የኢትዮጵያ ቱሪዝም 'አባት' አረፉ!!

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

የኢትዮጵያ ቱሪዝም 'አባት' አረፉ!!

Postby ዘርዐይ ደረስ » Wed Aug 09, 2017 9:50 pm

ቱሪዝምን በኢትዮጵያ ለማስፋፋት ግንባር ቀደም የነበሩት አቶ ሃብተሥላሴ ታፈሰ በዛሬው እለት ከዚህ አለም በሞት ተለዩ፡፡በነገራችን ላይ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የኢትዮጵያ ቱሪዝም መታወቂያ የነበረውን Thirteen Months of Sunshine የሚለውን ሎጎ ያስተዋወቁት እሳቸው ነበሩ፡፡
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1096
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: የኢትዮጵያ ቱሪዝም 'አባት' አረፉ!!

Postby ሾተል » Sun Sep 17, 2017 2:31 pm

ዘርዐይ ደረስ wrote:ቱሪዝምን በኢትዮጵያ ለማስፋፋት ግንባር ቀደም የነበሩት አቶ ሃብተሥላሴ ታፈሰ በዛሬው እለት ከዚህ አለም በሞት ተለዩ፡፡በነገራችን ላይ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የኢትዮጵያ ቱሪዝም መታወቂያ የነበረውን Thirteen Months of Sunshine የሚለውን ሎጎ ያስተዋወቁት እሳቸው ነበሩ፡፡

እናንተ ዘርአይ ደረስ…

እንኩዋን ለ አገራችን ለ 2010 አመተ ምህረት በሰላም አደረሳችሁ።እንዲሁም ለመላው የዋርካ ታዳሚዎችና ባልተቤቶች እስከነ መላው ቤተሰባችሁ አደረሳችሁ።እኛንም በሰላምና በጤና አደረሰን።አዲሱ አመት ለሁላችንም የሰላም ይሁንልን እንጂ ይሄ የሰሜን ኮርያው ውርጋጥ ሃይድሮጅን ቦንብ የኮምፒውተር ጌም መስሎት መጫኛውን ጠንቁሎት እሱም እስከ ምስኪኑ የሰሜን ኮርያ ህዝብ መቱን ደባይቶ የሱ ጦስ እኛንም አግኝቶን ሁላችነም ባንድ ላይ ተጠራርገን ካላለቅን ማለቴ ነው።ነገረ አለሙ አስጊ ቢሆንም ወደ አምላክ የተጠጋ ባይሆን ተወድያኛው አለም አቶም ቦንብ የለ ሃይድሮጂን የሚያሰጋ ስላልሆነ ያው ተስፋችነን በ ሃያሉ ጌታ አድርገን ንሰሃ ገብተን በንሰሃ ማጽጃ ታጥበን ጸድተን ተቀሽረን ከጠበቅን እንኩዋን አቶም ቦምብ ተተኩሶብን አይደለም የቦንቡ ቀላ ጫፍ ላይ አስረው ቢለቁን ስጋችነ እንጂ ድራሽ አባቱ የሚጠፋው ነፍሳችነ የዘላለም ህይወት ታገኛለችና አምላክ በጥበቡ ሁላችነንም ወደ እሱ ይመልሰን…

እናላችሁማ ወንድማችን ዘርአይ ያእቆብ ነፍሳቸውን ይማረውና ከላይ ስለነገርከን ታሪክ ሰሪ ከዚህ በፊት በራሳችን ንዝህላልነት ወይም ከ መረጃ እጥረት ይሆናልና ስለታሪክ ሰሪው ምንም ሰምተን የምናውቀው አንዳችም ነገር ስለሌለ እባክህን ስለኚህ ታላቅ ሰው ታሪክና ሰርተው ስላለፉት ነገር የምታውቀው ወይም ተከትቦ ያገኘሀው ነገር ካለ አካፍለንና ምንም ከሞት ባንመልሳቸውም ታላቅ ስራቸውን አውቀን ልጅ ስንወልድ ወይም ለጎረቤት ልጆችም ቢሆን ስራቸውን እናስተላልፍ ዘንድ ነውና በሉ እንግዲህ ያላችሁን ጣል ጣል አድርግልን።

መልካም ቀን ይሁንላችሁ

ሾተል ነን...ከ ኦስትርያ ቪየና ምድር
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9647
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria


Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 5 guests