እንረዳዳ - የአማርኛ ዘዬያችን በእንግሊዘኛ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

እንረዳዳ - የአማርኛ ዘዬያችን በእንግሊዘኛ

Postby ሀዲስ 1 » Fri Jan 04, 2013 6:40 pm

ሰላም : ሰላም : ሰላም !!!

ይህንን ክፍል ልከፍት ያሰብኩበት ምክንያት : ምናልባትም በእንግሊዘኛ መልክ ያለው ፅሁፍ ማሰናዳት ለሚፈልጉ ሰዎች ይረዳ ይሆናል በማለት ነው ::
በእርግጥ እኔው ራሴው ብዙም የጠለቀ የእንግሊዘኛ እውቀት ስለሌለኝ : እዚህ ቤት ውስጥ በአብዛኛ ተማሪ ለመሆን ነው ጉጉቴ ::

አንዴ አንዱ ጓደኛዬ --> የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች የሚለው የአማርኛ አባባል በእንግሊዘኛ እንዴት ሊመነዘር ይችላል ብሎ ላብ በላብ አደረገኝ :: አለማወቄ ጉድ አደረገኝ ብዬ ተናደድኩኝ ::

ግን ከዚሁ ብንጀምር : ለመሆኑ የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች የሚለው አማርኛ አባባል በእንግሊዘኛው እንዴት ይተረጎማል ?????

ሀዲስ ነኝ
what we learn from history is, we do not learn from history.

http://www.isil.org/resources/philosoph ... nglish.swf
ሀዲስ 1
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1643
Joined: Wed Mar 10, 2010 12:23 am

Postby ዲጎኔ » Fri Jan 04, 2013 10:07 pm

ሰላም ወገን ሀዲስ
ይገርምሀል ይህ ነገር በጣም አስፈላጊና ጠቃሚ ነው::በተለይ በሰሜን አሜሪካ diversity ስብጥርነት ታላቅነቱ በተግባር በሚታይበትና መሪውም በምርጫ ንግግሩ ገልጾታል::ትምህርት ቤት እያለሁ አንዱ ጉዋደኛዬ ከማግባቱ በፊት እጮኛ ሲያፈላልግ ሁሉ ያማክረኝ የነበረ በሰርጉ Ethiopian folkdance ዝፈን ሲለኝ ተፈተንኩኝ:: ድሮ ዘፈን አሪፍ ነበርኩ ሳገባ ግን በዘፈን አልነበረም:: የባለቤቴ ዘመዶች ብቻ ባልንጀሬ አይበልሽ ከፋ ሲሉ ነበር::እናቴ ከበሮ ይዛ ልታዘፍን ስትል አንድ ወንድም ልጅዎ ደስ የማይለውን ለምን ይደረጋሉ ሲላት ትውት አድርጋው በዝማሬ ነበር የተዳርኩት::ለዚያ ልጅ ማን እንደዚያ ይዘምር::ያለኝ ብቸኛ አማራጭ የሱም ፍላጎት ባህላዊ ስለነበር የሴትም የወንድም ሚዜዎች በሀገራችን የሚሉትን ተረጎምኩ adaptation /ውርስ ትርጉም:-
ይሄ የማንው ቤት የኮራ የደራ
የጂም አደለም ወይ የዚያ የቀብራራ
Whose house is this belong to?
It that not the home of Jim that proud guy?
ለልጅቷ ደግሞ
ባልንጀሬ ስሪ ጉልቻ
ከንግዲህ ቀረ የናት እንጎቻ
dear my friend cook for your home
no more meal make for you by your mom
ከዚያ አንዲት ጥቁር እጮኛዋ ነጭ በጣም ተገርማ እንደዚህ ያለ wisdom poem አላችሁ አለችኝ እንግዲህ እንዴት እነደሚገባቸው አላውቅም::በትክክል ግን ሁለት እግር አለኝ ተብሎ ሁለት ዛፍ ላይ አይወጣም you do not step up to two trees because you have two legs እንቁላል ቀስበቀስ በእግሩ ይሄዳል an egg will walk by its leg step by step የመሰሉ በስራዬ ሳስተምር እጠቀማለሁ::መዝሙሮች ሁለት ሶስት ጊዜ ወደእንግሊዝኛ ሞክሬያለሁ-አምላክ ለእኛ ብሎ ሲያፈሰው ደሙንና የምስራቹ ቃል በዳዊት ከተማ ነገር በእንግሊዝኛ ትርጉምና ጣእም እንዲኖረው አስተማሪዎቼ ረድተውኛል:: ምን አይነት ፍቅር ነው በቀራኒዮ መስቀል ለእኔ የገልጽከው የሚለው የአልማዝ በልሁ መዝሙር ፊንላንድ ሳለሁ በፊኒሽ አሜሪካም በእንግሊዝኛ ተተርጉሞ ይዘመራል::አፈርሳታ የሚል አፍሪካን ሲርየስ መጽሀፍት በአንድ የጦቢያ ሰው የተጻፈ መድብሎች ያሳተመ ፈልግና አንብበው::Chniewa Achebe ናይጀሪያ በእንደዚህ ያሉ መድበሎቹ በኦክፎርድ ፕሬስ ገናና ነው::
ይህ የቆጡን አወርድ ድንቅ ነው እንዴት እንደሚተረጎም ያ ድንቅ የዋርካ ሰው 4 get it ከየት ይምጣ? አሁን ካሉት ምናልባት እንስት ወይም ዋናው ቢሞክሩት ይሻላል::
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Fri Jan 04, 2013 11:56 pm

ዲጎኔ wrote:ይሄ የማንው ቤት የኮራ የደራ
የጂም አደለም ወይ የዚያ የቀብራራ
Whose house is this belong to?
It that not the home of Jim that proud guy?
ለልጅቷ ደግሞ
ባልንጀሬ ስሪ ጉልቻ
ከንግዲህ ቀረ የናት እንጎቻ
dear my friend cook for your home
no more meal make for you by your mom

ከዚያ አንዲት ጥቁር እጮኛዋ ነጭ በጣም ተገርማ እንደዚህ ያለ wisdom poem አላችሁ አለችኝ
በትክክል ግን ሁለት እግር አለኝ ተብሎ ሁለት ዛፍ ላይ አይወጣም you do not step up to two trees because you have two legs እንቁላል ቀስበቀስ በእግሩ ይሄዳል an egg will walk by its leg step by step የመሰሉ በስራዬ ሳስተምር እጠቀማለሁ::

:lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol:

ዲጎኔ......በስንት ዓመተ ምህረት ነው ከአማኑኤል ያመለጥከው :?: :lol: :lol:
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Postby መራራ » Sat Jan 05, 2013 6:07 pm

:lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: ሳቅ ሰውን የሚገል ቢሆን ዛሬ አልቆልኝ ነበር የምር :lol: :lol: :lol:

ዳግማዊ ዋለልኝ wrote:
ዲጎኔ wrote:ይሄ የማንው ቤት የኮራ የደራ
የጂም አደለም ወይ የዚያ የቀብራራ
Whose house is this belong to?
It that not the home of Jim that proud guy?
ለልጅቷ ደግሞ
ባልንጀሬ ስሪ ጉልቻ
ከንግዲህ ቀረ የናት እንጎቻ
dear my friend cook for your home
no more meal make for you by your mom

ከዚያ አንዲት ጥቁር እጮኛዋ ነጭ በጣም ተገርማ እንደዚህ ያለ wisdom poem አላችሁ አለችኝ
በትክክል ግን ሁለት እግር አለኝ ተብሎ ሁለት ዛፍ ላይ አይወጣም you do not step up to two trees because you have two legs እንቁላል ቀስበቀስ በእግሩ ይሄዳል an egg will walk by its leg step by step የመሰሉ በስራዬ ሳስተምር እጠቀማለሁ::

:lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol:

ዲጎኔ......በስንት ዓመተ ምህረት ነው ከአማኑኤል ያመለጥከው :?: :lol: :lol:
መራራ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 753
Joined: Sat Sep 25, 2004 9:58 am
Location: united states

Postby ዲጎኔ » Sat Jan 05, 2013 7:20 pm

ሰላም ለሁላችን ለሳቂዎቹ ባላንጦች /ተቃራኒዎች ጭምር
አማርኛ ወደ እንግሊዝኛ ትርጉም ከባድ ነው common mistakes ያስተማሩን ልብ ይሏል I visit my sick uncle vs I ask my sick uncle/ የታመመ አጎቴን ጠየቅሁ::
እንግዲህ ዲጎኔ የአቅሙን ሞክሯል እስኪ እናንተ የሀዲስን የትብብር ጥያቄ ከሳቁ ታገሱና የቆጡን አወርድ...ተርጎም አድርጉ!የኛ ጥቁሮች/አፍሪካ ችግር በሚጣጣር ላይ መሳቅ ነው ዲጎኔ ሲስቁበት አብሮ ይስቃል እንጂ አይናደድም ቅቅቅ :roll:
መቸስ ወያንታው ዳግማዊ የለገሰ ዜናዊ የመጀመሪያ ፕሬስ መግለጫ..ኢሀዲግ ግራው ሲመቱት ቀኙን አይሰጥምን ጨርሶ አይሞክራትም ቅቅቅ :roll:
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby ሀዲስ 1 » Sun Jan 06, 2013 4:15 am

ሰላም ለታላቁ ዲጎኔ !!!

ለመልስህ በጣም አመሰግናለሁኝ ::
የተሰመረባት አባባልህም ተመችታኛለች ::
እስኪ ታዲያ አትጥፋ :: መተርጎም የሚያስፈልጋቸውን አባሎችንም አቀራርብ ::

የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች የሚለው አባባል ታዲያ በምን ይመሰል ዘመዶቼ !!!!

ሀዲስ ነኝ ::ዲጎኔ wrote:ሰላም ለሁላችን ለሳቂዎቹ ባላንጦች /ተቃራኒዎች ጭምር
አማርኛ ወደ እንግሊዝኛ ትርጉም ከባድ ነው common mistakes ያስተማሩን ልብ ይሏል I visit my sick uncle vs I ask my sick uncle/ የታመመ አጎቴን ጠየቅሁ::
እንግዲህ ዲጎኔ የአቅሙን ሞክሯል እስኪ እናንተ የሀዲስን የትብብር ጥያቄ ከሳቁ ታገሱና የቆጡን አወርድ...ተርጎም አድርጉ!የኛ ጥቁሮች/አፍሪካ ችግር በሚጣጣር ላይ መሳቅ ነው ዲጎኔ ሲስቁበት አብሮ ይስቃል እንጂ አይናደድም ቅቅቅ :roll:
መቸስ ወያንታው ዳግማዊ የለገሰ ዜናዊ የመጀመሪያ ፕሬስ መግለጫ..ኢሀዲግ ግራው ሲመቱት ቀኙን አይሰጥምን ጨርሶ አይሞክራትም ቅቅቅ :roll:
what we learn from history is, we do not learn from history.

http://www.isil.org/resources/philosoph ... nglish.swf
ሀዲስ 1
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1643
Joined: Wed Mar 10, 2010 12:23 am

Re: እንረዳዳ - የአማርኛ ዘዬያችን በእንግሊዘኛ

Postby ስራ ፈት » Sun Jan 06, 2013 6:30 am

ሀዲስ 1 wrote:ሰላም : ሰላም : ሰላም !!!

ይህንን ክፍል ልከፍት ያሰብኩበት ምክንያት : ምናልባትም በእንግሊዘኛ መልክ ያለው ፅሁፍ ማሰናዳት ለሚፈልጉ ሰዎች ይረዳ ይሆናል በማለት ነው ::
በእርግጥ እኔው ራሴው ብዙም የጠለቀ የእንግሊዘኛ እውቀት ስለሌለኝ : እዚህ ቤት ውስጥ በአብዛኛ ተማሪ ለመሆን ነው ጉጉቴ ::

አንዴ አንዱ ጓደኛዬ --> የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች የሚለው የአማርኛ አባባል በእንግሊዘኛ እንዴት ሊመነዘር ይችላል ብሎ ላብ በላብ አደረገኝ :: አለማወቄ ጉድ አደረገኝ ብዬ ተናደድኩኝ ::

ግን ከዚሁ ብንጀምር : ለመሆኑ የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች የሚለው አማርኛ አባባል በእንግሊዘኛው እንዴት ይተረጎማል ?????

ሀዲስ ነኝ

ጥሩ ቤት ነው እኛም በምናውቀው እንሳተፍ በጠየከው እንጀምራለን

የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች
While trying to pull down something from the attic she lost what she had under her armpit.

ልጅ ለናቷ ምጥ አስተማረች
A silly daughter teaches her mother how to bear children

ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታል
A belt fastened while running will come undone while running.

ሞት ያማራት አይጥ የድመትን አፍንጫ ታሸታለች
A mouse that wants to die goes to sniff the cat's nose.

ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኸ
When the hyena is gone, the dog begins to bark.

በሽታውን የሚደብቅ መዳኒት አይገኝለትም
He who conceals his disease cannot expect to be cured.

ቀስ በቀስ እንቁላል በእግሩ ይሄዳል
Step by step, the egg will walk on its legs

ኩራት እራት አይሆንም
Pride is no substitute for a dinner.

ያባይን ልጅ ውሃ ጠማው
The son of the nile thirsts for water.

ድር ቢያብር አንበሳ ያስር
When the webs of the spider join, they can trap a lion

ሁለት እግር አለኝ ተብሎ ሁለት ዛፍ አይወጣም
You may well have two legs but you still can't climb two trees at the same time.

በሉ እንግዲህ ለዛሬ አይበቃኝም :?: ደህና እደሩ
Last edited by ስራ ፈት on Sun Jan 06, 2013 6:02 pm, edited 2 times in total.
ስራ ፈት
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 65
Joined: Mon Jan 17, 2005 8:37 pm

Re: እንረዳዳ - የአማርኛ ዘዬያችን በእንግሊዘኛ

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Sun Jan 06, 2013 10:00 am

ሠላም ስራ ፈት

ስራ ፈት wrote:የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች
While trying to pull down something from the antique she lost what she had under her armpit.አባባል እኮ ቃል በቃል የሚተረጎም አይመስለኝም......ምክንያቱም መልዕክቱን እና ለዛውን ያጣና የሆነ ተረት ወይም ድርሰት ይመስላል :D...ለምሳሌ ከላይ የጠቀስኩትን ትርጉምህን ብናይ......"የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች" ለሚለው የሰጠኸው ቀጥተኛ ትርጉም እንኳን አማርኛውን አባባል ሊገልፅ ጭራሽ ያልተቋጨ መነባንብ ይመስላል.....While trying to pull down something from the antique she lost what she had under her armpit. :D (በነገራችን ላይ antique ያልከው attic ለማለት ፈልገህ ይመስለኛል)

በእኔ ግምት አባባሎችን በቀጥታ ለመተርጎም ከመሞከር ይልቅ ተዛማጅ የእንግሊዝኛ አባባሎችን መጠቀም የተሻለ ይሆናል

ለምሳሌ..."የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች" ለሚለው የአማርኛ አባባል..."A bird in the hand is worth two in the bush" የሚለው የእንግሊዝኛ አባባል ጥሩ የሚገልፀው ይመስለኛል......ሁለቱም አባባሎች "ሌላ አገኛለሁ ብለህ በእጅህ ውስጥ ያለውን እንዳታጣ" የሚል መልዕክት ነው ያላቸውና

አንዳንዴ ደግሞ እጅግ የተቀራረበ አባባሎችንም ታገኛለህ...ለምሳሌ....."የፈሰሰ ውሀ አይታፈስም" ለሚለው አማርኛ አባባል "Don't cry over spilt milk" የሚለው የእንግሊዝኛ አባባል እጅግ በጣም ይገልፀዋል......ውሀ እና ወተት ከመሆናቸው ውጪ :D ሁለቱም አባባሎች "የሆነው ሆነ" የሚል መልዕክት አላቸው

በእኔ አስተያየት ከዲጎኔና ከአንተ ሙከራዎች ይልቅ የአማርኛ አባባሎችን ወደእንግሊዝኛ አባባሎች በዚህ መልኩ ማስረዳት የተሻለ ይመስለኛል.....የግድ የአማርኛውን አባባል በቀጥታ ወደእንግሊዝ አፍ እንተርጉመው ካላችሁም መፍትሔው አባባሎቹን የግድ ቃል በቃል እየተረጎሙ የአባባልነት ለዛውን ማሳጣት ሳይሆን የአባባሉን ይዘት በጠበቀ መልኩ ቅልብጭ አድርጎ ለመግለፅ መሞከር የሚበጅ ይመስለኛል

ስራ ፈት wrote:
ሀዲስ 1 wrote:ሰላም : ሰላም : ሰላም !!!

ይህንን ክፍል ልከፍት ያሰብኩበት ምክንያት : ምናልባትም በእንግሊዘኛ መልክ ያለው ፅሁፍ ማሰናዳት ለሚፈልጉ ሰዎች ይረዳ ይሆናል በማለት ነው ::
በእርግጥ እኔው ራሴው ብዙም የጠለቀ የእንግሊዘኛ እውቀት ስለሌለኝ : እዚህ ቤት ውስጥ በአብዛኛ ተማሪ ለመሆን ነው ጉጉቴ ::

አንዴ አንዱ ጓደኛዬ --> የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች የሚለው የአማርኛ አባባል በእንግሊዘኛ እንዴት ሊመነዘር ይችላል ብሎ ላብ በላብ አደረገኝ :: አለማወቄ ጉድ አደረገኝ ብዬ ተናደድኩኝ ::

ግን ከዚሁ ብንጀምር : ለመሆኑ የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች የሚለው አማርኛ አባባል በእንግሊዘኛው እንዴት ይተረጎማል ?????

ሀዲስ ነኝ

ጥሩ ቤት ነው እኛም በምናውቀው እንሳተፍ በጠየከው እንጀምራለን

የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች
While trying to pull down something from the antique she lost what she had under her armpit.

ልጅ ለናቷ ምጥ አስተማረች
A silly daughter teaches her mother how to bear children

ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታል
A belt fastened while running will come undone while running.

ሞት ያማራት አይጥ የድመትን አፍንጫ ታሸታለች
A mouse that wants to die goes to sniff the cat's nose.

ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኸ
When the hyena is gone, the dog begins to bark.

በሽታውን የሚደብቅ መዳኒት አይገኝለትም
He who conceals his disease cannot expect to be cured.

ቀስ በቀስ እንቁላል በእግሩ ይሄዳል
Step by step, the egg will walk on its legs

ኩራት እራት አይሆንም
Pride is no substitute for a dinner.

ያባይን ልጅ ውሃ ጠማው
The son of the nile thirsts for water.

ድር ቢያብር አንበሳ ያስር
When the webs of the spider join, they can trap a lion

ሁለት እግር አለኝ ተብሎ ሁለት ዛፍ አይወጣም
You may well have two legs but you still can't climb two trees at the same time.

በሉ እንግዲህ ለዛሬ አይበቃኝም :?: ደህና እደሩ
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Re: እንረዳዳ - የአማርኛ ዘዬያችን በእንግሊዘኛ

Postby ስራ ፈት » Sun Jan 06, 2013 6:23 pm

ሰላም ዳግማዊ ስለ እርምቱ አመሰግናለው attic በሚለው ይስተካከል ማታ የፃፉት ፁሁፍና ማታ ይዘዋት ያደሩት ቺክ ጠዋት ሲነሱ እንከን አያጣቸውም :lol: ::

ይሄ ነገር ብዙ አከራካሪ ይመስለኛል:: አማርኛን አነጋገሮችን ወደ እንግሊዝኛ ስናመጣቸው ዘይቤያቸውን ባለቀቀ መልኩ መሆን ያለባቸው ይመስለኛል:: ተዛማጅ ትርጉም ከፈለግንለት ኢትዮጵያዊ ዘይቤው ይጠፋል:: ሁሉም አገር የራሱ አነጋገር አለው አንዳንዴም በእንግሊዝኛ ስታነበው ትርጉም አይሰጥም::

ስለ ትርጉም ካነሳህ ቁራን ለማንበብ አረብኛውን የምትማረው ኦርጅናል ሀሳቡን እንድትረዳ በማሰብ ነው:: ምን ግዜም ትርጉም ችግር አለው ቃል በቃል የተተረጎመን ነገር ለመረዳት ይከብዳል:: የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች ቅኔ ነገር ነው:: ብዙ የምትመኝ ያላትንም አጣች ለማለት ነው እንጂ ቆጥ ላይ ወጥታ እቃ ስትፈልግ በብብቷ የያዘችውን ጣለችው ለማለት እንዳልሆነ ግልፅ ነው:: ይሄንን አባባል ታዲያ የአነጋገር ዘይቤውን ሳይለቅ እንዴት ነው በእንግሊዝኛ የምንተረጉመው :?: ይመስለኛል የጠያቂው ሀሳብ ::

እኔ እንግዲህ የተማርኩት በነመለስ ግዜ ነው:: በሀይለስላሴና በመንጌ ግዜ የተማሩ ተማሪዎች ቦንብ ናቸው, የድሮ የስምተኛ ተማሪ የዛሬ ዩንቨርስቲ ተማሪ ነው ይባላል:: እንግዲህ እኛም የተቻለንን ከሞከርን ላይቀር የድሮ ተማሪዎች እስቲ ደግሞ ችሎታቸውን ያሳዩን::
:D መልካም ቆይታ::
ስራ ፈት
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 65
Joined: Mon Jan 17, 2005 8:37 pm

Re: እንረዳዳ - የአማርኛ ዘዬያችን በእንግሊዘኛ

Postby ዲጎኔ » Mon Jan 07, 2013 1:45 am

ሰላም ለሁላችን ይሁን
ወገን ስራ ፈት/እንደአንተ ላለ ጸሀፊ የማይገባ ኒክ/
ስለመልካሙ ስራህ እጥፍ ምስጋና ይድረስህ:: ይህ ከአንዱ ቁዋንቁውዋ ወደሌላ መተርጎም ባህላዊ እሴቶች ስላሉበት አልፎ አልፎ ስሜት የማይሰጡ ወይ ከኦርጂናሉ የተለዩ ትርጉሞች ይከተላሉ::አብዛኛው ግን የሁለቱንም ባህሎች ለተረዳ ውርስ ትርጉም adaptation ጥሩ ሲሆን ዳግማዊ እንዳለው የሚቀራረቡትን ተዛማጅ ትርጉም ማስቀመጥ ይሻላል::ለምሳሌ የፈሰሰ ውሀ አይታፈስም Do not cry over spilled milk የነገረ መለኮት ሰዎች በተለይ እንግሊዝኛ ተናጋሪዎች በዚህ ተቸግረዋል::ለምሳሌ NIV ውርስ ትርጉም አይነት ሲሆን ESV ደግሞ ቃል በቃል ትርጉም ነው::እኔ የሚመቸኝ ውርስ ትርጉሙ ነው:: መድሀኒያለም Our savior እንጂ Medicine of the world አይሆንም::የአጼው ዘመን ተርጉዋሚዎችን አደንቃለሁ በተለይ መጽሀፍ ቅዱስ የ1954 እትም ኢትዮጲያን ቨርሽን ሊባል ይቻላል:Bread of life ይህይወት እንጀራ ብለው የተረጎሙ ውርስ ትርጉም ሲሆን የህይወት ዳቦ ቢል ስሜት አይሰጥም:: የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለችን ጥሩ ተማርኩ ወደላይ ለማውረድ ስትንጠራራ በብቷ የያዘችው ጣለች ከሚለው ይልቅ አንዱን በደንብ ሳትይዝ ሌላ ስትፈልግ ሁለቱንም አጣች ወይም ከሁለት ያጣ ይመጥናል::አሁን እኔ የምመርጥ Ethiopic የሚለውን የመግባቢያ አማርኛ እንጂ የአማሮቹን ክላሲካል አማርኛ አይደለም::ያንን ሳፊ ጎንደረዎቹ ወይም መንዜዎቹ ሊመርጡት ይችላሉ የእኔና መሰሎቸ ምርጫ ግን ከሁሉም ብሄር ብሄረሰቦችና ሀይማኖቶች እየተዋሰ ያደገውን የጦቢያ መግባቢያ ቁዋንቁዋ ነው::ዋርካ ላይ በዚህ የሚተቹኝ ቢኖሩ አይደንቀኝ ያ ለእኔ ማንነቴ ነውና ሁሉን ያካተተ እንዲህ ያለ ስነቃል ስራ ላይ በርቱ እላለሁ::በተረፈ እንግሊዝኛው ችሎታ እንዳልከው እየቀነሰ ቢመጣም ከአሁኑ ትውልድም የሚደነቁ እያየን ነው::

ስራ ፈት wrote:ሰላም ዳግማዊ ስለ እርምቱ አመሰግናለው attic በሚለው ይስተካከል ማታ የፃፉት ፁሁፍና ማታ ይዘዋት ያደሩት ቺክ ጠዋት ሲነሱ እንከን አያጣቸውም :lol: ::

ይሄ ነገር ብዙ አከራካሪ ይመስለኛል:: አማርኛን አነጋገሮችን ወደ እንግሊዝኛ ስናመጣቸው ዘይቤያቸውን ባለቀቀ መልኩ መሆን ያለባቸው ይመስለኛል:: ተዛማጅ ትርጉም ከፈለግንለት ኢትዮጵያዊ ዘይቤው ይጠፋል:: ሁሉም አገር የራሱ አነጋገር አለው አንዳንዴም በእንግሊዝኛ ስታነበው ትርጉም አይሰጥም::

ስለ ትርጉም ካነሳህ ቁራን ለማንበብ አረብኛውን የምትማረው ኦርጅናል ሀሳቡን እንድትረዳ በማሰብ ነው:: ምን ግዜም ትርጉም ችግር አለው ቃል በቃል የተተረጎመን ነገር ለመረዳት ይከብዳል:: የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች ቅኔ ነገር ነው:: ብዙ የምትመኝ ያላትንም አጣች ለማለት ነው እንጂ ቆጥ ላይ ወጥታ እቃ ስትፈልግ በብብቷ የያዘችውን ጣለችው ለማለት እንዳልሆነ ግልፅ ነው:: ይሄንን አባባል ታዲያ የአነጋገር ዘይቤውን ሳይለቅ እንዴት ነው በእንግሊዝኛ የምንተረጉመው :?: ይመስለኛል የጠያቂው ሀሳብ ::

እኔ እንግዲህ የተማርኩት በነመለስ ግዜ ነው:: በሀይለስላሴና በመንጌ ግዜ የተማሩ ተማሪዎች ቦንብ ናቸው, የድሮ የስምተኛ ተማሪ የዛሬ ዩንቨርስቲ ተማሪ ነው ይባላል:: እንግዲህ እኛም የተቻለንን ከሞከርን ላይቀር የድሮ ተማሪዎች እስቲ ደግሞ ችሎታቸውን ያሳዩን::
:D መልካም ቆይታ::
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby ስራ ፈት » Tue Jan 08, 2013 6:41 am

ሰላም ዲጎኔ
ያልከው ገብቶኛል እንደሚመስለኝ ብዙዎቹ ሰዎች ያንተን አስተሳሰብ ይጋራሉ ብዬ አስባለው::

እኛ ወኔ እንጂ በስራ እምብዛም ነን:: ይሄን ያልኩበት ምክንያት ቋንቋችንን ለማሳደግ ምንም ነገር ስናደር አይታይም:: ለምሳሌ ኢትዮጵያ ውስጥ አማርኛ እንደምንማረው ለምን ኦሮሚፋ አይሰጥም :?: :: ምን ይጎዳናል :?: እኛ ስንማር እርሻ, ሙዚቃና እጅስራ የሚባሉ እጅግ ጥቅም አልባ ሰብጀክቶች ይሰጡ ነበር:: ይገርምሀል አንዱንም አላስታውሰውም::

በዚ ፋንታ በሸገር ለምሳሌ ኦሮሚፋ ቢሰጥ አብዛኛው ሰው ቤዚክ የሆነ እውቀት ይኖረዋል ማለት ነው:: አማራ ክልል ኦሮሚፋ ቢማሩም ጥሩ ይመስለኛል, ምክንያቱም ቋንቋቸው በሁሉም ኢትዮጵያ ስለሚነገር ከወላጆቻቸው ቋንቋ በቀር ሌላ ቋንቋ መናገር አይጠበቅባቸውም::

ሲዳማው, ኦሮሞውና ሌላው ኢትዮጵያዊ ግን የራሱን ቋንቋ ማሳደግና መናገር ብቻ ሳይሆን አማርኛ ማወቅ ይጠበቅበታል:: ስለዚህ በሸገርና በአማራ ክልል ኦሮሚፋ ቢሰጥ አንደኛ እነዚህን ሁለቱን ህዝቦች ያቀራርባል:: ብሎም አማራው ለኦሮሞ ባህልና ታሪክ እንግዳ አይሆንም:: በሸዋ እንደሚታየው ኦሮሞው ከማንም በላይ ከአማራው ጋር ነው የተዋለደውና የተጋባው:: ስለዚህ ሁለቱ ህዝቦች በሁለት የተለያዩ ቋንቋ መግባባት ከቻሉ ባህላችን ያምራል ፍቅራችንም ይጨምር ነበር::

ይሄንን ለማሳደግ ብዙ ጥረትና ትግስትን ይጠይቃል:: ወደ ፊትም እንደሚሆን አልጠራጠርም ሰላም ያድርሰን ብቻ::

እንግዲህ እንደዚህ መፈላሰፌ ካልቀረ አንድ የልጆች ዘፈን እስቲ ልጋብዛቹ:: እኔ መቼም ልጆቹን ወድጃቸው ልሞት ነው:: ያገሬ ልጆች አዲሶቹ ኢትዮጵያዊያን ብዬ መቼም በኩራት ተነፋፍቼ የተቀመጥኩበት ሶፋ ሁሉ አልበቃ አለኝ:: :D :D መልካም ቀን ለሁላችን::

http://youtu.be/ei0In0HGYVU
ስራ ፈት
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 65
Joined: Mon Jan 17, 2005 8:37 pm

Postby ልብነድንግል » Wed Jan 09, 2013 2:57 am

ስራ ፈት wrote:ሰላም ዲጎኔ
ያልከው ገብቶኛል እንደሚመስለኝ ብዙዎቹ ሰዎች ያንተን አስተሳሰብ ይጋራሉ ብዬ አስባለው::

እኛ ወኔ እንጂ በስራ እምብዛም ነን:: ይሄን ያልኩበት ምክንያት ቋንቋችንን ለማሳደግ ምንም ነገር ስናደር አይታይም:: ለምሳሌ ኢትዮጵያ ውስጥ አማርኛ እንደምንማረው ለምን ኦሮሚፋ አይሰጥም :?: :: ምን ይጎዳናል :?: እኛ ስንማር እርሻ, ሙዚቃና እጅስራ የሚባሉ እጅግ ጥቅም አልባ ሰብጀክቶች ይሰጡ ነበር:: ይገርምሀል አንዱንም አላስታውሰውም::

በዚ ፋንታ በሸገር ለምሳሌ ኦሮሚፋ ቢሰጥ አብዛኛው ሰው ቤዚክ የሆነ እውቀት ይኖረዋል ማለት ነው:: አማራ ክልል ኦሮሚፋ ቢማሩም ጥሩ ይመስለኛል, ምክንያቱም ቋንቋቸው በሁሉም ኢትዮጵያ ስለሚነገር ከወላጆቻቸው ቋንቋ በቀር ሌላ ቋንቋ መናገር አይጠበቅባቸውም::

ሲዳማው, ኦሮሞውና ሌላው ኢትዮጵያዊ ግን የራሱን ቋንቋ ማሳደግና መናገር ብቻ ሳይሆን አማርኛ ማወቅ ይጠበቅበታል:: ስለዚህ በሸገርና በአማራ ክልል ኦሮሚፋ ቢሰጥ አንደኛ እነዚህን ሁለቱን ህዝቦች ያቀራርባል:: ብሎም አማራው ለኦሮሞ ባህልና ታሪክ እንግዳ አይሆንም:: በሸዋ እንደሚታየው ኦሮሞው ከማንም በላይ ከአማራው ጋር ነው የተዋለደውና የተጋባው:: ስለዚህ ሁለቱ ህዝቦች በሁለት የተለያዩ ቋንቋ መግባባት ከቻሉ ባህላችን ያምራል ፍቅራችንም ይጨምር ነበር::

ይሄንን ለማሳደግ ብዙ ጥረትና ትግስትን ይጠይቃል:: ወደ ፊትም እንደሚሆን አልጠራጠርም ሰላም ያድርሰን ብቻ::

እንግዲህ እንደዚህ መፈላሰፌ ካልቀረ አንድ የልጆች ዘፈን እስቲ ልጋብዛቹ:: እኔ መቼም ልጆቹን ወድጃቸው ልሞት ነው:: ያገሬ ልጆች አዲሶቹ ኢትዮጵያዊያን ብዬ መቼም በኩራት ተነፋፍቼ የተቀመጥኩበት ሶፋ ሁሉ አልበቃ አለኝ:: :D :D መልካም ቀን ለሁላችን::

http://youtu.be/ei0In0HGYVU

ሰላም ስራ-ፈት

መልካም ሀሳብ ነበር,,,,,,ሀይስኩል እያለሁ ይሄ ሀሳብ ተነስቶ
የትኛውን የቋንቋ መማር ትፈልጋላቹ ተብሎ ምርጫ ሁሉ ተደርጎ ነበር::ምርጫውንም ትግሪኛ ቋንቋ በጠባብ ልዩነት ኦሮሚፋን ማሸነፉ ተነግሮን ትምሩ ዛሬ ነገ ይጀመራል ተብሎ ሲጠበቅ/ስንጠብቅ(ለነገሩ እኔ የመረጥኩት ጉራጊኛን ነበር ነጋዴ የመሆን ቅዠት ስለነበረኝ) የውሀ ሽታ ሆኖ ቀረ::
ልብነድንግል
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 126
Joined: Sun Jun 28, 2009 10:54 pm
Location: usa

Re: እንረዳዳ - የአማርኛ ዘዬያችን በእንግሊዘኛ

Postby ሀዲስ 1 » Wed Jan 09, 2013 8:30 pm

ይልቁኑ ዛሬ ወደሁለተኛው ፎሊስ ደረጃ ከፍ ላደርግህ ፈለኩኝ :lol: :lol: :lol:

ለካ ማሰብም ትችላለህ ? ...... ቂቂቂቂቂቂ ....

የስራ ፈትን ተሳትፎ ቃርሜ .... ይሄ ነገር ግን እንዲህ ከሚሆን ብዬ ሀሳቤንም ሳልጨርስ ያንተን : ከኔ ያገናኘኝን አስተያየት አየሁና
ለካ ይሄ ሰውዬም ማሰብ ጀመረ !!!!!አልኩኝ ::

ይቅርታ ስራ ፈት !!!
በእኔ እይታም አባባሎቻችን መተርጎም ("ተ" -> ይጥበቅ) ሳይሆን ያለባቸው : የእንግሊዘኛ አቻቸውን (ተዛማጃቸውን) ነው ማግኘት ያለባቸው :: ነገሩ ከባድ ስራና ትልቅ እውቀት የሚጠይቅ ይመስለኛል :: እንደውም ትልቅ የቋንቋ ትምህርትን መላበስ የሚያስፈልገው ይመስለኛል ::
ከዛ በፊት ግን አቻቸውን የምንፈልግላቸው አነጋገሮቻችን ስንጠቀም ምን ለማለት እንደፈለግን ጠንቅቀን ማወቅ ያለብን ይመስለኛል :: ለምሳሌ -->
የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች ..... ማለት .... አልጠግብ ባይነትን : ገብጋባነትን የሚያመላክት ይመስለኛል :: ምናልባትም :!: አልጠግብ ባይ ሲተፋ ያድራል :!: የሚለውን አባባል ሊቀይር ይችላል ::

እስኪ በዚህ ሂደቱ እንቀጥልና የምንስማማበትን (አጥጋቢ የሚመስለንን) በድምፅ እናፀድቀዋለን ::

ሀዲስዳግማዊ ዋለልኝ wrote:ሠላም ስራ ፈት

ስራ ፈት wrote:የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች
While trying to pull down something from the antique she lost what she had under her armpit.አባባል እኮ ቃል በቃል የሚተረጎም አይመስለኝም......ምክንያቱም መልዕክቱን እና ለዛውን ያጣና የሆነ ተረት ወይም ድርሰት ይመስላል :D...ለምሳሌ ከላይ የጠቀስኩትን ትርጉምህን ብናይ......"የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች" ለሚለው የሰጠኸው ቀጥተኛ ትርጉም እንኳን አማርኛውን አባባል ሊገልፅ ጭራሽ ያልተቋጨ መነባንብ ይመስላል.....While trying to pull down something from the antique she lost what she had under her armpit. :D (በነገራችን ላይ antique ያልከው attic ለማለት ፈልገህ ይመስለኛል)

በእኔ ግምት አባባሎችን በቀጥታ ለመተርጎም ከመሞከር ይልቅ ተዛማጅ የእንግሊዝኛ አባባሎችን መጠቀም የተሻለ ይሆናል

ለምሳሌ..."የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች" ለሚለው የአማርኛ አባባል..."A bird in the hand is worth two in the bush" የሚለው የእንግሊዝኛ አባባል ጥሩ የሚገልፀው ይመስለኛል......ሁለቱም አባባሎች "ሌላ አገኛለሁ ብለህ በእጅህ ውስጥ ያለውን እንዳታጣ" የሚል መልዕክት ነው ያላቸውና

አንዳንዴ ደግሞ እጅግ የተቀራረበ አባባሎችንም ታገኛለህ...ለምሳሌ....."የፈሰሰ ውሀ አይታፈስም" ለሚለው አማርኛ አባባል "Don't cry over spilt milk" የሚለው የእንግሊዝኛ አባባል እጅግ በጣም ይገልፀዋል......ውሀ እና ወተት ከመሆናቸው ውጪ :D ሁለቱም አባባሎች "የሆነው ሆነ" የሚል መልዕክት አላቸው

በእኔ አስተያየት ከዲጎኔና ከአንተ ሙከራዎች ይልቅ የአማርኛ አባባሎችን ወደእንግሊዝኛ አባባሎች በዚህ መልኩ ማስረዳት የተሻለ ይመስለኛል.....የግድ የአማርኛውን አባባል በቀጥታ ወደእንግሊዝ አፍ እንተርጉመው ካላችሁም መፍትሔው አባባሎቹን የግድ ቃል በቃል እየተረጎሙ የአባባልነት ለዛውን ማሳጣት ሳይሆን የአባባሉን ይዘት በጠበቀ መልኩ ቅልብጭ አድርጎ ለመግለፅ መሞከር የሚበጅ ይመስለኛል

ስራ ፈት wrote:
ሀዲስ 1 wrote:ሰላም : ሰላም : ሰላም !!!

ይህንን ክፍል ልከፍት ያሰብኩበት ምክንያት : ምናልባትም በእንግሊዘኛ መልክ ያለው ፅሁፍ ማሰናዳት ለሚፈልጉ ሰዎች ይረዳ ይሆናል በማለት ነው ::
በእርግጥ እኔው ራሴው ብዙም የጠለቀ የእንግሊዘኛ እውቀት ስለሌለኝ : እዚህ ቤት ውስጥ በአብዛኛ ተማሪ ለመሆን ነው ጉጉቴ ::

አንዴ አንዱ ጓደኛዬ --> የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች የሚለው የአማርኛ አባባል በእንግሊዘኛ እንዴት ሊመነዘር ይችላል ብሎ ላብ በላብ አደረገኝ :: አለማወቄ ጉድ አደረገኝ ብዬ ተናደድኩኝ ::

ግን ከዚሁ ብንጀምር : ለመሆኑ የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች የሚለው አማርኛ አባባል በእንግሊዘኛው እንዴት ይተረጎማል ?????

ሀዲስ ነኝ

ጥሩ ቤት ነው እኛም በምናውቀው እንሳተፍ በጠየከው እንጀምራለን

የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች
While trying to pull down something from the antique she lost what she had under her armpit.

ልጅ ለናቷ ምጥ አስተማረች
A silly daughter teaches her mother how to bear children

ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታል
A belt fastened while running will come undone while running.

ሞት ያማራት አይጥ የድመትን አፍንጫ ታሸታለች
A mouse that wants to die goes to sniff the cat's nose.

ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኸ
When the hyena is gone, the dog begins to bark.

በሽታውን የሚደብቅ መዳኒት አይገኝለትም
He who conceals his disease cannot expect to be cured.

ቀስ በቀስ እንቁላል በእግሩ ይሄዳል
Step by step, the egg will walk on its legs

ኩራት እራት አይሆንም
Pride is no substitute for a dinner.

ያባይን ልጅ ውሃ ጠማው
The son of the nile thirsts for water.

ድር ቢያብር አንበሳ ያስር
When the webs of the spider join, they can trap a lion

ሁለት እግር አለኝ ተብሎ ሁለት ዛፍ አይወጣም
You may well have two legs but you still can't climb two trees at the same time.

በሉ እንግዲህ ለዛሬ አይበቃኝም :?: ደህና እደሩ
what we learn from history is, we do not learn from history.

http://www.isil.org/resources/philosoph ... nglish.swf
ሀዲስ 1
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1643
Joined: Wed Mar 10, 2010 12:23 am

Postby ሀዲስ 1 » Thu Jan 10, 2013 11:23 pm

ለዳግማዊው !!!

በእኔ አስተያየት ያንተ አማራጭ : የአማርኛን አነጋገር ዘይቤዎች ከእንግሊዘኛው ጋር ለማቀራረብ ተቀራራቢ መፍትሄ (ፍቺ) ነው :: ሆኖም እኔ እንደመሰለኝ ከሆነ የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች የሚለውን አባባል የመነዘርክበት የእንግሊዘኛ አነጋገር ዘዴ በጣም ቢቀራረብም : ግን 100% ይወክለዋል ብዬ ለማለት ይከብደኛል ::

በዕኔ አባባል --> የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን መጣሏ እኮ በመንገብገቧ መሰለኝ እኮ !!! ወይስ ሌላ ነው ውስጠ ወይራው ???
A bird in a Hand is worth two in the bush የሚለው አባባል መስገብገብን የሚያሳይ አልመሰለኝም እኮ ዳ-ግ

ሌሎቻችሁስ ምን ይመስላችኃል ?????

ሀዲስ
what we learn from history is, we do not learn from history.

http://www.isil.org/resources/philosoph ... nglish.swf
ሀዲስ 1
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1643
Joined: Wed Mar 10, 2010 12:23 am

Re: እንረዳዳ - የአማርኛ ዘዬያችን በእንግሊዘኛ

Postby እቴጌይት » Sat Jan 12, 2013 1:53 am

ሠላም ለዚህ ቤት

ሀዲስ ጥሩ አምድ ከፍተሀል ወንድሜ!
እኔም ከላይ ሌሎች እንዳሉት ተረትና ምሳሌዎችና አባባሎች ቃል በቃል ሳይሆን ጭብጣቸውን በሚገልጽ አባባል ቢተረጎሙ ይሻላል ብዬ አስባለሁኝ::
ታች ስራ ፈት ከዘረዘራቸው አባባሎች ውስጥ የተወሰኑትን ልሞክር እስቲ:-

ሲሮጡ የታጠቁት -ሲሮጡ ይፈታል:-
Haste makes waste

በሽታውን የሚደብቅ መዳኒት አይገኝለትም
Nothing ventured, nothing gained

ቀስ በቀስ እንቁላል በእግሩ ይሄዳል
One step at a time. (or one may walk over the highest mountain one step at a time).

ኩራት እራት አይሆንም
Pride goeth before a fall

ድር ቢያብር አንበሳ ያስር
The whole is greater than the sum of its parts

ሁለት እግር አለኝ ተብሎ ሁለት ዛፍ አይወጣም
To do two things at once is to do neither

ደህና ቆዩ

ስራ ፈት wrote:
ጥሩ ቤት ነው እኛም በምናውቀው እንሳተፍ በጠየከው እንጀምራለን

የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች
While trying to pull down something from the attic she lost what she had under her armpit.

ልጅ ለናቷ ምጥ አስተማረች
A silly daughter teaches her mother how to bear children

ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታል
A belt fastened while running will come undone while running.

ሞት ያማራት አይጥ የድመትን አፍንጫ ታሸታለች
A mouse that wants to die goes to sniff the cat's nose.

ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኸ
When the hyena is gone, the dog begins to bark.

በሽታውን የሚደብቅ መዳኒት አይገኝለትም
He who conceals his disease cannot expect to be cured.

ቀስ በቀስ እንቁላል በእግሩ ይሄዳል
Step by step, the egg will walk on its legs

ኩራት እራት አይሆንም
Pride is no substitute for a dinner.

ያባይን ልጅ ውሃ ጠማው
The son of the nile thirsts for water.

ድር ቢያብር አንበሳ ያስር
When the webs of the spider join, they can trap a lion

ሁለት እግር አለኝ ተብሎ ሁለት ዛፍ አይወጣም
You may well have two legs but you still can't climb two trees at the same time.

በሉ እንግዲህ ለዛሬ አይበቃኝም :?: ደህና እደሩ
እቴጌይት
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 656
Joined: Sun Sep 23, 2007 10:38 pm

Next

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 5 guests