ትልቅ እርዳታ ፈልጋለው

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ትልቅ እርዳታ ፈልጋለው

Postby ጉዳይ » Mon Jun 25, 2012 9:40 pm

ውድ ኢትዮጵያዊያኖች ሰላምታዬ ይድረሳችው እያልኩኝ ይቺን ችግሬን የሆነ መብቴ ብትፈልጉልኝ በማለት መጥቻለው;; የችግረኛ ልጅ መሆን መቼም አለምታደል ቢሆንም ጠንክረው ከሰሩ ሰው መሆን ይቻላል ብዬ አምናለው:: እኔም የደሀ ልጅ እንደመሆኔ ያገኘውትን ስራ በመስራት ቤተሰቦቼን ለመርዳት ደፋ ቀና እላለው:: ቤተሰቦቼም በከፊልም ቢሆን ከችግራቸው ተላቀው እፎይ ብለው መኖር ጀምረዋል:: ድሮ ድሮ ጓደኛ የምላቸው ሰዎች ነበሩ እኔ በየዋህነት እቤቴ እያመጣው ስጋብዛቸውና በችግራቸው ለመድረስ የተቻለኝን ሳደርግ ብዙ ቆይቻለው:: እነሱ ግን ምን እንዳደረኩዋቸው አይታወቅም ጥምድ አድርገው ይዘውኝ በጀርባየ የተለያዩ ወሬዎችን በማውራት ሰላም እየነሱኝ ይገኛሉ:: ይሄንን ስላቹ የራሴን ደብቄ እንዳይመስላችው እውነቱ ይሄ ነው ስራ ሰርቼ ከመግባት ሌላ ነገር አላውቅም:: ግዜ ሲኖረኝ ከነዚ ልጆች ጋር አሳልፍ ነበር:: አሁን ግን በከተማው የማውቀው ኢትዮጵያዊ ሁሉ አያናግረኝም ምን አውርተው እንደሆነ አላውቅም:: ከነሱ መሀል አንደኛውን መንገድ ላይ አግኝቼ ባናግረው ጭራሽ ለሰላምታም ዘግቶኝ አለፈ:: እነሱ ይቅሩ የኔን ላይፍ በጀርባዬ እያወሩ በጥብጠውኛል:: ያለ ብሄሬ ብሄር ይሰጡኛል የተቸገረ ብረዳ ጉረኝ ይላሉ ብቻ እንዲሁ እየተከታተሉ ምንም ጥፋት ሳይሆርብኝ ሰላሜን ነስተውኛል, ምን ባደርግ ያሻለኝ ይሆን :?: :: እነሱን አጥፍቼ እራሴም ከማጥፋቴ በፊት ምክራችሁን ለግሱኝ::
ጉዳይ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 5
Joined: Mon Jun 25, 2012 9:15 pm

Re: ትልቅ እርዳታ ፈልጋለው

Postby ፊሊፖስ » Mon Jun 25, 2012 11:18 pm

ሰላም ወንድሜ!

በጣም አዘንኩ; እምባዬም ዱብዱብ አለ:: :( ይህ የተለመደ ነገር ሆኗል:: ሲደርስብን አይታወቀንም; ምን አድርጌ ቢሆን ነው እያልን እራሳችንን እስከመጠራጠር ሁሉ እንደርሳለን:: አዎ! ጥሩ ስታደርግ የሚያሽሟጥጡ: መጥፎ መጥፎውን የሚመልሱ አይጠፉም:: በዚህ አትገረም; በነርሱም ላይ አትናደድባቸው; ዲያብሎስ ስራውን እየሰራ ነው:: ለምን ይህን ትሰራላችሁ? ምን አደርግኩዋችሁ? ብለህ እራስህን አትጉዳ: እንዲያውም ለነርሱ እዘንላቸው:: ከሰላምታ ውጭ ግኑኝነትህን አቁመህ ጸሎት ከማድረግ ሌላ መቆጨት አያስፈልግም::

ንጉሥ ዳዊት ይህን ብሎ ነበር:

"ጽድቅን ስለ ተከተልሁ፥ በበጎ ፋንታ ክፉን የሚመልሱልኝ ይጠሉኛል
አቤቱ፥ አንተ አትጣለኝ፤ አምላኬ፥ ከኔ አትራቅ።
አቤቱ መድኃኒቴ፥ እኔን ለመርዳት ፍጠን"

መዝ.38 ሙሉውን አንብበው::
A QuEstion oF BalAnCe

Image
ፊሊፖስ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 123
Joined: Thu Nov 08, 2007 12:16 pm

Postby ጉዳይ » Tue Jun 26, 2012 3:20 am

ወንድሜ ፊሊፖስ ስለወድማዊ ምክርህ ምስጋናዬ ለማቅረብ እወዳለው:: ተግባራዊ ለማድረግም እሞክራለው:: ለዳቢሎስ ፀሎት እንጂ ሌላማ ምን ያሸንፈዋል ብለህ ነው::
ጉዳይ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 5
Joined: Mon Jun 25, 2012 9:15 pm

Postby ካለድ » Tue Jun 26, 2012 8:18 am

ጉዳይ .....ያሄን ያህል መጨነቅ አስፈላጊ መስሉ አያታየኝም አንተ ስለ እርስህ ኑረ እንጂ ሰው አለ አላለ ለምን ቦታ ትስጣለህ '''ሀበሻ ለ እራሱ ሳያኖረ ስለ ሰው ሲኖረ ሳያኖረ እየሞተ ነው'''
ካለድ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 599
Joined: Sat Jan 06, 2007 4:11 pm

Postby ወለላዬ » Tue Jun 26, 2012 4:18 pm

""አንድ ሰው በተሻለ ህይወት ላይ ሲደርስ እውነተኛ ጠላቶችና ሀሰተኛ ወዳጆች ያፈራል"" የሚባል አባባል አለ ይሄንንም ማወቅ አለብህ
ደሞም አትበድል እንጂ በመበደልህ እራስህ መልሰህ በራስህ መጉዳት አይገባህም:: እናም ዘና በል:: በደፈናው ሁሉም የጠሉህም አይምሰልህ የጥቂቶች የፈጠራ ወሬ ሊሆን ስለሚችል ታገስ::
ሁሉም ሰው ይውደደኝ ብለህም አጠብቅ በዚህ አለም ብዙ የተለያየ አስተሳሰብ ያላቸው ሰዎች መኖራቸውን አትዘንጋ. ...
ወለላዬ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 403
Joined: Wed Jan 26, 2005 11:20 am
Location: united states

Re: ትልቅ እርዳታ ፈልጋለው

Postby ገደል » Tue Jun 26, 2012 4:31 pm

ጉዳይ wrote:ውድ ኢትዮጵያዊያኖች ሰላምታዬ ይድረሳችው እያልኩኝ ይቺን ችግሬን የሆነ መብቴ ብትፈልጉልኝ በማለት መጥቻለው;; የችግረኛ ልጅ መሆን መቼም አለምታደል ቢሆንም ጠንክረው ከሰሩ ሰው መሆን ይቻላል ብዬ አምናለው:: እኔም የደሀ ልጅ እንደመሆኔ ያገኘውትን ስራ በመስራት ቤተሰቦቼን ለመርዳት ደፋ ቀና እላለው:: ቤተሰቦቼም በከፊልም ቢሆን ከችግራቸው ተላቀው እፎይ ብለው መኖር ጀምረዋል:: ድሮ ድሮ ጓደኛ የምላቸው ሰዎች ነበሩ እኔ በየዋህነት እቤቴ እያመጣው ስጋብዛቸውና በችግራቸው ለመድረስ የተቻለኝን ሳደርግ ብዙ ቆይቻለው:: እነሱ ግን ምን እንዳደረኩዋቸው አይታወቅም ጥምድ አድርገው ይዘውኝ በጀርባየ የተለያዩ ወሬዎችን በማውራት ሰላም እየነሱኝ ይገኛሉ:: ይሄንን ስላቹ የራሴን ደብቄ እንዳይመስላችው እውነቱ ይሄ ነው ስራ ሰርቼ ከመግባት ሌላ ነገር አላውቅም:: ግዜ ሲኖረኝ ከነዚ ልጆች ጋር አሳልፍ ነበር:: አሁን ግን በከተማው የማውቀው ኢትዮጵያዊ ሁሉ አያናግረኝም ምን አውርተው እንደሆነ አላውቅም:: ከነሱ መሀል አንደኛውን መንገድ ላይ አግኝቼ ባናግረው ጭራሽ ለሰላምታም ዘግቶኝ አለፈ:: እነሱ ይቅሩ የኔን ላይፍ በጀርባዬ እያወሩ በጥብጠውኛል:: ያለ ብሄሬ ብሄር ይሰጡኛል የተቸገረ ብረዳ ጉረኝ ይላሉ ብቻ እንዲሁ እየተከታተሉ ምንም ጥፋት ሳይሆርብኝ ሰላሜን ነስተውኛል, ምን ባደርግ ያሻለኝ ይሆን :?: :: እነሱን አጥፍቼ እራሴም ከማጥፋቴ በፊት ምክራችሁን ለግሱኝ::

አንተ ካልከው ተነስተን ጉዋደኞችህ በሙሉ ተሳስተዋል አንተ ብቻ ልክ ነህ:: እንድንልህ ፈልገህ ከሆነ: ተሳስተሀል:: የምትለው ነገር እውንት ከሆነ እራስህን መርምር:: ምናልባት ችግሩ አንተ ዘንድ ሊሆን ይችላል
ገደል
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 489
Joined: Sat Jan 02, 2010 12:03 am

Postby ጉዳይ » Tue Jun 26, 2012 5:19 pm

ሰላም ውድ ወገኖች ካለድ, ወለላዬ, ገደል

የሰጣችሁኝ አስተያየት እጅግ ጠቃሚ ነው ምስጋናዬ ይድረሳችው:: የሚገርመው እኔ ይሄ 2012 ከገባ ሁለት ስራ በሳምንት ስድስት ቀን ከመስራት ሌላ ሰውን የማስቀይምበትም ግዜ የሌኝም:: የት አግኝቼ ላስቀይማቸው ወንድሜ ገደል ባለኝ ግዜ እየደወልኩኝ የጠፋውት ስራ ስለበዛ ነው ሰላም ናችው ወይ ብዬ እጠይቃለው:: ግማሾቹ ስራም አይሰሩም እንግዲህ እኔ የምሰራበት ቦታ አስገብቻቸው ሁሉ ሳምንትም ሳይሰሩ ነው የወጡት:: ለማንኛውም ስለ አስተያየታችው ምስጋናዬ ይድረሳችው እንደናንትም አይነት ቅን አስተሳሰብ ያለው ሰው በውጭው አለም መኖሩ እራሱ በቂ ነው::
ጉዳይ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 5
Joined: Mon Jun 25, 2012 9:15 pm

Postby ሳምራውው33 » Tue Jun 26, 2012 6:04 pm

ጉዳይ wrote:ሰላም ውድ ወገኖች ካለድ, ወለላዬ, ገደል

የሰጣችሁኝ አስተያየት እጅግ ጠቃሚ ነው ምስጋናዬ ይድረሳችው:: የሚገርመው እኔ ይሄ 2012 ከገባ ሁለት ስራ በሳምንት ስድስት ቀን ከመስራት ሌላ ሰውን የማስቀይምበትም ግዜ የሌኝም:: የት አግኝቼ ላስቀይማቸው ወንድሜ ገደል ባለኝ ግዜ እየደወልኩኝ የጠፋውት ስራ ስለበዛ ነው ሰላም ናችው ወይ ብዬ እጠይቃለው:: ግማሾቹ ስራም አይሰሩም እንግዲህ እኔ የምሰራበት ቦታ አስገብቻቸው ሁሉ ሳምንትም ሳይሰሩ ነው የወጡት:: ለማንኛውም ስለ አስተያየታችው ምስጋናዬ ይድረሳችው እንደናንትም አይነት ቅን አስተሳሰብ ያለው ሰው በውጭው አለም መኖሩ እራሱ በቂ ነው::

እኔም አለሁልህ ወንድሜ :!: :!: :!:
ሳምራውው33
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 530
Joined: Thu Jun 21, 2007 12:23 am

Re: ትልቅ እርዳታ ፈልጋለው

Postby እምቢ ለሀገር » Wed Jun 27, 2012 2:08 pm

ጉዳይ wrote:ውድ ኢትዮጵያዊያኖች ሰላምታዬ ይድረሳችው እያልኩኝ ይቺን ችግሬን የሆነ መብቴ ብትፈልጉልኝ በማለት መጥቻለው;; የችግረኛ ልጅ መሆን መቼም አለምታደል ቢሆንም ጠንክረው ከሰሩ ሰው መሆን ይቻላል ብዬ አምናለው:: እኔም የደሀ ልጅ እንደመሆኔ ያገኘውትን ስራ በመስራት ቤተሰቦቼን ለመርዳት ደፋ ቀና እላለው:: ቤተሰቦቼም በከፊልም ቢሆን ከችግራቸው ተላቀው እፎይ ብለው መኖር ጀምረዋል:: ድሮ ድሮ ጓደኛ የምላቸው ሰዎች ነበሩ እኔ በየዋህነት እቤቴ እያመጣው ስጋብዛቸውና በችግራቸው ለመድረስ የተቻለኝን ሳደርግ ብዙ ቆይቻለው:: እነሱ ግን ምን እንዳደረኩዋቸው አይታወቅም ጥምድ አድርገው ይዘውኝ በጀርባየ የተለያዩ ወሬዎችን በማውራት ሰላም እየነሱኝ ይገኛሉ:: ይሄንን ስላቹ የራሴን ደብቄ እንዳይመስላችው እውነቱ ይሄ ነው ስራ ሰርቼ ከመግባት ሌላ ነገር አላውቅም:: ግዜ ሲኖረኝ ከነዚ ልጆች ጋር አሳልፍ ነበር:: አሁን ግን በከተማው የማውቀው ኢትዮጵያዊ ሁሉ አያናግረኝም ምን አውርተው እንደሆነ አላውቅም:: ከነሱ መሀል አንደኛውን መንገድ ላይ አግኝቼ ባናግረው ጭራሽ ለሰላምታም ዘግቶኝ አለፈ:: እነሱ ይቅሩ የኔን ላይፍ በጀርባዬ እያወሩ በጥብጠውኛል:: ያለ ብሄሬ ብሄር ይሰጡኛል የተቸገረ ብረዳ ጉረኝ ይላሉ ብቻ እንዲሁ እየተከታተሉ ምንም ጥፋት ሳይሆርብኝ ሰላሜን ነስተውኛል, ምን ባደርግ ያሻለኝ ይሆን :?: :: እነሱን አጥፍቼ እራሴም ከማጥፋቴ በፊት ምክራችሁን ለግሱኝ::

ወድ ጉዳዩ! በስደት ስትኖር ብዙ ነገሮች ይደርስብሀል:: ስደት ላይ የምትተዋወቀውን ሰው የጀርባ ታሪኩን አታዉቀውም..አብዛኛው ስደተኛ ቁስለኛ ነው::ቁስሉን ግን አያሳይህም ይደብቀዋል:: ለምሳሌ...በስደት የምታውቀውን ጓደኛህን አግኝተኸው ለስላምታ ትክሻውን ስትገጨው በልብስ የተደበቀውን ቁስሉን ልትነካው ትችላለህ:: ያኔ ጓደኛህ እሪሪሪ ይላል! ሆን ብለህ ነውም ይላሀል:: ኧረ ባክህ እኔ...ብትለው አይሰማህም:: እንዴውም እየዞረ..ሆን ብለህ በቁስሉ ውስጥ እንጨት እንደሰደድክበት ለሌሎች ይነግርብሀል:: አብዛኛው ሰውም ያምነዋል:: አንተም ከወገኖችህ ትገለላለህ:: ሃገር ቤት ቢሆን አንዱ ቢያስቀይምህ ወይም ቢጠላህ ብዙ የሚወዱህ ወግኖች ስላሉ በነሱ ታካክሰዋለህ:: ስደት ግን መጥፎ ነው:: በሰው ሃገር የሃገርህ ልጆች ያለምክንያት ሲጠሉህ ሆድ ይብስሃል! ይሄኔ አላስፈላጊ ድብርት እና እራስን ወደ መጠራጠር ትገባለህ.....እኔ ግን እልሃለሁ ወንድሜ ጉዳዩ ይህ ነገር ያለ የነበር ወደ ፊትም የሚኖር ነው እና ተረጋጋ:: በተለይ ለስደት አዲስ ከሆንክ..ነገሮች ቀስ እያሉ ይገቡሃል! እንዴውም ቆይተህ 'ያኔ እኮ.."እያልክ ትስቃለህ:: ግን ግን..አንተ ብቻ ሁሌም መልካም ሁን! ህሊናህን አዳምጠው!
ሰውን ፍርድ ስጡኝ ከማለትህ በፊት ህሊናህ ይዳኝህ:: ከሰው ብትጣላ..ህሊናህ ሰላም ከሆነ ቤትህ ገብተህ የሰላም እንቅልፍህን ትለጥጣለህ::ከህሊናህ ከተጣላህ ግን የት ትደበቃለህ?

አክባሪህ!

FREE REYOT ALEMU,ESKINDER NEGA,ANDUALEM ARAGE AND ALL POLITICAL PRISONERS!!

እምቢተኛው :!:
ነፃነት የጠማው
ETHIOPIA ETHIOPIA ETHIOPIA
እምቢ ለሀገር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 262
Joined: Mon Feb 13, 2012 5:08 pm

Re: ትልቅ እርዳታ ፈልጋለው

Postby recho » Wed Jun 27, 2012 3:50 pm

እምቢ ለሀገር wrote:ወድ ጉዳዩ! በስደት ስትኖር ብዙ ነገሮች ይደርስብሀል:: ስደት ላይ የምትተዋወቀውን ሰው የጀርባ ታሪኩን አታዉቀውም..አብዛኛው ስደተኛ ቁስለኛ ነው::ቁስሉን ግን አያሳይህም ይደብቀዋል:: ለምሳሌ...በስደት የምታውቀውን ጓደኛህን አግኝተኸው ለስላምታ ትክሻውን ስትገጨው በልብስ የተደበቀውን ቁስሉን ልትነካው ትችላለህ:: ያኔ ጓደኛህ እሪሪሪ ይላል! ሆን ብለህ ነውም ይላሀል:: ኧረ ባክህ እኔ...ብትለው አይሰማህም:: እንዴውም እየዞረ..ሆን ብለህ በቁስሉ ውስጥ እንጨት እንደሰደድክበት ለሌሎች ይነግርብሀል:: አብዛኛው ሰውም ያምነዋል:: አንተም ከወገኖችህ ትገለላለህ:: ሃገር ቤት ቢሆን አንዱ ቢያስቀይምህ ወይም ቢጠላህ ብዙ የሚወዱህ ወግኖች ስላሉ በነሱ ታካክሰዋለህ:: ስደት ግን መጥፎ ነው:: በሰው ሃገር የሃገርህ ልጆች ያለምክንያት ሲጠሉህ ሆድ ይብስሃል! ይሄኔ አላስፈላጊ ድብርት እና እራስን ወደ መጠራጠር ትገባለህ.....እኔ ግን እልሃለሁ ወንድሜ ጉዳዩ ይህ ነገር ያለ የነበር ወደ ፊትም የሚኖር ነው እና ተረጋጋ::

በጣም ጥሩ አገላለጽ ነው ! ብዙው ሰው ከስደት በፊት ያለ ሂወቱ ምን እንደሚመስል ለማወቅ አስቸጋሪ ነው ... እኔ እንዳየሁት ያልሆነውን ሆነን ለመታየት በምናደርገው ጥረት በርግጥ ትክክል የሆነው ማንነታችንን ስለምንደብቅ በተለይ ወንድማችን ከላይ እንዳለው እኔ የደሀ ልጅ ነኝ እያልክ በቀጥታ ተናገርህ ከሆነ ያም የችግሩ ምንጭ ነው .. ምናልባት ያንተ እውነተኛነት ለጉዋደኞችህ ስድብ ነው .. ያልሆኑትን ሆነው ተኮፍሰው ከጎረቤታችው ቤት ሲደረግ የነበረውን እንደራሳችው ታሪክ እያረጉ እየኖሩ ያሉ ቢሆኑ .. አንተ መጥተህ የራስህን እውነተኛነት ብቻ እያየህ እሱንው ስትናገር .. አካባቢህ ላይ ያሉትን ሰዎች ሂሊናቸው ውሸታም ውሸታም እያለ እንዲመሰክርባቸው ታደርጋለህ ... ከህሊና ወቀሳ ያመለጡ ሲመስላቸው አንተ ላይ ይወርዱብሀል ...

እኔ በጅጉ የረዳኝን ጥቂት ነጥቦች ላስጨብጥህ
1 ሁሌም ራስህን ሁን ... በተለይ አዲስ ስለሆንክ ብቻ የሆነውን ያልሆነውን ብለው ሂወትህን ሊመሩልህ ጥረት ቢያደርጉ አትቀበል .. ምክር ትሩ ነው .. ግን በራስህ መንገድም ነገሮችን ለማጣራትና ለማወቅ ጥረት አድርግ እንጂ ጉዋደኞችህ ሂወትህን እንዲመሩ አትፍቀድ .. አድርገህው ከሆነ .. ራስህን ችለህ ከነሱ እኩል ነገሮችን መምራት ስትችል .. ጠላት ቁጥር አንድ እነሱ ናቸው ..
2 ሚስጥርህን ጠብቅ ... ብዙ ስለራስህ አታውራ... ብዙም ስለ ገቢህ , እድገትህ ሆነ ውድቀትህ አታውራ .. ብዙ ባወቁህ ቁጥር ለጥቃት ትጋለጣለህ ...
3 እጅ አትስጥ .. ማንም ምንም ስላረገልህ ላይህ ላይ እንዲረማመዱ አትፍቀድ .. ገና ለገና አንተ አዲስ እያለህ ስለረዱህ ብቻ ዝቅ አርገው ሊያኖሩህ ከፈለጉ , ገደል ይግቡ !
4 አንገትህን ቀን አርገህ ተራመድ ! አንተ ሙሉ ሰው ነህ .... የማንንም እርዳታ አትፈልግም .. ወንድማለም አሜሪካን አገር 10 አመት እና 1 አመት የኖረ ሰው ሁለቱም በተመጣጣኝ ሁኔታ ተቀራራቢ ኑሮ ይኖራሉ ... አንደ በእግርህ እስክቆም ብቻ ሰው ያስፈልግሀል ከዛ ግን ዩ አር ኦን ዩር ኦውን .. የማንም ፍቅርም ሆነ አዘኔታ ከዛ አያስፈልግህም ... ጉዋደኛ ቢኖር ሂወት ያቀላል .. ከዛ ውጪ ግን ሂወትህን እስኪረብሽ ድረስ የሚመጣ አበሻም ይሁን ሌላ እኩል ይዳኛል ... አላርፍ ካሉ ይሄ ጨርቆስ አይደለም ህግ ያለበት አገር ነው .. ለነገሩ ለራስህ መቆምህን ካወቁ ይተውሀል ! አይ ካሉ ... ከዛ ይታሰብበታል ...

ባጭሩ .. አንተ ላይ ብቻ የደረሰ አይደለም ... ሁላችንም በተለይ አዲስ ሆነህ ግራ ሲገባህ ያዩ ሰዎች ራስህን ችለህ ... ሂወትህን አሸንፈህ ስትቆም የማይወዱ ብዙዎች አሉ ... አይ ኖው አሁን አለም የተደፋብህ ይመስላል .. ትንሽ ስትቆይ ግን ያስቅሀል .. ትረስት ሚ ..! አይ ወዝ ዜር .. ! ቆፍጠን ብለህ ርሳቸውና ኑር ... አፍተር ኦል ሂወትህ የራስ ብቻ ናት .. ለሱ ደግሞ የማምን አፕሩቫል አያስፈልግህም ... ራስህን ከስራ ውጪ ያለውን ቢዚ አድርግ .. መአት ሺ የሚደረግ ነገር አለ ... ሪቾ ኦልሞስት ለ 1 አመት ጉዋደኛ አልነበራትም .. እኔ ምንም ካልሆንኩ አንተም ምንም አትሆንም .. እመነኝ .. !

ገድዬ መሞት ምናምም .. ዎርዝ አያረግም .. መፍታት ሳለ መሞት አለ ያገሬ ሰው .. አልተጋባቹ .. ለምን ብለህ ትሞታለህ ..? :)

መልካም እድል ...
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Re: ትልቅ እርዳታ ፈልጋለው

Postby ሳምራውው33 » Wed Jun 27, 2012 4:21 pm

recho wrote:

ሪች የምትመክሪው ምክር አንድዋም እንክዋን መሬት ላይ ጠብ አትልም :!: :!: :!:
ሳምራውው33
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 530
Joined: Thu Jun 21, 2007 12:23 am

Postby recho » Wed Jun 27, 2012 4:45 pm

ሳምራውውው :lol: ታንክስ ብሮ .. ምክርና ቦክስ እኮ ቀላል ነው ... ማቀበል አይደል ? ለተቀባዩ ነው ከባድ :lol:

ባለጉዳይ .. አንድ በስራ አጋጣሚ ያገኘሁዋትን ልጅ ችግር ላካፍልህ ... የምትሰራው ከ 5 ሀበሾች ጋር ነው .. እንደገባች አካባቢ አብረዋት ምሳ ይበልሉ .. ራይድ ይሰጡዋታል , ሻፒንክ አብረዋት ይሄዳሉ .. ባጭሩ አላመዱዋት .. ስራ ለመደች .. መልክዋ ወጣ .. ፊትዋ ላይ የነበረው ጭንቀት ጠፍቶ ሳቅ እና እረፍ እየተነበበባት ሲመጣ የብዙዎችን አቴንሽን ሳበች .. ገንዘብ ሴቭ ማደረግ ጀመረች .. የሂወት አቅጣጫ ገባት .. ይሄ ፕሮሰስ የፈጀው ልጅትዋ እንደነገረቺኝ 6ወር አካባቢ ነው ... ይሄኔ ቀስ በቀስ አካባቢዋ ላይ ያሉት ሁኔታዎች መቀየር ጀመሩ .. አብረዋቸው የሚሰቱትን ስፓኒሾች አሳመጹባት .. እና በሎካል ቻናል ላይ እስዋን የሚመለከት ነገር እንደወጣ እና ገና አገርቤት ሁሉ ቤተሰቦችዋ እንዲያዩት እንደሚላክ አወሩላት .. ልጅትዋ የቁዋንቁዋ ችግር አለባት .. ምንም ቢልዋት አትሰማም ስለዚህ እየተረጎሙ የሚነግሩዋት ራሳቸው የበፊት ጉዋደኞችዋ ናቸው .. ስለዚህ ከፍተኛ የሆነ ጭንቀት ውስጥ ገባች ... አንቺ ትላንትና እንደዚህ ስናረግልሽ እንደዚህ ተቸግረሽ ምናምም ስለሚልዋት ፈጽሞ ፊታቸው መሳቅ እንኩዋን እስከማትችል ደረስ ተሸማቀቀ .. እዚህ ጋር አልቆመም .. ከስራ ውጪ የፈለጋት ለብሳም ሆነ ከፈለጋት ጋር ወጣ ገባ እንዳትል ሆነ .. ፈን ነው ለነሱ .. ስለፈራች ብቻ .. እና እየተከታተሉ አጠቁዋት ... ልጅትዋ መታመም ጀመረች .. ይሄኔ ነው እኔ ያለሁበት ቦት አለእርዳታ የመጣችው.. እውነት ነው የምነግርህ .. ልጅትዋ ቆዳ እና አጥንት እንጂ ስጋ የሚባል ነገር የለባትም .. የምታለቅሰው እንባ ጉድ ነው .. በጉዋደኝነት ዘመን ያወራችላቸውን የራስዋን ሚስጥር እያሳዩ አስፈራርተዋታል .. ምንም ወንጀል ሰርታ አይደለም ግን ሚስጥርዋ ነውና በየሰው ሁሉ አፍ ሲገባ አስደንግጥዋታል .. ብሎም የልጅትዋን እንጊሊዘኛ አለመቻል እና መዋከብ ያዩት .. የአሜሪካ መንግስት የስዋ ሚስጥር (ምንም ይሁን ምን ) እንደ ከባድ ችግር ቆጥሮት በሎካል ቲቪ ሁሉ እያሳየው ነው አንቺ ስላላየሽ ነው ሲልዋት አምናለች :lol: አይ ኖው የማናት ዳም ልትሉ እንደምትችሉ .. የቸገረው እና ግራ የገባው ምንም የማይሆነው የለም ..

ኢንተርቬንሽን ... ሰዎቹ ሲጠየቁ .. ለነሱ ሞር ኦፍ ፈን ነበር !!!! :twisted: ግን ከላይ እንዳልኩት .. ያለነው ህግ ያለበት አገር ነው .. ማንም በማንም ሂወት ውስጥ ጣልቃ ገብቶ እንቅልፍ ሊነሳና ሊያውክ አይችልም ... ! የሚያስከትለው መዘዝ ከባድ መሆኑን ሲያውቁ አርፎ ይቀመጣል !

ልጅትዋ ያጠፋችው ጥፋት ... ስለራስዋ ብዙ አሳውቃለች .. የነዚህን ሰዎች ምንነት ምንም የምታውቀው ነገር ሳይኖር ስለራስዋ ሁሉን ዘርግፋለች ያ ለጥቃት ጋርድዋታል ! ሌላው ሰዎቹ በላይዋ ላይ አለቃ እንዲሆኑ አድርጋለች .. እርዳታ ሌላ ባርነት ሌላ መሆኑን ከጅምሩ አላሳወቀችም .. ስለዚህ ባሪያቸው ሊኮበልል እንዳለ ጌታ የስዋ ቀና ቀና ማለት ረብሽዋቸዋል ... !

ወንድማለም .. ይሄንን ሁሉ የዘረዘርኩት አሁን .. አንተ ብቻ ሳትሆን ኦልሞስት ሁሉም ሰው ላይ የሚደርስ መሆኑን አይተህ ራስህን ከመረበሽ ሂወትህን እንዴት አርገህ በጥሩ ሁኔታ እንደምትመራ እንድትተጋ ለመንገር ያክል ነው .. ስራፈቶች ጋር አርፈህ ስራ አትፍታ .. ያለህው አሜሪካን አገር ከሆነ ሂወት ኢዝ ሞር ዛን ለቤተሰብ ገንዘብ መላክና 6ቀን መስራት .. ብዙ ዲስከቨር የምታደርገው ነገር አለ ... ያንን የምታደርግ እንደሆነ ለነሱ ክራፕ ጊዜ አይኖርህም .. ያለህው ላንድ ኦፍ ኦፖርቺኒቲ ላይ ነው .. ማንም ድራግ አርጎ እንዲያስቀርህ አትፍቀድ .. አድጋለሁ ካልክ እንስከፈቀድክበት ድረስ ማደግ ትችላለህ ... የዛኔ መጥተው እግርህ ስር ይወድቃሉ .. በቀል እንዳታስብ ሌላ .. ይሄንን ቼን ማቆም የምንችለው በዚህ ሁኔታ ነው .. ብለጣቸው እና አሳያቸው .. ሚስጥሩ .. ሰልፍ ዴቨሎፕመንት .. !!! እመነኝ .. ከስርህ ይወድቃሉ ...

እንደገና መልካም እድል ..
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby ገደል » Wed Jun 27, 2012 6:23 pm

recho.... ምክርሽ ከሞላ ጎደል ጥሩ ነው:: በመጨረሻ ያልሺው ግን ጥሩ ይሁን አይሁን አላውቅም "አንገትህን ቀና አድርገህ ተራመድ" ነው ያልሺው:: እዩኝ እዩኝ በል ነው የምትይው:: ይልቅ አንገቱን ደፍቶ (low profile ይዞ) በተግባሩ ቀና ቢል የተሻል አይሆንም?

ሌላው እኔ ለማመን የሚያስችግረኝ ነገር እንዴት በርካታ ሰዎች ተሳስተው አንድ ሰው ልክ ይሆናል? በተለይ በአንድ ወቅት ሲረዱትና ሲደግፉት የነበሩ ሁሉ በአንድ ጊዜ በአንድ ላይ ተቀይረው ጠላት ይሆኑታል?
ለዚህ ነው ተበደልኩ የሚለው ወገን ራሱን መርመር አለበት የምለው::

አንድ እኔ የሰማሁትን በአጭሩ ልንገራችሁ:: ከባለ ጉዳዩ ጋር እውቅና የለኝም ግን ከሁነኛ ሰው ነው ጉዳዩን የሰማሁት::

አንድ ሰው ከሀገር ቤት በDV አሜሪካ ይገባል:: የዚህ ሰው አብሮ አደግ የሆነ አሜሪካ ብዙ ጊዜ የኖረና ጥሩ የባለሙያ ሥራ ያለው የተደላደለ ኑሮ የሚኖር ሰው መጠጊያ ሰጥቶት ለአንድ አመት ከምናምን አስቀምጦታል:: ከዚያም በላይ ሥራ በመፈልግ ረድቶት አንድ ጥሩ ሥራ በደረጃው አስቀጥሮታል:: እዚህ ላይ አላበቃም: ቤት ገዝቶ ሲወጣ ኮሳይነር ሆኖታል:: ታሪኩን ላሳጥረውና:: ይህ ደግ ሰው በምላሹ ያገኘው ጥሩ ነገር አልነበረም:: ተረጂው የረጂውን ሰው ሚስት ያባልግ ነበር:: ማባላግ ብቻ አይደለም እገዛው ቤት ከገባ በሁዋላ ሴትዮዋን ገፋፍቶ እንዲፋቱ አድርጎ ውሎ ሳያድር ጠቀለላት:: በአዲሱ ትዳር ብዙም ሳይቆዩ ሰውዬው ከሥራ ሌይ ኦፍ ተደረገ (ተባረረ): ሞርጌጅ መክፈል አቃተው:: በዚህ ጊዜ የአካባቢው አበሾች ጉዳዩን ይከታተሉ ነበርና ሰውዬውን አገለሉት::ጋዝ ስቴሽን ያላቸው አበሾች ሁሉ አንቀጥርም አሉት:: በጠቅላላው ከማህበራዊ ጉዳይ አገለሉት:: ታሪኩ ረጂም ነው ግን በጊዜ ማጠር እዚህ ላይ ላቁመው::

ታድያ ይህ ሰው ተበደልኩ ብሎ ቢጮህ የሚሰማው አለ?
ገደል
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 489
Joined: Sat Jan 02, 2010 12:03 am

Postby recho » Wed Jun 27, 2012 6:51 pm

ገደል wrote:recho.... ምክርሽ ከሞላ ጎደል ጥሩ ነው:: በመጨረሻ ያልሺው ግን ጥሩ ይሁን አይሁን አላውቅም "አንገትህን ቀና አድርገህ ተራመድ" ነው ያልሺው:: እዩኝ እዩኝ በል ነው የምትይው:: ይልቅ አንገቱን ደፍቶ (low profile ይዞ) በተግባሩ ቀና ቢል የተሻል አይሆንም?

ሰላም ገደል
ፈጽሞ እዩኝ እዩኝ በል አላልኩም ... መሸማቀቅ መፍራት እና እዩኝ እዩኝ ማለት ፈጽሞ ሁለት የተለያዩ ነገሮች ናቸው ... ብዙ ጊዜ አዲስ ሆነህ ቡሊንግ ሲደርስብህ ያለው ስሜት አሸማቃቂ እና በራስ የመተማመን ስሜትህን ፈጽሞ የሚያጠፋ አሰቃቂ ነገር ነው ... ያ ደግሞ ቅስም ሰብሮ አንገት አሰብሮ ግራ መጋባት ውስጥ የሚከትና ከፍተኛ የሆነ ዲፕረሽን የሚፈጥር ነገር ነው .. አንድ ሰው ምንም እንዳላጠፋ ካመነ .. ሰዎች አሉኝ አላሉኝ በሚል ስሜት አንገቱን ደፍቶ መኖር የለበትም ብየ አምናለሁ ለዚህም ነው ከጊልት ነጻ የሆነ ህሊና ካለህ አንገትህን መስበር የለብህም ቀና ብለህ ተራመድ ያልኩት ... ብዙ ሰዎች ውሸትን አምነው ስለተቀበሉ እውነት ሊያደርጉት አይችሉም .. እንዲሁም ሁሉም ሰው አንድ ውሸት እውነት ነው ብለው ስላመኑበት እውነት ሊያደርጉት አይችሉም ... ያ ነው የኔ ቲየሪ .. ብዙ ጊዜ ( ሁልጊዜ አይደለም ግን አብላጫው) እንደዚህ አነት አድማ በአንድ ማስተር ማይንድ ነው የሚመራው .. ስለዚህ ቴክኒካሊ አንድ ሰው ነው ያመነበት .. ሌላው ቢቃወም የሚደርስበትን ስለሚያቅ ጅራፉ ወደሱ እንዳይዞር አብሮ ያጨበጭባል ... ያ ደግሞ ብዙ ሰው ትክክል ሆኖ አንድ ሰው ተሳሳተ አይባልም ... እንደዚህ እያረጉ ሂወታቸውን የሚገፉ ብዙ አሉ .. አዲስ ነገር አይደለም ....

አንድ ሰው ከሀገር ቤት በDV አሜሪካ ይገባል:: የዚህ ሰው አብሮ አደግ የሆነ አሜሪካ ብዙ ጊዜ የኖረና ጥሩ የባለሙያ ሥራ ያለው የተደላደለ ኑሮ የሚኖር ሰው መጠጊያ ሰጥቶት ለአንድ አመት ከምናምን አስቀምጦታል:: ከዚያም በላይ ሥራ በመፈልግ ረድቶት አንድ ጥሩ ሥራ በደረጃው አስቀጥሮታል:: እዚህ ላይ አላበቃም: ቤት ገዝቶ ሲወጣ ኮሳይነር ሆኖታል:: ታሪኩን ላሳጥረውና:: ይህ ደግ ሰው በምላሹ ያገኘው ጥሩ ነገር አልነበረም:: ተረጂው የረጂውን ሰው ሚስት ያባልግ ነበር:: ማባላግ ብቻ አይደለም እገዛው ቤት ከገባ በሁዋላ ሴትዮዋን ገፋፍቶ እንዲፋቱ አድርጎ ውሎ ሳያድር ጠቀለላት:: በአዲሱ ትዳር ብዙም ሳይቆዩ ሰውዬው ከሥራ ሌይ ኦፍ ተደረገ (ተባረረ): ሞርጌጅ መክፈል አቃተው:: በዚህ ጊዜ የአካባቢው አበሾች ጉዳዩን ይከታተሉ ነበርና ሰውዬውን አገለሉት::ጋዝ ስቴሽን ያላቸው አበሾች ሁሉ አንቀጥርም አሉት:: በጠቅላላው ከማህበራዊ ጉዳይ አገለሉት:: ታሪኩ ረጂም ነው ግን በጊዜ ማጠር እዚህ ላይ ላቁመው::

አይደረግም አልልህም .. ይደረጋል .. ከዚህ በላይም ይደረጋል .. ሰው ክፉ ነው ... ለዚህ ነው በየትኛውም አይነት ሪሌሽን ሽፕ ላይ ድንበር የሚያስፈልገው ... ሰው መርዳትም በቅጡ ... ሁሉም ነገር በአግባቡ ... ሚስትየውም ትልቅ ድርሻ አላት ... ስለዚህ መጀመሪያ ደረጃ ይሄ ሰውዬ ተበደልኩ ብሎ አይጮህም ... ጮሆ ከሆነም የሚሰማው የራሱን የገደልማሚቱ ነው ... ምክኒያት በሰፈረው ቁና ተሰፈረ.. ውጤቱ ታየ.... ስለዚህ ምንም ቢል ህሊናው ይፈርድበታልና መቼም ቀና ብሎ አይሄድም ...

[/quote]
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby ገደል » Wed Jun 27, 2012 8:55 pm

ሪቾ.......በአንገት መድፋት በኩል የምንስማማ ይመስለኛል::ትንሽ የቃላት ግርግር ቢኖርም::
መሸማቀቅ መፍራት እና እዩኝ እዩኝ ማለት ፈጽሞ ሁለት የተለያዩ ነገሮች ናቸው

እኔም አንድ ናቸው አላልኩም እኮ ሪቾዬ :D :D

ሳይሸማቀቁ አንገት መድፋት አይቻልም እንዴ?
ገደል
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 489
Joined: Sat Jan 02, 2010 12:03 am

Next

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests