ትልቅ እርዳታ ፈልጋለው

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby recho » Wed Jun 27, 2012 9:04 pm

ገደል wrote:ሳይሸማቀቁ አንገት መድፋት አይቻልም እንዴ?
:lol: :lol: :lol: አንተ ልጅ እንደው .. አሁን ደስ ሲለው ወይንም በጣም ሪላክስ ሲያደርግ አንገቱን የሚደፍ ሰው አይተሀል ? አንገት መድፋት እኮ የመሸማቀቅ ምልክት ነው ... :lol: አይ ደስ ስላለውና ሂወት ስለተስተካከለለት አንገቱን ደፋ የምትለው ሰው ካለ እንጃ እንግዲህ ..

አይ ቲንክ ሎው ፕሮፋይል ይዞ መኖር .. ( ብራግ አለማድረግና እዩኝ እዩኝ አለማለትን ) ከ ጭንቀት የተነሳ አንገት መድፋት ጋር አዘባርቀነዋል .. አማርኛ ከዚህ በላይ ማስረዳት አልችልም በውነትን :D
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby ጉዳይ » Wed Jun 27, 2012 11:10 pm

ለምክራችው ምስጋናዬ ወደር የለውም እጅግ ማወቅ ያለብኝን ነገር ነው የነገራችሁኝ::

ወንድሜ እንቢ ለሀገር, ሳምራው, ሪቾ

ስለሰጣችሁኝ አስተያየት እጅግ አመሰግናለው:: ሪቾ የተናገርሽው በእውንት ሁሉም ትክክል ነው:: የኔን ስተት ቁልጭ ብሎ እንዳይ ነው የረዳኝ:: አዲስ እያለው እምብዛም የረዳኝ ሰው የለም እንደመጣው ቀጥታ ወደ ስራ ገባው ግን እንደዛሬው ሁለት ስራ ስለማልሰራ ቶሎ ቶሎ እንገናኝ ነበር:: ስለራሴ ምንም ነገር ሲጠይቁኝ ልደብቅ ብዬ አላውቅም ማወቅ የሚፈልጉትን ሁሉ እነግራቸው ነበር:: ይሄ ሁሉ እጅግ ከብዙ ፋሚሊ ስለወጣው ሰው ካጠገቤ ሲጠፋ እረበሽ ነበር:: ሪቾ ቅድም የደሀ ልጅ ነኝ በማለት ያነሳሽው ነጥብ እጅግ ትክክልና ባላየውት አንግል እንዳይም አድርገሽኛል:: እኔ ስለ ራሴ ሳወራ የደሀ ልጅ እንደሆንኩኝና ቤተሰቦቼ አንድ ውጭ ዘመድ አለኝ የሚሉት እኔ እንደሆንኩኝ ደጋግሜ እናገራለው:: በተለይ ስለ እናቴ አውርቼ አልጠግብም:: አሁን አሁን ሳስበው ከነሱ መካከል አንድም ሰው ስለ ቤተሰቡ ምንም ነገር አጫውቶኝ አያውቅም:: አንድ ስራ እየሰራው ቤተሰቦቼን ማስተዳደርና እዚህም መኖር ከበድ ስላለኝ ሁለተኛ ስራ ስገባ ነው ይሄ ሁሉ ነገር የመጣው:: እንዲያው ብቻ አሁን መንፈሴንም አነቃቃችሁት በኔ ላይ የደረሰ ብቻ መስሎኝ ተጨንቄ ነበር:: እንደናንተ አይነትም ለካ ወገን አለኝ:: እውነት ፈጣሪ ለምትወዷቸው ዘመዶቻችውና ለአገራችው አፈር ያብቃችው:: ትልቅ ትምህርት የሚሆን ምክር ነው የሰጣችሁኝ::
ጉዳይ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 5
Joined: Mon Jun 25, 2012 9:15 pm

Postby -...- » Wed Jun 27, 2012 11:11 pm

ትልቅ ክብር ለrecho ዛሬ :: ከላይ በሰጠሽው ምክር ተከብረሻል ተደንቀሻል ተመስግነሻል:: ግሩም ምክር ትክክለኛ ምክር

ተወደሻልም
ምናለ ያ ባልሽ ፈቶሽ እኔ ባገባሁሽ !

ገደል ሬቾ አንገትክን ቀና አድርገህ ሂድ ስትል በራስህ መተማመን ይኑርህ ማለቷ ነው :: She is talking confidence you are talking humility .

እኔ ለአቤቱታ አቅራቢው የምለው ሰው የፈለገውን ቢል ምን ቸገረህ ? ሰርተህ ራስክን የምታስተዳድር ሰው እንኳን ሳታጠፋና አጥፍተህ እንኳን ሰው ስላንተ ብያወራ ደንታ አትስጣቸው :: ስማ ሰርቀው ሰው አታለው : ሰው ገድለው : ሽርሙጥና ሰርተው የሚኖሩ አሉ ታዲያ አንተ ህጋዊ ስራ እየሰራህ ሰው አልገደልክ የፈለጉትን ቢያወሩ ምን አስጨነቀህ ? እንዲሁ በጭንቀት ከምትሰቃይ የፈለጉትን ስላንተ ቢያወሩ ምን ሊያደርጉኝ ይችላሉ ብለህ ራስክን ጠይቅ:: ቢከፋ ቢከፋ ስላወሩብህ ምን ትሆናለህ > ያውም የውሸት ወሬ :: ትንሽ ስትቆይና ስትለማመድ ወሬና ወሬኞችን ንቀህ መኖር ትለምዳለህ ::

እስከዚያው ከrecho የተሻለ ምክር አታገኝምና የመከረችህን ደጋግመህ አንብበው :: ፈረንጆች እንደሚሉትም Grow some balls and have a little self confidence. የሰው ፊት እያየህ ሙድክን በሌላ ሰው ስራ ተለዋዋጭ አታድርገው:: ሲሰለችህ የሰው ፊት እያዩ መኖሩን ትተወዋለሁ እስከዚያው ልትቆጣጠረው ካልሞከርክ ትንሽ ኢሞሽናሊ ይደቁስሀል::

እንዳይብስብህ እንጂ ዋናው ችግር ያለው ካንተ መሆኑን እወቅ :: የራስ መተማመን ስለሌለህ ሰው ምናለኝ እያልክ የሰው ፊት እያየህ ትሸማቀቃለህ :: ቀስ በቀስ በራስህ ለመተማመን ሞክር :: ምንም ጥፋት እንዳልሰራህና የውሸት ወሬ እንደሚያወሩብህ ራስክን አሳምነው :: ይህንን ልብህ ካወቀና ካመነው አያስጨንቅህም አትፈራምም:: እየበረታህና እየናቅካቸው ትመጣለህ ::

ዌስትኮስት የሚሆነውን ልንገርህ :: መልከመልካም : ንጽህናውን የሚጠብቅና ጥሩ የሚለብስ አበሻ ሲያዩ ዲሪቶ ለብሰው ጸጉራቸው ተንጨባሮ የፍየል ወጠጤ የፍየል ወጠጤ የሚሸቱ የሾተል አይነት ጓጉንቸሮች ጌ ነው ብለው ያስወሩብታል :: አብዛኛው ደንታ አይሰጠውም አንዱን ግን ጨርቁን አስጥለዉት ሀገር ለቆ አትላንታ አስኪደውታል :: ስለዚህ በራስ መተማመን ለሰላም ኑሮ ቁልፍ ነው ::
Last edited by -...- on Thu Jun 28, 2012 12:24 am, edited 1 time in total.
ሞቼ እየተነሳሁ ልሙት እንደገና
አንድ ሞት ላገሬ አይበቃትምና
-...-
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 401
Joined: Thu Feb 09, 2012 8:36 pm

Re: ትልቅ እርዳታ ፈልጋለው

Postby ሓየት11 » Wed Jun 27, 2012 11:11 pm

የአበሻ ቲፒካል በሽታ ናት ይቺ ... ለራስህ ሳይሆን ለሰው ነው የምትኖረው ወንድማችን ... ከጀርባህ ምን ይወራ ምን ... አጥፍቶ ለማጥፋት ድረስ የሚያስኬድህ ጉዳይ ምንድን ነው :?:

ምናልባት ቀጥሎ የማወራው ነገር አንተን አይመለከትም ይሆናል ... ነገር ብዙ ጊዜ ከታዘብኩት አንድ እውነታ ላካፍል::

ሰውን በሀሜት መቦጭቅ የሚወድ ሰው ... ሰዎች ሲቦጨቁት ከማንም በላይ መቋቋም አይችልም:: ...የሚሆነውን ያሳጣዋል:: ... አቅሉን ይስታል:: ,,, የሰውን ስም ሲያጠፋ የሚውል ደግሞ ... ስሙ ሲያጠፉት ያጋጠመው ለት ... አለም የተዘቀዘቀችበት ነው የሚመስለው .... ቅቅቅቅቅ ... አልታዘባችሁም? አላጋጠማችሁም?

በሌላ በኩል ደግሞ ... የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ባህሪ ሆኖ ... በተለይ ደግሞ በአበሻው ዘንድ በደንብ ይታያል ... ህይወቱን የሚመዝነው ... ራሱ ባስቀመጠው ግብ ብቻ ሳይሆን ... ሰዎች (በቅርብ የሚያውቃቸው ሰዎች) በደረሱበት ደረጃም ጭምር ነው:: ... ሰውዬው ከፍ ብሎ ከሆነ ... አንተ ከትላንት የተሻለ ኑሮ ብትኖር ራሱ ... ዝቅ ያልክ ሆኖ ይሰምሃል:: ... ሰውዬው አጥቶ ከሆነ ደግሞ ... አንተ ከትላንት የወረደ ኑሮ እየኖርክም ቢሆን (በራስህ ስንፍና ምክንያት ሆኖም) ... ከሰውዬው የተሻለ ኑሮ ካለህ (ዕድል ጠማበትም ቢሆን) ... ትጽናናበታለህ ... እንጂ ያስቀመጥከውን ግብ ባለመምታትህ ... ራስህን አትወቅስውም:: ... መጥፎም አይደል :?:


መፍትሄው ... ለራስህ ብቻ መኖር ነው:!: ... ሰው የፈለገውን ቢል አትጨነቅም ... ስለ ሰውም አትጨነቅም ... ራስህን የምትመዝነው ...አንተ ራስህ ካስቀመጥከው ... ከግብህ አንጻር ብቻ ይሆናል:: ...


ከነ ሪቾ የተረፈውን
ያለንን ለመጨመር ያክል ነው :wink:

ጉዳይ wrote:ውድ ኢትዮጵያዊያኖች ሰላምታዬ ይድረሳችው እያልኩኝ ይቺን ችግሬን የሆነ መብቴ ብትፈልጉልኝ በማለት መጥቻለው;; የችግረኛ ልጅ መሆን መቼም አለምታደል ቢሆንም ጠንክረው ከሰሩ ሰው መሆን ይቻላል ብዬ አምናለው:: እኔም የደሀ ልጅ እንደመሆኔ ያገኘውትን ስራ በመስራት ቤተሰቦቼን ለመርዳት ደፋ ቀና እላለው:: ቤተሰቦቼም በከፊልም ቢሆን ከችግራቸው ተላቀው እፎይ ብለው መኖር ጀምረዋል:: ድሮ ድሮ ጓደኛ የምላቸው ሰዎች ነበሩ እኔ በየዋህነት እቤቴ እያመጣው ስጋብዛቸውና በችግራቸው ለመድረስ የተቻለኝን ሳደርግ ብዙ ቆይቻለው:: እነሱ ግን ምን እንዳደረኩዋቸው አይታወቅም ጥምድ አድርገው ይዘውኝ በጀርባየ የተለያዩ ወሬዎችን በማውራት ሰላም እየነሱኝ ይገኛሉ:: ይሄንን ስላቹ የራሴን ደብቄ እንዳይመስላችው እውነቱ ይሄ ነው ስራ ሰርቼ ከመግባት ሌላ ነገር አላውቅም:: ግዜ ሲኖረኝ ከነዚ ልጆች ጋር አሳልፍ ነበር:: አሁን ግን በከተማው የማውቀው ኢትዮጵያዊ ሁሉ አያናግረኝም ምን አውርተው እንደሆነ አላውቅም:: ከነሱ መሀል አንደኛውን መንገድ ላይ አግኝቼ ባናግረው ጭራሽ ለሰላምታም ዘግቶኝ አለፈ:: እነሱ ይቅሩ የኔን ላይፍ በጀርባዬ እያወሩ በጥብጠውኛል:: ያለ ብሄሬ ብሄር ይሰጡኛል የተቸገረ ብረዳ ጉረኝ ይላሉ ብቻ እንዲሁ እየተከታተሉ ምንም ጥፋት ሳይሆርብኝ ሰላሜን ነስተውኛል, ምን ባደርግ ያሻለኝ ይሆን :?: :: እነሱን አጥፍቼ እራሴም ከማጥፋቴ በፊት ምክራችሁን ለግሱኝ::
ሓየት11
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2945
Joined: Sun Apr 06, 2008 7:34 pm
Location: ላን'ሊይ

ያለብሄሬ ብሄር ይሰጡኛል

Postby ካሳው » Sat Jul 07, 2012 7:02 pm

ሰላም ጉዳይ

ከላይ የተሰጡህ አስተያየቶች ገንቢወች ናቸው;; እኔ ግን ሁሉም ጉዋደኞችህ ባንዴ ባንተ ላይ ፊታቸውን ያዞሩበት የሆነ ምክንያት ይኖራቸዋል ባይ ነኝ;; ችግሩን ማወቁ ደግሞ መፍትሄወችን ለመፈለግ ይረዳል;;

ያለብሄሬ ብሄር ይሰጡኛል; የተቸገረን ብረዳ ጉረኛ ይሉኛል ስትል ምን ማለትህ ነው;; ችግሩ ያለው እዛ ላይ ይመስለኛል;; ለምሳሌ አንተ የገዢው ፓርቲ ደጋፊ ከሆንክና ረዳሁ የምትለው ነገር ከዛ ጋር የተያያዘ ከሆነ እና ጉዋደኞችህ ደግሞ በሀገር ቤት መልካም አስተዳደር የለም ስለዚህ መወገድ አለበት ብለው የሚያምኑ ከሆነ ልዩነት አለ ማለት ነው;; እንደዚህ አይነት ልዮነትን ይዞ በጉዋደኝነት መቀጠል ደግሞ ለኛ ማህበረሰብ ከባድ ነው;; አንተ በቀላሉ ያየከው ወይም ያልጻፍከው; ነገር ግን በነሱ ዘንድ ክብደት የሰጡት ጉዳይ ሊኖር ይችላልና ስለዚ ጉዳይ አንተ ምን ትላለህ


ለማንኛውም ህሊናህ ልክ ነው ብሎ የሚያምንበትን እና ለወደፊቱ የማያሳፍርህን ስራ ከመስራት ወደሁዋላ አትበል;;

መልካም ቀን

ሰላም
ካሳው
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 91
Joined: Mon Nov 17, 2003 12:56 pm
Location: ethiopia

Postby ጉዳይ » Sat Jul 07, 2012 7:34 pm

እንዴት ናችው ዋርካዎች ሰላም ልበላችሁ ብዬ ነው::
ካሳው ሰላም ወንድሜ ጥያቄዎችህን ለመመለስ ያህል ካለ ብሄሬ ህሄር ይሰጡኛል ማለቴ እኔ ቤተሰቦቼ ኦሮሞዎች ሲሆኑ ተወልጄ ያደኩት ያው አዲስ አበባ ነው:: በኢትዮጵያዊነቴ የማምን ወንድሞቼ አጎቶቼ በደረግ ሰራዊት ውስጥ የተዋደቁ አሁን ባለው መንግስትም በባድሜ ግዜ ውድ ህይወታቸውን የሰጡ ቤተሰብ ወገን ነኝ:: የፓለቲካ ወሬ ከማንም ጋር አላወራም እውቀቱም ኢንትረስቱም የለኝም:: አገሬን ግን በጣም የምወድና ማንም የአገሬን ብሄሮች ሲሰደብ መስማት እንደማልፈልግ ከአንዴም ሁለት ግዜ አሳይቻቸዋለው:: ለምሳሌ አብዛኞቹ የማውቃቸው ልጆች ኤርትራዊ ቢሆኑም ሁሉም አዲስአባ ተወልደው ነው ያደጉት:: ኦሮሞዋች, አማራዎችና በጥቂቱ አንድ ሁለት የሚሆኑ የትግራይ ልጆች አሉ መካከላችን:: እንግዲህ የአገሬ ሰው ሲሰደብ ቆሜ የማይበት ምንም ምክንያት የለም ብዙ ግዜ ለስድብ ሲነሱ ስለምቆጣ እኔ ፊት አያወሩም:: በዚህም ይመስለኛል ካለ ብሄሬ ሌላ ብሄር ነው እያሉ ማውራት ጀመሩ:: የተቸገረ ሰው ካለ ከረዳው ጉረኛ ለምን እንደሚሉኝ አላውቅም:: እንግዲህ ጥላቻቸው ከምን እንደመጣ እኔም አላውቀውም ይገርምሀል አሁን የምፅፍልህ አንደኛውም ስራ ጨርሼ ወደ አንደኛው ለመሄድ ከማርፍበት ትንሽ የእንቅልድ ሰአት ቆጥቤ ነው:: ለነሱ ግዜም የለኝም አሁን የኔ ደስታ የቤተሰቦቼ ጠግቦ ማደር ነው:: በእውነቱ ጥሩ ምክር ነው እዚህ ቤት ያገኝውት እየተጠቀምኩበትም ነው:: በድጋሚም ለዋርካ ተሳታፊ ምስጋናየን ለማቅረብ ግን እወዳለው::
ጉዳይ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 5
Joined: Mon Jun 25, 2012 9:15 pm

Postby ቢተወደድ » Fri Jul 20, 2012 2:51 pm

ሰላም ላንተ ይሁን

ከላይ ብዙ አዋቂዎች ሊምክሩ ሞክረዋል; የምጨምርልህ ቢኖር
የፈለጉትን ይቀባጥሩ
ቀለብ አይሰፍሩልህ
ቁምጣ አያሰፉልህ

አንተ ብቻ በርታ::
When we do it right No-one remembers,
When we do it wrong No-one forgets.
ቢተወደድ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1965
Joined: Tue Jul 21, 2009 3:21 pm
Location: Dabra Za`Yet

Previous

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests