የዛቲ ግጥሞች

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ዛቲ » Mon Mar 24, 2014 7:03 pm

በፍቅር ያሰረች ጠፍራ በበርቱ
ቃሌን የረሳችው ያደረገች ከንቱ
የተባባልነውን ያልቆጠረች ከቁብ
ከሷ ጋር ቁጭ ብዬ አይኖቿ የሚጋልብ
ታግሼ ታግሼ በዛሬው ቀን በቃኝ
ቃል ተበልቶ ከርሟል እኔ መች አወቅሁኝ
እመነኝ እመነኝ እመነኝ እያለች
ከጓሮዬ ገብታ ስትቀጥፍ ኖራለች

****************************************
አንት ጨለማ
ለብሰህ ነበር ግርማ ግርማማ እንደ ካባ
መሸሸጊያ ባትሆን ለቀማኛ ሌባ
ቀንን ያደፈጠ ተሸሽጎ ከቤት
ጌታ እንዳየ ውሻ አንተ ስትመጣለት
ይወጣል በድፍረት እከዩን ሊሰራ
ጨለማ ካንተ ጋር ይፈጥርና ጎራ

***********************************
ማን ነን

ከጊዜው ተጉዘን ከዘመን ዘምነን
ከስልጣኔው ጋር እኩል ተረማምደን
ከዛሬ ተዋውቀን የትላንቱን ረስተን
የታሪክን መፅሃፍ ጥርቅም አርገን ዘግተን
ቋንቋችንን ትተን ከነሱ ቀይጠን
ስነምግባራችን ያበሻነት ወጉን
አይኑን የቀለሰ እፍርፍር ያለውን
ከላያችን ገፈን ማንነታችንን
ማናችሁ ብንባል ማን ነን እንላለን

***********************

ባዳ

ውጥር ልጥጥ ቢል ቆዳው እንዲያ ተነፍቶ
ፊቱ ቢያብለጨልጭ ወዘናውን ተፍቶ
ያማረበት ዛሬ ወገን የኮራበት
ነገን ቅጭጭ ሲል ምንምን ብሎ ክስት
ይባላል ምን ነካው ምን አገኘው ፍዳ
ታማኝ ስላይደለ ይህ ሰውነት ባዳ

**************
ስትስቂ ስቄ ስታዝኚ አዝኛለው
ትክዝ ፍዝዝ ስትዪ እኔም ልክ እንዳንቺው
ስታኮርፊ ፊቴን ከሰል እየቀባው
እኔነቴን ትቼ አንቺን የምመስለው
ራስሽን ስትወጂ እንድትወጂኝ ብዬ ነው
ዛቲ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 13
Joined: Thu Oct 03, 2013 12:59 pm

Previous

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 8 guests