ስስቴ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ስስቴ

Postby እቴጌይት » Sat Mar 16, 2013 10:54 pm

አምሮባት ደምቃ እናቴ
እያለች በሕይወቴ
ከቅፍ እጇ ሳልወጣ
እጹብ ፍቅሯን ሳላጣ
አይቀሬ መለየቷ
የማላመልጠው ሞቷ
ውስጤ ሲቃ ሰንቆ
አብሮኝ ኗሪ ታምቆ
ያለመርዶ የሚነባ
ውስጤ አለኝ የነገ እምባ!!
እቴጌይት
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 656
Joined: Sun Sep 23, 2007 10:38 pm

Postby ክቡራን » Sat Mar 16, 2013 11:12 pm

ዕህታችን እቴጌ ግጥሞች ግጥም ብሎ ዝም ናቸው:: ምታቸው ከባድ ነው... ጥልቀት አላቸው.... ሲያስፈልግም ሰርን ይሰብራሉ:: ባጭር ስንኝ እንደ ጎመራ የሚፈነዳ ታላቅ ሀይልን መግለጸ ተሰጦኦ ነው:: ማንም ዝም ብሎ ተነስቶ ግጥም አይገጥምም:: ግጥም እኮ ገጣሚን ይሻል...ጥዑም ጠላ ጠማቂን እንደሚፈልግ ማለት ነው:: ግጥምና ገጣሚ ሲገናኙ ፈስስ እያለ በሚውርድ ጅረት ይመሰላሉ:: እኅታችን ሆይ ግጥሞችሽ እንዲህ አይብ ናቸው ካልኩ በኌላ አስተያየት ልሰጥሽ ፈለኩ :: አዳዲስ ቤት ከምትከፍቺላቸው ባንድ ቦታ ላይ ብትጽፊያቸው ምን ይመስልሻል..? ባለፈው የዘመኔ ጥማት በሚል የቌጠርሽው ቌጠሮ ነብር:: ግሩም ነው... አጃይብ ነው ይሉታል ወሎዬውች :: ዘውድ የደፋ ነው እንዳንቺ:: ባንድ ላይ ቢሰበሰቡልሽ አድናቂዎችሽ የብእርሽን ጭማቂ ያጣጥሙታል ብዬ አስባለሁ:: በመልካም እዪልኝ አደራ:: አክባሪሽ::
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7988
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby መራራ » Mon Mar 18, 2013 8:35 am

እኔም በሀሳብሽ እስማማለሁ ክቡዬ:: በዚህ አጋጣሚ ግን አንቺም ""ይቺን ጠቅ"" እያልሽ ወደ ዝምባሙ ቤትሽ ጎብኝ ለመውሰድ በቀን 7 አዳዲስ ቤት ከምትከፍቺ በ ""ፈረሰኛው ጎርጊስ አትለፉኝ"" በሚል አምድ ስር መጣጥፎችሽን ብታሰባስቢ? አደራሽን በመልካም እይልኝ አስተያየቴን:: :lol: :lol: :lol: :lol:


ክቡራን wrote:ዕህታችን እቴጌ ግጥሞች ግጥም ብሎ ዝም ናቸው:: ምታቸው ከባድ ነው... ጥልቀት አላቸው.... ሲያስፈልግም ሰርን ይሰብራሉ:: ባጭር ስንኝ እንደ ጎመራ የሚፈነዳ ታላቅ ሀይልን መግለጸ ተሰጦኦ ነው:: ማንም ዝም ብሎ ተነስቶ ግጥም አይገጥምም:: ግጥም እኮ ገጣሚን ይሻል...ጥዑም ጠላ ጠማቂን እንደሚፈልግ ማለት ነው:: ግጥምና ገጣሚ ሲገናኙ ፈስስ እያለ በሚውርድ ጅረት ይመሰላሉ:: እኅታችን ሆይ ግጥሞችሽ እንዲህ አይብ ናቸው ካልኩ በኌላ አስተያየት ልሰጥሽ ፈለኩ :: አዳዲስ ቤት ከምትከፍቺላቸው ባንድ ቦታ ላይ ብትጽፊያቸው ምን ይመስልሻል..? ባለፈው የዘመኔ ጥማት በሚል የቌጠርሽው ቌጠሮ ነብር:: ግሩም ነው... አጃይብ ነው ይሉታል ወሎዬውች :: ዘውድ የደፋ ነው እንዳንቺ:: ባንድ ላይ ቢሰበሰቡልሽ አድናቂዎችሽ የብእርሽን ጭማቂ ያጣጥሙታል ብዬ አስባለሁ:: በመልካም እዪልኝ አደራ:: አክባሪሽ::
መራራ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 753
Joined: Sat Sep 25, 2004 9:58 am
Location: united states


Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests