የዘመኔ ጥሎሽ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Re: መች ተወለድ ጌታ?

Postby ዲጎኔ » Sun Jan 13, 2013 11:28 pm

ሰላም እቴዋ እቴጌይቱ
በሰላ ብእር ጸሀፊይቱ
እንዲህ ስትዘግቢ ደስ ማለቱ
የእምነት ስፍራዎች ማውሳቱ
ልደት ህማማቱን ማስተጋባቱ
እንዳንረሳው እርሱን ጌታችን
ከሴጣን ከሞት በደሙ ያዳነን
አባ አባ ብለን እንጠራለን
በጌታ ሁላችንም አንድነን
ችግርሽ ይገባኛል እህታችን
ጥያቄሽ ነበር በህይወታችን
መልሱም አለ በመጽሀፋችን
አስቀምጧልና በወንጌላችን
አይዞሽ ተስፋ አለ ካባታችን
ሰዎች ሊወግሩን በጥፋታችን
ሲሽቀዳደሙ ለፍርዳችን
እርሱ ደረሰልን ጌታችን
ከናንተ ጥፋት የለሽ ማነው
መጀመሪያ ወጋሪው እንየው
እስኪ ከአንደበቱ እንስማው
ብሎ ሲጠይቅ ከዙሪያ ገባው
አንድ አልተገኘ በስብሰባው
ከዚያ ጎንበስ ብሎ ዳብስሶኝ
ምሬሀለሁ ብሎ ሲያጽናናኝ
ድጋሚ አትሳት ብሎ ሲመከረኝ
ጥፋቴና በደሌ ከልቤ ሲሰማኝ
እንባ ሲቃዬን ጌታ አበሰልኝ
ተምረሀል አታልቅስ አለኝ
ከዚያ ወደቤቴ አመራሁኝ
በምህረቱ ብዛት ተሳብኩኝ
እከዛሬ ድረስ በቤቱ አለሁኝ
በየቀኑ በፊቱ ንስሀ እየገባሁኝ
ፍቅር ምህረቱን መስክራለሁኝ


እቴጌይት wrote:ሠላም ዲጎኔ
ግሩም ግጥም ነች!
እስቲ እንካ ደግሞ ምላሽ:-

ዳግም ልደት መሻቴ
ኤሎሄ ማሰማቴ
ቤተልሔምን ስቼ
ጎልጎታንም ዘንግቼ
እንዳይመስልህ ከድቼ!
ግናስ
ሁለት ሺህ ዓመት ቆጥረን
ብርሀነ-ልደት ብለን
ብናንቦለቡል ሻማ
ዝማሬም ብናሰማ
ፍ'ቅርን ካላነገስን
በጎጥ ከተቧቀስን
የዘረ-አዳም መዳኛ
ገና- አልተወለደም ለኛ!


ዲጎኔ wrote:ሰላም ላንቹ ይሁን ለእህታችን
በበሳል ብእር ጽንፈኛ ረቺያችን
ከዋርካ እንስቶች 1ዷ አጋራችን
ያልሸው መርገም የሚወገደው
ክፋትና በደል ሁሉ የሚነጻው
መርገምና ሀጢያት የሚሰረየው
በጌታ በክርስቶስ ደም ብቻ ነው
ያ የሚሰራው በሱ ላመኑት ነው
የወንጌሉ ቃል እንዲህ ይላል
መሲሁ ከድንግሊቱ ተወልዷል
እውነትን በህይወቱ አሳይቷል
ለተቀበሉት ሁሉ አባት ሆኗል
በመስቀል መከራው ተሰውቷል
ሞትን አሸንፎም ድል ነስቷል
በትንሳኤው ቃሉን አጽንቷል
ልጆቹን ሊወስድ ይመለሳል

እቴጌይት wrote:የብሔር ቁርሾው ሳይክስም
...........................ቂም በቀሉ ሳይጠፋ
እርቀ ሠላሙ ሳይወርድ
..........................ከስሞ የፍትህ ተስፋ
የመርገም ጨርቁ እያለ
..........................የብሉይ መጋረጃ
ሳይቀደድ ግርዶሹ
..........................እየገዛ ጠበንጃ
በጽልመት ዘመን ስኖር
.......................ኅጢአቴ ሳይፈታ
መልካም ልደት አትበሉኝ
.......................ሳይወለድልኝ ጌታ!
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby ክቡራን » Mon Jan 14, 2013 12:07 am

አረ በህግ አምላክ ! በአቤ ጉበኛ በጸጋዬ ገብረ መድህን ይዣችሁለሁ!! በግጥም አትቀልዱ ...ወንድሜ ዲጎኔ ደስታ ከረሜላ እንድትሰጥህ ፈልገህ ከሆነ በሌላ ነገር ጅንጅናት!! መብትህ ነው:: ገጣሚ የለም ብለህ ግን በግጥም አትጫወት::
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7963
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ስራ ፈት » Fri Jan 18, 2013 11:10 am

ስላም ለቤቱ ተሳታፎዎች እቴጌ አመሰግናለው ብዙም ችሎታ ባይኖረኝም እንዳቅሚቲ ለመሳተፍ ሞክራልው:: ያለውን የወረወረ ንፉግ አይባልም አይደል::

ሕይወት

የሰው ልጅ አበሳ
የመከራ መቅጃ ጣሳ
ምን ይሆን ትርጉምሽ
እርባና መርገምሽ

ለምን ይሆን መራቤ
ሌላው ሲጠግብ በገንዘቤ
ሲንቦራጭቅ በጅረቴ
ምነው መሆኔ ምናምቴ
የበይ ተመልካች ስደተኛ
ሆደ ባሻ ግዞተኛ::

የሰላምን እንቅልፍ ተመኝው
የድሕነት ሸክም ያልተጫነው
ባገሬ መዝለል አማረኝ
በወንዜ መቦረቅ አሰኝኝ

ነፃነት ነፃነት አለች ነብሴ
የድህነት ዳማ ከሴ
የጭቆና ማብቂያ ደውል
ነፃነት ለኛ ይሁን:
ስራ ፈት
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 65
Joined: Mon Jan 17, 2005 8:37 pm

Postby ስርርር » Tue Jan 22, 2013 2:10 am

ድንቅ ግጥም! ... እቴጌይትና ዲጎኔም እንደዚሁ:: አንዳንድ ጋዜጠኞች ነን ባዮች ግን ራሳቸውን አስገመቱ:: አንድያውን ሁለተኛ ቍንቍዬ ነውና አልገባኝም. አሰረዱኝ...ማለት አንድ ነገር ነው:: ግጥም አትችሉም....ደግሞ ሌላ ነገር ነው:: ባይችሉም እንክዋን እንዲህ ለዛቢስ የሆነ ሂስ አይገባም::


እንደው ገድሎ ማዳን (አድኖ መግደል) አይሁንብኝና ይቺ እቴ...ጌይት አልተመቸችኝም:: ወንድም እህቶቻችን ሉጢዎች ማለት ይሆን? ውይንስ ...? ጥያቄ ነው:: በተረፈ ግጥሞቹ ነፍስ ናቸው...በርቱ
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

Postby ስራ ፈት » Tue Jan 22, 2013 8:00 pm


የነፃነትን ደውል አሰሙ
ያገሬ ልጆች ሁሉ ይስሙ
በባርነት ቀንበር ለወደቁ
በድህነት ለሚማቅቁ
የነፅነት መረዋ ይደወል
በነፃነት አዛን ይበል
ድምፃችሁ ይሰማ ባንድነት ውጡና
ነፃነት ከሌለ ነፃ ሰው የለምና ::
ስራ ፈት
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 65
Joined: Mon Jan 17, 2005 8:37 pm

Re: መች ተወለድ ጌታ?

Postby ባቲ » Fri Mar 01, 2013 8:19 pm

ውድድድድ!
እቴጌይት wrote:የብሔር ቁርሾው ሳይክስም
...........................ቂም በቀሉ ሳይጠፋ
እርቀ ሠላሙ ሳይወርድ
..........................ከስሞ የፍትህ ተስፋ
የመርገም ጨርቁ እያለ
..........................የብሉይ መጋረጃ
ሳይቀደድ ግርዶሹ
..........................እየገዛ ጠበንጃ
በጽልመት ዘመን ስኖር
.......................ኅጢአቴ ሳይፈታ
መልካም ልደት አትበሉኝ
.......................ሳይወለድልኝ ጌታ!
SaQ _Be _SaQ.....That's what I wish 4 all of Us
ስምየ ውዕቱ ክንዴ ባቲ
ባቲ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 942
Joined: Tue Jul 06, 2004 8:18 pm
Location: ethiopia

Previous

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: Bing [Bot] and 5 guests