ያማል (ከሰለሞን ሳህሌ)

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ያማል (ከሰለሞን ሳህሌ)

Postby እቴጌይት » Fri Apr 12, 2013 3:43 am

ሠላም ዋራካውያን በተለይ የጥበብ አፍቃሪዎች!

ስማቸው የማይታወቅ... ዝናን ያላተረፉ... ግን ድንቅ የሆኑ አንዳንድ ጻሕፍት አሉ:: በቅርቡ በአስደማሚ ብዕሩ የማረከኝ ገጣሚ ሰለሞንን ለማታውቁት ላስተዋውቃችሁ:: ያማል የሚለውን ግጥሙን ስቋደሳችሁ አንባብችሁ እንደ እኔ በእርካታ እየደጋገማችሁ እንድታታጥሙት ብቻ ሳይሆን... ከቻላችሁ ደግሞ ምላሽም እንድትከትቡ በመጋበዝ ነው! እኔም ከቻልኩ እንደ ሔለን ካሳ 'አይመመህ' ብዬ ብቅ እል ይሆናል :-

ያማል

እና እንደነገርኩሽ:-
የሚወዱትን ሰው- ቀጥሮ እንደመጠበቅ
የነፍሰ-ጡርን ሞት - አይቶ እንደመሳቀቅ
ባልታሰበ ናዳ - ተመቶ እንደመድቀቅ
ከተስፋ ጉልላት - ተገፍቶ እንደመውደቅ
ታምር በበዛባት - በዚች ቧልተኛ ዓለም
ከዚህ የበለጠ - ምንም ሕመም የለም!!

አውቶብሱ ያማል
ሚኒ ባሱ ያማል
ላዳ ታክሲው ያማል!
የማይጎል የሰው ጎርፍ -ደራሽ ማዕበሉ
የእምባ ቅጥልጥሉ
ምን ብዬ ልንገርሽ - ያማል ይሄ ሁሉ!

እና እንደነገርኩሽ
የሚወዱትን ሰው - ቀጥረው ካረፈደ
ያሚያፈቀሩትን ሰው -ቀጥረው ካረፈደ
ነገረ ተበላሸ -ሕመም ተወለደ
ጨጓራ በገነ
እሳት በእንፋሎክት መልክ - በእህታ ተነነ
የሚሆነው ሳይሆን - የማይሆነው ሆነ
ሁሉም ተቀይሮ - ተተካ በሲቃ
ምን ብዬ ልንገርሽ - ይሄም ያማል በቃ!
ወጪ ተራማጁ
አስመሳይ ሰጋጁ
ጸሐዩ ዝናቡ
የለምን ምክንያት - የለምን ሰበቡ
ተቆራጭ አበባ - ሊቆረጥ ማበቡ
ውል የለሽ ደመና -ተራራ መክበቡ
እልፍ ኣዕላፍ ኮከብ -ጨረቃን ማጀቡ
አህ..ደግሞ ለሷ ግጥም - እናቷን ጨረቃ
ምን ብዬ ልንገርሽ - ይሄም ያማል በቃ!!

እና እንደነገርክኩሽ
ጉንጭ የማትሞላ ኬክ - አስር ብር የሸጠ
የካፌ አሳላፊ - ወደ እኔ አፈጠጠ
ዘይት የነካውን - መንታ እጁን አጣምሮ
ምን ልታዘዝ ይላል - ቁልቁል አቀርቅሮ
ህም ምን ልታዘዝ ይላል?
እንዴት ቅጥሉ ሰው- ቅጥሉን ሰው ያዛል?
....
ማኪያቶ ልዘዝ?
ካፑቺኖ ልዘዝ?
ጥቁር ቡና ልዘዝ?
ለምን ሰው አላዝም??.....
መታዘዝ መናዘዝ - እርግማን የሆነው
ካፌውን ሲያስልፍ
እራሱን ግን የሚያልፍ
ቁልቁል አቀርቅሮ
ሞቱን ባንገት ቀብሮ
ምን ልታዘዝ ይላል!!!
.....
አንድ ማክያቶ - ካንድ እሷ ጋር ልበል?
አንድ ካፑቺኖ - ካንድ እሷ ጋር ልበል?
ከጥቁር ቡና ጋር - እሷን አምጣ ልበል?
ተይ አታስለፍልፊኝ - ይሄ ሁሉ ያማል!!

የላስቲክ አበባ - የአርቲ ቡርቲ ስዕል
የጭቃ እሾህ ወግቶት - እዥ ያወጣ ቁስል
ትልቁ ነቀዙ ሰው- የማንቀዙን ያህል -
ተይ አታስለፍልፊኝ - ይሄ ሁሉ ያማል!

እና እንደነገርኩሽ
ላንቺ ያዝኩት አበባ - መጠውለግ አመጣ
ጸሐይ ገባ ወጣ
ዝናብ ቀረት መጣ
ጨረቃ የለችም...ህምም እናቷን ስላልኳት?
ደግሜ ሰድቤ - ሺህ ዓመት እንዳይገርማት
እ..ና...ቷ...ን - እናቷን ጨረቃ
ተይ አታስለፍልፊኝ - ይሄም ያማል በቃ!!

ግን..ግን...እኔ አንቺን ስወድሽ
እኔ አንቺን ስወድሽ
ይሄን ሁሉ ችዬ ነው የምጠብቅሽ
ቢሆንም ግን ያማል!!


ድንቅ አይደለም ትላላችሁ?
እቴጌይት
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 656
Joined: Sun Sep 23, 2007 10:38 pm

Postby ልዑል20 » Wed Apr 17, 2013 4:12 pm

ድንቃ ድንቅ መድበል......ወድጄዋለሁ

ለአንችም ምስጋና ስላቓደሽን
ልዑል20
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 11
Joined: Wed Apr 10, 2013 6:00 pm


Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests