የዲጎኔ ግጥሞች

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby varka911 » Tue Nov 05, 2013 2:33 pm

ዲጎኔ wrote: ... እንዲህ እናንተን መሰል ጨዋ ወገኖች ተሳትፎ በክፉወያኔዎችና መሰሎቻቸው ተቃዋሚ ነን ተብዬዎች የቆነሰች ዋርካችን መአዛ ጠርኗን ይለውጣል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ::

ጋሽ ዲጎኔ ሰላም ብያለሁ :D

ለስንቱ ማስተማሪያና መደበሪያ መሆን ስትችል ዋርካ የጥቂቶች መጸዳጃ ፎረም ስትሆን ማየቱ ይደብራል:: ከላይ በትክክል እንዳስቀመጥከው ዋርካን ባግባቡ ኢትዮጵያውያን እንዳይጠቀሙበት እያደረጉ ያሉት ወየንታዎች ብቻ ሳይሆን በገቢርም በአእምሮ ስንክልናም ከነሱ የማይሻሉ ተቃዋሚ ነን ባዮች ጭምር ናቸው::

ይገርምሀል ሁለት ሰዎች አሉ ዋርካን መከታተል ከጀመርኩ ጀምሮ አንዲት ቁምነገር ጽፈው አይቻቸው የማላውቅ:: ግን ደግሞ ዋርካ ስር ድንጋይ ተንተርሰው ውለው የሚያድሩ ናቸው:: የስላሴ ታምር ተወርቶ አያልቅም ጨርሶ ይግረምህ ሲሉኝ አንደኛው በቅርቡ ሳት ብሎት መሬት ጠብ የማትል ቁምነገር ጽፎ አስነበበኝ:: በጣም እየገረመኝ እጠቅሳለሁ :wink:

salar (ወይንም dalar ሊሆን ይችላል :lol: ) እንደጻፈች/ው
well, thats your opinion for me you are one of the dumbs in here... all you do is vomit and Troll.. i have never seen Constructive and Civlized answer from you, you are stupid and low life .... you should be ashamed of yourself.

ያው እንግዲህ የሁለተኛውን ስም መጥቀስ አያስፈልገኝም ማለት ነው :D

የአቶ ተመስገን አባባልን ተግባራዊ እያደረክ ዋርካን ተንፈላስባት እንጂ እጅ እንዳትሰጥ :D

አክባሪህ 911 የዋርካው ነኝ
Get your second chance On my First Aid!
varka911
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 101
Joined: Tue Oct 22, 2013 2:30 pm

Postby ዲጎኔ » Wed Nov 06, 2013 3:01 am

ሰላም ለሁላችን በያለንበት
ዋርካ ዛፉ ስር ምንማማርበት
ቅኑ ከጠማማ የሚከትበበት
ወገን ከመሰሪ የሚተያይበት
እንዲህ ጌታ የጥንቱ ወዳጄ
እዚህ ለከፈተው ያለኝ በጄ
ባደኩበት ግጥም ተወራርጄ
ብቅ ብያለሁ ከምወደው ደጄ
ግን ዋና ነገር እንዳትዘነጉ
የሰነቃል አይነተኛው ወጉ
ለታፈነ ህዝብ ሀቅ አውጉ
አፋኝ ግፈኛን በጽኑተዋጉ
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby መራራ » Wed Nov 06, 2013 7:08 am

የ ንጋቷ ኮኮብ እማሆይ መራራ ውጪ ተከሰሻል:
አልጫ ሀያትን ስም አስቀይረሻል:: :lol: :lol:
ጉልቻ ቢቀየር ወጥ አያጣፍጥም አይደል ወይ ተረቱ:
ቫርካ ብሎ መጣ ከ እነ ዝተቱ::
አንዲት ማንኪያ ሀሞት ውስጡ የሌለው:
እንደ እባብ ቆዳ ተቀያያሪው:
ሊቅም ነኝ እያለ እንዲያ እንዳልፎከረ:
እድሜ ለ ልእልቷ መና ሆኖ ቀረ:: :lol: :lol
ስኳር ደምብዛቱ ሪህ እና ጨጓራ:
ሀብቱ ናቸው ተብለው ስሙ የሚጠራ:
ከቆመ እባብ ጋር ልዩነት የሌለው:
የቀድሞው ሀያት የዛሬ ቫርካ ነው:: :lol: :lol: :lol:
መራራ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 753
Joined: Sat Sep 25, 2004 9:58 am
Location: united states

Postby ሙዝ1 » Wed Nov 06, 2013 8:16 am

varka911 wrote:

የአቶ ተመስገን አባባልን ተግባራዊ እያደረክ ዋርካን ተንፈላስባት እንጂ እጅ እንዳትሰጥ :D

አክባሪህ 911 የዋርካው ነኝ

አክባሪዉ 911 ቂቂቂ ሙድ ትይዛለህ አይደል? ቂቂቂቂ ያቺ አባባል አቶ ተመስገን ከየት እንደወሰዳት አጥተኸው ነዉ? ዲጎኔ ወንድማችን ሁሌም ኮት ሲያደርጋት ወደ አቶ ተመስገን ሲወስዳት ፈገግ እላለሁ .... አንባቢዉና ምርጡ ጋዜጠኛ ዲጎኔ የ Shiv Khera ን መጽሀፍ ለምን አላነበበም ብየም አልመጻደቅም ሎል ለሁሉም ዲጎ ወንድማችን መጽሀፏን አንብባትማ በነጻ ኦንላይን ታገኛታለህ .... u can win የምትል ነች

በተረፈ ግን የስከዛሬዉ ዲጎኔ ላይ ለነበረኝ ትንኮሳ ትልቅ ደቦል ድንጋይ ተሸክሜ ይቅርታ እጠይቃለሁ ... .... በጣም የዋህና ቅን ሰዉ እንደሆንክ ለዚህ ቤት የሰጠኸዉ መልስ ያስታዉቃል:: ጌታ ግን ዲጎኔ ይቅር ባይ ሆኖ ቢያልፍህም ያንተ ነፍስህ አይማርም ...
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Postby varka911 » Wed Nov 06, 2013 3:15 pm

ሰላም ወንድማችን ሙዝ1, አካም አለኻ? :D

ከጋሽ ዲጎኔ ጋር ልታቧቅሰኝ ነው እንዴ አላማህ? እኔ ሙድ እየያዝኩበት አይደለሁም:: የምሬን ነው:: አንተም ዘግይተህ እንደተረዳኸው ጋሽ ዲጎኔ ቀና ልብ ያለው ሰው ነው:: ተንኮልና ክፋት የለበትም:: ይህንን ቅንነቱንና የዋህነቱን እንደ ጅልነት እየቆጠሩ ሊደበሩበት የሚሞክሩ ዋልጌዎችን ሳይ ስለነሱ አዝናለሁ:: እንኳን የዕድሜ ባለጠጋ ቀርቶ እንዲሁ ቅን ሰው በቀናነቱ ሊከበር ይገባዋል:: የሀይማኖትና የፖለቲካ አመለካከቱ ከእነሱ ጋር ስላልገጠመ ብቻ ግጣም ባጣ ልቅ አፋቸው ሲያዋክቡት ስታይ የምር በኋላቀርነታችን አታዝንም?

ስማ እንጂ አንባቢ ሰው መሆንህን አላጣነውም እኮ ግን ምናለ የኛን ሞራልም ብትጠብቅልን:: እንዴ? ሺቭሴራን :D አላወቃችሁም ብለህ ልታሳንስን ትሞክራለህ እንዴ:: እኛም እኮ የ7ኛ ክፍል ኬምስትሪ አስተማሪያችንን እናውቃለን:: እሱን የማያውቅ ሰው 7ኛ ክፍል አልደረሰም ማለት ግን አይቻለንም :lol:

ሙዝ1 wrote:
varka911 wrote:

የአቶ ተመስገን አባባልን ተግባራዊ እያደረክ ዋርካን ተንፈላስባት እንጂ እጅ እንዳትሰጥ :D

አክባሪህ 911 የዋርካው ነኝ

አክባሪዉ 911 ቂቂቂ ሙድ ትይዛለህ አይደል? ቂቂቂቂ ያቺ አባባል አቶ ተመስገን ከየት እንደወሰዳት አጥተኸው ነዉ? ዲጎኔ ወንድማችን ሁሌም ኮት ሲያደርጋት ወደ አቶ ተመስገን ሲወስዳት ፈገግ እላለሁ .... አንባቢዉና ምርጡ ጋዜጠኛ ዲጎኔ የ Shiv Khera ን መጽሀፍ ለምን አላነበበም ብየም አልመጻደቅም ሎል ለሁሉም ዲጎ ወንድማችን መጽሀፏን አንብባትማ በነጻ ኦንላይን ታገኛታለህ .... u can win የምትል ነች

በተረፈ ግን የስከዛሬዉ ዲጎኔ ላይ ለነበረኝ ትንኮሳ ትልቅ ደቦል ድንጋይ ተሸክሜ ይቅርታ እጠይቃለሁ ... .... በጣም የዋህና ቅን ሰዉ እንደሆንክ ለዚህ ቤት የሰጠኸዉ መልስ ያስታዉቃል:: ጌታ ግን ዲጎኔ ይቅር ባይ ሆኖ ቢያልፍህም ያንተ ነፍስህ አይማርም ...
Get your second chance On my First Aid!
varka911
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 101
Joined: Tue Oct 22, 2013 2:30 pm

Postby ዲጎኔ » Thu Nov 07, 2013 2:09 am

ሰላም ይሁንልን ለሁላችን
ለሙዝ የጎዛምን ወይናችን
አሎሎው ይውደቅ ከትከሻችን
እንከባበር በማንነት ልዩነታችን
ያለፈውን እንርሳ እንራመድ ወደፊት
እስኪ እንደሰዎቹ ዋርካን እናሳምራት
መወያያ መማማሪያ መድረክ እናርጋት
አቶ ተመስገን የጠቀሱ ድንቅ አባባል
ተቃዋሚ ጉዋዶቹንም ለሚዘልፈው
አንጃ አተላ ያላቸው በሸንጎው
ዛረ ግን የምስጥ ቀለብ የሆነው
የወያኔው መሪን ደባ ሳንረሳው
እኛ በህይወት እዚህ ያለነው
ለህዝቡ በጎ ነገር እንስጠው
መባላት መለያየቱ ይብቃው
ይህን በሳይበር እንጀምረው

ሙዝ1 wrote:
varka911 wrote:
የአቶ ተመስገን አባባልን ተግባራዊ እያደረክ ዋርካን ተንፈላስባት እንጂ እጅ እንዳትሰጥ :D

አክባሪህ 911 የዋርካው ነኝ

አክባሪዉ 911 ቂቂቂ ሙድ ትይዛለህ አይደል? ቂቂቂቂ ያቺ አባባል አቶ ተመስገን ከየት እንደወሰዳት አጥተኸው ነዉ? ዲጎኔ ወንድማችን ሁሌም ኮት ሲያደርጋት ወደ አቶ ተመስገን ሲወስዳት ፈገግ እላለሁ .... አንባቢዉና ምርጡ ጋዜጠኛ ዲጎኔ የ Shiv Khera ን መጽሀፍ ለምን አላነበበም ብየም አልመጻደቅም ሎል ለሁሉም ዲጎ ወንድማችን መጽሀፏን አንብባትማ በነጻ ኦንላይን ታገኛታለህ .... u can win የምትል ነች

በተረፈ ግን የስከዛሬዉ ዲጎኔ ላይ ለነበረኝ ትንኮሳ ትልቅ ደቦል ድንጋይ ተሸክሜ ይቅርታ እጠይቃለሁ ... .... በጣም የዋህና ቅን ሰዉ እንደሆንክ ለዚህ ቤት የሰጠኸዉ መልስ ያስታዉቃል:: ጌታ ግን ዲጎኔ ይቅር ባይ ሆኖ ቢያልፍህም ያንተ ነፍስህ አይማርም ...
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby መራራ » Thu Nov 07, 2013 10:09 am

የጉድ አገር ገንፎ እያደር ይፋጃል:
የ ዲጎኔም ግጥም እያደር ይዝላል::
በ: ሏ ሟ ሯ ሷ ሿ የሚጽፈው ግጥም:
ወይ ለ ወሬ አይመች ወይ ለ ጆሮ አይጥም::
አርፎ እንዳይቀመጥ ዲጎኔ ሞረቴው ከ ሩቅ ማዶ እያለ:
ታገል ሰይፉ ብሎ ጌታ ጠርቶት የለ?
ታዲያ ቢያሰለቸን በ አቦጊዳ ገጥሞ:
ይመታልኝ ቢለን ከበሮና አታሞ:
የ በእውቀቱን ስራ ያነበብ አይን: ያደመጠ ጆሮ:
እንደምን አያዝን በ ጌታ አምርሮ:: :lol: :lol: :lol:ዲጎኔ wrote:ሰላም ይሁንልን ለሁላችን
ለሙዝ የጎዛምን ወይናችን
አሎሎው ይውደቅ ከትከሻችን
እንከባበር በማንነት ልዩነታችን
ያለፈውን እንርሳ እንራመድ ወደፊት
እስኪ እንደሰዎቹ ዋርካን እናሳምራት
መወያያ መማማሪያ መድረክ እናርጋት
አቶ ተመስገን የጠቀሱ ድንቅ አባባል
ተቃዋሚ ጉዋዶቹንም ለሚዘልፈው
አንጃ አተላ ያላቸው በሸንጎው
ዛረ ግን የምስጥ ቀለብ የሆነው
የወያኔው መሪን ደባ ሳንረሳው
እኛ በህይወት እዚህ ያለነው
ለህዝቡ በጎ ነገር እንስጠው
መባላት መለያየቱ ይብቃው
ይህን በሳይበር እንጀምረው

ሙዝ1 wrote:
varka911 wrote:
የአቶ ተመስገን አባባልን ተግባራዊ እያደረክ ዋርካን ተንፈላስባት እንጂ እጅ እንዳትሰጥ :D

አክባሪህ 911 የዋርካው ነኝ

አክባሪዉ 911 ቂቂቂ ሙድ ትይዛለህ አይደል? ቂቂቂቂ ያቺ አባባል አቶ ተመስገን ከየት እንደወሰዳት አጥተኸው ነዉ? ዲጎኔ ወንድማችን ሁሌም ኮት ሲያደርጋት ወደ አቶ ተመስገን ሲወስዳት ፈገግ እላለሁ .... አንባቢዉና ምርጡ ጋዜጠኛ ዲጎኔ የ Shiv Khera ን መጽሀፍ ለምን አላነበበም ብየም አልመጻደቅም ሎል ለሁሉም ዲጎ ወንድማችን መጽሀፏን አንብባትማ በነጻ ኦንላይን ታገኛታለህ .... u can win የምትል ነች

በተረፈ ግን የስከዛሬዉ ዲጎኔ ላይ ለነበረኝ ትንኮሳ ትልቅ ደቦል ድንጋይ ተሸክሜ ይቅርታ እጠይቃለሁ ... .... በጣም የዋህና ቅን ሰዉ እንደሆንክ ለዚህ ቤት የሰጠኸዉ መልስ ያስታዉቃል:: ጌታ ግን ዲጎኔ ይቅር ባይ ሆኖ ቢያልፍህም ያንተ ነፍስህ አይማርም ...
መራራ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 753
Joined: Sat Sep 25, 2004 9:58 am
Location: united states

Postby ቱሉቦሎ » Thu Nov 07, 2013 6:22 pm

ዋልጌ ስድ አደጉ ቢቆላ ምላሱን
ወየንቲ ቢጮህ ቢያወርድ ስድቡን
ጥይት ቢንጣጣ መድፍ ቢተኮስ
ጋሬጣ ቢደቀን ሆዳም ቢተራመስ
እሾህ አሜከላ ምስማር ቢነሰነስ
ለእውነት ለሃቁ ለቀጥታው መስመር
ለሰው ልጆች ጥቃት ለጭቁኖች ችግር
ድምጹን የማይገታው ዝምብሎ የማያልፈው
የዘር ፖለቲካ ፍጹም ያልለከፈው
ቅን ኢትዮያዊ ሃቀኛ ወገኔ
እድሜው ይርዘምልኝ ወንድሜ ዲጎኔ
ቱሉቦሎ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 195
Joined: Tue Sep 04, 2012 8:13 pm

Postby ሙዝ1 » Fri Nov 08, 2013 5:58 am

varka911 wrote:ሰላም ወንድማችን ሙዝ1, አካም አለኻ? :D

ሰላም ሰላም ፈዩማ ጽቡቅ ...

ዋናዉ አንባቢነቴን ማመንህ ላይ ነዉ ሎል .... ቁጥር 1 የዋርካ ምሁር በመሆኔ ኩራት ይሰማኛል .... አመዳም ነገር ነህ .... ደግሞ የት እንደሆነ አላወኩም እንጂ አዉቅሀለሁ ልበል? ከቀድሞ ወዳጆቻችን አንዱ ትሆን? :lol:

ወንድሜ ዲጎኔ .... ሀሳብህን በተመቸህ መንገድ መግለጽ ያንተ ማንም የማይነጥቅህ መብትህ ነዉ .... እዉነት እዉነት እልሀለሁ የገጣሚነት እንጥፍጣፊዉም የለህም .... ይህ ዝርጠጣ አይደለም .... ይህ የወያኔነቴ ማሳያ አይደለም ... ይህ ያየሁት እዉነት ነዉ::

ወንድሜ ዲጎኔ .... አሁንም ምልከታዎችህንና ግምገማዎችህን በተመቸህ መንገድ መግለጽ ያንተ ፋንታ ነዉ .... ... የዋርካዉ ዲጎኔ ከእዉነተኛዉ አንተነተህ በቀጥታ የሚወጣ ትንታኔ ከሆነ ዋርካ ላይ እየሰጠህ ያለኸዉ ... .... እዉነት እዉነት እልሀለሁ አንተ የዋህ ሰዉ ነህ .... የዋህ ብሎሀል ከላይ ያለዉ 911 ወንድማችን እዉነት ነዉ ለማለት ያስደፍረኛል .... ዲጎኔ ወንድሜ የዋሀን ደግሞ ሀይማኖት ላይ እንጂ ፖለቲካ ላይ ምንም አይነት ቦታ ኖሯቸዉም አያዉቅም .... ትክክለኛ ሀይማኖትኞችን ማለቴ ነዉ .... ስለዚህ አንተ .... ብልጣብልጥ ... ተገለባብጭ .... ካልሆንክ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ቦታ የለህምና አርፈህ ቁጭ በል ... እንደዉ እናት ለልጇ ምጥ አስተማረች እንዳይሆንብኝ እንጂ ከየዋህነት ዉጣና ከዘመንህ ጀምሮ እስካሁን ያሉትን ፖለቲከኞቻችንን ተመልከት ... .... የነገ ፖለቲከኞችም ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ መገንዘብ አይከብድህም .... እናም በጊዜ ቦታህን ፈልግ ...

ወንድሜ ዲጎኔ .... ሰዉ ለሆነ ሰዉ .... ሰዉነቱን በየቀኑ እየተማረ ላደገ ሰዉ እንደ እድሜ ታላቅ ትምህርት ቤት የለም .... እናም ያንን ሀብትህን ኢንቨስት አድርግ ... ወደ ጥናትና ምርምር አዘንብል ... ትልቅ ሀብት ነህ .... ይሄን የምለዉ ከወጣትነትህ ጊዜ ጀምሮ ትርፍ ጊዜህን እንደኔ በየዉስኪ ቤቱ እየተቃጠልክ .... መቃጠልህንም ለማብረድ በሚሞቁ ለስላሳ የሴት ጭኖች መካከል በመናወዝ ጊዜህን አላሳለህክም ከሚል መነሻ ነዉ:: ... ምክንያቱም ከልጅነትህ ጀምረህ ለህዝቦች እኩልነትና ከጭቆና ነጻ የማድረግ እርሾዉን በዉስጥህ ስላስቀመጥ ወደ መሸታ ቤት ሄደህ ጊዜህን አታባክንም በሚል ግምት ነዉ:: መሸታ ቤት ካልሄድክ ደግሞ ከሰዎች ጋር በመወያየት .... መጻህፍትን በማገላበጥ ... አልያም ከራስህ ጋር ስብሰባ በመቀመጥ በመቆዘም በየደቂቃዉ የእዉቀት (ቃል ስላጣሁ ነዉ እዚህ ጋ እዉቀት ያልኩት .... ከknowledge በላይ ያለዉ wisdom ነዉ? እሱን ለማለት ነዉ) ሀብትን ስታካብት ኖራሀል ማለትም ነዉ::

በል ይሄን ሁሉ ያልኩህ በስምህ ቤት ስለተከፈተ አንተ እንድትሆን የምፈልገዉን ወንድማዊ ምኞቴን ለመግለጽ ነዉ::

መልካሙን ሁሉ ይግጠምህ
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Fri Nov 08, 2013 7:46 am

ሙዝ1 wrote:እንደዉ እናት ለልጇ ምጥ አስተማረች እንዳይሆንብኝ እንጂ ከየዋህነት ዉጣና ከዘመንህ ጀምሮ እስካሁን ያሉትን ፖለቲከኞቻችንን ተመልከት ... .... የነገ ፖለቲከኞችም ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ መገንዘብ አይከብድህም .... እናም በጊዜ ቦታህን ፈልግ ...............................

ወንድሜ ዲጎኔ .... ሰዉ ለሆነ ሰዉ .... ሰዉነቱን በየቀኑ እየተማረ ላደገ ሰዉ እንደ እድሜ ታላቅ ትምህርት ቤት የለም .... እናም ያንን ሀብትህን ኢንቨስት አድርግ ... ወደ ጥናትና ምርምር አዘንብል .

ሙዝ1

አሁንስ የዋሁ ዲጎኔ ሳይሆን አንተው ራስህ ነህ :D

ራስህን ፈልግ ብለህ የመከርከውን ሰውዬ መልሰህ ደግሞ በእድሜ ትምህርት ቤት ያካበትከውን ኢንቬስት አድርግ ትለዋለህ እንዴ :?: :lol: :lol: ጭራሽ ደግሞ ጥናትና ምርምር :lol: :lol: :lol: :lol:

ከቶ ለምን ይሆን......ምን ቆርጦህ.........ጉድጓዱ ተምሶ; ልጡ ረስርሶ ያለውን የብስራተ ወንጌል ሜጋፎንና ስፒከር ተሸከሚ; እንዲሁም የዘኬ ቤት ወሬ አመላላሽ አንጋፋ ሰውዬ እንዲህ ግራ የምታጋባው :?: :D

እንደው ሌላው ቢቀር......የዋርካ ዝነኛው አልቃሽ መራራ እንኳን በሁለት ስንኝ ለዲጎኔ ያልቀሰለት ልቅሶ "እያነባሁ እስክስታ አስመትቶኛል" :lol:

"የጉድ አገር ገንፎ እያደር ይፋጃል :
የ ዲጎኔም ግጥም እያደር ይዝላል ::" :lol: :lol: :lol: :lol:
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Postby መራራ » Fri Nov 08, 2013 12:10 pm

የትዬ አሰፋሽ ልጅ አተላ ቀለቡ
ከ አንተስ ይሻለኛል ዲጎኔ እንደልቡ::
እሱ ኢትዮጽያዊ የደሀ ጠበቃ:
አንተ ተጫኝ ካድሬ የ ህወሀት እቃ::
እኔ ጠላሁ እንጂ አቅሙን መርሳቱን:
እገጥማለሁ ብሎ ግጣሙን ማጣቱን:
በብዙ ይበልጣን እንዳንተስ አይነቱን::
ሞኝባገኝ ልምሻ ፖሊዮና ኩፍኝ የፈጠሩብህ ጣጣ:
መሀይም መሆንህ የ እውቀት ቆማጣ::
የገለማ አይምሮ ተሸክሞ ዟሪ:
ልትሆንስ አትችልም ዲጎኔን መካሪ::ዳግማዊ ዋለልኝ wrote:
ሙዝ1 wrote:እንደዉ እናት ለልጇ ምጥ አስተማረች እንዳይሆንብኝ እንጂ ከየዋህነት ዉጣና ከዘመንህ ጀምሮ እስካሁን ያሉትን ፖለቲከኞቻችንን ተመልከት ... .... የነገ ፖለቲከኞችም ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ መገንዘብ አይከብድህም .... እናም በጊዜ ቦታህን ፈልግ ...............................

ወንድሜ ዲጎኔ .... ሰዉ ለሆነ ሰዉ .... ሰዉነቱን በየቀኑ እየተማረ ላደገ ሰዉ እንደ እድሜ ታላቅ ትምህርት ቤት የለም .... እናም ያንን ሀብትህን ኢንቨስት አድርግ ... ወደ ጥናትና ምርምር አዘንብል .

ሙዝ1

አሁንስ የዋሁ ዲጎኔ ሳይሆን አንተው ራስህ ነህ :D

ራስህን ፈልግ ብለህ የመከርከውን ሰውዬ መልሰህ ደግሞ በእድሜ ትምህርት ቤት ያካበትከውን ኢንቬስት አድርግ ትለዋለህ እንዴ :?: :lol: :lol: ጭራሽ ደግሞ ጥናትና ምርምር :lol: :lol: :lol: :lol:

ከቶ ለምን ይሆን......ምን ቆርጦህ.........ጉድጓዱ ተምሶ; ልጡ ረስርሶ ያለውን የብስራተ ወንጌል ሜጋፎንና ስፒከር ተሸከሚ; እንዲሁም የዘኬ ቤት ወሬ አመላላሽ አንጋፋ ሰውዬ እንዲህ ግራ የምታጋባው :?: :D

እንደው ሌላው ቢቀር......የዋርካ ዝነኛው አልቃሽ መራራ እንኳን በሁለት ስንኝ ለዲጎኔ ያልቀሰለት ልቅሶ "እያነባሁ እስክስታ አስመትቶኛል" :lol:

"የጉድ አገር ገንፎ እያደር ይፋጃል :
የ ዲጎኔም ግጥም እያደር ይዝላል ::" :lol: :lol: :lol: :lol:
መራራ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 753
Joined: Sat Sep 25, 2004 9:58 am
Location: united states

Postby varka911 » Fri Nov 08, 2013 4:18 pm

ይቺን ይወዳል ዲጎ :roll: :!:

ለህይወቴ ኣንድም ሳልሳ
ከእድሜዬ ኣንዲትም ቀን ሳላነሳ
ልሳን ሆኜ በቆምኩኝ ለወጌኔ ኣበሳ
እንዴት በማንም ለፍዳዳ ስሜ በክፋት ይነሳ?
እኮ እንዴት? ለምንስ ሲባል
ስሜ በማንም ዝቃጭ ይነሳል?

የቋጠርኳቸው ስንኞች ባይጥሙህ
ግፈኞችን ማውገዜ ባይዋጥልህ
ሃሰተኛ መናፍቆችህን ኣለመቀበሌ ባያስደስትህ
እንጦረጦስ ውረድ እንጂ ከስሜ ምን ኣለህ?
እኔ እንደሆን ኣይደለም ለሳይበራዊ ድንፋታ
ለግፈኞች ጡጫና ግልምጫም ኣልረታ፡፡

ፍቅርን እንደጦር ሰብቆ
ደግነትን ከክፋት ፈልቅቆ
ነፃ እንዳወጣው የሰውን ልጅ በሞላ
ከተጋረጠበት የሃጥያት ኣሜኬላ፤
የኔም ህይወት የክርስቶስን መንገድ ተከትላ
ለወገን ፍትህ የህይወት መስዋእትነትን ከፍላ
ለግማሽ ምእተኣመት ታከተኝን ሳታውቅ ስለ መታገሏ
ምድረ ዋልጌን እንዴት ላስረዳ ሆኜ ከመገኘቴ ሌላ ።

እናም ተመከር ወዳጄ••• ማነህ የነፃነት ጋሬጣ
ኣትሁንና የኣገር ሸክም ••• የወገን ባላንጣ
እንደኔ የህይወት ግብህን በግዜ ለይ ••• ኣገርህን ነፃ እንድታወጣ።

ኣሻፈረኝ ካልክም ••• በል ••• መብትህ ነው
የታባህ እንደምትደርስ •••ግን ••• እኔም ኣያለው
ይቺን ከመጠቅጥቅ እንደማታልፍ ደግሞ ጠንቅቄ ኣውቃለው።
Get your second chance On my First Aid!
varka911
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 101
Joined: Tue Oct 22, 2013 2:30 pm

Postby ዲጎኔ » Sat Nov 09, 2013 1:43 am

ሰላም ለሁላችን ዋርካዊያን
በስነግጥም አምድ ከያኒያን
በተለይ ወገን ሀቅ ተዋንያን
ቱሉቦሎና ባለልዩ ኒኩ አጋር
የዲጎኔ እምባ ጠባቂ አውታር
ሁሉን ያሳተፉ ከዳር እስከዳር
በግጥም መርህ ሀቅን በመዘከር
እናንተ ግን የዲጎኔን ግጥም ተቺዎች
ሀሳቡን ሳይሆን ሰውየውን አጥቂዎች
ዛሬም ልበል ጉዳይ የለኝ ከወራጆች
የወያኔውና የቀደሙት ገዥ ጀሌዎች
እንኩዋን እንዲህ ባማረ ግጥም ቀርቶ
ድሮም ተፋልመናል በኡኡታ ቀረርቶ
ለመጥቀስ ያህል ይህውና እንቶ ፈንቶ
በተፈሪ አጣን ፍርፋሪ
በኢያሱ ዳቦ ነው ትራሱ
ያልተገራን ፈረስ ጠቅል እያላችሁ
ከማይጨው ደንብሮ ሎንደን ገባላችሁ
መንጌ ብኮንቦሮው የሰበሰበን
መለስ በልጋጉ አዝረከረከን
መለስ የበላው ይመለስ
በሉ ገጣሚያን ጦቢያችን ያላችሁ
ከቶ እንዳትሸሹ ስድቡን ፈርታችሁ
ወያኔ በስድብ አቻ የሌለው ከመሪው
ጉዋዶቹን በከቻ ፕሬስ አተላ ያለው
ብሄሮች ህዝቦችን አዋርዶ የሰደበው
አሰስ ገሰሱን ብሎ በሸንጎ የቀረሸው
ስለዚህ ጀሌዎች እዚ ቢያላዝኑብን
የአዞ እንባ በ30 ኒክ ቢያፈሱልን
አንዳች ከአላማችን አይነቀንቁን
ጦቢያ ነጻ ሳትወጣ ከቶ አያታልሉን
የፈለጋቸው ስድብና ስም ያውጡልን
ባንክ ዘረፉ ኢሰፓ ደርጎች ይበሉን
ለወያኔ ደባ አንዳች ጆሮ አይኖረን
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby recho » Sat Nov 09, 2013 1:22 pm

ሙዝ1 wrote: ደግሞ የት እንደሆነ አላወኩም እንጂ አዉቅሀለሁ ልበል? ከቀድሞ ወዳጆቻችን አንዱ ትሆን? :lol:
ቂቂቂቂቅቅቅ አንዳንድ ፐርሰናሊቲዎች ፈጽሞ ለመደበቅ አስቸጋሪዎች ናቸው ... አሁን ገልቡ ስም ቢቀይር ገና ሳይጽፍ ራሱ ስሙን አይተን አናውቀውም? :lol: 911 ነቄ ቢያሎ :wink: ዌልካም ባክ ብለናል :lol: :lol: :lol:
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby varka911 » Sun Nov 10, 2013 2:47 am

ታንኩ ብያሎ ደጓ እህቴ :D

አባልጅነትን ሰኵር አደረኩ ማለት ነው::

አካም ነሽሳ? ሁሉም አሸወይና?

በይ ይቺን ለልጃችን እንደተጠቀለለች ስጭልኝ :D

recho wrote:
ሙዝ1 wrote: ደግሞ የት እንደሆነ አላወኩም እንጂ አዉቅሀለሁ ልበል? ከቀድሞ ወዳጆቻችን አንዱ ትሆን? :lol:
ቂቂቂቂቅቅቅ አንዳንድ ፐርሰናሊቲዎች ፈጽሞ ለመደበቅ አስቸጋሪዎች ናቸው ... አሁን ገልቡ ስም ቢቀይር ገና ሳይጽፍ ራሱ ስሙን አይተን አናውቀውም? :lol: 911 ነቄ ቢያሎ :wink: ዌልካም ባክ ብለናል :lol: :lol: :lol:
Get your second chance On my First Aid!
varka911
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 101
Joined: Tue Oct 22, 2013 2:30 pm

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 5 guests