ህይወት ስትፈተን ልትቆም ስትዋትት
መከራ እየገፋት ሊጥላት ሲባትት
ጥንካሬ ሲልም ጥቃቱ ሲበዛ
ደስታ ጭራሽ ጠፍቶ ጭቆና ሲንዛዛ
በጣጥሰህ ምትጥለው የፈተናን መረብ
በተስፋ ብቻ ነው ጥንካሬ ሚያብብ::
ተስፋም የሚታሰብ ተስፋ ሲፈተን ነው
በደስተኞች አለም ተስፋ የሌለ ነው::
አልሞተም ወርቅሰው አልሞተም ቃኘው:
ይሄው በዲጎኔ አይኔ እያየው::
ሞቷል አትበሉኝ ወርቅሰው አልሞተም:
ሄዷል አትበሉኝ ወርቅሰው አልሄደም:
አራምባ እና ቆቦን ሁሌም እንዳንረሳ:
ዛሬም በ ዋርካችን ተቀምጧልሳ::
ሀ-ግስ እና ለ-ግስ እረ እነ ሁካይ:
ይህን ግጥም አይተው በህይወት አሉ ወይ? :lol: :lol:
የ ድንቅነሽ ወዳጅ የ ላርዲ ጓደኛ:
የ ሶስት ሺ ዘመን ቃኚ ዘለሰኛ:
ከ ወዲያኛው ማዶ ሁሌም ነኝ የሚለንን:
ግጥም እንድትደፈር ሁሌም ያኑርልን:: :lol: :lol: :lol:
ክቡራን wrote:ጥበብ እኮ ታምራት ገለታንም ጠርታለች:: ዚቁ ያለው ግን ጥሪውን በመልካም ተግባር ላይ ማዋሉ ላይ ነው:: ""ያልቦካ ጸሎት ከመከራ አያድንም "" ዲሞጥሮስ የሚባለው አስተማሪዬ እኮ ነው::
እነሆ ጠቢባን ሆይ ተጠበቡ... ያላወቁቹ ደሞ እወቁ ወይም ደሞ ጠበብ መስሏቹ የዋጣችሁትን ቴትራ ሳይክሊን አስታውኩት :::: :D
መተሬ= ውርስ ትርጉም= ስናይፕር ተኴሽ :D
http://www.youtube.com/watch?v=t4iGx1z5gls
በልዕልት መራራ ስም የገባው ሀማል wrote:ሰለሞን ጠቢቡ የ ሳባ አማላይ:
ታምራት ጠቢብ ነው ባዮችን ብታይ:
የጥበብን ሚስጥር ምጡቅነቷን:
ላለማወቃቸው ሰም እና ወርቋን:
ታዝላቸው ነበር ""ጥበብ"" የሸማኔውን:: :lol: :lol: :lol:
ተጻፈ በ ልእልት መራራ:: መታሰቢያነቷ ለ ሳምራውው33 ትሁንልኝ:: :lol: :lol: ዱላነቷ ደግሞ ለ ካርቦንዬ :lol: :lol: :lol:ክቡራን wrote:ጥበብ እኮ ታምራት ገለታንም ጠርታለች:: ዚቁ ያለው ግን ጥሪውን በመልካም ተግባር ላይ ማዋሉ ላይ ነው:: ""ያልቦካ ጸሎት ከመከራ አያድንም "" ዲሞጥሮስ የሚባለው አስተማሪዬ እኮ ነው::
እነሆ ጠቢባን ሆይ ተጠበቡ... ያላወቁቹ ደሞ እወቁ ወይም ደሞ ጠበብ መስሏቹ የዋጣችሁትን ቴትራ ሳይክሊን አስታውኩት :::: :D
መተሬ= ውርስ ትርጉም= ስናይፕር ተኴሽ :D
http://www.youtube.com/watch?v=t4iGx1z5gls
መራራ wrote:ሰለሞን ጠቢቡ የ ሳባ አማላይ:
ታምራት ጠቢብ ነው ባዮችን ብታይ:
የጥበብን ሚስጥር ምጡቅነቷን:
ላለማወቃቸው ሰም እና ወርቋን:
ታዝላቸው ነበር ""ጥበብ"" የሸማኔውን:: :lol: :lol: :lol:
ተጻፈ በ ልእልት መራራ:: መታሰቢያነቷ ለ ሳምራውው33 ትሁንልኝ:: :lol: :lol: ዱላነቷ ደግሞ ለ ካርቦንዬ :lol: :lol: :lol:
ቦቹ wrote:መራራ wrote:ሰለሞን ጠቢቡ የ ሳባ አማላይ:
ታምራት ጠቢብ ነው ባዮችን ብታይ:
የጥበብን ሚስጥር ምጡቅነቷን:
ላለማወቃቸው ሰም እና ወርቋን:
ታዝላቸው ነበር ""ጥበብ"" የሸማኔውን:: :lol: :lol: :lol:
ተጻፈ በ ልእልት መራራ:: መታሰቢያነቷ ለ ሳምራውው33 ትሁንልኝ:: :lol: :lol: ዱላነቷ ደግሞ ለ ካርቦንዬ :lol: :lol: :lol:
እንዴ እንዴ ወይዘሮ በላይነሽ ሰላም ብለናል ቅቅቅቅቅ :lol: :lol: ለካ ጥሩ ገጣሚ ሆነዋል እንደዚህ አይ ጥሩ ነው:: እኔ የምለው ግን ዘንድሮ ምነው ገጣሚ በዛሳ :wink: :wink: ያም ተነስቶ ሆዴ ዴ ዴ ዴ ቻ ቻ ቻ ዋ ዋ ዋ: :lol: :lol: ቅቅቅቅቅ ይሁን ዋርካ ላይ ካልተለማመድን የት ልንለማመድ ነው:: ይቺ ድሮ ውቤ በረሃ ቡጊ እያስነኩ በነበረበት ዘመን ላይ የተገጠምች ግጥም ነች:: የግጥሙ ባለቤት እርሶና ባለቤቶት አቶ ብርሌ እንደሆኑ ብዙ ሰዎች ይናገራሉ...... :lol:
ትምሕርት ቤት ሆነን የጠየከኝን
እንጦጦ አፋፉ ላይ የሰጠውክን
ፋዘር ተቆጥቷል መልስ ድንግሌን
ፋዘርሽ ቢቆጡ ቢፈርጡ እንደንቧይ
የፈሰሰ ውሃ ይታፈሳል ወይ
የፈሰሰ ውሃ ከታፈሰላቸው
አባትሽ ለናትሽ ይመልሱላቸው
እንኳን ያንቺ ድንግል የትናትናው
ያባይ ድልድል ፈርሷል ጣልያን የሰራው......... :D :D
ዲጎኔ wrote:ሰላም/አሻማ
ወገን ቦቹ ድሮ ለአዲስ አመት ይቀርቡ የነበሩ ዜማዎችን አስታወስከኝ:-
አስኮበለልኩዋት ያችን ልጅ
አባትዋ ከሰው ታሰርኩ እንጂ
እኔም ወድጄ እሷም ወድዳ
ብቻየን አየሁ የቁም ፍዳ
የሻማ እያሉ መንጋዱራ
በቃሪያ ጥፊ ፊቴ በራ
በከያኒ ጌጡ አየለ
አውሮፕላን መጣ እየገሰገሰ
በዘፈን አንደኛ ጥላሁን ገሰሰ
ከከያኒ ጥላሁን ዜማና ግጥሞች ግብረገብ ያለው እነሆ:-
የእውነትን መንገድ ተሳስቼ
ተቀጣሁ በውሸት ተመርቼ
እውነት ማሪኝ ብያለሁ
ይቅርታ እጠይቃለሁ
በሀሰት ለለወጧት እውነትን ባፋቸው
የቁምነገር አምላክ ይቅር ይበላቸው
የትግልና የከሴ/ከርቼሌ ጉዋዳችን ከያኒ ቶማስ አበበ እንዲህ ብሎ ነበር:-
አበባ ምንጣፉ የእኔም ድሪቶዬ
የገንዘቡ ካዝና የእኔም ስልቻዬ
እበላው እጠጣው እቀምሰው የለለኝ
ከርታታው ምስኪኑ ጭቁኑ ቶማስ ነኝ
ክቡራን wrote:ሀማል መራራ:- ለማስተካከል ያህል ነው ግጥም ብለህ የጫርከውን ..ነገር....
ሰለሞን ጠቢቡ የሳባ አማላይ..
ታምራት ጠቢብ ነው ባዮችን ቢያይ..
ነው የሚባለው ብታይ...አይባልም:: አንተ የጾታ ዲሲኦሬንትሽን ስላለብህ ሰለሞንም አለበት ማለት አይደለም:: ማን መሆንህን ለማሳየት ያህል ብቻ ነው:: ሰላሙን::በልዕልት መራራ ስም የገባው ሀማል wrote:ሰለሞን ጠቢቡ የ ሳባ አማላይ:
ታምራት ጠቢብ ነው ባዮችን ብታይ:
የጥበብን ሚስጥር ምጡቅነቷን:
ላለማወቃቸው ሰም እና ወርቋን:
ታዝላቸው ነበር ""ጥበብ"" የሸማኔውን:: :lol: :lol: :lol:
ተጻፈ በ ልእልት መራራ:: መታሰቢያነቷ ለ ሳምራውው33 ትሁንልኝ:: :lol: :lol: ዱላነቷ ደግሞ ለ ካርቦንዬ :lol: :lol: :lol:ክቡራን wrote:ጥበብ እኮ ታምራት ገለታንም ጠርታለች:: ዚቁ ያለው ግን ጥሪውን በመልካም ተግባር ላይ ማዋሉ ላይ ነው:: ""ያልቦካ ጸሎት ከመከራ አያድንም "" ዲሞጥሮስ የሚባለው አስተማሪዬ እኮ ነው::
እነሆ ጠቢባን ሆይ ተጠበቡ... ያላወቁቹ ደሞ እወቁ ወይም ደሞ ጠበብ መስሏቹ የዋጣችሁትን ቴትራ ሳይክሊን አስታውኩት :::: :D
መተሬ= ውርስ ትርጉም= ስናይፕር ተኴሽ :D
http://www.youtube.com/watch?v=t4iGx1z5gls
ቦቹ wrote:ዲጎኔ wrote:ሰላም/አሻማ
ወገን ቦቹ ድሮ ለአዲስ አመት ይቀርቡ የነበሩ ዜማዎችን አስታወስከኝ:-
አስኮበለልኩዋት ያችን ልጅ
አባትዋ ከሰው ታሰርኩ እንጂ
እኔም ወድጄ እሷም ወድዳ
ብቻየን አየሁ የቁም ፍዳ
የሻማ እያሉ መንጋዱራ
በቃሪያ ጥፊ ፊቴ በራ
በከያኒ ጌጡ አየለ
አውሮፕላን መጣ እየገሰገሰ
በዘፈን አንደኛ ጥላሁን ገሰሰ
ከከያኒ ጥላሁን ዜማና ግጥሞች ግብረገብ ያለው እነሆ:-
የእውነትን መንገድ ተሳስቼ
ተቀጣሁ በውሸት ተመርቼ
እውነት ማሪኝ ብያለሁ
ይቅርታ እጠይቃለሁ
በሀሰት ለለወጧት እውነትን ባፋቸው
የቁምነገር አምላክ ይቅር ይበላቸው
የትግልና የከሴ/ከርቼሌ ጉዋዳችን ከያኒ ቶማስ አበበ እንዲህ ብሎ ነበር:-
አበባ ምንጣፉ የእኔም ድሪቶዬ
የገንዘቡ ካዝና የእኔም ስልቻዬ
እበላው እጠጣው እቀምሰው የለለኝ
ከርታታው ምስኪኑ ጭቁኑ ቶማስ ነኝ
ሰላም ዲጎኔ ዋርካን በግጥም ድባብ መተሀታል ግን ደስ ይላል:: ልብን ይመስጣሉ ግጥሞችህ ጭቁኑ ቶማስ ደግሞ ያሳዝናል ይቺ መከረኛ አገር መቼም ስንቱ ስንት ነገር አይቶባታል:: ለማንኛውም እኔ የግጥም የማንበብ ፍቅር እንጂ የመጻፍ ችሎታው የለኝምና ከተጻፉት መካከል አንደኛውን ለትዝታ መዝዤ ልጋብዝህ..........እንሆ በረከት
ሃ ገ ሬ
{ሰአሊና ገጣሚ ገብረ ክርስቶስ ደስታ}
አገሬ ውበት ነው፣
ለምለምና ነፋስ የሚጫወትበት፣
ፀሃይ የሞላበት፣ ቀለም የሞላበት።
አገሬ ቆላ ነው፣ ደጋ ወይና ደጋ፣
እዚያ ብርሃን አለ ሌሊቱ እስኪነጋ።
አገሬ ተራራ ሸለቆ ረባዳ፣
አገሬ ጅረት ነው ገደልና ሜዳ፣
ውበት ነው በበጋ ፀሃይ አትፋጅም፣
ክረምቱም አይበርድም፣
አይበርድም፣ አይበርድም።
አገሬ ጫካ ነው፣
እንሰሳት አራዊት የሚፈነጩበት፣
በወጥመድ ሳይገቡ ሳይነካቸው ጠላት።
እዚያ አለ ነፃነት፣
በሃገር መመካት፣
በተወላጅነት፣
በባለቤትነት፣
እዚያ አለ ነፃነት።
አገሬ ሃብት ነው፤
ጎመኑ ስብ ጮማ፣ ቆሎ ክትፎ ስጋ፣
ድርቆሹ ፍትፍት ነው፣ ቃሪያው ሙክት ሠንጋ፣
ጠጁ ነው ወለላ፣
ከኮኛክ ያስንቃል የመንደሩ ጠላ።
እህሉ ጣእም አለው እንጀራው ያጠግባል፣
ከቢራ ከሻምፓኝ ውሃው ይጣፍጣል፣
በዓሉ ይደምቃል፣
ሙዚቃው ያረካል፣
ጭፈራው ዘፈኑ ችግርን ያስረሳል።
እዚያ ዘመድ አለ፣
ሁሉም የናት ልጅ ነው፣
ሁሉም ያባት ልጅ ነው፣
ጠላትም አንዳንዴ ይመጣል መቃብር፣
ባለጋራም ቸር ነው “ያገር ልጅ ሲቸገር” ፤
ገነት ነው አገሬ።
ምነው ምን ሲደረግ ?
ምነው ለምን እንዴት ?
ዘራፊ ቀማኛ ምቀኛ ወንበዴ፣
ጥርኝ አፈር በጁ ስንዝር ወሰን አልፎ፣
የተቀደሰውን ያፍሪቃ ላይ ደሴት፣
ባያገኝ ለማርከስ ጠላት ይመኝ እንዴት።
እምቢኝ አሻፈረኝ፣
አሻፈረኝ እምቢ፣
መቅደስ ነው አገሬ፣
አድባር ነው አገሬ፣
እናትና አባት ድኸው ያደጉበት፣
ካያት ከቅደም አያት የተረካከቡት፣
አፈር የፈጩበት፣
ጥርስ የነቀሉበት።
አገሬ ዓርማ ነው፣ የነጻነት ዋንጫ፣
በቀይ የተጌጠ ባረንጓዴ ቢጫ።
እሾህ ነው አገሬ፣
በጀግናው ልጅ አጥንት የተከሰከሰ፣
ጠላት ያሳፈረ አጥቂን የመለሰ።
አገሬ ታቦት ነው ፣ መቅደስ የሃይማኖት፣
ዘመን የፈተነው በጠበል በጸሎት።
ለምለም ነው አገሬ፣
ውበት ነው አገሬ፣
ብሞት እሄዳለሁ ከመሬት ብገባ፣
እዚያ ነው አፈሩ፣ የማማ ያባባ።
ስሳብ እሔዳለሁ ቢሰበርም እግሬ፣
አለብኝ ቀጠሮ ከትውልድ አገሬ።
አለብኝ ቀጠሮ
ከትውልድ አገሬ፣
ካሳደገኝ ጓሮ።
ምክክር wrote:ሀገር
ክብሬ መመኪያዬ የቆዳዬ ቀለም:
መልኬ መለያዬ የተናኘ በደም::
ኢትዮጵያ ሀገሬ ሥሜ መጠሪያዬ:
ድጋፍ አለኝታዬ:
ምርኩዝ ከዘራዬ::
ልዩ ምልክቴ:
የኔ ማንነቴ:
እትብት ውልደቴ
ልጅነት ልደቴ:
ዞሮ መግቢያ ቤቴ::
ባዕድ አገር ሁኜ
በዕምባ ከማምባራቅ:
ጥሪኝ ወደ ምስራቅ:
እኔም እንደ ጸሐይ
ፏ ብዬ ልፈንጥቅ::
የስሜ መጠሪያ:
ዋሴ ነሽ ኢትዮጵያ::
ለሀገር ናፋቂዎች...ለሀገር ወዳዶች::
Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ
Users browsing this forum: No registered users and 3 guests