አንጋፋው ጋዜጠኛና ደራሲ ነጋሽ ገብረማርያም አረፉ!!

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

አንጋፋው ጋዜጠኛና ደራሲ ነጋሽ ገብረማርያም አረፉ!!

Postby ዘርዐይ ደረስ » Fri Jul 21, 2017 3:25 am

አንጋፋውና ዝነኛው ጋዜጠኛን ደራሲ ነጋሽ ገብረማርያም ሐምሌ 10 ቀን 2009 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል::ቀብራቸውም ጉርድ ሾላ በሚገኘው በሳህሊተ ምሕረት ቤተክርስትያን ተፈጽሟል::ጋዜጠኝነትን በዩኒቨርሲቲ ደረጃ በመማር የመጀመርያው ኢትዮጵያዊ እንደሆኑ የሚነገርላቸው አቶ ነጋሽ በ1918ዓ.ም በአርሲ አርባጉጉ ልዩ ሥሙ ሚኔ በተባለ ቦታ ላይ ተወለዱ ከዚያም ገና በሕጻንነታቸው ከእናታቸው ጋር ወደ ሐረር የሄዱ ሲሆን ፊደል የቆጠሩትም እዚያው ነው::ብዙም ሳይቆዩ ወደ አዲስ አበባ በመሄዳቸው በተፈሪ መኮንን ት/ቤት የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ለመከታተል በቁ::በ1936 ከመምህራን ማሰልጠኛ ተመርቀዋል::በሥራ ዓለምም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣በአሜሪካ ቤተ መጻሕፍትን በትርጉም ሥራ አገልግለዋል::በዚህ ጊዜ ነበር በ1947 ዓ.ም ስኮላርሺፕ አግኝተው ወደ አሜሪካ የተጓዙት::በመጀመርያ በሞንታኖ ከዚያም በሰራክሊዩስ ዩኒቨርሲቲ ተምረው ወደ አገራቸው ተመልሰዋል::እንደተመለሱም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ዋና አዘጋጅነት፣የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ም/ሥራ አስኪያጅነት፣በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዋና ሥራ አስኪያጅነት አገልግለዋል::አቶ ነጋሽ የመጀመርያ ድርሰታቸው የሆነውን ‚ሴተኛ አዳሪ‘ የተሰኘውን መጽሐፍ እናኑ አጎናፍር በሚል የብዕር ሥም በ1956 ለማሳተም በቅተዋል::የድል አጥቢያ አርበኞች የሚባለውንና በፋሽስት ኢጣልያ ወረራ ላይ የተመረኮዘወን ቲያትርም የደረሱት እሳቸው ነበሩ::በተለይ ግን ከህዝብ ጋር ያስተዋውቃቸው በ1975 በብሔራዊ ቴያትር የታየውን የርሳቸው ድርሰት የሆነው ‚የአዛውንቶች ክበብ‘ የተሰኘው ቴያትር ነበር::አቶ ነጋሽ ባለትዳርና የ 2 ልጆች አባት ነበሩ::በነገራችን ላይ ወንድማቸው አሰፋ ገብረማርያም በህይወት አሉ?
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1096
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: አንጋፋው ጋዜጠኛና ደራሲ ነጋሽ ገብረማርያም አረፉ!!

Postby ጌታህ » Fri Jul 21, 2017 12:20 pm

May his soul rest በሰላም !!! ይማራቸው !!!

ጌታህ ከፒያሳ
ጌታህ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1209
Joined: Sat May 30, 2009 3:05 pm


Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: Bing [Bot] and 2 guests