አስተያየት መስጫ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው አጭር ልብ ወለድ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ክቡራን » Wed Oct 24, 2012 2:26 pm

አንድ ነገር ረስቼ , ባለፈው በስካራም መጣጥፍ ህይወቴ ታነጸ ያለከውን አንብቤ እስኪ አብራራልኝ ብዬህ እኮ ዝም አልከኝ ወንድሜ ዲጎኔ ...ፍቃድህ ሆኖ ትንሽ ማብራሪያ ብታክልበት ብዬ ነው:: :D
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8154
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby recho » Wed Oct 24, 2012 2:29 pm

ክቡራን wrote:አንድ ነገር ረስቼ , ባለፈው በስካራም መጣጥፍ ህይወቴ ታነጸ ያለከውን አንብቤ እስኪ አብራራልኝ ብዬህ እኮ ዝም አልከኝ ወንድሜ ዲጎኔ ...ፍቃድህ ሆኖ ትንሽ ማብራሪያ ብታክልበት ብዬ ነው:: :D
ክቡ ሆዴ :lol: :lol: :lol: :lol: ቶፕ ቀልድ ኦፍ ዘ ዴይ ብያታለሁ .. መልሱን ለመስማት በጉጉት ላይ ነኝ .. ( ኢን ሲሪየስ ኖት ታዲያ ማሪያምን ነገር እየፈለግኩኝ አይደለም :lol: ከምሬ አስቆኝ ነው )
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby ዲጎኔ » Wed Oct 24, 2012 3:51 pm

ሙዝ1 wrote:የስታተስ ልዩነት ነዉ .... ቂቂቂቂ ....
ቂቂቂቅ ሀሀሀሀሀ ውውውውው ሂሂሂሂ
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby ሙዝ1 » Wed Oct 24, 2012 5:29 pm

ዲጎኔ wrote:
ሙዝ1 wrote:የስታተስ ልዩነት ነዉ .... ቂቂቂቂ ....
ቂቂቂቅ ሀሀሀሀሀ ውውውውው ሂሂሂሂ


አይዞህ አትስጋ .... በተግባር እየታየ ያለ ነገር ነዉ :lol: :lol: :lol: ... አንተ እኔን የምትበልጠኝ በእድሜና በጸጉር ቀለም ብዛት ነዉ .. :wink: .... ቀብዣራ ባትሆን ኖሮ በጥቁርና ነጭ የተጻፈዉን አንብበህ መልስን ትሰጥ ነበር .... ያዉ በዝቅተኝነት ስሜት ህይወትህን ሙሉ የገፋህ ስለሆንክ ያልኩት ስድብ መሰለህና ተደናብረህ ፖለቲካዊ ይዘት ያለዉ አስመሰልከዉ ... ... ለነገሩ ይህንን ያክል ጊዜ በህይወት ስትኖር የምትፈልገዉን እንኳን ጠንቅቀህ የማታቅ ህይወት ያቀረበችልህን ብቻ የምትመገብ ድዉይ ለመሆንህ ከዋርካ በላይ ምስክር ይኖር ይሆን? ገንገበት ....
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Postby ዲጎኔ » Wed Oct 24, 2012 5:47 pm

ሰላም ለሁሉ የስድቡ ሊቀሊቃውንት ለገሰ ዜናዊ ሳይበር ተላላኪ ጭምር
ከአሁን በሁዋላ እኔም እንደአቶ ተመስገን ጌታህ መለስን እንዳሉት በወረድክበት ወርጄአለመላለስም!ከወደቃችሁበት መቀመቅ እድትወጡ የሚደርስላችሁን እጅ ነካሾች ናችሁና ታሳዝናላችሁ...መቀመቁ ይመቻችሁ....

ውድ እንስት ይቅርታ በመልካሙ ዘገባህ በርታ! ስማቸው የተነቀፈ የእምነት ታላቆቼን ገድል በተከፈተላቸው አምድ በማንሳቴ በተሳዳቢዎችተወረፍኩ::የሰዎቹን ስራ ከወደደን ዘራቸውና እምነታቸውንም ማውጋት ነውር አልነበረም:: ስነምግባር የጎደለው ከቅምቢቢት..ጋር ያደገ የሸገር ወያኔ መሁኑን ባውቅም ቀና መለስኩ በለየለት የሳይበር ወያኔ አጋሩም ተወረፍኩ ቤትህ የበለጠ እንዳይበላሽ ሄጃለሁ ....

ሙዝ1 wrote: በዝቅተኝነት ስሜት ህይወትህን ሙሉ የገፋህ ድዉይ ...... ገንገበት ....
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby ዞብል2 » Wed Oct 24, 2012 6:25 pm

ሙዝ1(ጋሽ አምበርብር) :P ዲጎኒ(ጉማሬውን) ኑሮ እና መኖር የተደባለቀበት ሳይሆን :wink: የባረቀብት ሰው ስለ ሆነ ተወው :wink:ይሄ ያልተወራረደ ዕድሜ ያካበተ ሽምትር ከረገመህ :wink: ባለ 2ሺ የእርሻ ኤክስፕርቶች ሀላፊ ያደርግህና መያዣ መጨበጫ እንዳያሳጣህ :P :lol: :lol:

** በዝቅተኝነት ህይወትህን የገፋህ ድውይ :P ይቺ አሪፍ አባባል ናት :lol: :lol:

**ዲጎው በል አንጥፈህ ተቀመጥ ዋርካም ከተገፉት....እንዲህ ከሆኑት...... ከዚህ ማዶ ምናምን.....ወዘተ ከሚል አጭበርባሪ ሆዳም ታርፋለች :P :lol: :lol:

ዞብል ከአራዳ
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2270
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

ተመስገን ገብሬ

Postby እንሰት » Wed Oct 24, 2012 8:36 pm

ዘርዐይ ደረስ wrote:ሰላም እንሰት:-

የደራሲውን ሥም ባላስታውስም 'የጉለሌው ሰካራም' የመጀመርያው የአማርኛ አጭር ልብወለድ መሆኑን ማንበቤ ትዝ ይለኛል::በመጽሐፍ መልክ መታተሙን ግን ከአንተ ጽሑፍ ነው የተረዳሁት::ደራሲው በጋዜጣ ላይ ያወጣው ይመስለኝ ነበር::የመጀመርያው የአማርኛ አጫጭር ልቦለድ መድበል በ1948 የታተመው የታደሰ ሊበን 'መስከረም' ነው ሲባል ነበር የምሰማው::ለማንኛውም ይህን 'ፋና ወጊ' ዋርካችን ላይ አምጥተህ ስላካፈልከን ምሥጋናዬ ከፍ ያለ ነው::በነገራችን ላይ ስለደራሲው የህይወት ታሪክ የምታውቀው ነገር ካለ ብታካፍለን::መቼም ዲጎኔ ሃገሪቱ ያሏትን ታዋቂ ሰዎች ሁሉ ወደሱ ማኅበር በመሰብሰብ የታወቀ ስለሆነ የእሱን ምስክርነት መቀበል ያስቸግራል::


ሰላም ዘርአይ ደረስ
ጥያቄህን ለመመለስ ከመዳከሬ በፊት እዚያ ዋርካ ጄኔራል ቤት ለከፈትከው አምድ የአአምሮ ጤና ሁሌ አመሰግንሀልሁ እያልኩ ንፉግ ሆንኩ መሰለኝ አልሞላልኝም:: ያው አሁን Thank you! Thank you! Thank you! keep it up!

ወደ ጥያቄህ
የተመስገን ገብሬ መረጃ ምንጬ ዘላለም እንዳለው አቶ ዘሪሁን አስፋው ነበር:: ዘሪሁን ሲያወራ እንዳደመጥኩት ተመስገንን ያወቀው በሀዲስ አለማየሁ ፍቅር እስከ መቃብር ነው:: ሀዲስ አለማየሁ ምስጋና ለተመስገን አቅርበውለታል:: ሁለቱ ሰዎች ትውውቅ እንዳላቸው በዚህ መረዳት ይቻላል:: አክሎም አቶ ዘሪሁን ተመሰገን ገብሬ ሱዳን ተሰዶ እንደነበር አውግቷል:: በምን ምክንያት እንደነበር ግን አላውቅም ነው ያለው::

በወሬ ብቻ እንዳይሆን ብዬ አቶ ዘሪሁን የጻፍውን የስነ ጽሁፍ መሰረታውያን ተውሼ ገረፍ ገረፍ አድርጌ አይቼልህ ነበር ጠላትህ ይደንግጥ ክው ነው ያልኩት 383 ገጽ መጽሀፍ ውስጥ የተመስገን ስም የትም አልታየም::

ይሄ ምናልባት ዲጎኔ ወዳለው የታሪክ አገኘሁ ሽሚያ ተገብቶ ይሆናል በዶ/ር ፈቃደ አዘዘ እና በአቶ ዘሪሁን አስፋው መካከል "ተመስገንን እኔ ነኝ እኔ ነኝ ያገኘሁት'

መልካም የስራ ሳምንት
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby ሙዝ1 » Thu Oct 25, 2012 11:46 am

ሰላም እንሰት ...
በመጀመሪያ ላጠፋሁት ጥፋት ይቅርታ እየጠየኩኝ ዘርዐይ ደረስ (በጣም የምወደዉ ስም) ለጠየቀህ ጥይቄ መልስ በመስጠት ጥፋቴን አወራርዳለሁ ....

በመጀመሪያ ይሄ ቤት ጸዐ ዲጎኔ ... ጸዐ ርኩስ መንፈስ ብዬ እጀምራለሁ :wink:

በዚህ ዘመን ስለ ተመስገን ገብሬ ለማወቅ ከባድ አይደለም .... ... ምክንያቱም ህይወቴ (ግለ ታሪክ) በተመስገን ገብሬ ከ1901 - 1941 የምትል መጽሀፍ አዲስ አበባ ዉስጥ በ25 ብር ትሸጣለች ... በዚህች መጽሀፍ ዉስጥ ከተመሰገኑ ሰዎች መካከል አቶ ደረጄ ገብሬ , ጥበቡ በለጠና አፈወርቅ በቀለ ከኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ጋር ሲገኙበት .... አመስጋኞችም ክብረ ተመስገን ... ሄኖክ ተመስገንና እስራኤል ተመስገን ናቸዉ ... ሶስቱም የተመስገን ገብሬ ልጆች ናቸዉ::

መጽሀፏ ባለ 190 ገጽ ስትሆን ማዉጫዋ ላይ የተዘረዘሩት አርዕስቶች ምስጋናን ጨምሮ 14 ሲሆኑ .... 5ኛዉ ንዑስ እርዕስ የጉለሌዉ ሰካራም ነዉ:: በመጽሀፏ ዉስጥ ከዉልደታቸዉ እስከ አሟሟታቸዉ ያሉ ነገሮች ሁሉ ተካተዋል ... ጋብቻም ጭምር :wink: እንዲሁም በሌሎች ሰዎች ስለ ተመስገን ገብሬ የተጻፉ ምስክርነቶችም እንዲሁ::

የመጽሀፉ የፊት ገጽ አረንጓዴ ቀለም ሲኖረዉ መሀል ለመሀል ቢጫና ቀይ የጸሀይ ዉጋገን መሳይ ነገር አለዉ:: ከሩቅ 3 የቆሎ ተማሪ የሚመስሉ በመጠን እያደጉ እያደጉ የሚቀርቡ በመጨረሻም በዘመናዊ ሱፍ ሽክ ብለዉ ጭራቸዉን የያዙ የተከበሩ... ጎልማሳዉ አቶ ተመስገን ገብሬ ፎቶ በጉልህ ይታያል::

እስኪ ህይወቴ ከሚለዉ ምዕራፍ 1 ዉስጥ ትንሽ ላስነብባችሁ ....

የመጀመሪያዉ አራቱ አንቀጾች ስለ ደብረ ማርቆስና ስለ ያኔዉ አስተዳደሯ የሚተርክ ሲሆን አምስተኛዉ አንቀጽ ላይ እንዲህ ብሎ የተመስገንንን ታሪክ ይጀምራል ...

በግንቦት 15 ቀን 1901 ከዚያች ከጥቀርሻማዋ ጎጆ ጥላ በታች በአሙስና በዓርብ መሀከል በመንፈቅ ሌሊት ተወለድኩ:: ሰዉ ወደ አለም በተወለደ ጊዜ ዓለምን በማልቀስ እንደሚጀምረዉ እንዲሁ ክፉና በጎ ሳላዉቅ ከዚያች ጎጆ ዉስጥ ዓለምን በማልቀስ ጀምርሁ:: ከህይወቴ ጋር የመጀመሪያዉ እንባ ጀመረ:: እንደ ታደሉ ህጻናቶች እናቴ በደረቷ ሁለት ሳምንት ያህል ታቀፈችኝና አጠባችኝ:: ከዞያ በሗላ እናቴ ስለ ታመመች ከወለደችኝ እናት ዕቅፍ ተነጥቄ ያልወለደችኝን እንድታሳድገኝ ለሞግዚት ተሰጠሁ::

በሚል ወደዚህ ምድር እንዴት እንደመጣ ያትትልናል::
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Postby ሙዝ1 » Thu Oct 25, 2012 3:16 pm

እንዳያችሁት ከላይ በአይምሮ የማያስታዉሰዉን የተነገረዉን ጽፎልናል .... እስኪ ደግሞ ልጅነቱን እንዴት እንደሚገልጸዉ እናንብብ ....

ምንም እንኳ ቤታችን ጥቅርሻ የሞላት ብትሆን ይቤታችን እጥር የቤተ መንግስት እጥር ዉበቱን አይመስለዉም:: የቤቱ እጥር ልዩ ልዩ አትክልት ነበርና ከወይራዎችና ከጽዶች ከዝግባዉ በቀር ሁሉ በየጊዚያቸዉ ያብቡ ነበርና ከቤት ጥግ ከጥላ ሁነን አበባ የሚቀስሙት ንቦች ሲያዘምሩ እንሰማቸዉ ነበር::አንዳንዶች እሾህ ያላቸዉ ናቸዉ እንጂ ማራቸዉ እንደ እናት ጡት የሚጠባ አበቦች አሉ:: በየጊዚያቸዉ አበቦች ሲያብቡ የአበቦችን ፈሳሽ ማር ልጆች ሁሉ እንጠባዉ ነበር:: ልጆች ወደ ቤት በገባን ጊዜ ዉሻ ስለአልነበረን የጎረቤት ልጆች መጥተዉ ማር ያላቸዉን አበቦችን ቆርጠዉ ሰርቀዉ ይወስዱ ነበር:: የአበቦችን ማር አጠራቅመን በቀለህ ሞልተን ልጆች ለልጆች እንሸጥ ነበር:: እንዲሁ ከጥቀርሻማ ቤታችን በሗላ የሊባኖስ ዉበት ነበር:: ከዛፎቹ ላይ የተንጠለጠሉትን የወፍ ጎጆዎችን እንዳናፈርስ: ጫጩቶችን እንዳንጫወትባቸዉ እንቁላላቸዉንም እንዳንሰብር አባታችን እንደ ሀይማኖት ያስተምረን ነበር:: የቤታችን የጢስ መዉጫ መስኮት እንኳ አልነበረዉምና በቤት ዉስጥ መብል ሲሰራ ጢሱ ከቤት ዉስጥ አያስቀምጥም ነበር:: አበቦች ጨርሰዉ እስከሚጠፉ ወራት ቀን ሁሉ የደስታ ቀን ነበር::

ከቤታችን አጠገብ ከፍተኛ ትምህርት የሚማሩበት ተማሪ ቤት ነበርና ከዚያ እየሄድሁ ስጫወት መዋል ለመድሁ:: ከሚማሩት ጋራ አብሬ እንደ ቀበላ አብሬ እጮህ ነበር:: ሌሎች ልጆች ወይም ወንድሜ ካልመቱኝ ወደ ቤቴ ለመመለስ ከቶ አልወድም::

እያለ ይቀጥላል ....
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Postby እንሰት » Fri Oct 26, 2012 6:18 pm

ለቁምነገረኛው ወንድሜ ሙዘይድ;

ምን ይባላል ከማመስገን በስተቀር... ለማንኛውም ብዙ ዝርዝር ለመጻፍ ጊዜ የሚኖርህ አይመስለኝም ስለ ድርሰት ስራውና ከሀዲስ አለማየሁ ጋር ስለነበረው ወዳጅነት እንዲሁም ስለ ህይወቱ ፍጻሜ ብትተርክልን ደስ ይለኛል:: ስለ ተመስገን የሚኖረን እውቀትም የተሙዋላ ይሆናል::

በድጋሚ ምስጋና!

ሙዝ1 wrote:እንዳያችሁት ከላይ በአይምሮ የማያስታዉሰዉን የተነገረዉን ጽፎልናል .... እስኪ ደግሞ ልጅነቱን እንዴት እንደሚገልጸዉ እናንብብ ....

ምንም እንኳ ቤታችን ጥቅርሻ የሞላት ብትሆን ይቤታችን እጥር የቤተ መንግስት እጥር ዉበቱን አይመስለዉም:: የቤቱ እጥር ልዩ ልዩ አትክልት ነበርና ከወይራዎችና ከጽዶች ከዝግባዉ በቀር ሁሉ በየጊዚያቸዉ ያብቡ ነበርና ከቤት ጥግ ከጥላ ሁነን አበባ የሚቀስሙት ንቦች ሲያዘምሩ እንሰማቸዉ ነበር::አንዳንዶች እሾህ ያላቸዉ ናቸዉ እንጂ ማራቸዉ እንደ እናት ጡት የሚጠባ አበቦች አሉ:: በየጊዚያቸዉ አበቦች ሲያብቡ የአበቦችን ፈሳሽ ማር ልጆች ሁሉ እንጠባዉ ነበር:: ልጆች ወደ ቤት በገባን ጊዜ ዉሻ ስለአልነበረን የጎረቤት ልጆች መጥተዉ ማር ያላቸዉን አበቦችን ቆርጠዉ ሰርቀዉ ይወስዱ ነበር:: የአበቦችን ማር አጠራቅመን በቀለህ ሞልተን ልጆች ለልጆች እንሸጥ ነበር:: እንዲሁ ከጥቀርሻማ ቤታችን በሗላ የሊባኖስ ዉበት ነበር:: ከዛፎቹ ላይ የተንጠለጠሉትን የወፍ ጎጆዎችን እንዳናፈርስ: ጫጩቶችን እንዳንጫወትባቸዉ እንቁላላቸዉንም እንዳንሰብር አባታችን እንደ ሀይማኖት ያስተምረን ነበር:: የቤታችን የጢስ መዉጫ መስኮት እንኳ አልነበረዉምና በቤት ዉስጥ መብል ሲሰራ ጢሱ ከቤት ዉስጥ አያስቀምጥም ነበር:: አበቦች ጨርሰዉ እስከሚጠፉ ወራት ቀን ሁሉ የደስታ ቀን ነበር::

ከቤታችን አጠገብ ከፍተኛ ትምህርት የሚማሩበት ተማሪ ቤት ነበርና ከዚያ እየሄድሁ ስጫወት መዋል ለመድሁ:: ከሚማሩት ጋራ አብሬ እንደ ቀበላ አብሬ እጮህ ነበር:: ሌሎች ልጆች ወይም ወንድሜ ካልመቱኝ ወደ ቤቴ ለመመለስ ከቶ አልወድም::

እያለ ይቀጥላል ....
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby ዘርዐይ ደረስ » Fri Oct 26, 2012 9:33 pm

እንሰትና ሙዝ:-ሰላም ለእናንተ ይሆን እያልኩ

እንሰት:-የአእምሮ ጤንነትን ቀን በሚመለከት የከፈትኩት ርእስ በ2005 ቢሆንም ከ 5 ዓመታት በኋላ ነው አስፈላጊነቱ ታይቶኝ በያመቱ ማሰብ የጀመርኩት::እኔ እንኳን ያንተን ማበረታቻ እስካነብ ሌላ ታዳሚ ስላልተሳተፈበት ተቀባይነት ያገኘ አልመሰለኝም ነበር::ለላው ቢቀር 'ሳይካትሪስቱና' 'ፈላስፋው' ቆቁ ይሳተፋል ብዬ ነበር :lol: ለማንኛውም ሲመችህ ብቅ ብለህ አስተያየትህን አካፍለን::

ወደ ጉዳያችን ስመለስ የዘሪሁን አስፋውና የፈቃደ አዘዘ 'የታሪክ ሽሚያ' አልገባኝም::እነሱ ህፃናት እያሉ ምናልባትም ሳይወለዱ በማተሚያ ቤት የታተመ መጽሐፍ እንዴት ከእነሱ በፊት በነበሩት ሐያስያን ሳይታወቅ ቀረ?በተጨማሪም ባለፈው እንዳልኩት ታደሰ ሊበንስ ለምንድነው የመጀመርያው የአማርኛ አጭር ልብወለድ ደራሲ የሚባለው(ወይ የ'መስከረም' መግብያ ላይ ወይም ደግሞ ሌላ ቦታ ያነበብኩ ስለመሰለኝ ነው::)

p.s.:-ታሪኩና የኛ 'ሽኩቻ' እንዳይቀላቀል ከቻልክ ይህን ክፍል ለአስተያየት መስጫ አድርገኸው ለታሪኩ ሌላ ርእስ ብትከፍት የሚሻል ይመስለኛል::

ሙዝ 1:-እኔም ስለ ፈጣን ምላሽህ እያመሰገንኩ አድካሚ እንዳይሆንብህ እንሰት ከጠየቀው በተጨማሪ ደራሲው ከነ ዲጎኔ ማኅበር ጋር የነበረው ግንኙነት እስከምን ድረስ እንደነበር ጽፎ ከሆነ ብታካፍለን::
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1158
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Postby ሙዝ1 » Fri Nov 02, 2012 9:11 am

ሰላም እንሰትና ዘርዐይ ደረስ ....
ያላችሁትን አቀርባለሁ ... መጽሀፉ ግለ ታሪክ እንደመሆኑ መጠን .... ከዉልደት እስከ ሞት ያለዉን ነገር ያካተተ ነዉ:: ጊዜ ሲኖረኝ ጎራ እያልኩ ከመጽሀፉ ወደ ዋርካ እገለብጣለሁ::
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Postby ቱሉቦሎ » Fri Nov 02, 2012 1:36 pm

ሙዝ1 wrote:ሰላም እንሰትና ዘርዐይ ደረስ ....
ያላችሁትን አቀርባለሁ ... መጽሀፉ ግለ ታሪክ እንደመሆኑ መጠን .... ከዉልደት እስከ ሞት ያለዉን ነገር ያካተተ ነዉ:: ጊዜ ሲኖረኝ ጎራ እያልኩ ከመጽሀፉ ወደ ዋርካ እገለብጣለሁ::


ሙዝ1 ምነው የጥንቱ አገረሸብህና ዲጎኔን ወረፍከው ? በእምነቱ ይጥፋል ሰው ያከብራል ክፉ አይናግርም
በጉዳዩ መከራከር ሲገባህ በመሳደብህ ጥፋተኛው አንተ ስለሆንክ ይቅርታ ጠይቅ

በቀይ ያቀለምኳት ጽሁፍህ አስደንቃኛለች :: ግለታሪኳ ከውልደት እስከሞት ከሆነች የመጨረሻዋን(የመሞቱን) ከመቃብር ሆኖ ነው የጣፋት ?
ቱሉቦሎ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 195
Joined: Tue Sep 04, 2012 8:13 pm

Postby እንሰት » Mon Nov 05, 2012 10:14 pm

ሙዝ1 wrote:ሰላም እንሰትና ዘርዐይ ደረስ ....
ያላችሁትን አቀርባለሁ ... መጽሀፉ ግለ ታሪክ እንደመሆኑ መጠን .... ከዉልደት እስከ ሞት ያለዉን ነገር ያካተተ ነዉ:: ጊዜ ሲኖረኝ ጎራ እያልኩ ከመጽሀፉ ወደ ዋርካ እገለብጣለሁ::


ሰላማት ሙዘይድ
ያክብርልን ከማለት ውጪ ምን እንላለን:: ሊታወቅ ስለሚገባው ስለ ተመስገን የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖረን እያደረክ ነውና:: BTW በሾተል አጠራር ኮፒ ፔስቶች ስላለን ኤለክትሮኒክ ኮፒውን በጉዋሮ ብትልክልኝ ኮፒ ፔስቱን አግዝህ ነበር::
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby ሙዝ1 » Sat Nov 10, 2012 7:43 am

ሰላም እንሰት .... መጽሀፏ በሀርድ ኮፒ ነዉ ያለችኝ ... ያዉ እየለቀምኩ መጻፍ ነዉ ....

የተመስገን ገብሬ አሟሟት --- ከገጽ 136 - 141

የመጀመሪያዉ አንቀጽ ስለ ኢትዮጵያ የኪነ ጥበብ ሰዎች አሟሟት ሚስጥራዊነት ያትታል ስሞችን እየጠቀሰ .... ነጋድራስ ገብረህይወት ባይከዳኝ ... ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ .... ሰአሊና ገጣሚ አገኘሁ እንግዳ ... ድምጻዊ አሰፋ አባተ .... አቤ ጉጎነኛና በአሉ ግርማ በዝርዝሩ ዉስጥ ተካተዋል ....

ሁለተኛዉ አንቀጽ እንዲህ ሲል ይጀምራል ....

በ1939 ዓ.ም. ጃንሆይ ጎጃምን ለመጎብኘት ሲሄዱ ሀገሩን የሚያዉቀዉ ተመስገን ገብሬ ነዉ ተብሎ በወቅቱ ከነበሩት የጸሀፌ ትዕዛዝ ማዕረግ ካላቸዉ ባለስልጣን ጋር ሆነዉ አጅበዉ ሄዱ:: ከተመስገን ጋርም አብረዉ ነበር አንድ ድንኳን ዉስጥ ያደሩት:: እዚያም ጽሀፌ ትዕዛዙ በንጋታዉ ጥዋት ተነስተዉ "" እኔ ጃንሆይን ላናግርና ላለባብስ እሄዳለሁ አንተ ቁርስህን በልተህ ቀስ ብለህ ና"" ብለዉት ሄዱ:: እስከዚያ ቀን ድረስ ተመስገን ጠነኛ ነበር:: ምንም አይነት ህመም አልነበረበትም:: በዚያን እለት አንዲት ሴት ቁርሱን ይዛለት መጣች:: ያንን ቁርስ በልቶ 15 ደቂቃ አልቆየም ሆዴን ተቃጠልኩ አለ:: በጠናም ታመመ:: ጸሀፌ ትዕዛዙም የተመስገንን በጠና መታመም ለጃንሆይ ይነግሯቸዋል:: እርሳቸዉም መታመሙን በሰሙ ጊዜ እንግዲህ ምንም ስለማይረዳን ወደ አዲስ አበባ ይመለስ ብለዉ ከደብረ ማርቆስ ወደ አዲስ አበባ ላኩት:: ወደ አዲስ አበባም ሲመጣ ባለቤቱ ትቀበለዋለች:: ምን ሆንክ ትለዋለች:: እሱም ሲመልስ ለቁርስ የበላሁት ስላልተስማማኝ ሆዴን አሞኝ መጣሁ አለ::

በዚህ ህመሙ የተነሳ በተደጋጋሚ ጊዜ በቀዳማዊ ሀይለ ስላሴ ሆስፒታል ዉስጥ ኦፕራሲዮን ሁኗል:: በኦፕራሲዮኑ ጊዜም የሚወጡት በርካታ ነብስ ያላቸዉ ነገሮች ናቸዉ:: ያ ደግሞ ደሙን ይጨርሰዋል:: ከዚያም ደም ከጓደኞቹ መዉሰድ ጀመረ:: የተመስገን ገብሬ የደም አይነት " O " የሚባለዉ ነዉ:: ከርሱ ደም ጋር የሚመሳሰለዉ ደግሞ የዶ/ር አማኑኤል ገ/ስላሴ ነዉ:: እናም እሳቸዉ ነበሩ በየጊዜዉ ድማቸዉን የሚሰጡት:: በየጊዜዉ ሀኪም ቤት ይገባል ይወጣል:: ህመሙ አልሻል አለዉ:: ከዚያም ለስራ ጉዳይ ወደ ድሬ ዳዋ ይሄዳል:: እዚያም ድ/ር ምራይቱ የሚባል ሀኪም ያክመዉ ነበር:: በድሬዳዋም እንደራሴ አቶ ብርሀነ መስቀልና ባለቤታቸዉ ው/ሮ ሜሪ እነስኪ ያስታምሙት ነበር:: ....

ይቀጥላል
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests