የሀበሻ ጀብዱ 2

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

የሀበሻ ጀብዱ 2

Postby ፓን ሪዚኮ » Fri Oct 05, 2012 12:39 pm

አቢቹ

አባይ ወንዝ መዳረሻ ጎሀጽዮን የምትባል ትንሽ ; ጥንታዊ እና ታሪካዊ ከተማ ነዋሪዎች እንዲሁ በዘልማድ "ልጁ ገደል" እያሉ የሚጠሯት አንዲት አፋፍ አለች ::

ከዚቺው የልጁ ገደል አፋፍ ላይ ሆኖ ታላቁ የአባይ ወንዝ ጎጃምንና ሸዋን ለሁለት ከፍሎ ;ከሁለቱም ጥቅላይ ግዛቶች ያለ የሌለውንበሙሉ እየጠራረጉ በሚገብሩት ገባር ወንዞቹ እየተረዳ በግርማ ሞገሱና በሀይለኝነቱ እየኮራ የሀገር ንብረት እየዘረፈ ያለ አጋች ወደ ሱዳን ሲገሰግስ ቁልጭ ብሎ ይታያል ... አጋች የሌለው ዘራፊ

አንድ አዛውንት ሁል ግዜ ከሰአት በኋላ በማንኛውም የአየር ጸባይ አካላቸውን መሸከም የተሳናቸው የሚመስሉ እግሮቻቸውን ይጎትታሉ እንጂ በግሮቻቸው ይሄዳሉ : ይራመዳሉ ተብሎ ማሰብ በማይቻልበት ሁኔታ እያዘገሙ ከልጁ ገደል አፋፍ ላይ ካለች አንዲት ትንሽና ጠፍጣፋ ቋጥኝ ላይ ይቀመጡና ጀንበር እስከምትጠልቅ ድረስ ከዛች ቋጥኝ ላይ ሳይነሱ በዚያ የአባይ ቆላማ ቀበሌ ላይ ሲያፈጡ አምሽተው እንዳመጣጣቸው ሁሉ እግሮቻቸውን እየጎተቱ ወደ ቤታቸው ይመለሳሉ:[/b]
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Re: የሀበሻ ጀብዱ 2

Postby ሓየት11 » Fri Oct 05, 2012 2:15 pm

ፓኑ ዘ ግሬት

እንዴት ነህ ወዳጄ ...

የሓበሻ ጀብዱ ቅጽ ሁለት ደረሰ ነው የምትለኝ? ... ጎሽ ጎሽ ... ተባረክ:: ... ዋርካ ያፈራችህ ብቸኛው ጀግና ወጥቶሀል:: ... የምሬን ነው ... ትልቅ ታሪክ ሰርተህ በማለፍ ላይ ነህ:: ... ግን ግን አደራ የምልህ ነገር አለኝ ...

በመጀሪያው ቅጽህ የነበሩ ድክመቶችን አስተካክለህ ና ::... የቃላት ችግር, የአረፍተ ነገሮች አለመገጣጠምና መንዛዛት እዚህም እዛም ሲደጋገም ... የሚጥመውን ታሪክ አሰልቺ ያደርገዋልና ... ጥንቃቄ ወስደህ ስራው:: ... ባይሆን ... ከቢራ ብኋላ ... መከለሱንና መጻፉን ተወው ... ቅቅቅ ... ህትመት ላይም የሚጎድሉ ገጾች እንዳይኖሩ ... በጥንቃቄ ይመርመርልን ...

ሀያሲ ወ አንባቢ
ሓየት ነን

ከአድናቂዎችህ መንደር

ፓን ሪዚኮ wrote:አቢቹ

አባይ ወንዝ መዳረሻ ጎሀጽዮን የምትባል ትንሽ ; ጥንታዊ እና ታሪካዊ ከተማ ነዋሪዎች እንዲሁ በዘልማድ "ልጁ ገደል" እያሉ የሚጠሯት አንዲት አፋፍ አለች ::

ከዚቺው የልጁ ገደል አፋፍ ላይ ሆኖ ታላቁ የአባይ ወንዝ ጎጃምንና ሸዋን ለሁለት ከፍሎ ;ከሁለቱም ጥቅላይ ግዛቶች ያለ የሌለውንበሙሉ እየጠራረጉ በሚገብሩት ገባር ወንዞቹ እየተረዳ በግርማ ሞገሱና በሀይለኝነቱ እየኮራ የሀገር ንብረት እየዘረፈ ያለ አጋች ወደ ሱዳን ሲገሰግስ ቁልጭ ብሎ ይታያል ... አጋች የሌለው ዘራፊ

አንድ አዛውንት ሁል ግዜ ከሰአት በኋላ በማንኛውም የአየር ጸባይ አካላቸውን መሸከም የተሳናቸው የሚመስሉ እግሮቻቸውን ይጎትታሉ እንጂ በግሮቻቸው ይሄዳሉ : ይራመዳሉ ተብሎ ማሰብ በማይቻልበት ሁኔታ እያዘገሙ ከልጁ ገደል አፋፍ ላይ ካለች አንዲት ትንሽና ጠፍጣፋ ቋጥኝ ላይ ይቀመጡና ጀንበር እስከምትጠልቅ ድረስ ከዛች ቋጥኝ ላይ ሳይነሱ በዚያ የአባይ ቆላማ ቀበሌ ላይ ሲያፈጡ አምሽተው እንዳመጣጣቸው ሁሉ እግሮቻቸውን እየጎተቱ ወደ ቤታቸው ይመለሳሉ:[/b]
ሓየት11
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2945
Joined: Sun Apr 06, 2008 7:34 pm
Location: ላን'ሊይ

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot], Google Adsense [Bot] and 6 guests