የጥበብ እልፍኝ::

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ሙዝ1 » Tue Dec 17, 2013 12:28 pm

እስኪ እኔም ያለኝን ልወርዉር ... በጣም የምወዳት የግሽ ደቤን ግጥም ....

ለምን ሞተ ቢሉ

ለምን ሞተ ቢሉ
ንገሩ ለሁሉ
ሳትደብቁ ከቶ
"ከዘመን ተኳርፎ
ከዘመን ተጣልቶ"

1968 ላይ ጽፏት በ1992 ላይ በታተመችዉ ለራስ የተጻፈ ደብዳቤ (የብርሀን ፍቅር ቅጽ 2)::

ይህ ሰዉ በ1968 ላይ ከዘመን ጋር መጣላቱ .... ከዘመኑ ጋ መኳረፉ ለምን ይሆን? የያኔዉ እንቅስቃሴዉ ትዉልድ የሚሻገር አሉታዊ ጫናዉ ታይቶት ይሆን? ለራሱ ለትዉልዱ ብቻ ሳይሆን ለሀገርና ለቀጣዩ ትዉልድ ያመጣዉ አንካሳ እድል ተገልጦለት ይሆን?
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Postby ቦቹ » Tue Dec 17, 2013 5:08 pm

ሰላም ሙዝ
"ከታች ጠብቄሽ ነበረ" የተሰኘችዋ ግጥም እኔም በጣም የምወዳትና በቃሌ ሁሉ የምችላት ግጥም ነች:: የደቤ ግጥም የሆነ ሀይል አለው:: ስላካፈልከን ስንኝ እያመሰገንኩኝ የደቤ ስም ከተነሳ ላይቀር ከደቤ ስራዎች ላቋድሳችሁ::

ይቅርታ ለይቅርታ

ኅሊናዬ ያንጎራጉር ዐይን እንባ ያውርድ
በድያለሁና ጓደኛ ዘመድ::
እንደፅኑ ቋጥኝ ጎርፍ እንዳይገፋው
ግጭትን ለመናቅ ፍቅር አቅም አለው::

ግን ዶፉን እንደናቀ..
ለጣይ ለሙቀቱ እንዳልተጨነቀ..
እንደግሽር ቋጥኝ በቀን ማዕበል
ቀን ባመጣው ሰበብ ፍቅርም ይወድቃል::

ወዳጄ አትንፈገው ልብህን ብርሀን
ያስተውል መተከዝ ማልቀስ ማዘኔን::
ራሴን ገፋሁት ጠላሁህ አሰኘኝ
ከእኔው ለመታረቅ አንትን አስፈለገኝ::
ቅር መሰኘቴ በገዛ ፍጥረቴ
ሲዖል መገንባት ነው በገነቱ ቤቴ
ብዬ ለይቅርታህ ምኔም መታከቴ::

'በሠፈሩት ቁና....' እንዳይሆን ነገሩ
ይሰማህ ወንድሜ ያሣቤ ምስጢሩ
አቤት ባይ ሲመጣ
ይቅር ላለማለት ጆሮህን እንዳትሰጥ
በርህን ስትዘጋ ጥሪው ውጪ ሲቀልጥ
አቤት ባይ ስትሆን ድምጥህ እንዳይቋረጥ::

1968 ደበበ ሠይፉ
ያ ተፈሪ - በንቲ!
ጀበሲ ኦፍኤጊ!
ኢትዮጵያን ነመገንቲ!
ተፈሪ በንቲ!


ኢጆሌ! ወረ አድአ
ቦቹ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 357
Joined: Fri Dec 31, 2004 1:26 am

Postby ቦቹ » Tue Dec 17, 2013 9:26 pm

ጥሬ ጨው

መስለውኝ ነበረ ፡
የበቁ የነቁ
ያወቁ የረቀቁ
የሰው ፍጡሮች ፡
ለካ እነሱ ናቸው ፡
ጥሬ ጨው..ጥሬ ጨው
ጥሬ ጨዋዎች ፡
መፈጨት-መሰለቅ- መደለዝ-መወቀጥ-
መታሸት-መቀየጥ
ገና እሚቀራቸው ፡
“ እኔ የለሁበትም!” ዘወትር ቋንቋቸው ።


ደበበ ሰይፉ , የብርሃን ፍቅር
1971 ዓ.ም
ያ ተፈሪ - በንቲ!
ጀበሲ ኦፍኤጊ!
ኢትዮጵያን ነመገንቲ!
ተፈሪ በንቲ!


ኢጆሌ! ወረ አድአ
ቦቹ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 357
Joined: Fri Dec 31, 2004 1:26 am

Postby ቦቹ » Tue Dec 17, 2013 9:35 pm

መሰላል

መሰላል ለመውጣት
አለው ትልቅ ብልሀት፡፡
የላዩን ጨብጦ፤
የታቹን ረግጦ፣
ወደላይ መመልከት
እጆችን ዘርግቶ በሀይል መንጠራራት፡፡
ጨብጦ መጎተት የላዩን፣
ላይ ታች እንዲሆን፡፡አንድ በአንድ እየረገጡ
መሰላል የወጡ፣
ብልሆች የማይጣደፉ
ሞልተዋል በያፋፉ፡፡
ዘርግተው የጨበጡትን መርገጥ
የመውጣት ሕግ ነው የማይለወጥ፡፡
ሲወርዱ ግን ያስፈራል
የረገጡትን ያስጨብጣል፡፡

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም፣ እንጉርጉሮ፣ 1967)
ያ ተፈሪ - በንቲ!
ጀበሲ ኦፍኤጊ!
ኢትዮጵያን ነመገንቲ!
ተፈሪ በንቲ!


ኢጆሌ! ወረ አድአ
ቦቹ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 357
Joined: Fri Dec 31, 2004 1:26 am

Postby ቦቹ » Tue Dec 17, 2013 9:41 pm

አክሱምን አቃጥሉት!
==================

በስዉር-በስዉር ሳታወጡ ይፋ
አክሱምን አቃጥሉት ላሊበላም ይጥፋ!
ሁሉም ቢተባበር የሚያቅት አ’ደለም
ጢያና ጀጎልን ባንድ ላይ ለማዉደም
መስጅድ፣ ቅርሳ ቅርሱ፣ ፍልፍል ቤተ-መቅደስ
በዘዴ-በዘዴ በየተራ ይፍረስ
የጥበብ መጸሐፍት ጥንታዊ ብራና
በእሳት ይቀጣጠል ጋዝ ይርከፍከፍና!!
የአያቶቹ ጥበብ ደብዛዉ የጠፋበት
ለምን ይኸ ትዉልድ ወቀሳ ይብዛበት?
አክሱም፣ ፋሲል ግምብን ማቃጠል ነዉ ጥሩ
በዘመናችን ላይ እንዳይመሰክሩ!!

ሰለሞን ሞገስ::
ያ ተፈሪ - በንቲ!
ጀበሲ ኦፍኤጊ!
ኢትዮጵያን ነመገንቲ!
ተፈሪ በንቲ!


ኢጆሌ! ወረ አድአ
ቦቹ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 357
Joined: Fri Dec 31, 2004 1:26 am

Postby ቦቹ » Tue Dec 17, 2013 10:04 pm

ይህ የናንተ ዘመን፣
ለካስ ከስሮ ኖሯል- የዘመን መናኛ፣
ያጠናፈረው ነው - የመታውመጋኛ፣
የደገመው ዳፍንት፣
ከፍ ብሎ አጋሰስ- ዝቅ ብሎጌኛ፣
(ዮሃንስ አድማሱ)
ያ ተፈሪ - በንቲ!
ጀበሲ ኦፍኤጊ!
ኢትዮጵያን ነመገንቲ!
ተፈሪ በንቲ!


ኢጆሌ! ወረ አድአ
ቦቹ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 357
Joined: Fri Dec 31, 2004 1:26 am

Postby ቦቹ » Tue Dec 17, 2013 10:12 pm

ዝናቡ ዘነበ - ደጁ ረሰረሰ፣
ቤት ያላችሁ ግቡ - የኛማ ፈረሰ፣
(የአማራ አርሶአደሮች)
ያ ተፈሪ - በንቲ!
ጀበሲ ኦፍኤጊ!
ኢትዮጵያን ነመገንቲ!
ተፈሪ በንቲ!


ኢጆሌ! ወረ አድአ
ቦቹ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 357
Joined: Fri Dec 31, 2004 1:26 am

Postby ቦቹ » Tue Dec 17, 2013 10:25 pm

በዚህ ሙት ሕዝብ፣ በድክመቱ ብትልቁ፥ በፈተናው ብትበልጡ፣
በብሶቱ ብትፈይዱ፣
በመክሊቱ ብትነግዱ…
ይህ ፍጹም ባድማ፣ ይህ ፍጹም ድቅድቅ ጨለማ
እሚበራ እንዳይመስላችሁ፣ በናንት የይስሙላ ቁራጭ ሻማ።
(ደበበ ሰይፉ)
ያ ተፈሪ - በንቲ!
ጀበሲ ኦፍኤጊ!
ኢትዮጵያን ነመገንቲ!
ተፈሪ በንቲ!


ኢጆሌ! ወረ አድአ
ቦቹ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 357
Joined: Fri Dec 31, 2004 1:26 am

Postby ቦቹ » Tue Dec 17, 2013 10:42 pm

በክርስቶስ ፈንታ - ፈልጉ ክርታስ፣
የምንለጥፍበት - የጊዜውን ነፍስ፣
በስላሴ ፈንታ - ፈልጉ ሰሌዳ፣
የምንደጉስበት - የጊዜውን ፍዳ፣
(ዮሃንስ አድማሱ)
ያ ተፈሪ - በንቲ!
ጀበሲ ኦፍኤጊ!
ኢትዮጵያን ነመገንቲ!
ተፈሪ በንቲ!


ኢጆሌ! ወረ አድአ
ቦቹ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 357
Joined: Fri Dec 31, 2004 1:26 am

Postby ቦቹ » Tue Dec 17, 2013 11:21 pm

ማንም በዕድሜው ብዛት አያስጠራም ስሙን
በጥቂቱም ዕድሜው ይሠራል ሐውልቱን፡፡
ታሪክ ሲያበላሸው ረጅሙም ያጥራል፣
ታሪክ ሲያሳምረው አጭሩም ይረዘማል፤
ብዙ ዘመን ቢኖር ዕድሜውም ቢበዛ፤
በሳቅ በጨዋታ ዋዛን በፈዛዛ፣
ሲለዋውጥ ኖሮ ሃሳቡን ሳይገዛ፣
እንዲሁ ይቀራል እንዲያው እንደዋዛ፡፡

(“ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ፤ አጭር የሕይወቱና የጽሑፉ ታሪክ” (2004)፤ ገጽ 191)
ያ ተፈሪ - በንቲ!
ጀበሲ ኦፍኤጊ!
ኢትዮጵያን ነመገንቲ!
ተፈሪ በንቲ!


ኢጆሌ! ወረ አድአ
ቦቹ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 357
Joined: Fri Dec 31, 2004 1:26 am

Postby varka911 » Wed Dec 18, 2013 9:43 pm

ወንድማችን ካብሮም
(በብህትውና ስሙ ባሻሽብሩ :lol: )
እኔ ነኝ ያለ ግብዳ የሬሳ ሳጥኑን ገዝቶ
በዘይት ወልውሎ ከፈኑን አሰናድቶ
ድንገት የሄድኩ እንደሆን ወደ መሌ አገር
አደራ ይቺ ኑዛዜ ከመቃብሬ እንዳትቀር
በማለት የከተበልንን ግጥማዊ ኑዛዜ
ይዤ ከች ብያለሁና ሳይለየን በጊዜ
አንብበን እንድረስለት ሳይገታን ትካዜ

ካርቦን ወንድማችን ቀጠለ
ቁጭት በውስጡ እየተንቀለቀለ ...

"ህይወቴን በሙሉ ዋርካ ላይ በሲባጎ ታስሬ
በቁሜ ስማቅቅ ስንገላታ ኖሬ
ስቃዬን ጨርሼ ይኸው ዛሬ ገና
እንቅልፌን አግኝቼ ማረፌ ነውና
የምትሄዱ በዚህ በመቃብር ቦታ
እንዳትቀሰቅሱኝ እባካችሁ እለፉ በርጋታ፡፡"

ይህን ቀድሞ የሰማ አንዱ ልማታዊ ወያላ
በቁጭት ይገስጸው ገባ ያን አመዳም አንቡላ

"የለም የለም አንተማ ሞተህ አትቀበርም
ለሬሳህ ማረፊያ ቅንጣት መሬት አትባክንም
መጪው ትውልድ ራዕይህን ይወርስ ዘንድ
አመድህ ቅርስ ይሆናል አካልህ ሲነድ

መሬቱም ይውላል ለልማት
... ይሰጣል ለህንድ
የወየንታ አጋርነትህ ይረጋገጣል
... የትም ብትሄድ"

:lol:

ወንድማችን ሙዝ1 ስለ ሞት ስትቀኝ ጊዜ እኔም ያለኝን ላካፍል ብዬ ነው :wink:

ሙዝ1 wrote:እስኪ እኔም ያለኝን ልወርዉር ... በጣም የምወዳት የግሽ ደቤን ግጥም ....

ለምን ሞተ ቢሉ

ለምን ሞተ ቢሉ
ንገሩ ለሁሉ
ሳትደብቁ ከቶ
"ከዘመን ተኳርፎ
ከዘመን ተጣልቶ"

1968 ላይ ጽፏት በ1992 ላይ በታተመችዉ ለራስ የተጻፈ ደብዳቤ (የብርሀን ፍቅር ቅጽ 2)::

ይህ ሰዉ በ1968 ላይ ከዘመን ጋር መጣላቱ .... ከዘመኑ ጋ መኳረፉ ለምን ይሆን? የያኔዉ እንቅስቃሴዉ ትዉልድ የሚሻገር አሉታዊ ጫናዉ ታይቶት ይሆን? ለራሱ ለትዉልዱ ብቻ ሳይሆን ለሀገርና ለቀጣዩ ትዉልድ ያመጣዉ አንካሳ እድል ተገልጦለት ይሆን?
Last edited by varka911 on Thu Dec 19, 2013 10:32 pm, edited 1 time in total.
Get your second chance On my First Aid!
varka911
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 101
Joined: Tue Oct 22, 2013 2:30 pm

Postby ዲጎኔ » Thu Dec 19, 2013 3:41 am

ሰላም ለወገኖች ለጥበብ ቤተኞች
ስነቃል መግለጫ የእልፍኙ ልጆች
ይህን ድንቅ ቤት ሲያሞቁ ወገኖች
ባተሌ ነበርኩኝ ካለሁበት ሰዎች
አሁን ግን መጣሁ ያለኝን ላካፍል
እግረመንገዴንም እርኩሱን ላቃጥል
ዋርካ ላይ ለዛ አጥቶ የሚንዘላዘል
በወገን ቫርካ የተገላጠ ባለጭንብል
ጋዜጠኛ ነኝ ባይ የወያኔ እኩይ ሽል
ቢሰማ ይበጀው ነበር የሚነገረውን
ጆሮዳባ ልበስ ብሎ ሀቅ የገፋውን
ለሆዱ ሲል ግፈኛ የሚያወድሰውን
ወገን ቦቹ በጥበብህ እልፍኝ
ይህው መጣሁ በግጥሜ ስንኝ
ልቀላቀል እኔን ከሚመስሉኝ
ልፋለም በብእር ሁሉ ይስማኝ
ግጥም ዋና ግቡ እንዳይስትብኝ
ግፈኛ ጀሌውን መነረት አለብኝ
ለዛሬ ግን እዚህ ላይ ይብቃኝ
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby ክቡራን » Thu Dec 19, 2013 5:12 am

አይኑን በጨው ና ባቼቶ ያጠበው ወንድማችን ዲጎኔ እኔን ከመሚስሉኝ ጋር ልቀላቀል ብሎ ይሄን ከዚህ በታች ያለውን የአሻሮ- ቡና ቀላቀለበት:: :lol:
ወገን ቦቹ በጥበብህ እልፍኝ
ይህው መጣሁ በግጥሜ ስንኝ
ልቀላቀል እኔን ከሚመስሉኝ ....

ኦሮግ ኦሮግ ኦሮግ....እንዼ በቃ እፍረትም ጠፋ ማለት ነው..?? ሀያት ጺላው እግዚአብሄር የጅህን ይስጥህ....እንዲህ ሞራል እየሰጠህ አፍህን በጅህ ይዘህ እየሳቅ ወንድማችንን እሳት ውስጥ ትማግደዋለህ:: የግጥም እሳት ከሰማይ ወርዳ ትብላህ እሺ!! :lol: ጉድ ጉድ ጉድ!!!!! ከነ ዮሀንስ አድማሱ ና ከነ ዮፍታሄ ንጉሴ ጋር ከነ ደበበ ሰይፉ ጋር ...ልቀላቀል እኔን ከሚመስሉኝ ጋር ተባለልኝ... :lol: :lol: እሪ ብሎ በጩሀት ዋርካን መልቀቅ ዘንድሮ ነው:: :D ""ዳሩ ዳኛ የለም "" አለ በዛብህ እኮ ነው!!
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7972
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ቦቹ » Thu Dec 19, 2013 8:50 pm

ዲጎኔ wrote:ሰላም ለወገኖች ለጥበብ ቤተኞች
ስነቃል መግለጫ የእልፍኙ ልጆች
ይህን ድንቅ ቤት ሲያሞቁ ወገኖች
ባተሌ ነበርኩኝ ካለሁበት ሰዎች
አሁን ግን መጣሁ ያለኝን ላካፍል
እግረመንገዴንም እርኩሱን ላቃጥል
ዋርካ ላይ ለዛ አጥቶ የሚንዘላዘል
በወገን ቫርካ የተገላጠ ባለጭንብል
ጋዜጠኛ ነኝ ባይ የወያኔ እኩይ ሽል
ቢሰማ ይበጀው ነበር የሚነገረውን
ጆሮዳባ ልበስ ብሎ ሀቅ የገፋውን
ለሆዱ ሲል ግፈኛ የሚያወድሰውን
ወገን ቦቹ በጥበብህ እልፍኝ
ይህው መጣሁ በግጥሜ ስንኝ
ልቀላቀል እኔን ከሚመስሉኝ
ልፋለም በብእር ሁሉ ይስማኝ
ግጥም ዋና ግቡ እንዳይስትብኝ
ግፈኛ ጀሌውን መነረት አለብኝ
ለዛሬ ግን እዚህ ላይ ይብቃኝ


እንኳን ደህና መጣህ ልበልህ በግጥሜ
የብእሩ አርበኛ ዲጎኔ ወንድሜ
ለየዋሁ ህዝቤ መብት ግድ የሚለኝ
ኢጆሌ ወረ አድአ እኔ ቦቹ ነኝ::
ያ ተፈሪ - በንቲ!
ጀበሲ ኦፍኤጊ!
ኢትዮጵያን ነመገንቲ!
ተፈሪ በንቲ!


ኢጆሌ! ወረ አድአ
ቦቹ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 357
Joined: Fri Dec 31, 2004 1:26 am

Postby varka911 » Thu Dec 19, 2013 10:54 pm

ወንድሜ ዲጎኔ ህብረ-ቅልቅል
የሰባ እንቁ ዘሮች ድቅል
እንቅልፍ አያውቅም እሱ ወያኔን ሳይፈነቅል
ዲሞክራሲን በፋንታው ከማማው ላይ ሳይሰቅል::
እንኳን መጣህልን ጋሼ
የራዕይ የዓላማ ሞክሼ
ገባርህ ልሳኑ ዳግም እንዲፈታ
ድንቅ ነው መገኘትህ ከዚህ ቦታ
ከጥበብ ቤተሰቦች ከተባረኩት በጌታ::
ዲጎኔ wrote:ሰላም ለወገኖች ለጥበብ ቤተኞች
ስነቃል መግለጫ የእልፍኙ ልጆች
ይህን ድንቅ ቤት ሲያሞቁ ወገኖች
ባተሌ ነበርኩኝ ካለሁበት ሰዎች
አሁን ግን መጣሁ ያለኝን ላካፍል
እግረመንገዴንም እርኩሱን ላቃጥል
ዋርካ ላይ ለዛ አጥቶ የሚንዘላዘል
በወገን ቫርካ የተገላጠ ባለጭንብል
ጋዜጠኛ ነኝ ባይ የወያኔ እኩይ ሽል
ቢሰማ ይበጀው ነበር የሚነገረውን
ጆሮዳባ ልበስ ብሎ ሀቅ የገፋውን
ለሆዱ ሲል ግፈኛ የሚያወድሰውን
ወገን ቦቹ በጥበብህ እልፍኝ
ይህው መጣሁ በግጥሜ ስንኝ
ልቀላቀል እኔን ከሚመስሉኝ
ልፋለም በብእር ሁሉ ይስማኝ
ግጥም ዋና ግቡ እንዳይስትብኝ
ግፈኛ ጀሌውን መነረት አለብኝ
ለዛሬ ግን እዚህ ላይ ይብቃኝ
Get your second chance On my First Aid!
varka911
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 101
Joined: Tue Oct 22, 2013 2:30 pm

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests