ወንድሜ እንሰት ስለዚች መጽሃፍ ጠቀስ አድርጎ ስላጓጓኝ ላኩልኝ ብዬ ሰሞኑን አነበብኳት ። መጽሃፊቱ የተጠረዘችው በሰከራም ሳይሆን አይቀርም ። ገጾቹ ያለይዘትና ያለቦታቸው ተዘበራርቅው በማፈላለግ አንብቤያታለሁ ። ከታች ያስደነቀኝን የስፓኒሹ ኮ/ልና የራስ ሙሉጌታ ንግግር እነሆ ስፓኒሹ እንደጻፈው
ራስ ሙሉጌታ በሕንጣሎ ጦር ግንባር ቆስለው ለሞት ሲያጣጥሩ ይህንን ነገሩኝ ብሎ ኮሎነል አልኸንድሮ ዴል ባዬ በጻፈውና ዶር ተስፋዬ መኮንን ባየልኝ ቀይ አንበሳ ብሎ በተረጎመው መጽሃፍ ገጽ 189 ላይ
--------------------
-ራስ ሙሉጌታ ከንግዲህ ለሶስት ደቂቃ እንኳን አይቆዩም ። በድጋሚ ሳቁ ።
"በህይወት ዘመኔ ጥሩ መንገድ ተጉዣለሁ " ሲሉ በተኩራራና በሚያምር የትያትር ድምጽ ተናገሩ ፡፡ "ከምንም የሆንኩትን ለመሆን ችያለሁ ። አሁን መሞት እችላለሁ ።
" አዳምጥ ፈረንጅ " በማለት ቀጠሉ ። " ሁሉም የአብሲኒያው ኃይለኛው ራስ መሆኔን ያውቃሉ ። ሆኖም ግን ሰዎች ከሚገምቱት በላይ ኃይለኛና ብዙ ማድረግ እንደምችል ግን በፍጹም አያውቁም ።
ሁሉም ምኒልክን ያከብራል ። በኢትዮያ ታሪክ ውስጥ ትልቁ ሰው አድርገው ያዩታል ። የማይሸነፍ ሰው አድርገውም ቆጥረውታል ።
እናም እሺ ፡ ምኒልክን የምበልጠው ትልቁ ሰው እኔ ነኝ ። እኔ ነኝ የኢትዮጵያውያንን ጀግና የገደልኩት ። "
እርስዎ ኖት የገደሏቸው ? እንዴት ?
" በመርዝ ነው የገደልኳቸው ። አዲስ አበባ ላይ አንድ ግሪካዊ ዶክተር ነው መርዙን የሰጠኝ ። ያለህመም ሞት፡ የማይታይ ፍንጭ የሌለው ። ገዳይ ወይም ዱካው ያልተገኘ ሞት ። ሁሉም ነገር በምስጢር ። በአንዲት የቡና ስኒ ምኒልክ ሞትን ፉት አሏት ። ማንም በፍጹም የጠረጠረ የለም ። ከኢትዮጵያ ችሎት ውስጥ ማቀነባበሩን ከረዱኝ ከሶስት ታላላቅ ሰዎች በስተቀር "
______________________________
እውነተኛ ታሪክ ወይስ የፈረንጁ ፈጠራ ታሪክ
ጉዲ ሰዲ ይላል ዲጎኔ ሲገርመው