ቅምጥሏ ፍቅሬ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ቅምጥሏ ፍቅሬ

Postby ወፌ » Fri Sep 21, 2012 12:33 am

....................ቅምጥል አፍቅሬ
;....................ለሷ ተቸግሬ
......................ኩሽና እዳትገባ ካልጋ እንዳትነሳ
.......................ምግብ አብሳይ ቀጠርኩ ሳስብላት ለሷ
........................የእንጀራው ጠርዝ እንዳይቆርጣት ብዬ
------------አጉራሽም ቀጠርኩኝ አሳቢ መስዬ
........................ቅምጥሏ ፍቅሬ ድንገት ቢያስነጥሳት
.........................ይማርሽ የምትል ሌላም ቀጠርኩላት
..........................የሞልቃቃ ነገር መጨረሻው አያምር
.......................ቅጥ ያጣውን ፍቅሬን ውስጤን ስላየችው
....................ባል ቀጥረህ አምጣልኝ ብላኝ አረፈችው::
ወፌ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 77
Joined: Fri Aug 24, 2007 4:27 pm

Re: ቅምጥሏ ፍቅሬ

Postby ሳምራውው33 » Fri Sep 21, 2012 10:48 am

ወፌ wrote:....................ቅምጥል አፍቅሬ
;....................ለሷ ተቸግሬ
......................ኩሽና እዳትገባ ካልጋ እንዳትነሳ
.......................ምግብ አብሳይ ቀጠርኩ ሳስብላት ለሷ
........................የእንጀራው ጠርዝ እንዳይቆርጣት ብዬ
------------አጉራሽም ቀጠርኩኝ አሳቢ መስዬ
........................ቅምጥሏ ፍቅሬ ድንገት ቢያስነጥሳት
.........................ይማርሽ የምትል ሌላም ቀጠርኩላት
..........................የሞልቃቃ ነገር መጨረሻው አያምር
.......................ቅጥ ያጣውን ፍቅሬን ውስጤን ስላየችው
....................ባል ቀጥረህ አምጣልኝ ብላኝ አረፈችው::

ካፈቀሩ አይቀር እንዲህ ነው ማፍቀር
ምንም ሳያስቀሩ የልቧን መቸር ::
የማሞላቀቅህ ገደብ ልክ የሌለው
ታይቶ ማይታወቅ ብዙ ምግባር ያለው
አበላሽተሀታል በጣም አሞላቀህ
በል ቶሎ ተለያት ባሉንም አምጥተህ ::

ወይስ.......
The love of money is the root of all evil.

ሳምራውው 33 የግጥም አርበኛ
ስንኝ ቋጣሪ በውብ አማርኛ ::
_________________
ሳምራውው33
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 530
Joined: Thu Jun 21, 2007 12:23 am

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest

cron