መጽሀፍ ግምገማ Book reviewየኢሀዲግ ቀይ ስክሪቢቶ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

መጽሀፍ ግምገማ Book reviewየኢሀዲግ ቀይ ስክሪቢቶ

Postby ዲጎኔ » Wed Jun 11, 2014 2:26 pm

ሰላም ዋርካዊያን
በህይወቴ ደስ የሚለኝ መጽሀፍ ግመገማ ሲሆን አያሌዎችን ገምግሜያለሁ የራሴንም አስገምግሜያለሁ-ከገምጋሚዎቼ አማረ ማሞ አረፋይኔ ሀጎስና ብርሀኑ ዘሪሁን ገንቢዎቼ ሲሆኑ ጎጂዎቼ አይጠሩ!
እዚህ የሚገመገም የኢህአዲግ ቀይ እስክሪቢቶ በርእዮት አለሙ ይሆናል::ማሳሰቢያ ለተራ አሉባልታ መልስ የለኝም በነጥቦቹ ላይ ግን እወያያለሁ::
ደራሲ -ርእዮት አለሙ
ገጽ ብዛት- 204
አሳታሚ -ርእዮት አለሙ
የህትመት ዘመን-ሐምሌ 2004
መጽሀፉ በአራት ክፍሎቹ የጦቢያን ታሪክና የትግሉን ተግዳሮትና የሴቶች ተሳትፎን በተአማኒ ማስረጃ ያትታል::
በመግቢያው ደራሲዋ ደቡብ ህዝቦችና አማራ እጮኛዋ ትግራይ ብሄር መሆኑ ፍንጭ ይሰጣል::
ደራሲዋ የዘመኑ ትውልድ ብትሆንም ያለፉ ዘመኖችን ታጋዮችና ጸሀፊዎች ከታላቁ መጽሀፍ ቅዱስ ጭምር በሚገባ አስቀምጣለች::ወያኔ ከዲሞክራሲ ጋር እንደማይተዋወቅ የሀገርውስጥና አለም አቀፍ ሪፖርት ቀርቧል::የህብረተሰቡ ግማሽ አካል የሆኑት ሴቶችን ለፖለቲካ ማድመቂያ እንጂ ተገቢው መብታቸው እንዳልተከበረም ጠቅሳለች::የመጽሀፉ የመጀመሪያ ክፍል የጦቢያ ድህነትና በወያኔ መባባሱ ቀርቧል::
ይቀጥላል
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby ክቡራን » Wed Jun 11, 2014 6:12 pm

ወይ ጥጋብ ይህን ጻፈ..::

በህይወቴ ደስ የሚለኝ መጽሀፍ ግመገማ ሲሆን አያሌዎችን ገምግሜያለሁ የራሴንም አስገምግሜያለሁ -ከገምጋሚዎቼ አማረ ማሞ አረፋይኔ ሀጎስና ብርሀኑ ዘሪሁን ገንቢዎቼ ሲሆኑ ጎጂዎቼ አይጠሩ !...

እረ በህግ አምላክ!! እረ በቀደሙ አባቶቻችን ቅዱሳን!! ይዥሀላሁ:: ያለምን ህግ ባትፈራ ሰውንም ባታከብርም በእጊዚአብሄር ስም ይዠሀላሁ....ስነ ስርአት ብትይዝ መልካም ይመስለኛል:: የርእዮትን መጽሀፍ አነባለሁ:: አነተ ግን ከነ አማረ ና ብርሀኑ ዘርይሁን አረፈ አይኔ ጋራ ሆኜ ገምጋሚ ነበርኩ የሚለውን ሀርግ ሳነብ ግን አጥወልውሎኝ ከወንበሬ ላይ ልወድቅ ነበር:: :D
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7972
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ዲጎኔ » Wed Jun 11, 2014 6:35 pm

ሰላም ለሁላችን
ወያንታ ክቡ አባባሌን ተረደተህ በተለመደ መሰናክልነትህ ከሆነ መልስ የለኝም::ራሴን ከፍ እንዳደረግሁ ቆጥረህ ጥጋብ ያልከኝ ታናሽ ነኝ::ጋሸ አማረ የማዘጋጀው ጋዜጣ አርትኦት በቀይ እያረመ ያስተማረኝን ነው ገምጋሚ ያልኩ እንጂ እኩል ተቀምጬ አደለም እኩል የተቀመጥን ፒያሳ ክራሲስ ቡና ጋብዞኝ ስናወጋ ነው::ጋሼ ብርሀኑ በተሸለምኩበት ጽሁፌ ከሌሎች ተወዳዳሪዎች ጋር ገምግሞ አሳልፎኛል::የድሮ ኩራዝ ሀላፊ የረሳሁት አሰፋው ዳምጤ አለ::አረፋይኔ ኩራዝ ሲያትምልኝ በሄራልድ ላይ ያለውና እርምት ሰጥቶ ለህትመት ስላበቃልኝ ነው::በል እቃ እቃ ተጫዋች አለ ቦቹ ከታቢው እደግ በርእዮት ስራ ግምገማ ሞክር::ት/ቤት ሳለሁ የትልልቆቹን ደራሲዎች የሪክዋረን purpose driven የዳን ብራውን Davinchi Code መጽሀፍት Book review ስናረግ የእነሱ እኩያ መሆን ሳይሆን የኮርሱ ግዴታ ነው ክቡሻ!
ዲጎኔ ሞረቴAlternative Journalism School Evanston IL
ከነክቡና ሴኩቱሬ ሀሬ ደደቢት ማሰልጠኛ ሩቅ ማዶ

ክቡራን wrote:ወይ ጥጋብ ይህን ጻፈ..::
በህይወቴ ደስ የሚለኝ መጽሀፍ ግመገማ ሲሆን አያሌዎችን ገምግሜያለሁ የራሴንም አስገምግሜያለሁ -ከገምጋሚዎቼ አማረ ማሞ አረፋይኔ ሀጎስና ብርሀኑ ዘሪሁን ገንቢዎቼ ሲሆኑ ጎጂዎቼ አይጠሩ !...

እረ በህግ አምላክ!! እረ በቀደሙ አባቶቻችን ቅዱሳን!! ይዥሀላሁ:: ያለምን ህግ ባትፈራ ሰውንም ባታከብርም በእጊዚአብሄር ስም ይዠሀላሁ....ስነ ስርአት ብትይዝ መልካም ይመስለኛል:: የርእዮትን መጽሀፍ አነባለሁ:: አነተ ግን ከነ አማረ ና ብርሀኑ ዘርይሁን አረፈ አይኔ ጋራ ሆኜ ገምጋሚ ነበርኩ የሚለውን ሀርግ ሳነብ ግን አጥወልውሎኝ ከወንበሬ ላይ ልወድቅ ነበር:: :D
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby ክቡራን » Wed Jun 11, 2014 10:52 pm

ጋሽ ብርሀኑ ዘርይሁን ገምግሞ ያሳለፈውን ጽሁፍ ስካን አድርገህ እዚህ ፖስት ልታደርገው ትችላለህ..??? እንድንማማርበት...!!!እውነተኛውን ስምህን ዋይት አውት ማድረግ ትችላለህ.... ችግር የለውም:: :D እኔ መቼም በብርሀኑ ዘርይሁን የተገመገመውን ጽሁፍ ከማየትና አምላኬን ከማመስገን የበለጠ ደስታ የማገኝ አይመስለኝም:: ጎሽ ጎሽ..!! የብርሀኑ ዘሪሁንን የግምገማ ውጤት ወንድማችን ዲጎኔ ሊያሳየን በዝግጅት ላይ መሆኑን ሳሳብ ልቤ ደስ አላት:: ሀሌሉያ:: :D
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7972
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ዲጎኔ » Thu Jun 12, 2014 3:25 pm

የኢሀዲግ እስክሪቢቶ ላይ በጎ አስተያየት ካሰፈሩት ውስጥ ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማሪያምና የአለም አቀፍ ጋዜጠኞች ፋውንዴሽን ዴሬክተር እሊዛ ሙኞዝ ይገኛሉ::በወያኔ እስር እንግልት ሳትበገር በሙያዋ የገፋችውን እንስት የሚከተሉ እልፍ እንስት እንደበቀሉ ባለፈው የጣይቱ ልጆች በሚል ሰለተሰለፉ ብቻ ወያኔ ያሰራቸው ማስረጃ ናቸው::
መጽሀፉ በክፍል 1 የዳሰሰው የጦቢያ ድህነት ከመሰረታዊ ፍላጎቶች በታች እጅግ የወረደው በአንድ አካባቢ በልደታ ክፍለከተማ የተደረገውን የናሙና ጥናት በማቅረብ ነው::
በዚሁ ትንተና የወያኔው መሪ በቀን ሶስት ጊዜ አበላለሁ ብሎ ፎግሮ ያባባሰው ድህነት በአማካይ አንድሰው የምግብ ፍጆታ ለቁርስ አንድ ዳቦ ያቺ ኮሳሳዋ ያም የማይገኝበት ጊዜ አለ ምሳ ግማሽ እንጀራ በቆሎ ራት እንዲሁ ግማሽ እንጀራ በሽሮ አንዳንዴ ደሞዝ መዳረሻ ላይ በቆሎ ብቻ ይታደራል!
ይህ አማካይ ሲሆን ከዚ ያነሰ ምን ሊሆን ነው?ሆድ አደር ጀሌዎቹ የሚቀናጡትን ጥናቱ አያካትትም! ምስኪን ሀገር!
ደራሲዋ በታሪክ የተሟላ ማስረጃ ስለምታቀርብ በአጼው ዘመን በ1924 ስለተመሰረተ ፓርላማ ብዙ አባላቱ በንጉሱ ይመረጡ ስለነበረው ጽፋለች::በ1948 መጠነኛ ለውጥ መደረጉን ጠቅሳ የህዝቡ የኑሮ ለማሻሻል ባይረዳም የኑሮ ደረጃው ሳይዘው ህዝቡ መምረጡን ታወሳለች::ተመራጮቹ ለመረጣቸው ህዝብ ኑሮ መሻሻል ተቆርቁዋሪ እንዳልነበሩ ተዘግቧል::ከ54 አመት በሁዋላ በ2002 የጦቢያ ምርጫ ቦርድ ያሳተመው ሀተታ ሊመረጥ የሚገባው ከ2000 ብር ያላነሰ ተንቀሳቃሽ ንብረት ወይም 1000 ብር የማይንቀሳቀስ ንብረት ያለው መሆን እንዳለበት ይገልጻል::በአጼ ዘመን የነበረው ደንብ ዝቅተኛ ኑሮ ያለው ስልጣኑን ለከፍተኛ ኑሮ ነዋሪ አስከብሮ ከ1934 ጀምሮ የህዝቦች አመጽ በትግራይ ባሌ ጎጃም ወሎና ሲዳማ መከሰቱ ተጠቅሷል::
ለንጽጽር ወያኔ አርሶ አደሩን ኢሀዲግን ካልመረጥክ እህል የለህም በሴፍቲነ አትታቀፍም የግብርና ግባቶች አታገኝም በሚል ዛቻ ተረጂዎች ያለፍላጎት ኢሀዲግን እንዲመርጡ መገደዳቸው አለማቀፍ ህብረተሰብ የሚሰጠው እርዳታ ለፖለቲካ መዋሉ ተብራርቷል::
'ለጮማው ጌታ የማይንበረከኩ ሰብእናዎች ጠፉ' ደራሲዋ በአዲስ ፕሬስ ጋዜጣ ነብዩ ሀይሉ ቅንብር የስነማህበረሰብ ሊቅ ሰለሞን ጉዲሳ ያሉት ሀቅ ቀርቧል:-
'ማንኛውም ሰው መሰረታዊ ፍላጎቱን ለማግኘት ሞራላዊ ድንጋጌ ሊጥስ ይችላል'/ህዝቡ እየተሰቃየ ለወያኔ ያጎበደዱ ኮንደሚኖ ናፋቂ ሞራልየለሽ ዳያስፖራዎችንም ይመለከታል/
ስለደራሲዋ ድንቅ ሰብእና ምሁራዊ ግምገማ ደግሞ እነሆ:-
http://ethiomedia.com/17file/6032.html
ይቀጥላል
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby ዲጎኔ » Mon Jun 16, 2014 7:42 pm

እምቢ ለምኞትና መደለያ
ደራሲዋና መሰሎቿ የወያኔ ማባበያን እምቢ ብለው ከህዝብ ጎን በመቆማቸው ለእስር ሲበቁ በወያኔ በገፍ የሚመለመሉ የፓርቲ አባላት ታሪክና ማንነት ትዘረዝራለች::
ጥቅምና ኮንደሚኖ ቤት እየለገሰ ወያኔ የአባላት ምልመላ ቢያስፋፋም ፓርቲውና ፖሊሱ አድሮ ጥጃነቱ በአምቦ የተማሪዎች ሰልፍ ላይ የወረዱት ይመሰክራል::

ወያኔ የብዙ አባላት ምልመላ በከፈተኛ ደረጃ የጀመረው ከ1997 ሽንፈቱ በሁዋላ ነበር::ለዚህ ምክንያቱን ደራሲዋ በዘሪሁን ተስፋየ በአዲስ ነገር ላይ የተዘረዘሩትን ነጥቦች አቅርባለች::በዚሁ መሰረት ወያኔ በመንግስት መስሪያ ቤት ያሉ ዜጎች በአብዮታዊ ዲሞክራሲ በማጥመቅ መመልመል እንዳለበት የተማማሉበት ቀርቧል::ሌላ ምክንያቶች ቢኖሩም ዋና የአባልነት ብዛት መጨመር ወያኔ የፈለገው በከተሞች አካባቢ ያጣውን ተቀባይነት ለመለወጥ የስራና የትምህርት እድል አባላት ለመሰብሰብ መሳሪያ ያደረገ ካለፉ ታሪኮች በማስላት ነው::ይህ የአባላት ጅምላ ምልመላ ሀገሪቱን ለውድቀት እንደዳረጋት ምሁራን ዘግበዋል::አምዴ አማረ ያዘጋጀው የወያኔ ዘመቻ ውድቀትን እንዲህ አስፍሮታል:-
ስህተትን ከታሪክ የማይማሩ ያንኑ ይደግሙታል የሚል ነው::
ይቀጥላል
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states


Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests

cron