ኃይሉ ገ/ዮሀንስ (ገሞራው) ተሸለሙ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ኃይሉ ገ/ዮሀንስ (ገሞራው) ተሸለሙ

Postby ወለላዬ » Fri Sep 14, 2012 6:34 pm

የኢትዮጵያ ድምጽ ሬድዮ (ስዊድን) አመታዊ በአሉን አከበረ
ደራሲ ገጣሚና ባለቅኔ ኃይሉ ገብረዮሃንስ እና ጋዜጠኛ አህመድ አሊ ተሸላሚ ሆኑ
ማትያስ ከተማ

Ethiopia Zare (ሐሙስ መስከረም 3 ቀን 2005 ዓ.ም. September 13, 2012)፦ የኢትዮጵያን አዲስ ዓመት አንተርሶ የምስረታ በአሉን በየዓመቱ የሚአከብረው የኢትዮጵያ ድምጽ ራድዮ አስራ ዘጠነኛ አመቱን በርካታ ኢትዮጵያውያን ታዳሚዎች በተገኙበት ቅዳሜ ሴፕቴንበር 8,2012 (ጳጉሜ 3,2004 ዓ.ም) አከበረ። በበአሉ አከባበር ላይ ደራሲ ገጣሚና ባለቅኔ ኃይሉ ገብረዮሃንስን በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን የተዘጋጀላቸውንም የክብር ሽልማት ተቀብለዋል።

ለጋዜጠኛ አህመድ አሊ ደግሞ ከራድዮኑ ምስረታ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ላደረጉት አገልጐት የምስጋናና የክብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።በተጨማሪም ከአሜሪካንና ከእንግሊዝ የመጡት ድምጻዊ ተሾመ አሰግድና ድምጻዊት የዝና ነጋሽ በዓሉን የደመቀ አድርገውት ውለዋል።

ዝግጅቱ ረፋዱን ከ13፡00 ጀምሮ በምሳ ግብዣ የተጀመረው ሲሆን የዝግጅቱን መክፈቻ ያደረጉት የኢትዮጵያ ድምጽ ሬድዮ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ እንዳለ ወ/ስላሴ ናቸው ። አቶ እንዳለ በንግግራቸው የሬድዮኑን የስራ አገልግሎትና ለተጠቃሚው ያደረገውን የስራ ፍሬ ገልጸው ሬድዮ ለየት ብሎ እንዲታይ የሚአደርገው ደግሞ ዘርፈ ብዙ በሆነው ዝግጅቱ እንደሆነ ጠቁመዋል።በማያያዝም ህብረተሰቡ ያላቋረጠ ድጋፍ በማድረጉ አመስግነው ለወደፊቱም ይኸው ድጋፉ ሳያቋርጥ እንዲቀጥል አሳስበዋል።ከአቶ እንዳለ ንግግር ማብቂያ በኋላ የዝግጅቱ መሪ ወ/ሮ እመቤት ፋንታሁን ዝግጅቱ ምን አይነት መልክ እንዳለው አሳውቀው ዝግጅቱን የጀመሩት በክብር እንግዳውን በደራሲ በገጣሚና በባለ ቅኔ ኃይሉ ገብረ ዮሃንስ የህይወት ታሪክና ዙርያና ያበረከቷቸውን የስነጽሁፍ ስራ በመዘርዘር ነበር። ደራሲው ዘመናት በማይሽረው ብዕራቸው የሚታወቁ እንደሆኑ ገልጸው በተለይም ”በረከተ መርገም” በተባለ የግጥም ስራቸው ለእስር ለእንግልት ለስደትና ለመንከራተት እንዳበቃቸው አስረድተዋል።

ስለደራሲው በመጠኑ ለመግለጽና ማንነታቸውን ለማሳወቅ እንጂ ያላቸውን ታሪክና ስራ ለመዘርዘር ይህ አጭር ሰአት በቂ እንደማይሆን የገለጹት ወ/ሮ እመቤት ደራሲው በስደት አለም ለህዝብ ያበረከቷቸውን መጽሐፍቶች በዝርዝር አሰምተዋል። ከመጻህፍቶቹ መካከል ዜሮ ፊታውራሪ ፣ ቆርጠሃት ጣልልኝ፤ እናትክን ብሉልኝ የተባሉት ይገኙበታል።

ከዚህ አጭር ገለጻ በኋላ የተዘጋጀው የክብር ሸልማት ስጦታ የቦርዱ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ እንዳለ ወ/ስላሴ ለደራሲ ኃይሉ ገብረዮሃንስ አበርክተውል።ደራሲው በበኩላቸው በዚህ ስፍራ ከኢትዮጵያውያን ወገኖቻቸው ጋር በመገኘት በዓሉን አብረው በማሳለፋቸው እንደተደሰቱ ገልጸው ስለተደረገላቸም ክብርና ስጦታ አመስግነዋል።

ቀጥሎም የኢትዮጵያ ድምጽ ሬድዮን በማቋቋም በማደራጀትና በበምራት እንዲሁም የዝግጅት አቅራቢ በመሆን ለአስራ ዘጠኝ ዓመታት ያህል የስራ አገልግሎት በመስጠት የቆዩት ጋዜጠኛ አህመድ አሊ ለሰሩት በጎ አገልግሎት የምስጋናና የክብር ሽልማት ከእለቱ የክብር እንግዳ ከደራሲ ኃይሉ ገብረዮሃንስ ተቀብለዋል።

ጋዜጠኛ አህመድ አሊ እሬድዮኑን በመምራት በቆዩበት ወቅት አያሌ ችግሮች እንደደረሰባቸው ተዘርዝሮ ያንን ሁሉ ፈታኝ ችግር በመቋቋም ከመደበኛ ስራቸው ጎን ለጎን በማስኬድ የሬድዮኑን ህልውና ሲአስጠብቁ እንደቆዩ በሽልማቱ ስነስርአት ላይ ተገልጿል። ጋዜጠኛ አህመድ በዛሬው ቀን የተደረግልኝ ሽልማት ፍጹም ያላሰብኩት ሲሆን ከፍተኛም ደስታ እንዲሰማኝ አድርጎኛል ብለዋል።

በበዓሉ ላይ ከተገኙ ታዳሚዎች መካከል ቂስ ፍስሃ ተስፋዬ የኢትዮጵያ ድምጽ ሬድዮ አገልግሎቱ ከፍ ያለ እንደሆነ ገልጸው እስካሁን ስለሰራው እየሰራም ስላለው ተግባር አመስግነዋል። ንግግራቸውንም በመቀጠል የኢትዮጵያ ድምጽ ሬድዮ በመኖሩ ልንሰባበብበት በመቻላችን እድለኞች ነን፣ በጠጨማሪ ከዚህ በላይ ሊአሰባስበን የሚችል የማህበረሰቡ ማህበር ቢኖር ደግሞ ይበልጥ ጠቃሚነት እንደሚኖረው አስረድተዋል።

በየዝግጅቱ ጣልቃ ድምጻውያኑ ተሾመ አሰግድ የዝና ነጋሽ እንዳለ ጌታነህና መረሱ ወንድማገኝ በሙዚቃ መሳሪያና በድምጽ የበዓሉን እንግዳ ሲያዝናኑ አርፍደዋል።በነጻነት አሰፋ የተመራም የህጻናት አበባየሁ ሆይ ተደምጧል።እንዲሁም በቹቹ ባህላዊ ውዝዋዜ ተጋባዙ እየተዝናና አርፍዶ የእለቱ ዝግጅት በዚሁ ተጠናቋል።

Next >
ወለላዬ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 403
Joined: Wed Jan 26, 2005 11:20 am
Location: united states

Re: ኃይሉ ገ/ዮሀንስ (ገሞራው) ተሸለሙ

Postby እንሰት » Fri Sep 14, 2012 6:44 pm

Thank you Matias
እንኩዋን ከዘመን ዘመን አሸጋገረህ::

ወለላዬ wrote:የኢትዮጵያ ድምጽ ሬድዮ (ስዊድን) አመታዊ በአሉን አከበረ

እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby ወለላዬ » Fri Sep 14, 2012 6:56 pm

አሜን እንስት እንኵን አብሮ አሸጋገረን
ወለላዬ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 403
Joined: Wed Jan 26, 2005 11:20 am
Location: united states

Postby tianes » Sat Sep 15, 2012 1:34 pm

ደራሲው በአክራሪ ተቃዋሚነታችው ነው ወይስ በጥበብ ስራቸው የተሸለሙት? :lol:

""ቁንጣን በቁንጣን "" የተሰኘውን የኚህን ገጣሚ ልቦለድ መጽሃፍ ያነበበ ይኖር ይሆን?

የደራሲውን የጥበብ ችሎታ መገመት ለሚፈልግ ... በቂ መጽሀፍ ነው.... አልፎም ልቦለድ እንዴት እንደማይጻፍ ይማሩበታል... :!:

ወለላዬ .... ታገኘሀቸው... ልቦለዱን ላላ ግጥሙን ጠበቅ በልልኝ.....
የማያውቁበትን ሲያጠብቁ የሚያውቁት እንዳይላላ :lol:

ያ ጋዜጠኛ ያልከው ልክፍክፍ ግን ወያኔዎች ሽልማቱን አሁንም ደብድበው እንዳይነጥቁት ተጠንቀቅ በለው... :lol:

........
tianes
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 542
Joined: Mon Aug 20, 2007 10:54 pm

Postby ዲጎኔ » Sat Sep 15, 2012 5:53 pm

ሰላም ለሁላችን ይሁን ለልደቱ ከህደቱ ጀሌው ጭምር
የሀቀኛው መምህራን ማህበር መሪና ደፋሩ ሀቀኛው ጋዜጠኛ ለወያኔ ህጋዊ ተቃዋሚ ነን ባይ ጀሌዎች ባይጥምም ለእኛ ለገባሮቹ ዛሬም በወያኔና በራሳችን ባንዶች ለምንታሰረው ለምንሰደደው ለምንገረፈው ትክክል የቁርጥቀን ልጆች ናቸው
ውድ ወለላ ለዘገባህ እጅግ እያመሰገንኩ ለውድ ገሞራውና ለአህመድ እሰይ አሹ ኢሾ አሰየ በልልኝ::
ዲጎኔ ሞረቴ ከወ/ር ስሂን ተማሪዎች ሰፈር ከባንዶቹ ሩቅ ማዶ ዴሴ

tianes wrote:ደራሲው በአክራሪ ተቃዋሚነታችው ነው ወይስ በጥበብ ስራቸው የተሸለሙት? :lol:

""ቁንጣን በቁንጣን "" የተሰኘውን የኚህን ገጣሚ ልቦለድ መጽሃፍ ያነበበ ይኖር ይሆን?

የደራሲውን የጥበብ ችሎታ መገመት ለሚፈልግ ... በቂ መጽሀፍ ነው.... አልፎም ልቦለድ እንዴት እንደማይጻፍ ይማሩበታል... :!:

ወለላዬ .... ታገኘሀቸው... ልቦለዱን ላላ ግጥሙን ጠበቅ በልልኝ.....
የማያውቁበትን ሲያጠብቁ የሚያውቁት እንዳይላላ :lol:

ያ ጋዜጠኛ ያልከው ልክፍክፍ ግን ወያኔዎች ሽልማቱን አሁንም ደብድበው እንዳይነጥቁት ተጠንቀቅ በለው... :lol:

........
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby tianes » Sat Sep 15, 2012 10:50 pm

ዲጎኔ wrote:ሰላም ለሁላችን ይሁን ለልደቱ ከህደቱ ጀሌው ጭምር
የሀቀኛው መምህራን ማህበር መሪሰላም ዲጎ
አሁንም አልተሻለህም? በማታውቀው ነገር ጥልቅ ማለት አልተው አልክ አይደል....

የመምህራን ማህበሩ ጎሞራውና ገጣሚው ጎሞራው ለየቅል ናቸው... እንደገባኝ ሁለቱንም አታውቃቸውም.... ስለ ልደቱም እንዲሁ ነው ምንም አታውቅም.... የአለማወቅ ችግር በብዙዎች የሚታይ አገር አቅፍ ችግር ነው... ጦሱ በአገር ደረጃ የሚያደርሰው ጥፋት ይህ ነው አይባልም... ዛሬ ጠ. ሚንስትር መሰየም ያቃተው ፓርላማ ባለቤት የሆንነው በአንተ አይነቱ አላዋቂዎች: አርቀው አልተመልካቾችና ችኩሎች ምክንያት ነው....
"የአ.አን አስተዳደርና የታመነልንን 109 የፓርላማ ወንበር ይዘን ለመጪው ምርጫ እንስራ" ሲል የነበረውን አርቆ ተመልካች ሰምተን ቢሆን ኖሮ... ዛሬ መለስ ያባረራቸው የወያኔ ጅቦች ከያሉበት አይጠራሩም ነበር.. እ?
ሳታውቅ: ያነተ አይነቱ ለወይኔ ምንኛ ምቹ ነ :!: :!: :!:

በነገራችን ላይ ልደቱ ሰሞኑን ዶክትረቱን ጨምድዷልና ዶክተር ልደቱ አያሌው ብለህ መጥራት ተለማመድ... ከቻልክ ደግሞ ""መድሎት"" የተሰኘውን የልደቱን ታላቅ መጽሃፍ አንብብ ...
ዲጎ... አንተ ተዘርፍጠህ "ክህደቱ" እያልከ ስትሳደብ እሱ የትና የት ጥሎህ ሄደ!!! የመንደር ውሾችና ግመሉን አስታወሰከኝ :lol:

....
tianes
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 542
Joined: Mon Aug 20, 2007 10:54 pm

Postby ደጉ የት ገባ » Sat Sep 15, 2012 11:57 pm

tianes wrote:

ምነው ቲያኔስ እንዲሕ ታዋርደው ????
በልጅነት የተጀመረ ሌብነት በጉልምስናም ሐይ ባይ ካጣ በስተርጅና እስርቤት ካልከተተ በቀር ይለቃል ብለሕ አትጠብቅ:: ሰውየው የኑዛዜ ወረቀቱም ላይ እንደተሳደበና እንደተራገመ ታሪክ ሰርቶ እንደሚያልፍ አትጠራጠር:: የሱ በሽታ ከካንሰር የባሰ ነው>>>> አለማወቅን አለማወቅ !!!

መልካም አዲስ አመት
ደጉ የት ገባ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 548
Joined: Wed Feb 22, 2006 4:02 am
Location: usa

Postby ዲጎኔ » Sun Sep 16, 2012 3:12 am

ሰላም ለሁላችን ለልደቱ ክህደቱ ቡችሎችም ጭምር
በጦቢያ የፖለቲካ ታሪክ ልደቱከህደቱ ከነደጃች ሀይለስላሴ ጋር የሚቆጠር ባንዳ መሆኑን በተንሸራታች ሞባይል ሀገርኛ ዘይቤ የሚጠራው ህዝባችን ምስክር ነው::
ከዚህ በተረፈ ገሞራው ኒክ የያዘ እኔ የማቀው የመምህራን ማህበሩ የልደቱ ክህደቱ መልማይ በአደባባይ ይስረሸነው የአሰፋ ማሩ የትግል አጋር ነው::እርሱ ካልሆነም የእርሱን የብእር ስም የሚጋራ እንዳለ ማሳወቅ እንጂ የባንዳነት ቁስላችሁ ሲነካ የምትጠራሩ ማፈሪያዎች ማን ሊፈራችሁ!
አህመድ የስዊዲን ሬዲዮ ጋዜጠኛው ጥጋበኛ ወያኔዎች ጥርሱን ያወለቁት ለፍትህ ሲዘግብ እንጂ ይህ ቀላዋጭ ባንዳ እንደሚተቸው መንቀዥቀዡ አልነበረም::
ለማንኛውም ወለላዬ የቀደመውን ሀቀኛ ጸረ ባንዳ ታጋዮች ዝከር እንዳቀረበው የገሞራውን ማንነት እንዲያብራራ በአክብሮት ስጠይቅ አምዱ ወዳላስፈላጊ ስድብ የገባው ይህ ባለጌ ወጥ እየረገጠ ሀቀኛ ተቃዋሚዎችን በልቅ አፉ ሲሳደብ መሆኑን አበክሬ አሰመርበታለሁ::
ዲጎኔ ሞረቴው ከአስመሳይ ተለጣፊ ተቃዋሚዎች ሩቅ ማዶ
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby tianes » Sun Sep 16, 2012 11:33 am

ስለ ጎሞራው ገጣሚው ትንሽ እዚህ ተመልከት.....

http://www.youtube.com/watch?v=o7XvcIJG8Sw&feature=related

የመምህራን ማህበሩ ዋና ጸሀፊ መጠሪያ ስሙ ጎመራው ካሳ ይባላል የተከበረ ታላቅ ሰው ነው:: ዶ/ር ታዬ ታስሮ በነበረበት ወቅት ድርጅቱን በብቃትና በወኔ የመራ ሰው ነው.....

ጎሞራው ገጣሚው ደግሞ ሀይሉ ገ/ ዮሀንስ ይባላል:: ጎሞራው የብእር ስሙ ሲሆን በነውጣኛ ግጥሞቹ የሚታወቅ ሰው ነው... ከ1980 ዎች ጀምሮ ኑሮው ስዊድን ውስጥ ነው... ክሊፑ ላይ የተለያዩ መንግስታት አንገላተውታል ብሎ አቶ መለስ ዜናዊን ያሳያል.. አቶ መለስ ስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት ጎሞራው ስዊድን ነበር ... እና የት አግኝተው እንዳንገላቱት ባውቅ ደስ ይለኛል..

እንዲህ... የሆነውን ያልሆነው ዘባርቀው የሰውን ስም በሌለውና ባልሰራው ለመካብ ወይም ለማጥፋት ሲሞክሩ ደስ አይለኝም... በሚቻለኝ አጋልጣለሁ::
ያኔ ...ዲጎ ... ያምህና ስድብ ትጀምራለህ :lol:
tianes
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 542
Joined: Mon Aug 20, 2007 10:54 pm

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests