የጀርመኑ ዘጋቢ ታደሰ እንግዳው አረፈ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

የጀርመኑ ዘጋቢ ታደሰ እንግዳው አረፈ

Postby Edit » Tue Jul 17, 2012 6:55 am

ታዋቂው የዶይቸ ቬለ ዘጋቢ፡ ጋዜጠኛ ታደሰ እንግዳው ትናንት ባጋጠመው የመኪና አደጋ ሕይወቱ አልፋለች። ኢትዮጵያ የሚገኙ ምንጮቻችን እንደገለጹት፡ ታደሰ ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በተመረቀው ታናሽ ወንድሙ የምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ ከሌላ ወንድሙ ጋር ተካፍሎ ትናንት ጥዋት ወደ አዲስ አበባ ሲመለስ ነበር አደጋ ያጋጠመው። በአደጋው ከታደሰ ሌላ በምረቃው የተገኘ ወንድሙ ሲያርፍ፡ ተመራቂው ወንድሙ ደግሞ ክፉኛ ተጎድቶ በሕክምና ላይ ይገኛል። ታደሰ እንግዳው ባለፉት ስምንት ዓመታት በአዲስ አበባ የዶይቸ ቬለ ወኪል ሆኖ ሲሰራ የጋዜጠኝነት ተሰጥዖውን፡ ለጋዜጠኝነት ያለውን ፍቅር እና ክብር ያስመሠከረ ንቁ፡ ትጉሕ እና ቀልጣፋ ጋዜጠኟ ነበር:: ለቤተሰቦቹ እና ለወዳጆቹ መጽናናትን ይስጣቸው ::

ምንጭ የጀርመን ድምጽ ራድዮ
Edit
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 18
Joined: Sat Jan 05, 2008 2:33 pm

Postby ሳምራውው33 » Tue Jul 17, 2012 7:46 am

ውይ ውይ የኔ ወንድም ምን አገኘው ያን የመሰለ ድምፅ ያን የመሰለ የጋዜጠኝነት ችሎታ እንዲሁ በዋዛ ብን ይበል :?: ያሳዝናል R.I.P. መጽናናትን ለቤተሰቦቹ እና ለወዳጆቹ ይሁን::

መሌ ይቀድማል ብሎ ሰው ሁሉ ሲጠብቅ :roll: :roll: :roll:
ሳምራውው33
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 530
Joined: Thu Jun 21, 2007 12:23 am

Postby ሾተል » Tue Jul 17, 2012 9:28 am

ይኼ አባዱላ የሚሉት ሚኒባስ ህዝቡን ጨረሰ እኮ::መቼ ይሆን ይኸ አሰቃቂ የመኪና አደጋ የሚቆመው?
ፈጣኑ መኪና ገባላቸው.....አስፋልቱ ለጥ አለላቸው.....ጫቱ እንደልብ ተተከለላቸው.....የመኪኖቹ ባለቤቶች ገንዘብ አንሰፈሰፋቸው...ሹፌሮቹን 24 ሰአት ያለ እረፍት እንዲነዱና ገንዘብ እንዲሰበስቡ ግፊት ሰጧቸው....የዚህ ሁሉ ኮንብኔሽን ህዝቡን ጨረሰ::

ለማንኛውም በቃ ይበለን::

ለሟቹ ጋዜጠኛ ነፍስ ይማር ብለናል::ለቤተሰቦቹና ወዳጆቹ መጽናናትን ይስጥልን::

ሾተል ነን.....ያሳዝናል
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9643
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria


Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 5 guests