የዘመኔ ጥሎሽ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

የዘመኔ ጥሎሽ

Postby እቴጌይት » Thu Jan 10, 2013 11:58 pm

በባህል ወግ ማረጉ
ባገር ልማድ ለሰርጉ
ጥሎሽ ስታስጥል ለእኔ
ስትልክ ሙዜህን ያኔ...
ያባትህን ማስረሻ
ላያትህ ግፍ መካሻ
ቀርቶ ካልጋ መውረጃ
ላክልኝ በቃ ጠበንጃ!
Last edited by እቴጌይት on Fri Jan 11, 2013 7:21 am, edited 1 time in total.
እቴጌይት
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 656
Joined: Sun Sep 23, 2007 10:38 pm

Postby ሳምራውው33 » Fri Jan 11, 2013 2:51 am

ሰላም እቴጌይት

ጾም

የፍስግ አትቀምስም ረቡዕ እና አርብ
በልታ ትውላለች ጎመንና ክክ
የመጾም ትርጉሙን ውስጧ ስለሚያውቀው
የስጋ ፈተና ከብዷትም አያውቅ
ሰናይ ምግባር ያላት የተዋጣላት
የተመሰገነች ደግ ናት ቅድስት :!:
The love of money is the root of all evil.

ሳምራውው 33 የግጥም አርበኛ
ስንኝ ቋጣሪ በውብ አማርኛ ::
_________________
ሳምራውው33
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 530
Joined: Thu Jun 21, 2007 12:23 am

መች ተወለድ ጌታ?

Postby እቴጌይት » Fri Jan 11, 2013 7:05 am

የብሔር ቁርሾው ሳይክስም
...........................ቂም በቀሉ ሳይጠፋ
እርቀ ሠላሙ ሳይወርድ
..........................ከስሞ የፍትህ ተስፋ
የመርገም ጨርቁ እያለ
..........................የብሉይ መጋረጃ
ሳይቀደድ ግርዶሹ
..........................እየገዛ ጠበንጃ
በጽልመት ዘመን ስኖር
.......................ኅጢአቴ ሳይፈታ
መልካም ልደት አትበሉኝ
.......................ሳይወለድልኝ ጌታ!
እቴጌይት
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 656
Joined: Sun Sep 23, 2007 10:38 pm

Postby ክቡራን » Fri Jan 11, 2013 11:53 am

አረ አባካቹ ጎበዛዝትና ወይዛዛርት እንደው ገጣሚ ዋርካ ላይ ጠፍቷል ብላቹ ግጥምን መጫወቻ አታድርጉት!! :D ካንቺ በላይ የጻፈውን እንኴን ማቶ አድርገሽዋል... እንኴን ግጥም አይደለም እንጊሊዝኛም ስትጽፊ "የሼክስፒር" እንጊሊዝኛ ነው እያለ ሲያመስግንሽና ሲያደንቅሽ ይከርማል. I don't have any probelm with that...መደናነቅ መብት ነው.. :D እንደው ግን አንቺ ማርያም ነሽ..እመቤታችን ነሽ...ባዛኝቷ ነሽ እንዴት ነው ካንቺ ጌታ የሚወለደው..?? ጌታ ሳይወለድልኝ ..የምትዪው..? :wink:
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7990
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Re: መች ተወለድ ጌታ?

Postby ዲጎኔ » Fri Jan 11, 2013 2:24 pm

ሰላም ላንቹ ይሁን ለእህታችን
በበሳል ብእር ጽንፈኛ ረቺያችን
ከዋርካ እንስቶች 1ዷ አጋራችን
ያልሸው መርገም የሚወገደው
ክፋትና በደል ሁሉ የሚነጻው
መርገምና ሀጢያት የሚሰረየው
በጌታ በክርስቶስ ደም ብቻ ነው
ያ የሚሰራው በሱ ላመኑት ነው
የወንጌሉ ቃል እንዲህ ይላል
መሲሁ ከድንግሊቱ ተወልዷል
እውነትን በህይወቱ አሳይቷል
ለተቀበሉት ሁሉ አባት ሆኗል
በመስቀል መከራው ተሰውቷል
ሞትን አሸንፎም ድል ነስቷል
በትንሳኤው ቃሉን አጽንቷል
ልጆቹን ሊወስድ ይመለሳል

እቴጌይት wrote:የብሔር ቁርሾው ሳይክስም
...........................ቂም በቀሉ ሳይጠፋ
እርቀ ሠላሙ ሳይወርድ
..........................ከስሞ የፍትህ ተስፋ
የመርገም ጨርቁ እያለ
..........................የብሉይ መጋረጃ
ሳይቀደድ ግርዶሹ
..........................እየገዛ ጠበንጃ
በጽልመት ዘመን ስኖር
.......................ኅጢአቴ ሳይፈታ
መልካም ልደት አትበሉኝ
.......................ሳይወለድልኝ ጌታ!
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Re: መች ተወለድ ጌታ?

Postby ክቡራን » Fri Jan 11, 2013 2:37 pm

እረ እባካቹ ሰዎቼ በግጥም አትጫወቱ... :D ሀሳባችሁን በስድ ንባብ ግለጹት::

ዲጎ እንደገደገደው.. wrote:ሰላም ላንቹ ይሁን ለእህታችን
በበሳል ብእር ጽንፈኛ ረቺያችን
ከዋርካ እንስቶች 1ዷ አጋራችን
ያልሸው መርገም የሚወገደው
ክፋትና በደል ሁሉ የሚነጻው
መርገምና ሀጢያት የሚሰረየው
በጌታ በክርስቶስ ደም ብቻ ነው
ያ የሚሰራው በሱ ላመኑት ነው
የወንጌሉ ቃል እንዲህ ይላል
መሲሁ ከድንግሊቱ ተወልዷል
እውነትን በህይወቱ አሳይቷል
ለተቀበሉት ሁሉ አባት ሆኗል
በመስቀል መከራው ተሰውቷል
ሞትን አሸንፎም ድል ነስቷል
በትንሳኤው ቃሉን አጽንቷል
ልጆቹን ሊወስድ ይመለሳል

እቴጌይት wrote:የብሔር ቁርሾው ሳይክስም
...........................ቂም በቀሉ ሳይጠፋ
እርቀ ሠላሙ ሳይወርድ
..........................ከስሞ የፍትህ ተስፋ
የመርገም ጨርቁ እያለ
..........................የብሉይ መጋረጃ
ሳይቀደድ ግርዶሹ
..........................እየገዛ ጠበንጃ
በጽልመት ዘመን ስኖር
.......................ኅጢአቴ ሳይፈታ
መልካም ልደት አትበሉኝ
.......................ሳይወለድልኝ ጌታ!
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7990
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Re: መች ተወለድ ጌታ?

Postby እቴጌይት » Sat Jan 12, 2013 1:12 am

ሠላም ክቡራን
አማርኛ ሁለተኛ ቋንቋህ እንደሆነ ብገምትም 'ሳይወለድልኝ' እና "ሳልወልድ' የሚለው ቃል መካከል ያለውን ልዩነት ማወቅ ይከብድሀል ብዬ ግን አላስብም::

ሠላም ዲጎኔ
ግሩም ግጥም ነች!
እስቲ እንካ ደግሞ ምላሽ:-

ዳግም ልደት መሻቴ
ኤሎሄ ማሰማቴ
ቤተልሔምን ስቼ
ጎልጎታንም ዘንግቼ
እንዳይመስልህ ከድቼ!
ግናስ
ሁለት ሺህ ዓመት ቆጥረን
ብርሀነ-ልደት ብለን
ብናንቦለቡል ሻማ
ዝማሬም ብናሰማ
ፍ'ቅርን ካላነገስን
በጎጥ ከተቧቀስን
የዘረ-አዳም መዳኛ
ገና- አልተወለደም ለኛ!


ዲጎኔ wrote:ሰላም ላንቹ ይሁን ለእህታችን
በበሳል ብእር ጽንፈኛ ረቺያችን
ከዋርካ እንስቶች 1ዷ አጋራችን
ያልሸው መርገም የሚወገደው
ክፋትና በደል ሁሉ የሚነጻው
መርገምና ሀጢያት የሚሰረየው
በጌታ በክርስቶስ ደም ብቻ ነው
ያ የሚሰራው በሱ ላመኑት ነው
የወንጌሉ ቃል እንዲህ ይላል
መሲሁ ከድንግሊቱ ተወልዷል
እውነትን በህይወቱ አሳይቷል
ለተቀበሉት ሁሉ አባት ሆኗል
በመስቀል መከራው ተሰውቷል
ሞትን አሸንፎም ድል ነስቷል
በትንሳኤው ቃሉን አጽንቷል
ልጆቹን ሊወስድ ይመለሳል

እቴጌይት wrote:የብሔር ቁርሾው ሳይክስም
...........................ቂም በቀሉ ሳይጠፋ
እርቀ ሠላሙ ሳይወርድ
..........................ከስሞ የፍትህ ተስፋ
የመርገም ጨርቁ እያለ
..........................የብሉይ መጋረጃ
ሳይቀደድ ግርዶሹ
..........................እየገዛ ጠበንጃ
በጽልመት ዘመን ስኖር
.......................ኅጢአቴ ሳይፈታ
መልካም ልደት አትበሉኝ
.......................ሳይወለድልኝ ጌታ!
እቴጌይት
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 656
Joined: Sun Sep 23, 2007 10:38 pm

Postby ክቡራን » Sat Jan 12, 2013 3:01 am

ሰላም እቴጌይት:- እና እንቺ የትኛውን ነሽ ( ወይም የትኛውን መረጥሽ.? ) :D አየሽ በሁለቱም በኩል ብታዪው ስህተት ሰርተሻል...ስህትተሽ መነፈሳዊ- ወ -ስጋዊ እንደሆነ መናገርም ይቻላል:: "" ሳይወለድልኝ"" ማን ነው የሚወለድልሽ..??አንቺ የገጠምሽው ግጥም ቤት እንዲመታልሽ እንጂ ይዞት የመጥው ጦስ አልታየሽም:: ችኩል ገጣሚ እርሳስ ይነክሳል አሉ!! :D ጌታ ተወልዷል...! የአንቺ ግጥም ቤት እንዲመታ ተብሎ ክርስቶስ ዳግም አይወለድም::
ሌላውን "አማራጭሽን" እንፈትሽው! ሳልወልድ ' ልብሽ ትንሽ አላበጠም..እዚህ ጋ...? ጌታን ልትወልጂው ትፈልጊያለሽ ለካ!! ተሳስቼ ከሆነ አርሚኝ!! ለመሆኑ አማርኛ ስንተኛ ቌንቌሽ ነው ግን..? :D
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7990
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ስራ ፈት » Sat Jan 12, 2013 4:33 am

አገር ተወረረ ደንበር ተደፈረ
ሰንጋ ፈረስ ስቦ ሄደ እየፎከረ
ምሎ ተማምሎ ጠላቷን ሊያጠፋ
ገሰገሰ ጀግናው ከፊቷ ሊደፋ
ያለውም አልቀረ ለክብሯ ተሰዋ
ነጭን አስረገደ ጉድ አለች አድዋ::

የማይቻል ችሎ ታሪክን የፃፈው
መድፍን አገላብጦ መድፈን የሰበረው
በፈረስ ላይ ሆኖ ምድሩን ያሸበረው
ከነፍጥ ሁሉ ከፍቶ ወሬ ሊፈታው ነው::
ስራ ፈት
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 65
Joined: Mon Jan 17, 2005 8:37 pm

Postby እቴጌይት » Sat Jan 12, 2013 9:25 pm

ስራ ፈት

ፍሰቱም ሆነ ጭብጡ በጉልህ የሚስማማ ድንቅ ግጥም ነው ወንድሜ! ይልመድብህ እስቲ እየደጋገምክ መርቅልን ብያለሁ!

አክባሪህ
እቴጌይት
እቴጌይት
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 656
Joined: Sun Sep 23, 2007 10:38 pm

Postby ክቡራን » Sat Jan 12, 2013 11:27 pm

ወንድሜ ዲጎ የደገደገውን ሳነብ ይሄን አስተዋልኩ:-

ሰላም ላንቹ ይሁን ለእህታችን
በበሳል ብእር ጽንፈኛ ረቺያችን ( ይሄ እንኴን ፉገራ ነው ምን አስበህ ነው ይሄን ያልካት.. :lol: ;

ከዋርካ እንስቶች 1ዷ አጋራችን
ያልሸው መርገም የሚወገደው
ክፋትና በደል ሁሉ የሚነጻው
መርገምና ሀጢያት የሚሰረየው
በጌታ በክርስቶስ ደም ብቻ ነው
ያ የሚሰራው በሱ ላመኑት ነው
የወንጌሉ ቃል እንዲህ ይላል
መሲሁ ከድንግሊቱ ተወልዷል
እውነትን በህይወቱ አሳይቷል
ለተቀበሉት ሁሉ አባት ሆኗል
በመስቀል መከራው ተሰውቷል
ሞትን አሸንፎም ድል ነስቷል
በትንሳኤው ቃሉን አጽንቷል
ልጆቹን ሊወስድ ይመለሳል

እንደማስበው አንተ ጋ ያለው መንፈስ አራዳም ጭምር ነው:: የልጇ ልደት ሰከበር እንኴን አደረሳቹ ስትባል ምላሽ በመስጠት ፋንታ መልካም አዲስ አመት ይሁንላቹ ያልክ ሰውዬ ማንን ለመሸወድ ነው አሁን ይሄ ሁሉ የግጥም ድርደራ..?? መፍትሄው ግጥም አይደለም:: መፍትሄው በተሰበረ ልብ ንስኅ መግባት ነው::
እናንተ ሸክማቹ የከበደና በዶክትሪን የጦዛቹ ወደኔ ኑ እኔም በለመለመው መስክ አሳርፋችኌለሁ ያላል ቃሉ:: ጆሆቫዎች የክርስቶስን ልደት አያከብሩም ይባላል...ያንተ የቅዱሳን ማህበር ወደ ጆሆቫነት እንየተንደረደረ ነው እንዴ..??
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7990
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ዲጎኔ » Sun Jan 13, 2013 3:55 am

ያልተገራው ፈረስ ጠቅል እያላችሁ
ከማይጮ ደንብሮ ለንደን ገባላችሁ
ደርግ አደገ ሄደ ገሰገሰ
በ12 አመቱ ጥብቆ ለበሰ
አትነሳም ወይ አትነሳም ወይ
የግፍ አገዛዝ አይበቃህም ወይ
አትነሳም ወይ አትንቀሳቀስ
መብትህ ሲሰረቅ የምታለቅስ
ሲሰድቡ ሲንቁህ የማትመልስ
ትናት በደርጉ ጀርባህ የተላጠ
ዛሬ በወያኔው ቅሪትህ ተጋጠ
የታደለ ልጅህ ከሞት አመለጠ
የተቀረው ደግሞ ኑሮ እየዘቀጠ
ባገር ምድሩ ላይ መከራ ገመጠ
አትነሳም ወይ አትነሳም ወይ
የወያኔ ግፍ አይበቃህም ወይ
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby ክቡራን » Sun Jan 13, 2013 10:44 am

እባካቹ ሰዎቼ የራሳቹ ያልሆነ ግጥም ስትጽፉ ምንጩንም አብራቹ ጥቀሱ:: ነውር ነው :: በዚህ በፈረንጁ አለም ፕላጂያሪዝም ተብሎ ቡዙ መዘዝ ያስከትላል::
ዲጎ እንደራሱ አድርጎ ያለ ትምህርተ- ጥቅስ እ ንደ-ደገደገው.. wrote:ያልተገራው ፈረስ ጠቅል እያላችሁ
ከማይጮ ደንብሮ ለንደን ገባላችሁ
ደርግ አደገ ሄደ ገሰገሰ
በ12 አመቱ ጥብቆ ለበሰ
አትነሳም ወይ አትነሳም ወይ
የግፍ አገዛዝ አይበቃህም ወይ
አትነሳም ወይ አትንቀሳቀስ
መብትህ ሲሰረቅ የምታለቅስ
ሲሰድቡ ሲንቁህ የማትመልስ
ትናት በደርጉ ጀርባህ የተላጠ
ዛሬ በወያኔው ቅሪትህ ተጋጠ
የታደለ ልጅህ ከሞት አመለጠ
የተቀረው ደግሞ ኑሮ እየዘቀጠ
ባገር ምድሩ ላይ መከራ ገመጠ
አትነሳም ወይ አትነሳም ወይ
የወያኔ ግፍ አይበቃህም ወይ
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7990
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby እቴጌይት » Sun Jan 13, 2013 2:38 pm

ሠላም ዲጎኔ
ግሩም ግጥም ነው ወንድሜ! በርታ እላለሁኝ!
እስቲ ሌሎቹም ካሉህ ጣል ጣል አድርግልን::
አክባሪህ
እቴጌይት
እቴጌይት
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 656
Joined: Sun Sep 23, 2007 10:38 pm

ግጥም...

Postby ዳግማዊ ቅዥቢው » Sun Jan 13, 2013 3:29 pm

አሁን ይኼ ግጥም
ቢገጥም ባይገጥም
ከተባለ ግጥም
አይሆንም ወይ ግጥም?
ሰለሞን ሞገስ
***************************
አሁን ይሄ ቁላ
ቢቆላ ባይቆላ
ከተባለ ቁላ
አይሆንም ወይ ቁላ?
ዳግማዊ ቅዥቢው
መታሰቢያነቷ ለእቴጌይት ዓይነት ቁሊታም እንስቶች ትሁንልኝ
ዳግማዊ ቅዥቢው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 117
Joined: Mon Nov 26, 2012 1:08 am

Next

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests