ሙታሪካ; ሻቬዝ; ቦርከና እና ኢትዮጵያዊ ስብዕና

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ሙታሪካ; ሻቬዝ; ቦርከና እና ኢትዮጵያዊ ስብዕና

Postby ምረቱ » Wed Mar 20, 2013 8:43 pm

ሙታሪካ ከሞቱ ወደ ዓመት ገደማ ሊሆናቸው ነው:: የቻይና ዜና ምንጭ እንደሚያመለክተው ማላዊ ከሙታሪካ ሞት ምርመራ በኍላ አንዳንድ ቱባ ባለስልጣናትን አስራለች:: ጆይስ ባንዳ (እወነትም ባንዳ) ራሷ ትንሽ ቆይቶ የሚቀርላት አይመስለኝም::

ለማንኛውም የማላዊውን ዜና ቦርከናም ላይ ማግኘት ይቻላል:: ይሄው ሊንኩ http://borkena.com/?p=1000

ቬንዙዌላም አፍቃሪ ሕዝብ የነበረውን ኡጎ ሻቬዝ አሟሟት ማጣራት ጀምራለች:: የጉልበተኞቹ መንግስታት እጂ እንዳለበት የሚጠቁሙ ሁኔታዎች አሉ::

ጨናዊ እንኳን እንደው እውነት ሆኖ በእነሱ እጂ ሞቶ ከሆነ "በአፍቃሪው እጂ የሞተ ባንዳ" ያሰኘዋል::

በተረፈ ቦርከና ብሎግ ዌብ ሳይት ሆናለች:: ስራው ሙሉ በሙሉ አልተጠናቀቀም:: ይጠናቀቃል ተብሎ ግን ይገመታል:: ስነ-ስርዐት ያያዘ ከዘለፋ የጸዳ የመወያያ መድረክ እንደሚኖር በዚህ አጋጣሚ ላሳውቃችሁ እወዳለሁ:: ዋርካም ቦርከና የሚጠቀመውን ዓይነት ቲም እየተጠቀመ እንደሆነ ዛሬ አይሁ:: ይበል የሚያሰኝ ነው::

በነገራችን ላይ ስለ ቦርከና ዌብ ሳይት ዓላማ ጥያቄ ካላችሁ ከብዙ በጥቂቱ የድህረ-ገፁን ዓላማ እዚህ ላይ ማግኘት ትችላላችሁ http://borkena.com/?p=280

በተረፈ አሁንም ለፓለቲካ ትግል ስኬት የሚያስፈልግ አይነት የኑሮ ዘየ እና አስተሳሰብ አለ:: የህወሀት የበላይነት እስከዛሬ ድረስ ሊረጋገጥ የቻለው ቱባ በሚባሉ የውጭ የስነ-ልቦና ጦርነት ኤክስፐርቶች የህወሀት መሪዎች የተሰጣቸውን ምክር ግምት ውስጥ በማስገባት የጠንካራ ስብዕና ምንጭ የነበረዊን ኢትዮጵያዊ አስተሳሰብ በመናድ አልባሌ እና ግድ የለሽ ዜጋ ለመፍጠር ለመፍጠር በወሰዱት ዘመቻም ጭምር ነው:: ምን የመሳሰለ ለም መሬት ለውጭ ባለ ሀብት እየሸጠ ከመሬት ተነስቶ ዋልድባን አለማለሁ ሲል ሚስጥሩ ሌላ ነው:: በኢትዮጵያዊነት የሚጠረጠረውንም እስልምና መፈናፈኛ እያሳጣ የኤፈርት ድርጂቶች ከውጭ እንደሚያስመጡት እቃ ሀይማኖት አስመጥቶ በፓለቲካ ድጋፍ እና በህግ ሽፋን ተቀባይነት እንዲያገኝ ሲደረግ አሁንም ሚስጥሩ ሌላ ነው::

ስለ ኢትዮጵያዊ ማንነታችን ንቃተ-ህሊናችን እየዳበረ በመጣ ቁጥር እና ጠንካራ ኢትዮጵያዊ ሰብዕናችን በተመለሰ ቁጥር እንደ ህወሀት ያለ ቡድን ፈጽሞ ስጋት ሊሆን እይችልም:: "ኢትዮጵያን አፍርሰን እንሰራለን' ከነሚለው ቅዠቱ ባንድ ጀንበር ይጠፋል::

ወደ ግብዓቱ እንመለስ:: ማህበራዊ አስተሳሰባችንን እናድን:: በዚህ ጉዳይ ላይ ሀሳብ ማበርከት የምትፈልጉ የመወያያ መድረኩ እስከሚዘጋጂ በድህረ-ገጹ ላይ ፅሁፎቻችሁን በደስታ እንደማስተናግድ ማሳወቅ እፈልጋለሁ::

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
እግዚአብሔር ታላቅ ነው!
www.borkena.blogspot.com
facebook page: https://www.facebook.com/pages/Borkena/ ... 356?ref=hl
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest