ ስም ጥሩሉልኝ የኔ አለም
ከጎጃም በላይ ሀገር አለ ወይ
ለማሩ ወለላ የኔ አለም ለጤፉ ማማር
ጎጃም መፈጠር

እዩልኝ አቧራው ሲጨስ
http://www.youtube.com/watch?v=7kfdiQ4-Od8
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby ገልብጤ » Sun Dec 08, 2013 3:09 pm

አሻማ መናፍቅ ዲጎኔ
እኔ የምለው ግን ስንት ብሄር ደክለሀል

ገልብጤ ሞረቴው ...መናፍቁ ዲጎኔ የናይሎቲክ ብሄሮችን ከደከለበት ወዲያ ማዶ
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1680
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

Postby ዲጎኔ » Mon Dec 09, 2013 1:29 pm

ሰላም ማርቆሶች
ምነው ድምጻች ጠፋሳ! አስቴ ጠላ ጠጣን ዳንግላ በግሩም ምንቸት አብሽ በላን አሁን በወያኔ አፕርታይድ ግፍ ለሚሰቃዩ ይጦቢያ ህዝቦች አይፈይድምና የህዝቦችን ትግል የሚደግፍ ወግ አምጡ! መሸወዱ ይብቃ እኒያ ወንድማማቾች ጎጄዎች አቶ ምንውየለት ባንኩ አጠገብ በፎቶኮፒ የተጀመረ ቢዝነሳቸው ወደስታር ቢስዝነስ ሲያድግ እርጉሙ ወያኔ ያደረሰባቸውን አትርሱ ዳግም አትታለሉ::ሙሉጌታ ጎጄው ብቻ ወያኔን ጉድ ያደረገ የአዲግራት መድሀኒት ፋብሪካን በጋራ ከፍተው ሁውላ በወያኔ ጌቶች ቀጨን ትእዛዝ ድርሻውን ወስዷል ወንዳታ::
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby ለማ12 » Mon Dec 09, 2013 3:42 pm

ሰላም አቶ ዲጎን:

አሁን መጥፎ ልታናግረኝ ነው እንጂ
እነዚህ እዚህ ላይ ለመጥቀስ የሞከርካቸው ሰዎች እኔ ከዎያኔ ይሻላሉ የሚል ግምት የለኝም:

በየአካባቢው ወያኔ አሻንጎሊቶችን ፈጥሮ ሀገሪቱን ተጫወተባት ህዝቡንም ለስቃይ ዳረገ
አቶ ዲአጎን እውነቴን ነው የምልህ እኛ እንደምንለው ወያኔ ከትግራይ የመጡ አረሞች ብቻ አይደሉም በየቤቱ ያሉ ጅቦች ናቸው
22 አመት ንግድ የሚባል በሀገሪቱ የለም ዘረፋ እንጂ ስለዚህ መወገድ ያለበት በየቦታው ያለው ጅብ ጭምር ነው

እስኪ እዚህ ላይ ልታነሳቸው የሞከርካቸው ሰዎች ለሀገሩም ሆነ ለህዝቡ ይህን አደረጉ በለኝ


እናንተ እንደምትሉት ስዬ ከታምራት ይብሳል ምክንያቱም ትግሬ በመሆኑ ማለት አልፈልግም ምክንያቱም ፍርድ በግዚያብሄርም ዘንድ ያስጠይቃልና ነው ስዬም ሆነ ታምራት የዝንጀሮ ቆንጆ ናቸው ስለዚህ ማንም ከማን አይሻልም


ታምራት እኮ ነው ሀረር ወርዶ ጨርሱት ይህን ህዝብ ብሎ ገደል ያስጣለው
ታዲያ ስዬ ቢሰርቅ ከዚህ የባሰ ምን አደረገ እዚህ ላይ መልካም ሰው ነው ለማለት ሳይሆን ሁሉም ጅብ ነው ለማለት ነው
እውነት እልህ አለሁ ሁሉንም ያገሬ ድሀ ህዝብ ያውቃል እኛ እፊቱ ቆመን አናላውስህም እያልነው እንጂ
ስለዚህ ከፊቱ እንወገድለት ሰው ከሆንም ለጥፋታችን ይቅርታ እንጠይቅ አለዚ ይህ ወጣት ራሱ መንገዱን ፈልጎ ይውጣ አናደናቅፈው ነው እያልኩ ያለሁት:


እስኪ እነጌቱ ገለቱም ሆኑ
እነምኑየለት አጥናፉ ይህን ለዚህ መከረኛ ህዝብ ሰሩ በለኝ::

ወያኔ እንደሚለኝ ለሀይሎም ሀውልት አሰራ እንዳትለኝ አደራ::


እስኪ 1 ጥያቄ ልጠይቅህና የትግራይ ክፍለ ሀገር ድሀ ህዝብ ምን አጠፋ የማይካድ ነው ትንሽ አረሞች ከውስጡ በቅለዋል ታዲያ እሱ ምን ያድርግ:
ሰዎች ልጅ የሚወልዱት ይህን ይሆናል ብለው ነው?
የኤርትራን ክፍለሀገር ህዝብ ለዚህ ሁሉ መከራ የዳረገው ማነው?
ኢስያስ ብቻውን ነው?
በውጭ የሚኖረው በሽታ አይደለም ?
ዛሬ ኢሳያስ ነው ለዚህ ያበቃህ እያሉ ያሾፉበታል:
እስኪ የወያኔ ደጋፊ ትግራይ ከፍለሀገር ውስጥ አድዋን ጨምሮ ይህ ነው የሚለኝ ሰው አለ የትኛው? የት ? ማን?
እዚህ በውጭ የሚገኝ የወያኔ ደጋፊ ነኝ ባይ አይደለም ትንሽ ጥቅም ያገኘሁ እየመሰለው ሀገር እያጠፋ ያለው::

እባካችሁ ይህን መከረኛ ህዝብ ከሰሜን እስከ ደቡብ ብ
ከምስራቅ እስከ መእራብ ያለውን አትንኩት ችግሩ የሚአሰቃየው ይበቃል::
ስለዚህ ስንጽፍ ይህን ንመከረኛ ህዝብ የሚነካ አንጻፍ እኛው እንሰዳደብ

ሌላ ላይ ያልኩህ ለማናደድ አይደለም እናውቅልህ አለን እያልን የምንዘፍን ሰዎች ብንጠፋለት ይህ መከረኛ ህዝብ እፉ ይል ነበር:
ስለዚህ እባካችሁ ይህን ወጣት አገር የለሽ አናድርገው ዝም እንበል መንገዱን ፈልጎ ይወአ ከተቻለም አጥፍተናል ይቅርታ እንበል::


የመጫዎቻ ቦታችንን የቦለትካ አደርኩት.:
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1103
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby ሙዝ1 » Mon Dec 09, 2013 3:50 pm

ሰላም ዲጎ ታላቁ ....
አሁን እያነሳኸዉ ያለኸዉ ሀሳብ ድንቅ ነዉ:: ሁሉም ኢትዮጵያዊ በሁሉም ሀሳቦች ላይ ካለምንም ልዩነት መቀጠል ብንችል መልካም ነዉ:: ነገር ግን ይህ ሀሳብ በተአምር ተግባራዊ ሊሆን አይችልም:: ጎጃም ዉስጥ በፖለቲካ ሁሉም አንድ ሊሆን አይችልም:: የአመለካከት .... የነገሮች ተሞክሮ ... ነገሮችን የምናይበት አተያይ .... ይለያያል:: ጎጃም ዉስጥ አምርሮ ኢህአዴግን የሚጠላ ...... ከልቡ የሚያፈቅር .... ለጥቅም የቀረበ ..... ግድ የለሽ አቋም ያለዉ ..... አለ:: ምንም ይሁን ምን ግን እኛ ጎጃሜዎች ነን:: ጎጃሜነት ከጊዚያዊ የፖለቲካ ልዩነት በላይ ነዉ::

በዚህ ፖለቲካዊ እይታ እኔና ለማ12 በጣም በጣም ሩቅ ነን:: ሁሉም እንደሚያዉቀዉ እኔ ቀንደኛ የኢህአዴግ ደጋፊ ነኝ:: በፍጹም አንዱም ስብሰባዎች ላይ ተገኝቼ ባላዉቅም:: የየትኛዉም የፖለቲካ ፓርቲ አባልም አይደለሁም:: ለማ12 አቋሙን እናዉቀዋለን:: ተቃዋሚ ነዉ:: ግን አንተ እስከገባህበት ድረስ አብረን በፍቅር እየተጫወትን ነዉ:: ወደፊትም እንጫወታለን:: እኛ ጎጃሜዎች ነን:: ከሀይማኖትም .... ከፖለቲካ አመለካከትም በላይ የሆነ የሚያስተሳስረን ነገር አለ:: ማንም አይነግረንም:: ጠንቅቀን እናዉቀዋልን::
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 2 guests