«በ ል ጅ ነ ቴ !!» ምንጭ ፌስቡክ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

«በ ል ጅ ነ ቴ !!» ምንጭ ፌስቡክ

Postby መርከቡ » Thu Feb 02, 2017 1:49 am

በልጅነቴ፡-
ከብቶቻችን ዘመዶቻችን ይመስሉኝ
ነበር…
→አያቴ የናትና አባቴ እናት ትመስለኝ ነበር…
→ማደግን የምመኘው ሚስት አግብቼ
እንደልቤ ወጡ የበዛበት እንጀራ ለመብላት ነበር…
→ሱቅ እደሩ ተብለን ስንላክ ስኳር እንኳን አንቀምስም ነበር…
ወንድማችን ጧት መጥቶ የሚቆጥረው ይመስለናል… →
:
በቲቪ የማያቸው ህፃናት በሙሉ
አባታቸው አባባ ተስፋዬ እየመሰለኝ እቀና ነበር…
→አባትና እናቴ ወንድምና እህት
ይመስሉኝ ነበር…… አድጌ ዝምድና
እንኳን እንደሌላቸው ሳውቅ ገረመኝ… :
→እፅዋት ይወለዳሉ፣ ያድጋሉ፣ ይሞታሉ ሲባል ብዙ ነገር በጭንቅላቴ ይመላለስ ነበር… ይመገባሉ ሲባልማ እንዴት ሽንት ቤት እንደሚወጡ እገምት ነበር…
:
→ሽቶ ሲሸተኝ "ሸርሙጣ ሸርሙጣ
ሸተተኝ" የምል ጨዋ ነበርኩ…
:
→ቤታችን የተሰቀለች የቡራቅ ስእል አኔን ብቻ እያየች መሆኑን ለማረጋገጥ ከግድግዳ ግድግዳ አየተመላለስኩ አያት ነበር…ታዲያ አይኗ እኔ ላይ ነው…
:
→ኳስ ተጫዋቾች አንድ ኳስ ሲያባርሩና ሲራገጡ "ምናለበት ለሁሎችም አንድ አንድ ኳስ ቢሰጧቸው?!" ብዬ እመኝ
ነበር…… ሁሌም የምደግፈው የሚሸነፈውን ቡድን ነበር…
:
→አባቴ የሆነ የሚበላ ነገር የሚያመጣልኝ በፌስታል ስለነበረ አሁን ድረስ ፌስታል ሲንኮሻኮሽ ሆዴ ይጮሃል… አባቴም ትዝ ይለኛል…
:
→ኢቲቪ የሙሉአለምና የሰራዊት
ይመስለኝ ነበር… እነሱም ባልና ሚስት ነበር የሚመስሉኝ… አይደሉም ግን ?
→በምኖርባት ከተማ ላይ ያለው የመኪና መናኸሪያ አዲሳባ ይመስለኝ ነበር…
→ፈረንጆች የሚኖሩት ሰማይ ላይ ይመስለኝ ነበር…
:
አባቴን ሁሉም ሰው የሚፈራው
ይመስለኝ ነበር…
:
→ጋሪ ከነበቅሎው ልክ እንደመኪና
የፋብሪካ ውጤት ይመስለኝ ነበር…
:
→ሴቶች ከወንዶች የሚለዩት ፀጉር
በመሰራት ብቻ ይመስለኝ ነበር……
:
→መምህሮች እንደተራ ሰው ገበያ
ወጥተው አስቤዛ ሲሸምቱ ይገርመኝ ነበር…
:
→ለመጀመሪያ ጊዜ ፔፕሲ የጠጣሁበትን ቀን ከልደቴ ቀን እኩል አስታውሰዋለሁ…
:
→ብቻ ምን አለፋችሁ…………
እንደዛሬው ያ ሁሉ አልፎ ለማውራት
እንደምበቃ… ከናንተም ጋር
እንደምተዋወቅ አላውቅም ነበር……!!
ለምነህ ለምነህ ዳኛው ሲያደላብህ
ቅደደው ቅደደው አይልም ወይ ልብህ።
መርከቡ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 66
Joined: Sat Oct 11, 2003 7:41 am

Re: «በ ል ጅ ነ ቴ !!» ምንጭ ፌስቡክ

Postby እሰፋ ማሩ » Thu Feb 02, 2017 4:43 am

መርከቡ
ድንቅ ሰነቃል ነው፡፡ ለካ ፖለቲካ ብቻ ሳይሆን በኪነጥበብም ግሩም ዘጋቢ ነህ!
መርከቡ wrote:በልጅነቴ፡-
ከብቶቻችን ዘመዶቻችን ይመስሉኝ
ነበር…
→አያቴ የናትና አባቴ እናት ትመስለኝ ነበር…
→ማደግን የምመኘው ሚስት አግብቼ
እንደልቤ ወጡ የበዛበት እንጀራ ለመብላት ነበር…
→ሱቅ እደሩ ተብለን ስንላክ ስኳር እንኳን አንቀምስም ነበር…
ወንድማችን ጧት መጥቶ የሚቆጥረው ይመስለናል… →
:
በቲቪ የማያቸው ህፃናት በሙሉ
አባታቸው አባባ ተስፋዬ እየመሰለኝ እቀና ነበር…
→አባትና እናቴ ወንድምና እህት
ይመስሉኝ ነበር…… አድጌ ዝምድና
እንኳን እንደሌላቸው ሳውቅ ገረመኝ… :
→እፅዋት ይወለዳሉ፣ ያድጋሉ፣ ይሞታሉ ሲባል ብዙ ነገር በጭንቅላቴ ይመላለስ ነበር… ይመገባሉ ሲባልማ እንዴት ሽንት ቤት እንደሚወጡ እገምት ነበር…
:
→ሽቶ ሲሸተኝ "ሸርሙጣ ሸርሙጣ
ሸተተኝ" የምል ጨዋ ነበርኩ…
:
→ቤታችን የተሰቀለች የቡራቅ ስእል አኔን ብቻ እያየች መሆኑን ለማረጋገጥ ከግድግዳ ግድግዳ አየተመላለስኩ አያት ነበር…ታዲያ አይኗ እኔ ላይ ነው…
:
→ኳስ ተጫዋቾች አንድ ኳስ ሲያባርሩና ሲራገጡ "ምናለበት ለሁሎችም አንድ አንድ ኳስ ቢሰጧቸው?!" ብዬ እመኝ
ነበር…… ሁሌም የምደግፈው የሚሸነፈውን ቡድን ነበር…
:
→አባቴ የሆነ የሚበላ ነገር የሚያመጣልኝ በፌስታል ስለነበረ አሁን ድረስ ፌስታል ሲንኮሻኮሽ ሆዴ ይጮሃል… አባቴም ትዝ ይለኛል…
:
→ኢቲቪ የሙሉአለምና የሰራዊት
ይመስለኝ ነበር… እነሱም ባልና ሚስት ነበር የሚመስሉኝ… አይደሉም ግን ?
→በምኖርባት ከተማ ላይ ያለው የመኪና መናኸሪያ አዲሳባ ይመስለኝ ነበር…
→ፈረንጆች የሚኖሩት ሰማይ ላይ ይመስለኝ ነበር…
:
አባቴን ሁሉም ሰው የሚፈራው
ይመስለኝ ነበር…
:
→ጋሪ ከነበቅሎው ልክ እንደመኪና
የፋብሪካ ውጤት ይመስለኝ ነበር…
:
→ሴቶች ከወንዶች የሚለዩት ፀጉር
በመሰራት ብቻ ይመስለኝ ነበር……
:
→መምህሮች እንደተራ ሰው ገበያ
ወጥተው አስቤዛ ሲሸምቱ ይገርመኝ ነበር…
:
→ለመጀመሪያ ጊዜ ፔፕሲ የጠጣሁበትን ቀን ከልደቴ ቀን እኩል አስታውሰዋለሁ…
:
→ብቻ ምን አለፋችሁ…………
እንደዛሬው ያ ሁሉ አልፎ ለማውራት
እንደምበቃ… ከናንተም ጋር
እንደምተዋወቅ አላውቅም ነበር……!!
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1504
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests