የአቶ አልአዛር (አቶአ) ኮምቡጠር

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

የአቶ አልአዛር (አቶአ) ኮምቡጠር

Postby የተሞናሞነው » Tue Jan 08, 2013 7:01 am

(ከስብሃት ገ/እግዚአብሔር-አምስት ስድስት ሰባት)


ከቅብጠታት አንድ ቀን፣ አቶ አልአዛር ሲያቀብጣቸው ውሻቸውን ኮምቡጠርን ሁለት መለኪያ አረቄ የተቀላቀለበት ክትፎ አኮመኮሙት፡፡
“እናንተ የሰው ልጆች ኮተታችሁ ሲበዛ!” አላቸው
“አረቄዋ ከመቼው ስራዋን ሰራች!” እያሉ ውስጥ ውስጡን “እንዴት እባክህ?” ሲሉት
“የልብሳችሁ ብዛት! ሙታንታ-ካናቴራ-ሸሚዝ-ሹራብ-ኮት-ካፖርት-ባርኔጣ-ካልሲ-ጫማ-ቀበቶ-ጡት መያዣ!-አንሶላ-ብርድልብስ-አልጋልብስ-ፎጣ! ኸረ ወዲያ! ኮተታም ዘር!”
“ኸረ ባክህ? እናንተስ?”
“እኛማ ፀጉራችን በቃን፡፡ ፀጉራችን፣በቃይ ከውስጣችን!”
“እሺ!!!”
“ማበጠሪያ፣ፀጉር መያዣ፣ፀጉር መጠቅለያ፣የፀጉር ቅባት፣ የ…”
“በቃህ አታንዛዛብኝ!’
“ደሞ የቤታችሁ ጣጣስ ማድ ቤት-ምግብ ቤት-እንግዳ ቤት-ሽንት ቤት-እቃ ቤት-ወንበር-ጠረጴዛ-ሶፋ-ምንጣፍ-አልጋ-ቁም ሳጥን-አግድም ሳጥን! ሌላ ኮተት ዝባዝንኪ ግሳንግስ!”
“ሸይጣን ይንገስብህና! እናንተሳ ባክህን?”
“እኛማ ምድር ወለላችን ሰማይ ጣሪያችን፡፡ በቃ፡፡”
“ወይ ጉድ!”
“ሳህን-ማንኪያ- ሹካ-ኩባያ-ብርጭቆ-ጠርሙስ”
“በቃህ! በቃ ‘ንግዲህ!”
“ድስት-ጋን- ገንቦ”
“ኸረ ባክህ ይበቃል”
“የግሳንግሱ የኮተቱ ብዛት! ሰፌድ-መሶብ-አገልግል”
“በቃ!” ብለው ጮሁበት
“ኮተታም ዘር! ቅራቅንቦ!”
“ቅራቅንቦ?”
“ቅራቅንቦ-ሞፈር-ቀምበር-ኮርቻ-ወስፈንጥር-ወስፌ”
“እሰይ የኛ አዋቂ!”
“ግሳንግስ ቅራቅንቦ! ጋሪ-ብስክሌት-ዶቅዶቄ-መኪና-ባቡር-መርከብ-ኤሮፕላን-በሮኬት ጨረቃ ላይ መውጣት”
“ዝም በል አልኩህ! ሰካራም የውሻ ልጅ!”
“ጠላ-ጠጅ-አረቄ ወይን” ሲል አቶ አልአዛር ጆሮአቸውን ደፈኑ
“አለዚያ ያላሰብኩትን ሌላ ኮተት ያረዳኛል” ብለው እያሰቡ
ትንሽ ቆየት ብለው እጃቸውን ከጆሮአቸው ሲያወርዱ
“ክርስትና-እስልምና-ፍጥምጥም-ሠርግ-ተዝካር-ሰደቃ…..’
“ኸረ ስለማርያም ተወኝ!” አሉት
“ማርያም-ሚካኤል-አቦ-ራጉኤል-ጂብሪል…”
“ዝም በል’ኮ ነው ‘ምልህ! የውሻ ልጅ”
“አለቻ ስድብኤል!”
ስቀው ሲጨርሱ ቀጠለ “ገበሬ-ነጋዴ-ቄስ-ጠበቃ-ዳኛ-አናጢ”
“ኸረ በሕግ አምላክ ተወኝ!”
“ደሞ የሕጋችሁ ብዛት! ወንጀለኛ መቅጫ-ፍትሐ ብሔር-የባሕር ንግድ-የሥነ ሥርዓት-አቤት ግሳንግስ ኮተት!”
“ልብ አርግ ዋ!”
“ደግሞ የክሳችሁ አይነት፣ሰካራም-ተሳዳቢ-አጭበርባሪ-ነብሰ ገዳይ-እጅ እላፊ…”
“አሁንስ በቃ!” አሉና ተነስተው አንስተውት በሩን ከፍተው ውጪ አስቀምጠውት ተመልሰው በሩን ዘጉት::
“ሰካራም የውሻ ልጅ!” እያሉ ግማሽ እሳቁ፣ ለራሳቸው ሲመርቁላቸው አንድ መለኪያ አረቄ ቀዱ፡፡*ጋሽ ስብሃትን የምወደው 'አምስት ስድስት ሰባት' የተሰኘች መጽሀፉን ካነበብሁ ጊዜ ጀምሮ ነው :)
የተሞናሞነው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1129
Joined: Wed May 11, 2011 5:39 pm

Postby ጌታ » Wed Jan 09, 2013 8:35 pm

:lol: :lol: :lol: :lol:

አሪፍ መጣጣፍ ነች ሞንሟናው:: እኔም እንዳንተ አምስት ስድስት ሰባት ላይ አጋፋሪ እንደሻውን ያነበብኩ ጊዜ የሳቅሁት ሳቅ አይረሳኝም:: ዛሬም ባነበው እንደዛ ያስቀኝ ይሆን?
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3029
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby ስራ ፈት » Thu Jan 10, 2013 11:41 pm

ጌታ wrote::lol: :lol: :lol: :lol:

አሪፍ መጣጣፍ ነች ሞንሟናው:: እኔም እንዳንተ አምስት ስድስት ሰባት ላይ አጋፋሪ እንደሻውን ያነበብኩ ጊዜ የሳቅሁት ሳቅ አይረሳኝም:: ዛሬም ባነበው እንደዛ ያስቀኝ ይሆን?


መፅሀፉ በፒዲኤፍ አለኛና ሰጥቼህ ትሞክረዋለህ:: :D
ስራ ፈት
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 65
Joined: Mon Jan 17, 2005 8:37 pm

Postby ጌታ » Fri Jan 11, 2013 2:40 pm

ስራ ፈት wrote:
ጌታ wrote::lol: :lol: :lol: :lol:

አሪፍ መጣጣፍ ነች ሞንሟናው:: እኔም እንዳንተ አምስት ስድስት ሰባት ላይ አጋፋሪ እንደሻውን ያነበብኩ ጊዜ የሳቅሁት ሳቅ አይረሳኝም:: ዛሬም ባነበው እንደዛ ያስቀኝ ይሆን?


መፅሀፉ በፒዲኤፍ አለኛና ሰጥቼህ ትሞክረዋለህ:: :D


ስምህን ከስራ ፈት ወደ ስራ ብዙ ብትቀይረው ምን ይመስልሃል? አምስት ስድስት ሰባት መጽሐፉ አለኝ:: ከዛሬ ነገ እደግመዋለሁ እያልኩ ነው:: እስቲ ሌላ አሪፍ መጽሐፍ ካለህ ኢሜል አድርግልኝ:: ኢሜሌን ፕሮፋይሌ ላይ ታገኘዋለህ::

አመሰግናለሁ::
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3029
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby ገልብጤ » Fri Jan 11, 2013 3:07 pm

ጌታ
መሀልየ መሀልየ ዘ.-ካሳንቺስ እኔ አለኝና ሜይልህን ዱቅ አድርግልኝ ልጽደቅብህ
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1680
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

Postby ስራ ፈት » Fri Jan 11, 2013 3:47 pm

ይሄው መፅሀፉ አዘጋጅቼ አምጥቼልሀለው:: የምትፈልገው እንግሊዝኛ መፅሀፍ ካለ ጠቆም አድርገኝ አዲስ የወጣም ቢሆን ኮኔክሽን ስላለኝ በቀላሉ ማግኝት ችላለው: :D

እንግዲህ መፅሀፉን ለማግኝት አንድ ነገር ብቻ ያስፈልግሀል ከሌለህእዚህ ዳውሎድ አድርገው ዊንሬር ይባላል ፋይሎችን ለመክፈት ያገለግላል:: እንደኮምዩተርህ 32bit ወይም 64bit ምረጥና ዳውሎድ ካደረክ በኃላ ፋይሉን ክፈተው::
ስራ ፈት
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 65
Joined: Mon Jan 17, 2005 8:37 pm

Postby ጌታ » Fri Jan 11, 2013 6:27 pm

ገልቡ - በጣም የምፈልገው መጽሐፍ ነው:: በ getawarka@yahoo.com ስደደው::

ስራብዙ - እጅግ አመሰግናለሁ::
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3029
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby ስራ ፈት » Wed Jan 16, 2013 11:11 pm

ሰላም ጌታ ይሄውልህ ሊንኩን[url=http://www.mediafire.com/?1z6eqd1fa5fzntm[/u]እዚ[/url] ላይ
ስራ ፈት
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 65
Joined: Mon Jan 17, 2005 8:37 pm

Postby ገልብጤ » Wed Jan 16, 2013 11:20 pm

ስራ ፈት wrote:ሰላም ጌታ ይሄውልህ ሊንኩን[url=http://www.mediafire.com/?1z6eqd1fa5fzntm[/u]እዚ[/url] ላይ


እውነትም ስራ ፈት ያመጣህው ሊንክ መጥፎ ቫይረስ መሆኑን ታውቃለህ
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1680
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

Postby ስራ ፈት » Wed Jan 16, 2013 11:50 pm

ገልብጤ wrote:
ስራ ፈት wrote:ሰላም ጌታ ይሄውልህ ሊንኩን[url=http://www.mediafire.com/?1z6eqd1fa5fzntm[/u]እዚ[/url] ላይ


እውነትም ስራ ፈት ያመጣህው ሊንክ መጥፎ ቫይረስ መሆኑን ታውቃለህ


ያንተ ፋይረስ ተጋብቶበት ይሆናል እንጂ ፋይሉን ከየትም ጎትቼ አምጥቼው ሳይሆን እራሴ አፕሎድ አድርጌው ፓስወርድ አስገብቼበት ታጥቦ ታጥኖ የተቀመጠ ነው:: ካለ ፓስወርድም አይከፈተም እንዳነተ አይነቱ ዳውሎድ እንዳያደርገው ታስቦ ነው:: :D :D
ስራ ፈት
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 65
Joined: Mon Jan 17, 2005 8:37 pm

Postby ገልብጤ » Thu Jan 17, 2013 12:00 am

ስራ ፈት wrote:
ገልብጤ wrote:
ስራ ፈት wrote:ሰላም ጌታ ይሄውልህ ሊንኩን[url=http://www.mediafire.com/?1z6eqd1fa5fzntm[/u]እዚ[/url] ላይ


እውነትም ስራ ፈት ያመጣህው ሊንክ መጥፎ ቫይረስ መሆኑን ታውቃለህ


ያንተ ፋይረስ ተጋብቶበት ይሆናል እንጂ ፋይሉን ከየትም ጎትቼ አምጥቼው ሳይሆን እራሴ አፕሎድ አድርጌው ፓስወርድ አስገብቼበት ታጥቦ ታጥኖ የተቀመጠ ነው:: ካለ ፓስወርድም አይከፈተም እንዳነተ አይነቱ ዳውሎድ እንዳያደርገው ታስቦ ነው:: :D :D

ያንተ ፋይረስ

ቫይረስ ለማለት ነው
ቁቅቅቅቅቅቅቅ
የልምድ አዋቂነህ አይደል
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1680
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

Postby ስራ ፈት » Thu Jan 17, 2013 1:27 am

ገልብጤ wrote:የልምድ አዋቂነህ አይደል


ምን ላድርግ ብለህ ነው እንዳንተ በልምድ መሀይም ከመሆን የልምድ አዋቂ መሆን አይሻልም ትላለህ::
ስራ ፈት
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 65
Joined: Mon Jan 17, 2005 8:37 pm


Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests