ያላለለት

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ያላለለት

Postby እቴጌይት » Sun Aug 19, 2012 10:56 pm

ወንዙ ተገድቦ - መስኖ ተበጅቶ
አረሙ ተነቅሎ - ምድሩ ተኮትኩቶ
ተካዩ ቢለፋ - አብቃዩ ቢድከምም
ለቁጥቋጦ ያለው - አድጎ ዛፍ አይሆንም!


ወይስ ይሆናል?
እቴጌይት
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 656
Joined: Sun Sep 23, 2007 10:38 pm

Re: ያላለለት

Postby ዋኖስ » Sat Aug 25, 2012 5:16 pm

እቴጌይት wrote:ወንዙ ተገድቦ - መስኖ ተበጅቶ
አረሙ ተነቅሎ - ምድሩ ተኮትኩቶ
ተካዩ ቢለፋ - አብቃዩ ቢድከምም
ለቁጥቋጦ ያለው - አድጎ ዛፍ አይሆንም!


ወይስ ይሆናል?


ለቁጥቋጦ ያለው አድጎ ዛፍ አይሆንም፤

ጠዋት ፤

የተሰጠዉ እድሉ ከሆነ፤ ተደንግጎ ሕጉ፣

ቢወለድም አያድግ፤

ቢዘራም አይበቅል፤ ቢስማማዉም በልጉ።

እንዲያዉ ከንቱ ልፋት፤

እንዲያው ከንቱ ድክመት ቢሆን እንጅ ትርፉ፣

ቅንጣት አይጨምርም፤ የሰዉ ልጅ በዘርፉ።

እጅግ የሚገርሙኝ ሁለት ነገር አሉ፣

ሞት እና እንሽላሊት፤

ካብ አያቆማቸዉ ዙፋንን ሲደፍሩ ፤ ደርሰዉ ዘዉ ሲሉ።ዳሞት ከዳሞት [i]
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Re: ያላለለት

Postby ሳምራውው33 » Sat Aug 25, 2012 10:19 pm

እቴጌይት wrote:ወንዙ ተገድቦ - መስኖ ተበጅቶ
አረሙ ተነቅሎ - ምድሩ ተኮትኩቶ
ተካዩ ቢለፋ - አብቃዩ ቢድከምም
ለቁጥቋጦ ያለው - አድጎ ዛፍ አይሆንም!


ወይስ ይሆናል?


ከቁጥቋጦ አያልፍም
ፍጹም አይሆንም ዛፍ
ውጪው ሰውነቱ
አይረዝምም አይሎጋም
ቢደከም ቢለፋም
ለውጫዊው አካል
ውስጡ ከገረጣ
የውጭው አይፈካም
ቁምጭጭ ቅጭጭ ብሎ ቆጥቁጦ ይቀራል
የተካዩን ጉልበት አሟጦ ያስቀራል :!:
ሳምራውው33
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 530
Joined: Thu Jun 21, 2007 12:23 am

Postby እቴጌይት » Sun Aug 26, 2012 4:16 am

ግሩም ግሩም

ታዲይ ሲፈጥር ጌታ - እራሱ ደንግጎ
አንዱን ለቁጥቋጦ - አንዱን ለዛፍ አርጎ
ዕምቅድመ ዓለም ገና - ከወስነ ቀድሞ
ሰው ለምን ይደክማል -ይተጋል ደጋግሞ?
በቃ መተኛት ነው - መዋል ነው ተጋድሞ :lol: :lol:

ወይስ.............
እቴጌይት
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 656
Joined: Sun Sep 23, 2007 10:38 pm

Postby ሳምራውው33 » Sun Aug 26, 2012 10:12 pm

ተጋደሞ ተንጋሎ መተኛት ባል ከፋ
አንገትን ለትራስ ሰጥቶ ለመከዳ
ነገር ግን ሳይደክም ሳይለፋ ሳይተጋ
የሰው ልጅ ቢተኛ ሲመሽም ሲነጋ
ከንቱ ሆኖ ይቀራል ሸክም ሆኖ ላልጋ ::
ሳምራውው33
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 530
Joined: Thu Jun 21, 2007 12:23 am

Postby ዲያስፖራ » Mon Aug 27, 2012 3:02 pm

ከንቱ ይሆናል ብሎ ይንገራችሁ
አቦ አትመኑት ፍሬው አብቦ ባይን እያያችሁ
ይሰው ለጅ ደካሙ የሚታየው
ከሞተ በሁላ በልጅ ለጁ ላይ ነው
አልሰማችሁም ሞይ ሰም ከመቃብር በላይ
እሰቲ ዘርታችሁ እንስማ ፍሬውን ስናይ
ቀይ ባህር ድንበራችን ነው !!!!
I Love Ethiopia !!!
ዲያስፖራ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 781
Joined: Wed Apr 29, 2009 4:39 pm
Location: no

Postby አባዊርቱ » Wed Aug 29, 2012 6:01 pm

ፍሬውን ለማየት የአንድዬን ስራ
መታደልን ያሻል አያ ዲያስፖራ!!!
መታደልን ያልኩት ድንገት ያልገባቹ
ፍቅርን ከቅንነት አንድ ላይ ጠምዳቹ
ብታዩት መልካም ነው አንድዬ ይርዳቹ!!

ግና የፈጣሪን ረቂቁን ተግባር
ካነሳቹ አይቀር አድምጡኝ ከምር!!

ፈጣሪ በህጉ አንዱን ለቁጥቁዋጦ
ሌላኛውን ለዛፍ አሳምሮ አስቀምጦ
ምነኛ ቢታዘን ምነኛ ቢያለቅሱ
ተጋድሞ ከመዋል ይሰውረን እሱ:):)!!!
አባዊርቱ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 800
Joined: Mon Feb 23, 2004 4:11 am

Postby መላጣ » Thu Aug 30, 2012 1:14 pm

ወንዙ ተገድቦ በውኃ ቢረካ
ቁጥቋጦ አምሮበት ቅጠሉ ቢፈካ
ለማታለል እንጂ የለውም በረካ::

አልፎልኛል ብሎ ማን?
ቁጥቋጦ በሥሩ ቢመካ
ፈጣሪ ኃያል ነው ማንንም አይተካ
ከሥሩ ፈንቅሎ ያወጣል መቼ?
ጊዜአቱ ሲቃረብ ሁኔታው ሲሳካ::

የሰው ልጅ ድካሙ ተንኮሉ
ማብቂያ ሳያኖር ላመሉ
ያልፋታል ተንጋሎ ሰው ሁሉ::

ከዚህ አድነን ከመዓቱ
ከቁጥቋጦ ዘር ባለቤቱ:: :( :(
መላጣ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 606
Joined: Fri Feb 27, 2004 10:30 am

Re: ያላለለት

Postby ሓየት11 » Thu Aug 30, 2012 1:26 pm

ወንዙ ባይገደብ ... መስኖው ባይበጅም
አረም ባይነቀል - ምድሩ ባይኮተኮትም
ተካዩ ባይለፋ - አብቃዩ ባይደክምም
ለዛፍ ያለው እንደሆን ... ፈጽሞ አይቀጭጭም ... ቁጥቋምጦም አይሆንም ...

:lol: :lol: :lol:

ጸለምተኞችን የምናናውጠው
ሓየት ነን :wink:

እቴጌይት wrote:ወንዙ ተገድቦ - መስኖ ተበጅቶ
አረሙ ተነቅሎ - ምድሩ ተኮትኩቶ
ተካዩ ቢለፋ - አብቃዩ ቢድከምም
ለቁጥቋጦ ያለው - አድጎ ዛፍ አይሆንም!


ወይስ ይሆናል?
ሓየት11
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2945
Joined: Sun Apr 06, 2008 7:34 pm
Location: ላን'ሊይ

Postby ጦምኔው » Thu Aug 30, 2012 2:10 pm

እቴጌይት wrote:ግሩም ግሩም

ታዲይ ሲፈጥር ጌታ - እራሱ ደንግጎ
አንዱን ለቁጥቋጦ - አንዱን ለዛፍ አርጎ
ዕምቅድመ ዓለም ገና - ከወስነ ቀድሞ
ሰው ለምን ይደክማል -ይተጋል ደጋግሞ?
በቃ መተኛት ነው - መዋል ነው ተጋድሞ :lol: :lol:

ወይስ.............


ገና ኦሪት ዘመን ከመሬት ሲያበጀው
እስትንፋስን ሰጥቶ
አምሳያው አድርጎ በእጁ አድቦልቡሎ
ከዕጽዋት ለይቶ
ከፍጡራን በላይ በሁሉ አሰልጥኖ
ሁሉን አስገዝቶ
ለተፈጠረበት ታላቅ የጌታ ክብር
በክብር ተቀብቶ
ዝግጁ መሆኑን ጌታ ሲፈትነው
ዕጽን አሳይቶ
ነጻ ምርጫን ሰጠው ራሱን ከልሎ
ዛፍ ትሆን ቁጥቋጦ አንተው ምረጥ ብሎ::
ጦምኔው
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1529
Joined: Sun Jan 14, 2007 10:40 pm
Location: Right here

Postby ሓየት11 » Thu Aug 30, 2012 2:32 pm

ጠምኔው ራስታዎችን መሰልከኝሳ ... :lol:

እኔ ደሞ እንዲህ ልበላት እህታችንን ...ቅቅቅ

ሰው የሚደክም የሚለፋው
የሚተጋው ደጋግሞ
ለዛፍ ያለው ከዛፍ
ለቁጥቋጦ ያለውን ከቁጥቋጦ
ቶሎ ላድርስ ብሎ ነው::

እንጂማ

ምን ቢለፋ ምን ቢደክም
ምንስ ታምር ቢሰራ ምን ቢጸልይም
ዛፉን ለቁጥቋጦ
ቁጥቋጦውን ለዛፍ
ማብቃት አይችልም::

ደግሞም

ዘሩን መርጦ ችግኝ ካላፈላ
ጓሮውን አለሳልሶ - አፈሩን ካላብላላ
ውሀ አጠጥቶ - ችግኙን ካላጸደቀ
ተጋድሞማ ከዋለ - አልጋ ላይ ከወደቀ
ቁጥቋጦንስ ቢሆን እንዴት ጠበቀ :?: :?: :lol: :lol:


ጦምኔው wrote:
እቴጌይት wrote:ግሩም ግሩም

ታዲይ ሲፈጥር ጌታ - እራሱ ደንግጎ
አንዱን ለቁጥቋጦ - አንዱን ለዛፍ አርጎ
ዕምቅድመ ዓለም ገና - ከወስነ ቀድሞ
ሰው ለምን ይደክማል -ይተጋል ደጋግሞ?
በቃ መተኛት ነው - መዋል ነው ተጋድሞ :lol: :lol:

ወይስ.............


ገና ኦሪት ዘመን ከመሬት ሲያበጀው
እስትንፋስን ሰጥቶ
አምሳያው አድርጎ በእጁ አድቦልቡሎ
ከዕጽዋት ለይቶ
ከፍጡራን በላይ በሁሉ አሰልጥኖ
ሁሉን አስገዝቶ
ለተፈጠረበት ታላቅ የጌታ ክብር
በክብር ተቀብቶ
ዝግጁ መሆኑን ጌታ ሲፈትነው
ዕጽን አሳይቶ
ነጻ ምርጫን ሰጠው ራሱን ከልሎ
ዛፍ ትሆን ቁጥቋጦ አንተው ምረጥ ብሎ::
ሓየት11
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2945
Joined: Sun Apr 06, 2008 7:34 pm
Location: ላን'ሊይ

Postby እቴጌይት » Thu Aug 30, 2012 9:34 pm

ጦምኔው wrote:ለተፈጠረበት ታላቅ የጌታ ክብር
በክብር ተቀብቶ
ዝግጁ መሆኑን ጌታ ሲፈትነው
ዕጽን አሳይቶ
ነጻ ምርጫን ሰጠው ራሱን ከልሎ
ዛፍ ትሆን ቁጥቋጦ አንተው ምረጥ ብሎ::[/i]ዓፈሩን ሲጠፈጥፍ
...................ሸክላ ሰሪ ፈጣሪ
የዕጁን ሥራ ውጤቱን
..................መልክ ሲሰጥ ባህሪ
አንዱን አስውቦ ቀርጾ
................ለክብር ጌጥ ማኖሪያ
ሌላውን ለእሳት ውሎ
..............ካለው አመድ መዛቂያ
የአፈር ገሉ ቢለፋ
ቢጥር ልቡ እስኪጠፋ
ከጭስ ኑሮ እንዳይወጣ
ተደነግጎለት ዕጣ
አመድ አፋሽ ካረገው
አንጥረኛው ሲፈጥረው
ፈጣሪ ነጻ ፍቃድ
................ምርጫ ሰቷል ስትሉ
ሌት ተቀን የሚዝቀው
...............ምን ይላችኋል ገሉ?


መታሰቢያነቱ ያለጥፋታቸው ለመከራ ኑሮ ለተዳረጉ የሰው ዘሮች ይሁንልኝ :( :(
እቴጌይት
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 656
Joined: Sun Sep 23, 2007 10:38 pm

Postby ሳምራውው33 » Thu Aug 30, 2012 11:26 pm

እቴጌይት wrote:
ጦምኔው wrote:ለተፈጠረበት ታላቅ የጌታ ክብር
በክብር ተቀብቶ
ዝግጁ መሆኑን ጌታ ሲፈትነው
ዕጽን አሳይቶ
ነጻ ምርጫን ሰጠው ራሱን ከልሎ
ዛፍ ትሆን ቁጥቋጦ አንተው ምረጥ ብሎ::[/i]ዓፈሩን ሲጠፈጥፍ
...................ሸክላ ሰሪ ፈጣሪ
የዕጁን ሥራ ውጤቱን
..................መልክ ሲሰጥ ባህሪ
አንዱን አስውቦ ቀርጾ
................ለክብር ጌጥ ማኖሪያ
ሌላውን ለእሳት ውሎ
..............ካለው አመድ መዛቂያ
የአፈር ገሉ ቢለፋ
ቢጥር ልቡ እስኪጠፋ
ከጭስ ኑሮ እንዳይወጣ
ተደነግጎለት ዕጣ
አመድ አፋሽ ካረገው
አንጥረኛው ሲፈጥረው
ፈጣሪ ነጻ ፍቃድ
................ምርጫ ሰቷል ስትሉ
ሌት ተቀን የሚዝቀው
...............ምን ይላችኋል ገሉ?


መታሰቢያነቱ ያለጥፋታቸው ለመከራ ኑሮ ለተዳረጉ የሰው ዘሮች ይሁንልኝ :( :(


ፈጣሪማ ቸር ነው ከቶ ምን በደለ ?
ምድርን አሳምሮ ለአዳም አስረከበ
ትእዛዝንም እንዲህ አብሮ ተናገረ
ይህንን ሁል ፍሬ በልተህ ትጠግባለህ
አንዲትዋን ግን ፍሬ የበላህ እንደሆን
እድሜህ ይወሰናል ሞትን ትሞታለህ::
አዳምም አልቻለም ያቺን ፍሬ በላ
ሞትና እርግማንን በትውልዱ ዘራ::
የዚህ ዘር ውጤት ነው ምድርን የበከለው
ክፍፍል ልዮነት በኛ የፈጠረው
አንዱ ጠግቦ ሲያድር ሌላው የቸገረው::
ሳምራውው33
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 530
Joined: Thu Jun 21, 2007 12:23 am

Postby እቴጌይት » Fri Aug 31, 2012 1:11 am

ሳምራውው33 wrote:
ፈጣሪማ ቸር ነው ከቶ ምን በደለ ?
ምድርን አሳምሮ ለአዳም አስረከበ
ትእዛዝንም እንዲህ አብሮ ተናገረ
ይህንን ሁል ፍሬ በልተህ ትጠግባለህ
አንዲትዋን ግን ፍሬ የበላህ እንደሆን
እድሜህ ይወሰናል ሞትን ትሞታለህ::
አዳምም አልቻለም ያቺን ፍሬ በላ
ሞትና እርግማንን በትውልዱ ዘራ::
የዚህ ዘር ውጤት ነው ምድርን የበከለው
ክፍፍል ልዮነት በኛ የፈጠረው
አንዱ ጠግቦ ሲያድር ሌላው የቸገረው::


አዳም ቢበላ ቀጥፎ
ሕገ ትዕዛዝ ተላልፎ
ይቀጣ እንጂ ራስ ችሎ
በሥራው ተወንጅሎ
ምን ባጠፋ ነው ልጁ
ውላጅ ፍናጅ ቅናጁ
መከራ ሚያይ ያለ'ጁ?

ወይስ????
እቴጌይት
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 656
Joined: Sun Sep 23, 2007 10:38 pm

Postby ጦምኔው » Fri Aug 31, 2012 1:50 am

እቴጌይት wrote:
አዳም ቢበላ ቀጥፎ
ሕገ ትዕዛዝ ተላልፎ
ይቀጣ እንጂ ራስ ችሎ
በሥራው ተወንጅሎ
ምን ባጠፋ ነው ልጁ
ውላጅ ፍናጅ ቅናጁ
መከራ ሚያይ ያለ'ጁ?

ወይስ????


ጠልቀው ቢያነቡት ክታቡን
የፍጥረት መዝገብ ዶሴውን
አዳም ተፈጥሮው አልነበር!
ከገነት ወጥቶ ለመኖር
ወልዶ እና ከብዶ ለመክበር::
ነጻ ፈቃዱን ተጠቅሞ
ጎረሳት በለስ ዕጺቱን
ክፉ ደጉን ነጋሪቱን::
የመጣው መውለድ መዋለድ
ለጥቆ ነው ካዳም መሰደድ
ከምድረ ገነት መወገድ::
.
.
.
አዳም አባ ኩሉ ፍጥረት
ሲነገረው 'ንዲኖር በምድር
አንድ ግለሰብ ቢሆንም
ከአጋሩ ከሄዋን ጋር
ብቸኛው ሰው እርሱ ነበር::
.
.
.
ለይልኝ ይህችንማ
.
.


መውለድ መዋለዱ የመጣ
አዳም ከገነት ከወጣ
በፍቃዱ ጸጋውን ካጣ::


ሐየት :D ዕጽና ራስታ
ጦምኔው
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1529
Joined: Sun Jan 14, 2007 10:40 pm
Location: Right here

Next

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest