እንረዳዳ - የአማርኛ ዘዬያችን በእንግሊዘኛ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby እቴጌይት » Sat Jan 12, 2013 2:11 am

ሠላም በድጋሚ ለዚህ ቤት
ሀዲስ በነገራችን ላይ ዳግማዊ የቆጡን አወርድ ብላን የተረጎመበት አባባል በትክክል ጭብጡን የሚገልጸው ይመስለኛል::
ጭብጡ መስገብገን የሚያሳይ ሳይሆን በእጅህ በእርግጠናነት ያለውን አጥብቀህ ሳትይዝ ገና ለገና እጅህ ላይ የሌለን አገኛለሁ ብለህ ብትለቀው ሁሉንም አጥተህ ቁጭ ልትል ትችላለህ ነው:: ባጭሩ ብብትህ ውስጥ ያለውን መጀመሪያ ዋጋ ስጥ ነው:: ስለዚህ የቆጡን አወርድ ብላ ብብታ ውስጥ ያለውን የጣለችው ሁለት እርግብ ከጫካ አገኛለሁ ብላ በእጇ ያለውን እርግብ እንዳትለቅ ከተመከረችው ጋር ትይዩ ይመስለኛል::

በድጋሚ ለግሩም አምድህ አመሰግንሀለሁ!
እቴጌይት
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 656
Joined: Sun Sep 23, 2007 10:38 pm

Re: እንረዳዳ - የአማርኛ ዘዬያችን በእንግሊዘኛ

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Sat Jan 12, 2013 3:30 am

ሠላም ሀዲስ1

ሆኖም እኔ እንደመሰለኝ ከሆነ የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች የሚለውን አባባል የመነዘርክበት የእንግሊዘኛ አነጋገር ዘዴ በጣም ቢቀራረብም : ግን 100% ይወክለዋል ብዬ ለማለት ይከብደኛል ::


እቴጌይት እንዳስረዳችው በእኔም ግምት ጭብጣቸው አንድ ዓይነት ስለሆነ ጥሩ ይገልፀዋል የሚል እምነት አለኝ.....አንተ እንዳልከው ግን የአንድ ቋንቋ አባባልን 100% የሚወክል የሌላ ቋንቋ አባባል ማግኘት መቻሉን ግን እርግጠኛ አይደለሁም .....ተዛማጅ አባባሎችን እየፈለግን ያለነውም 100% የሚወክል ማግኘት ሰለማይቻል ይመስለኛል :D

ሠላም


ሠላም እቴጌይት

አባባሎቹን በጥሩ ሁኔታ ገልፀሻቸዋል........አሪፍ :!:

"ኩራት እራት አይሆንም
Pride goeth before a fall" ያልሽው ላይ ግን የአማርኛ ሐሳቡን ይበልጥ ለመግለፅ "Much Ado About Nothing"ን ብንጠቀም ምን ይመስልሻል :?:

ሠላም


እቴጌይት wrote:ሠላም ለዚህ ቤት

ሀዲስ ጥሩ አምድ ከፍተሀል ወንድሜ!
እኔም ከላይ ሌሎች እንዳሉት ተረትና ምሳሌዎችና አባባሎች ቃል በቃል ሳይሆን ጭብጣቸውን በሚገልጽ አባባል ቢተረጎሙ ይሻላል ብዬ አስባለሁኝ::
ታች ስራ ፈት ከዘረዘራቸው አባባሎች ውስጥ የተወሰኑትን ልሞክር እስቲ:-

ሲሮጡ የታጠቁት -ሲሮጡ ይፈታል:-
Haste makes waste

በሽታውን የሚደብቅ መዳኒት አይገኝለትም
Nothing ventured, nothing gained

ቀስ በቀስ እንቁላል በእግሩ ይሄዳል
One step at a time. (or one may walk over the highest mountain one step at a time).

ኩራት እራት አይሆንም
Pride goeth before a fall

ድር ቢያብር አንበሳ ያስር
The whole is greater than the sum of its parts

ሁለት እግር አለኝ ተብሎ ሁለት ዛፍ አይወጣም
To do two things at once is to do neither

ደህና ቆዩ
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Postby እቴጌይት » Sat Jan 12, 2013 9:31 pm

ዳግማዊ
'ኩራት እራት አይሆንም'ን ስረዳው ኩራት ጦም ማደርን ጥፋትን ውድቀትን ማስከተሉን የሚጠቁም ጭብጥ እንዳለው ነው:: 'Much ado about nothing' ስረዳው ደግሞ እዚህ ግባ የማይባል ኢምነት ነገርን ማካበድን (making a big fuss about a trivial matter) ይመስለኛል: እንጂ የኩራትን ጉዳት ጠቋሚ አይመስለኝም:: ባንጻሩ 'Pride goeth before a fall' ከኩራት ጀርባ ውድቀት (በአማርኛው ኮንቴክስት ጦም ማደር) መኖሩን ጠቋሚ ስለሆነ ጭብጡ የተሻለ የሚተረጉመው ይመስለኛል::

መልካም ጊዜ
እቴጌይት
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 656
Joined: Sun Sep 23, 2007 10:38 pm

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Mon Jan 14, 2013 12:28 am

ሠላም እቴጌይት

በእኔ እይታ "ኩራት እራት አይሆንም" ማለት ተጨባጭ ውጤትና ትርጉም የሌለውን ነገር ማካበድ ፋይዳ የለውም የሚል ሀሳብ ነው.....እንጂ አንቺ እንዳልሽው ከውድቀት ጋር አይገናኝም......እንደውም 'Much ado about nothing'ን አንቺው እንዳስቀመጥሽው ትርጉም በቀጥታ የሚገናኙ ተመሳሳይ አባባሎች ናቸው

እስቲ በድጋሚ እዪው...."ኩራት እራት አይሆንም" እና "ትዕቢት (ኩራት) ውድቀትን ትቀድማለች" የሚሉት አባባሎች ጭብጦቻቸው የተለያየ ይመስለኛል.....አንደኛው ኩራት እራት ስለማይሆን ኩራትህን ትተህ እራትህ የምታገኝበትን ዘዴ ፈልግ ወይንም ስራ የሚል ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ኩራት ይጥልሀል.....መውደቅህ አይቀርም የሚል ነው

ሠላም

እቴጌይት wrote:ዳግማዊ
'ኩራት እራት አይሆንም'ን ስረዳው ኩራት ጦም ማደርን ጥፋትን ውድቀትን ማስከተሉን የሚጠቁም ጭብጥ እንዳለው ነው:: 'Much ado about nothing' ስረዳው ደግሞ እዚህ ግባ የማይባል ኢምነት ነገርን ማካበድን (making a big fuss about a trivial matter) ይመስለኛል: እንጂ የኩራትን ጉዳት ጠቋሚ አይመስለኝም:: ባንጻሩ 'Pride goeth before a fall' ከኩራት ጀርባ ውድቀት (በአማርኛው ኮንቴክስት ጦም ማደር) መኖሩን ጠቋሚ ስለሆነ ጭብጡ የተሻለ የሚተረጉመው ይመስለኛል::

መልካም ጊዜ
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Postby እቴጌይት » Mon Jan 14, 2013 1:51 am

ዳግማዊ
እንዴት እንዳየሁት ለማስረዳት ልሞክር:-
በባህላችን ብዙዎቻችን ዘንድ ባለ ኩራት የተነሳ ራሳችንን ላለማስገመት እየራበን ጠግበናል እንላለን..የዚህ ቀዳሚ ኩራት ተከታይ ውጤት ደግሞ ጦም ማደር ይሆናል:: ድሀ ሆነን... ብር ሳይኖረን.. ኩራታችንን ለመጠበቅ በአደባባይ ግን ሰው ካልጋበዝን እንላለን..ውጤቱ ልጆቻችንን ጦም ማሳደርና የበለጠ መቸገር ይሆናል ወዘተ:: እና እኔ ይሄንን ተረት የምረዳው (ቀዳሚው) ባዶ ኩራት... ውጤቱ (የሚያስከትለው) ጦም ማደር መቸገር ውድቀት ነው በሚል መልኩ (እንደ ኩራት ውድቀትን ያስከትላል) እንጂ አትነ በተረዳኸው መልኩ ትንሿን ነገር አጋኖ ከማየት ጋር (Much ado about nothing) ጋር የሚቀራረብ አይመስለኝም::

ሠላም
እቴጌይት
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 656
Joined: Sun Sep 23, 2007 10:38 pm

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Mon Jan 14, 2013 4:40 am

ሠላም እቴጌይት

1. እየራበው ጠግቤያለሁ የሚል; ወይም ድሀ ሆኖ በአደባባይ ሰው ልጋብዝ የሚል ግድርድርና ግብዝ እንጂ ኩራተኛ ወይም ትዕቢተኛ አይደለም........በሌላ በኩል ደግሞ Pride goeth before a fall የሚለው አባባል የሚያሳየው የማን አለብኝነት ትዕቢትን ነው....ለዚህ ነው አባባሉ ከልክ ያለፈ ጥጋብ ወይም የተሳሳተ ሁሉን አውቃለሁ ባይነቱ ወደውድቀት ይመራዋል የሚለው.......ደሀ ሰው ግን እየራበውም ቢሆን ይግደረደራል እንጂ ቢያንስ በትዕቢት አይታማም......ስለዚህ ምሳሌሽ ትክክል አይመስለኝም

2. "ኩራት እራት አይሆንም" የሚለው አባባል በግልፅ የሚያስረዳው ኩራት እህል አይሆንም; አይበላም ማለት ነው.....አባባሉ እዚህ ጋር ያበቃል......አንቺ ግን ቅጥያ ታሪክ ፈጠርሽለት....ሰዎቹ ኩራት ካልበሉ ጦም ያድራሉ....ከዛም ይራባሉ....ከዛም ይወድቃሉ የሚል በጣም far-fetched የሆነ ትርጉም ነው.....በዚህ አይነትማ ለምሳሌ "ዥብ የማያውቁት ሀገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ" ይላል የሚለውን አባባል ዥቡ ቁርበት ተነጥፎለት; እግሩን አጥበውት ከተኛ በኻላ ሌሊት ተነስቶ የቤቱን ባለቤቶችና ከብቶች በላቸው እያልን ልንቀጥል ነው.....ነገር ግን አባባል ነው እንጂ ዥብን እንግዳ ብሎ አይደለም ቁርበት የሚያነጥፍ ወደቤቱም የሚያስጠጋ ያለ አይመስለኝም :D

3. Much ado about nothing ማለት ምንም ትርጉም ወይ ፋይዳ በሌለው ጉዳይ ላይ እጅግ ትኩረት መስጠት ወይም ማካበድ ነው........ይህም በቀጥታ እራት ላይሆን ነገር ኩራት ምንም ፋይዳ እንደሌለው ከሚናገረው "ኩራት እራት አይሆንም" ጋር አሁንም አንድ አይነት ይመስለኛል

በተረፈ ከደብረ ኤልያስ የተመረቀ መሪ ጌታ መጥቶ ቢገላግለን የተሻለ ይመስለኛል :D

ሠላም

እቴጌይት wrote:ዳግማዊ
እንዴት እንዳየሁት ለማስረዳት ልሞክር:-
በባህላችን ብዙዎቻችን ዘንድ ባለ ኩራት የተነሳ ራሳችንን ላለማስገመት እየራበን ጠግበናል እንላለን..የዚህ ቀዳሚ ኩራት ተከታይ ውጤት ደግሞ ጦም ማደር ይሆናል:: ድሀ ሆነን... ብር ሳይኖረን.. ኩራታችንን ለመጠበቅ በአደባባይ ግን ሰው ካልጋበዝን እንላለን..ውጤቱ ልጆቻችንን ጦም ማሳደርና የበለጠ መቸገር ይሆናል ወዘተ:: እና እኔ ይሄንን ተረት የምረዳው (ቀዳሚው) ባዶ ኩራት... ውጤቱ (የሚያስከትለው) ጦም ማደር መቸገር ውድቀት ነው በሚል መልኩ (እንደ ኩራት ውድቀትን ያስከትላል) እንጂ አትነ በተረዳኸው መልኩ ትንሿን ነገር አጋኖ ከማየት ጋር (Much ado about nothing) ጋር የሚቀራረብ አይመስለኝም::

ሠላም
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Postby እቴጌይት » Mon Jan 14, 2013 6:24 am

መግደርደር እኮ ኩራት ከሚገለጥበት አንዱ መንገድ ነው:: ትንሿን ነገር ቢግ ዲል ማድረግ ግን የተጨናቂነት ወይም የነጭናጫነት ወይም ቅድሚያ የሚሰጠውን ያለማወቅ ወዘተ ጉዳይ እንጂ ከኩራት ጋር የሚዛመድ አይደለም:: ለምሳሌ ግድርድሩ 'ጎንደሬ ቀን በበቅሎ ሌት በቆሎ' ሲባል ኩራቱን ለመግለጽ ነው:: ይሔ ኩራቱ ደግሞ እራት ስለማይሆነው ነው ቀን በቅሎ ላይ ተቆንኖ ሲጋበዝ ጠግቤያለሁ ሲል ይውልና ማታ ቆሎ በልቶ (ተርቦ) የሚያደረው! ኩራቱ እራቱ አለሆነውም:: ታዲያ ይሄ ትንሿን ነገር ቢግ ዲል ከማድረግ ጋር የሚገናኝ ሳይሆን ኩራቱ የሚበጀውን ነገር እንዳይገኝ ከማድረጉ (failure) ጋር ነው የሚዛመደው:: ለማንኛውም በመሪ ጌታ ልዳኝ ካልክ ወደ ሀገሬ ልዘልቅ ስለሆነ ስመለስ ብያኔውን ይዤልህ መጣለሁ!

ሠላም
እቴጌይት
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 656
Joined: Sun Sep 23, 2007 10:38 pm

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Mon Jan 14, 2013 6:50 am

ሠላም እቴጌይት

የሀገሬ ገበሬ ብር ሊበደር ሰው ቤት ሄዶ ብላ ሲባል አይ በልቻለሁ የሚለው የመግደርደር ወግ ሆኖበት እንጂ ብር ልመና ሄዶ የምን ኩራት አለ ብለሽ ነው........."ቀን በበቅሎ ሌት በቆሎ" ያልሽውም ቢሆን ግብዝነት እንጂ የምን ኩራት ነው......በዛ ላይ ደግሞ ቤቱ ገብቶ ቆሎም ሆነ የጓያ ሽሮ ከበላ ለምን ይራባል :?: ......አንቺ እንዳልሽውስ ለምን ይወድቃል :?: በዚህ አይነትማ ያመጣሽው አባባል መሆን ያለበት "poverty goes before the fall" ነው :D በተጨማሪም "ትዕቢት ውድቀትን ይቀድማል" ሲል እኮ እንቺ እንደምትዪው የረሀብ ወይም የድካም አካላዊ ውድቀት ሳይሆን የስታተስ ውድቀትን ነው የሚያሳየው

ስለዚህ እራት የማይሆነውን ኩራት "ቢግ ዲል" ማድረግ እንደማይጠቅም በትክክል የሚያሳየው Much ado about nothing ይመስለኛል

መልካም መንገድና ቆይታ :!:

እቴጌይት wrote:መግደርደር እኮ ኩራት ከሚገለጥበት አንዱ መንገድ ነው:: ትንሿን ነገር ቢግ ዲል ማድረግ ግን የተጨናቂነት ወይም የነጭናጫነት ወይም ቅድሚያ የሚሰጠውን ያለማወቅ ወዘተ ጉዳይ እንጂ ከኩራት ጋር የሚዛመድ አይደለም:: ለምሳሌ ግድርድሩ 'ጎንደሬ ቀን በበቅሎ ሌት በቆሎ' ሲባል ኩራቱን ለመግለጽ ነው:: ይሔ ኩራቱ ደግሞ እራት ስለማይሆነው ነው ቀን በቅሎ ላይ ተቆንኖ ሲጋበዝ ጠግቤያለሁ ሲል ይውልና ማታ ቆሎ በልቶ (ተርቦ) የሚያደረው! ኩራቱ እራቱ አለሆነውም:: ታዲያ ይሄ ትንሿን ነገር ቢግ ዲል ከማድረግ ጋር የሚገናኝ ሳይሆን ኩራቱ የሚበጀውን ነገር እንዳይገኝ ከማድረጉ (failure) ጋር ነው የሚዛመደው:: ለማንኛውም በመሪ ጌታ ልዳኝ ካልክ ወደ ሀገሬ ልዘልቅ ስለሆነ ስመለስ ብያኔውን ይዤልህ መጣለሁ!

ሠላም
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Re: እንረዳዳ - የአማርኛ ዘዬያችን በእንግሊዘኛ

Postby ሀዲስ 1 » Sun Jan 20, 2013 9:47 pm

ሰላም እቴጌይት !!!


አባባል ዘዬያችንን በጥሩ ሁኔታ ነው ያቀረብሽው :: ለነገሩ ገና ዛሬ ነው ያየሁት ::
በበኩሌ ያንቺና የዳግማዊ አያያዝ ጥሩ ነው :: በዚሁ ቀጥሉ ::
ጣዲያ ባትጠፉና : በየቀኑ አንድ አንድ እንኳን ብትሉን መልካም ነው :: ግን ያልተስማማችሁበትን ነጥብ ብትስማሙበትና አንድ ነጥብ ላይ ብትመጡ ጥሩ ይመስለኛል :: የትኛውን ይበልጥ ቀራቢ አድርገን መቀበል እንዳለብን እኛ እንድንለይ ማለቴ ነው ::

በተቀረ እስኪህ በርቱ

ሀዲስእቴጌይት wrote:ሠላም ለዚህ ቤት

ሀዲስ ጥሩ አምድ ከፍተሀል ወንድሜ!
እኔም ከላይ ሌሎች እንዳሉት ተረትና ምሳሌዎችና አባባሎች ቃል በቃል ሳይሆን ጭብጣቸውን በሚገልጽ አባባል ቢተረጎሙ ይሻላል ብዬ አስባለሁኝ::
ታች ስራ ፈት ከዘረዘራቸው አባባሎች ውስጥ የተወሰኑትን ልሞክር እስቲ:-

ሲሮጡ የታጠቁት -ሲሮጡ ይፈታል:-
Haste makes waste

በሽታውን የሚደብቅ መዳኒት አይገኝለትም
Nothing ventured, nothing gained

ቀስ በቀስ እንቁላል በእግሩ ይሄዳል
One step at a time. (or one may walk over the highest mountain one step at a time).

ኩራት እራት አይሆንም
Pride goeth before a fall

ድር ቢያብር አንበሳ ያስር
The whole is greater than the sum of its parts

ሁለት እግር አለኝ ተብሎ ሁለት ዛፍ አይወጣም
To do two things at once is to do neither

ደህና ቆዩ
what we learn from history is, we do not learn from history.

http://www.isil.org/resources/philosoph ... nglish.swf
ሀዲስ 1
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1643
Joined: Wed Mar 10, 2010 12:23 am

Postby ሀዲስ 1 » Mon Jun 24, 2013 8:48 pm

ምነው ይሄንን ቤት ረሳነው ???


ሀዲስ
what we learn from history is, we do not learn from history.

http://www.isil.org/resources/philosoph ... nglish.swf
ሀዲስ 1
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1643
Joined: Wed Mar 10, 2010 12:23 am

Re: እንረዳዳ - የአማርኛ ዘዬያችን በእንግሊዘኛ

Postby ቢተወደድ » Mon Jul 01, 2013 1:21 pm

እውነት ነው ሞኝ አይሙት እንዲያጫውት ማለት እንዲህ አይደል እንዴ?

ሀዲስ 1 wrote:ሰላም : ሰላም : ሰላም !!!

ይህንን ክፍል ልከፍት ያሰብኩበት ምክንያት : ምናልባትም በእንግሊዘኛ መልክ ያለው ፅሁፍ ማሰናዳት ለሚፈልጉ ሰዎች ይረዳ ይሆናል በማለት ነው ::
በእርግጥ እኔው ራሴው ብዙም የጠለቀ የእንግሊዘኛ እውቀት ስለሌለኝ : እዚህ ቤት ውስጥ በአብዛኛ ተማሪ ለመሆን ነው ጉጉቴ ::

አንዴ አንዱ ጓደኛዬ --> የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች የሚለው የአማርኛ አባባል በእንግሊዘኛ እንዴት ሊመነዘር ይችላል ብሎ ላብ በላብ አደረገኝ :: አለማወቄ ጉድ አደረገኝ ብዬ ተናደድኩኝ ::

ግን ከዚሁ ብንጀምር : ለመሆኑ የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች የሚለው አማርኛ አባባል በእንግሊዘኛው እንዴት ይተረጎማል ?????


ሀዲስ ነኝ
When we do it right No-one remembers,
When we do it wrong No-one forgets.
ቢተወደድ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1965
Joined: Tue Jul 21, 2009 3:21 pm
Location: Dabra Za`Yet

Postby ዲጎኔ » Thu Jul 04, 2013 4:26 am

ሰላም/አሻማ/ዳይቡሼ/ሰሮ/ዲጎና
ወገን ስራፈት/ባለመልካሙ ስራ ብየሀለሁ
የሀዲስ መልካም አምድ ሳይረሳ የኦሮሞኛ ማስተማሪያ የጳውሎስ ቅንብር ግብዣ ወደድኩት ተባረክ::ጳውሎስ ግን እንዲህ በቁቤና በኦሮምኛ የሚያስተምረው የኦሮሞ ዘር ኖሮበት ወይስ የዋሆቹ ቅኖቹ ኦሮሞዎች ፍቅር ግድ ብሎት?
ዲጎኔ ሞረቴው በአጼው ዘመን የደቡብ አዲስ አበባ የመጀመሪያ የህዝቦች ተመራጭ ዘውዴ በዳዳ ሰፈር ያደገው

ስራ ፈት wrote:
http://youtu.be/ei0In0HGYVU
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Previous

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 5 guests