ከባህር የወጡ አሶች..

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ከባህር የወጡ አሶች..

Postby ክቡራን » Thu Dec 20, 2012 1:44 am

ይሄን ርዕስ የመረጥኩት ያለ ምክንያት አይደለም...ስለ አርቲስቶቻችን የውጭ ህይወት ሳስብ የመጣልኝ ርዕስ ነው:: አርቲስቶቻችን ውጭ ሲወጡ አገር ቤት ከሚያገኙት በላይ የበለጠ አክብሮትና ተደማጭነት አላቸው..ብለን እናምናለን..? ይሄን የምለው አንዳንዴ አርብ መዝናናት አምሮኝ አበሻ ቤት ስሄድ የሚያጋጥመኝ ትእይንት የሙያተኞቹ መጻዊ ህይወት አደጋ ውስጥ የወደቀ ሀይል ተሰምቶኝ ነው:: አንዳንዴ ታዳሚ ጠፍቶ ለወንበሩና ለጠረፔዛው እንዲሁም ላአስተናጋጆቹና ለቡና ቤት ባለቤቶቹ ብቻ የሚዘፍኑበት ሁኔታ ደ..ጋግሜ ታዝቤአለሁ:: አንዴ ብቻ አይደለም.. በዚህ አይነት የመንፈስ ዝቅጠት ውስጥ ፈጠራ ሊመጣላቸው አይችልም..አይደለም ፈጠራ ቡዙዎቹ ሙያውን እየጠሉት የተለያየ ሱስ ተገዥ ሆነው እንደቀሩ ያደባባይ ሚስጥር ነው:: ቴዎድሮስ ታደሰና ልመንህ ታደሰ ካሜሪካ ኑሯቸው ያተረፉት ነገር ቢኖር የእሳት ምድጃ ሆኖ መቅረትን ነው:: ታዛቢ ይመስክር!! ቴዲ አለ:: የልመንህ ግን ይቅር ከሚኖሩት በታች ከሞቱት በላይ ሆኖ አገር ቤት ውስጥ ይንከላወሳል:: ለዚህ የዳረጋቸው ታዲያ በኔ ግምገማ ከባህር ውስጥ መውጣታቸው ነው እላለሁ:: እነሱ እኮ የህዝብ ሀብት... የህዝብ እሴት ናቸው...ትርፍ ጊዜ ማሳለፊያ አይደሉም..እዚህ ያለው ኮሚኒቲ እነሱን የሚፈልጋቸው በሳምንቱ መጨረሻ ብቻ ነው...ቢራ ሲፈልግ እነሱ ይፈልጋቸዋል...በቃ!!! ክትፎ ሲያምረው እነሱም ያምሩታል..አለቀ...እዚህ ላለው ህብረተሰብ ኪናዊ እሴት ሳይሆኑ ቁሳዊ ንብረት ናቸው:: ይሄ ሁኔታ ዲፕሬሽን እየፈጠረ ከመንገድ ያስወጣቸውን ክህሎታቸውን ቀምቶ የመንገድ ላይ ለማኝ ያደረጋቸውን ቡዙዎችን ማንሳት እንችላለን:: አንድ ዘፋኝ ላራት ሰው ላንቃው እስኪሰነጠቅ ድረስ እየዘፈነ እነሱም የራሳቸውን ወሬ እያወሩ የማያዳምጡበት ሁኔታ በብዛት አለ:: ሲጨርስ እንኴን በቅጡ አያጨበጭቡለትም:: በቅርቡ የኢትዮጵያ በዚህ ሳምንት ዋና አዘጋጅ ( ኢዲተር ኢን ቺፍ ) ካርቲስት በረከት በቀለ ጋር ያደረገው ቃለ ምልልስ ይህን ሀቅ ይመሰክራል :: እቺን ጠቅ::
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7963
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

ሕምምምም

Postby ዋኖስ » Thu Dec 20, 2012 11:30 pm

ሕምምምምም....


"ቆንጆ የዶሮ ወጥ ውስጥ ገብቶ የተገኘ ጸጉር" ሆኑብሕ ኣይደል?

እስኪ ብዙ መስማት እፈልጋለሁ በዚሕ ርዕሰ ጉዳይ ላይ


ዳሞት
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby ክቡራን » Fri Dec 21, 2012 1:50 am

ወንድሜ ዋኖስ ሀሳብዎ ግልጽ አይደለም":: አሳ ከባህር ውስጥ ወጥቶ ህይወት እንደሌለው እየታወቀ እርሶ ይባስ ብለው ሽክን ያለ ዶሮ ውስጥ ተሳስስተው የገቡ ጸጉሮች ናቸው ሲሉ ገለጿቸው:: ዶሮ ወጡ ማነው..? ዘለላ ጸጉሩስ ?? የእኔ አስተያየትና የርሶ ምሳሌ እንዴት እንደሚያያዝ አቡዬ ናቸው የሚያቁት:: ላስተያየትዎ ግን ላመሰግን:: 8)
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7963
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

ወዴት ወዴት

Postby ዋኖስ » Fri Dec 21, 2012 10:41 pm

አይይይ! ይቅርታ!

ለማንኛዉም አጠር መጠን ባለችና ግልጽ በሆነች አማርኛ ላስቀምጣት:: ብዙ መመላለስም ልምዱ ስለሌለኝ አለመለስምና!

ወዲሕ ነው ነገሩ! ጸጉርም ይሁን የዶሮ ወጥ ሁለቱም በተገቢዉ ቦታቸዉ ሲገኙ እጅግ ጠቃሚ ነገሮች ናቸው ባይ ነኝ:: ለምሳሌ በሰሞኑ ብርድ ወቅት ፊትን ልፎ ገርፎ ለሚጥለዉ ዉሽንፍራማ ቁር መላጣ ሰው የሚሰማዉን ስሜት መግለጽ አያዳግትም:: የዶሮ ወጥም ( ይቅርታ ገናን ጾም ለምጾሙ ) ጣት የሚያስቆረጥም እስኪደርስ ድረስ የሚበላዉ በተገቢዉ ወቅት ሲገኝ ነው:: ታዲያ ይሕን የዶሮ ወጥ የርኃብ ስሜት በተሰማሕ ሰዓት ለመብላት ተዘጋጅተሕ አንዴ ወደ አፍሕ ከጎረስሕ በኍላ ስታኝከዉ ረዥም ጸጉር ብታገኝበት የሚሰማሕን ስሜት ለአንተ ልተወዉ:: ስሜቱን እዚሕ ጋ መግለጽ የማልፈልገዉ የጠቅላላ ሰዉነት ቁጠት ያመጣብሕ ጸጉሩ ያለቦታዉ ገብቶ ስለተገኘ ነው:: እነኝሕ ከላይ ያነሳናቸዉ ሰዎችም አድማጭ ያጡ: ዦሮ የተነፈጉት: ምናልባት አለቦታቸዉ ተገኝተዉ ይሆናል:: ዳሩ ኃሳቤ ከአንተ ኃሳብ ጋር የሚቀራረብ እንጅ የሚጣረስ አይደለም:: ወጡም የኛው ሕብረተሰብ: ጸጉሩም ያዉ እንግዲሕ ቀሪዉ ሕዝብ ይሁን ለጊዜው::

ዋርካ ራሷ መኖሬንም ረስታኝ ነበር:: እንድመለስ ስለጋበዙኝ አመሰግናለሁ::

ከመልካም አክብሮት ጋ!

መልካም የፈረንጅ በዓል!

ዳሞት

ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby ክቡራን » Sat Dec 22, 2012 12:35 am

ጥሩ ነው አመሰግናለሁ ወንድም ዋኖስ ስለ ማብራሪያው:: መልካም ምሽት ይሁንልህ :: 8)
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7963
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm


Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests