ተዋናይት ህይወቴ አበበ:- ነፍስሽን ይማርልን :(

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ተዋናይት ህይወቴ አበበ:- ነፍስሽን ይማርልን :(

Postby የተሞናሞነው » Fri Dec 14, 2012 4:39 pm

በተለይም በብዙ አስቂኝ ድራማዎችና ፊልሞች ላይ ፍልቅልቅ እያለች ስትተውን ስታስቀን ስታዝናናን የነበረችው ተዋናይት ህይወቴ አበበ ዛሬ ከዚህ አለም በሞት እንደተለየች ከኢትዮጵያ ያሉ የፌስ ቡክ ጓዶች አሳዛኙን ዜና አካፍለውን እያነበብሁኝ ነው:: እጂግ በጣም ጥሩ ተሰጥኦ ያላት እድሜዋም ገና ወጣት የምትባል ተዋናይት ነበረች:. እጂግ አሳዘነችኝ....የሰላም ዘላለማዊ ረፍት እህታለም :cry:

እዚህ ላይ ከሸዋፈራው ደሳለኝ ጋር ስትተውን እዩዋት:-

http://www.youtube.com/watch?v=rzhObwLkuU8

እንዲሁም ባለ ቀለም ህልሞች የተሰኘው ኮሜዲ ፊልም ላይም ተውናለች :cry:
የተሞናሞነው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1129
Joined: Wed May 11, 2011 5:39 pm

Postby የተሞናሞነው » Fri Dec 14, 2012 6:31 pm

እዚህ 'ባለ ቀለም ህልሞች' ላይ ጀሪን ወክላ የተጫወተችው ህይወቴ ነበረች:: ተከታተሉት...እያስታወሳችኍትም ዘና በሉ:: http://www.youtube.com/watch?v=7iPLWD7-84I
የተሞናሞነው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1129
Joined: Wed May 11, 2011 5:39 pm

Postby ሳምራውው33 » Sat Dec 15, 2012 5:53 pm

እውነት ከሆነ መቼም በጣም ልብ ይሰብራል :!: ምን ሆና ይሆን በዚ በወጣትነት እድሜ የተለየችን :?:

ለማንኛውም ነብስ ይማር :!:
The love of money is the root of all evil.

ሳምራውው 33 የግጥም አርበኛ
ስንኝ ቋጣሪ በውብ አማርኛ ::
_________________
ሳምራውው33
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 530
Joined: Thu Jun 21, 2007 12:23 am

Postby ዲያስፖራ » Sat Dec 15, 2012 6:09 pm

ስንብት ለወጣት አርቲስት ህይወቴ አበበ ነፍሳን በገነት ያኑርልን ::

http://www.diretube.com/ethiopian-news/ ... a4bf4.html
ቀይ ባህር ድንበራችን ነው !!!!
I Love Ethiopia !!!
ዲያስፖራ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 781
Joined: Wed Apr 29, 2009 4:39 pm
Location: no

Postby ሾተል » Sat Dec 15, 2012 9:54 pm

ትላንትና ጥዋት የዚችን ታላቅ አርቲስት ሞት ከሰማሁ በሁዋላ ውስጤ በጣም በመደንገጥና በመንቀጥቀጥ እንዲሁም የስሜት አለመረጋጋትና መረበሽ አጋጥሞኝ ነው የዋልኩት::ተስፋ ሁሉ ቆረትኩ::

ደግሞ ሰሞኑን ከጉዋደኞቼ ጋር ስለዚች ምርጥ አርቲስት ሳወራና ሳስተዋውቃት እንዲሁም ከአፌ አላወጣት ብዬ ስለእሷ ታላቅነት ሳስብ እንደዚህ ከአፌ ሳትወጣ አድንቄያት ሳልጨርስ ሞቷን ስሰማ ምን አይነት ስሜት ላይሰማኝ ይችላል?

ይቺ ምርጥ አርቲስት ከሰራቻቸው ስራዎችዋ ምን አልባት ልብ ሳልላት ብዙ ስራዎችዋን አይቼ ከሆነ አላውቅም ነገር ግን ቅርብ ጊዜ ከሰራቻቸውና ስለዚች ምርጥ አርቲስት ችሎታነት ካደነቅኩላት ስራዎችዋ ውስጥ አንዱ ኤፍ ቢ አይ ሲሆን ለላው ደግሞ ባለቀለም ህልሞች የሚሉት ሲሆን እነዚህ ሁለት የፊልም ስራዎች ውስጥ ታለንቷን ያሳየችበትና ይቺ ልጅ ኢትዮዽያ ውስጥ አሉ ተብለው ከተኮለኮሉት አርቲስት ነን ባዮች አይደለም ወርልድ ክላስ አርቲስት ቢመጡ መወዳደርና የፊቱን ቦታ ማግኘት የምትችል በተፈጥሮዋ እራሷን ሆና በታላቅ ችሎታ የምትተውን ተዋናይ ነበረች::

በቃ ተፈጥራ የነበረው ለትወና ነበር......በጣም ነው በነዚህ ሁለት ስራዎችዋ ደጋግሜ በማየት የልጅቷን ችሎታ ያደነቅኩት::ድምጿ....እንቅስቃሴዋ....የፊት ኤክስፕሬሽኗ....ከስክሪፕቱ ጋር ያላት አንድነትና እራሱን መሆን.....ምኑ ቅጡ ብቻ ተክናው ነበር::

ግን እግዚአብሄር ሰጠ....እግዚአብሄር ለራሱ ሲል ወሰደ ነው::ሁሉም ነገር የሱ ስለሆነ ማን ሊቃወመው መብትና ሀይል ወይም ህሊና ይኖረዋል?

ህይወቴንስ ወሰደብን......ያሉትን ይባርክልን እንዳይባል ብዙም ያሉ አልታዩኝም....ግን በዘመድ አዝማን ወይም በሚሰጡት እኛ ኬንያኖች ኪቱ ኪዶጎ እንላለን...እኛ ፈረንጆቹ ደግሞ ሳም ቲንግ ስሞል እንላለን...እኛ ኢትዮዽያኖች ደግሞ ጉቦ እናለንና ያንን የሰጡ ቦታውን ወረውት ሲያበቁ እንደ ህይወቴ አይነቷ የጥበብ ውልደት ብዙ ቦታ ሳናያት ምን አልባት ቲፎዞም ገንዘብም ምንም ስላልነበራት ይሆናል ብቻ ሳናያት አመለጠችን::

ብቻ ልል የምችለው እግዚአብሄር አምላክ ነፍሷን በገነት መንግስተ ሰማያት አመቻችቶ ለዘላለም ያኑርልን.....ለቤተሰቦችዋ,ጉዋደኖቿ ...እንደኔ ላሉ አድናቂዎቿ እንዲሁም ለጥበብና ለኢትዮዽያ መጽናናትን ይስጥልን::

እንደገና ባለቀለም ህልሞች ላይ የሰሩትን ሁሉንም ተዋንያኖቹን እግዚአብሄር ይጠብቅልን::ቢሆንም እዛ ላይ የተወኑት ሁሉ ጎበዞች ናቸው ለማለት ሳይሆን ከሌሎቹ ይሻላሉ::ነገር ግን ዋናው ተዋናይ,ህይወቴ,ሱዳን አገር ተሰዶ የነበረው ወላቃው.....እኔ በእህቴ ሴት ነኝ ያለው....ለትወና የተፈጠሩ ምርጥ አርቲስቶቻችን ናቸው::ግን ያያቸው ብዙም የለም::

ህይወቴ በድጋሚ ነፍስሽን አምላክ ይማራት::ሁሌም እወድሻለሁ::

እንድንዝናና እግዚአብሄር የሰጠሽን ተሰጦን ስላካፈልሽን ከልባችን በክብርነታችን ሆነን እናመሰግናለን::


ሾተል ነን.......ከመሪር ሀዘን ጋር
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9644
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria


Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests

cron