ያላለለት

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby እቴጌይት » Fri Aug 31, 2012 11:31 pm

ጦምኔው wrote:
ጠልቀው ቢያነቡት ክታቡን
የፍጥረት መዝገብ ዶሴውን
አዳም ተፈጥሮው አልነበር!
ከገነት ወጥቶ ለመኖር
ወልዶ እና ከብዶ ለመክበር::
ነጻ ፈቃዱን ተጠቅሞ
ጎረሳት በለስ ዕጺቱን
ክፉ ደጉን ነጋሪቱን::
የመጣው መውለድ መዋለድ
ለጥቆ ነው ካዳም መሰደድ
ከምድረ ገነት መወገድ::
.
.
.
አዳም አባ ኩሉ ፍጥረት
ሲነገረው 'ንዲኖር በምድር
አንድ ግለሰብ ቢሆንም
ከአጋሩ ከሄዋን ጋር
ብቸኛው ሰው እርሱ ነበር::
.
.
.
ለይልኝ ይህችንማ
.
.


መውለድ መዋለዱ የመጣ
አዳም ከገነት ከወጣ
በፍቃዱ ጸጋውን ካጣ::


ድንቅ ድንቅ!!


ብዙና ተባዙ - ምድሪቷንም ሙሉ
ብሎ የባረካቸው - የመረቀው ቃሉ
ገና ከፊት እንጂ - ፍሬዋን ሳይበሉ
መች ኍላ ነበር - ገድፈው ከታበሉ?

እንደው ለነገሩ -ነው እንኳን ብንለው.....

የሰው ዘር ሲፈጠር-ምርጫ እንደተሰጠው
በፍቃዱ እንዲኖር- ልቡ በነገረው
'ዛፍ ይሁን ቁጥቋጦ'-ምረጥ ተብሎ ነበር
........................................ብለኸኝ አልነበር?
ታዲያሳ
አዳም ለታበየው - ለገባው ኩነኔ
የልጅ ልጁን መቅጣት - 'በረሀብ በጠኔ'
እንዴት ዳኝነት ነው - ምን ያለ ብያኔ?
....................
ገብሬ በሰረቀ - አመቴ ትታሰር?
አስናቀ ባገባ - መሀመድ ይሞሸር?

ወይስ..............
እቴጌይት
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 656
Joined: Sun Sep 23, 2007 10:38 pm

Postby ሳምራውው33 » Sat Sep 01, 2012 7:02 pm

እቴጌይት wrote:
ጦምኔው wrote:
ጠልቀው ቢያነቡት ክታቡን
የፍጥረት መዝገብ ዶሴውን
አዳም ተፈጥሮው አልነበር!
ከገነት ወጥቶ ለመኖር
ወልዶ እና ከብዶ ለመክበር::
ነጻ ፈቃዱን ተጠቅሞ
ጎረሳት በለስ ዕጺቱን
ክፉ ደጉን ነጋሪቱን::
የመጣው መውለድ መዋለድ
ለጥቆ ነው ካዳም መሰደድ
ከምድረ ገነት መወገድ::
.
.
.
አዳም አባ ኩሉ ፍጥረት
ሲነገረው 'ንዲኖር በምድር
አንድ ግለሰብ ቢሆንም
ከአጋሩ ከሄዋን ጋር
ብቸኛው ሰው እርሱ ነበር::
.
.
.
ለይልኝ ይህችንማ
.
.


መውለድ መዋለዱ የመጣ
አዳም ከገነት ከወጣ
በፍቃዱ ጸጋውን ካጣ::


ድንቅ ድንቅ!!


ብዙና ተባዙ - ምድሪቷንም ሙሉ
ብሎ የባረካቸው - የመረቀው ቃሉ
ገና ከፊት እንጂ - ፍሬዋን ሳይበሉ
መች ኍላ ነበር - ገድፈው ከታበሉ?

እንደው ለነገሩ -ነው እንኳን ብንለው.....

የሰው ዘር ሲፈጠር-ምርጫ እንደተሰጠው
በፍቃዱ እንዲኖር- ልቡ በነገረው
'ዛፍ ይሁን ቁጥቋጦ'-ምረጥ ተብሎ ነበር
........................................ብለኸኝ አልነበር?
ታዲያሳ
አዳም ለታበየው - ለገባው ኩነኔ
የልጅ ልጁን መቅጣት - 'በረሀብ በጠኔ'
እንዴት ዳኝነት ነው - ምን ያለ ብያኔ?
....................
ገብሬ በሰረቀ - አመቴ ትታሰር?
አስናቀ ባገባ - መሀመድ ይሞሸር?

ወይስ..............


ያዢ እንግዲ.....

አንዱ ስንዴ ሞቶ ሌላውን ይወልዳል
አዳምም ሞት ሞቶ ዘሩን ግን አብዝቷል::
ያዳም ዘር በምድር መቀጠል ካለበት
አዳም አፈር ሆኖ መቅረት ከሌለብት
ሀጢያት ኩነኔውን ማውረስ ግድ አለበት::

ያምላካችን ፍርዱ ልክ ሆኖ ምናየው
ስንዴውን ካዳም ጋር ካመሳሰልነው ነው::

አሁንስ... :roll: :roll: :roll:
ሳምራውው33
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 530
Joined: Thu Jun 21, 2007 12:23 am

Previous

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests