ከወያኔ ባለስልጣን ጋር ቃለመጠይቅ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ከወያኔ ባለስልጣን ጋር ቃለመጠይቅ

Postby እሰፋ ማሩ » Sun Aug 13, 2017 2:54 am

ክቡር ሚኒስትር ስብሰባው እንዴት ነበር?
•ሄሎ ክቡር ሚኒስትር፡፡
•እንዴት ነህ?
•በጣም ደህና ነኝ፤ ሁሉም ሰላም ነው?
•ኧረ በጣም ሰላም ነው፡፡
•ስብሰባው እንዴት ነበር?
•የትኛው ስብሰባ?
•ከዩኒቨርሲቲ አስተማሪዎች ጋር የነበራችሁ፡፡
•በጣም አስደናቂ ነበር፡፡
•እ…
•አንተ አልነበርክም እንዴ?
•አዎን እኔ አንድ የጥናት ጽሑፍ አዘጋጅ ነበር፡፡
•የጥናት ጽሑፍ?
•አዎን ክቡር ሚኒስትር፡፡
•የጥናት ጽሑፍማ ቀረበ፡፡
•የት ክቡር ሚኒስትር?
•እኛ እኮ ከአስማተሪዎቹ ጋር የተወያየነው በጥናት ጽሑፍ ላይ ተመሥርተን ነው፡፡
•እ… ያ ሦስት ዓመት ያለፈበት፡፡
•ስማ ብቻ ውይይቱ በጣም ልማታዊ ነበር፡፡
•ማለት ክቡር ሚኒስትር?
•የአገሪቷን የትምህርት ጥራት እንዴት እንደሚሻሻል በሚገባ ነው የተወያየነው፡፡
•ከእናንተ ጋር ውይይት ምን ለውጥ ያመጣል ብለው ነው፡፡
•እንዴት ማለት?
•ያው አድሮ ቃሪያ ናችኋ፡፡
•ስማ አሁን ኢኮኖሚያችን እኮ ከግብርና ወጥቶ ወደ ኢንዱስትሪ ተሸጋግሯል፡፡
•ምን እያሉ ነው?
•በቃ ቃሪያ ምናምን የሚሉ ተረትና ምሳሌዎች ቀርተዋል፡፡
•አይ ክቡር ሚኒስትር ቀልደኛ ነዎት፡፡
•ለማንኛውም ስብሰባችን የተሳለጠ ነበር፡፡
•እኔ ግን የሰማሁት ሌላ ነበር፡፡
•ምን ሰማህ?
•በጣም እንደተዋረዳችሁ፡፡
•ማን ነው የነገረህ?
•ስብሰባው ውስጥ የነበሩ ጓደኞቼ፡፡
•ፀረ ልማት አስተማሪዎች ናቸው ማለት ነው?
•ኧረ በትክክል የሰሙትን ነው የነገሩኝ፡፡
•ይኼ የበሬ ወለደ ወሬ ነው፡፡
•ቅድም ኢኮኖሚያችን ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ ተሸጋግሯል ሲሉ አልነበረ እንዴ?
•በደንብ ተሸጋግሯል፡፡
•አይ በሬ ምናምን እያሉ ሲተርቱ ብዬ ነዋ፡፡
•እና የኢንዱስትሪ ፓርካችን ወለደ ወሬ ነው ልበልህ?
•ለነገሩ እንደዚያ ማለት ይችላሉ፡፡
•እንዴት ሆኖ?
•ያው በሬ እንደማይወልደው ሁሉ፣ የአገሪቷ ኢኮኖሚ ሁሉንም ተጠቃሚ እያደረገ አይደለም፡፡
•ቀልድ ግን አያምርብህም፡፡
•እሱስ እውነትዎትን ነው፤ ቀልዱ የሚያምረው በእናንተ ነው፡፡
•እ…
•ይኸው ሕዝቡ ላይ እየቀለዳችሁ አይደል እንዴ?
•ከዚህ በላይ ምን እናድርግ?
•ለመሆኑ ምን አደረጋችሁ?
•አዳምጡን አላችሁ ሰበሰብናችሁ፡፡
•ሕዝቡ እኮ ያለው ሰብስቡን ሳይሆን አዳምጡን ነው ያለው፡፡
•ምን ማለት ነው?
•የምትሰበስቡት የሕዝቡን ሐሳብ ለመስማት እንጂ የእናንተን ሐሳብ ለመጫን አይደለም፡፡
•ወይ ጣጣ፡፡
•ለማንኛውም እናንተ ትምህርት ቤት ነው መግባት ያለባችሁ፡፡
•በዚህ ዕድሜያችን ትምህርት ልንማር?
•ለነገሩ ብትማሩም ለውጥ አታመጡም፡፡
•ለምን?
•ስለማይገባችሁ!

[የክቡር ሚኒስትሩ የእህታቸው ልጅ ቢሯቸው መጣች]
•እንዴት ነህ ጋሼ?
•አንቺ በጣም አደግሽ፡፡
•ምን ታደርገዋለህ ጋሼ?
•የት ነው ያለሽው?
•እየተማርኩ ነው ጋሼ፡፡
•የት ነው የምትማሪው?
•ዩኒቨርሲቲ ነዋ፡፡
•የአገር ውስጥ ዩኒቨርሲቲ?
•አዎና ጋሼ፡፡
•የእኔ የመጀመሪያ ልጅ ጓደኛሽ እኮ ቻይና ነው የምትማረው፡፡
•ታዲያ እኔ ቻይና መማር የምችልበት አቅም የለኝም፡፡
•እኔ አስተምርሻለኋ፡፡
•እንዴት አድርገህ?
•ስንትና ስንት ስኮላርሽፕ አይደል እንዴ ለመንግሥት የሚመጣለት?
•እ…
•አየሽ ያቺ እናትሽ እኮ አፍራሽ ስለሆነች ነው ያራራቀችን፡፡
•በል እናቴን ለቀቅ አድርጋት፡፡
•ከእኔ ሥር ሥር ባትጠፋ ይኼኔ የት ደርሳችሁ ነበር፡፡
•ጋሼ አንተ የት ደረስክ?
•ይኸው በየቦታው አይደል እንዴ ሕንፃ የገነባሁት፡፡
•አይ መፍረሻው የደረሰ መሰለኝ፡፡
•ማን አባቱ ነው የሚያፈርሰው?
•መሠረቱ አሸዋ ነው ብዬ ነው፡፡
•ኧረ አለት ድንጋይ ላይ ነው የሠራሁት፡፡
•ጋሼ ሕዝብ ሲነሳብህ አሸዋ ላይ መገንባትህ ይገባሃል፡፡
•አንቺም እናትሽም አፍራሾች ናችሁ፡፡
•ለማንኛውም ከአስተማሪዎቻችን ጋር የነበራችሁ ስብሰባ እንዴት ነበር?
•እጅግ ልማታዊ ነበር፡፡
•እኔ ግን የሰማሁት የተገላቢጦሽ ነው፡፡
•ምን ሰማሽ?
•አስተማሪዎቹ አመፁባችሁ አሉ፡፡
•ምን?
•አንዳንድ ቦታ እንደ ሕዝቡ አናወራም ብለው በፀጥታ ተቃወሟችሁ አይደል?
•ሕዝቡ አውራ ሲባል አያወራም?
•አውራ ፓርቲ ብቻ በሚያወራበት መድረክ እንዴት ያውራ?
•ምን?
•አሁን ከተማሪው ጋርም መሰብሰባችሁ አይቀርም አይደል?
•ይመስለኛል፡፡
•እንግዲያው ከተማሪውም ከዚህ የባሰ ተቃውሞ ነው የሚጠብቃችሁ፡፡
•ለምን?
•ማውራት ብቻ አይጠቅምማ፡፡
•ታዲያ ምንድን ነው የሚጠቅመው?
•ማዳመጥ!

[ክፉኛ የተገመገሙ የክቡር ሚኒስትሩ ጓደኛ ሚኒስትር ደወሉላቸው]
•ሄሎ ክቡር ሚኒስትር፡፡
•እንዴት ነህ ወዳጄ?
•ምንም አልተረፍኩም ክቡር ሚኒስትር፡፡
•ምን ሆንክ?
•በቃ ከታተፉኝ፡፡
•ማለት?
•ግምገማው ነዋ ክቡር ሚኒስትር፡፡
•እንዴት ማለት?
•አንዴ ሲያወጡኝ…
•እሺ፡፡
•አንዴ ሲያፈርጡኝ…
•ወይ ጉድ፡፡
•አንዴ ሲሰቅሉኝ…
•እ…
•አንዴ ሲቀብሩኝ…
•ተላለቅን በለኛ፡፡
•በቃ ሁሉም ጉዴ ነው የወጣው፡፡
•እ…
•ያለኝ የፎቅ ብዛት ሲወራ…
•ደሞ ብዛትህ ተነሳ?
•ያለኝ ሀብት መጨመሩ ሲወራ…
•ስኳርህም እዛው ጨመረ?
•ብቻ ምን ልበልዎት?
•እኔንማ በቃ ይጨርሱኛል ማለት ነው?
•ያስቡበት ክቡር ሚኒስትር፡፡
•አብረውን እንዳልበሉ እንደዚህ ይጫወቱብን?
•ክቡር ሚኒስትር የእኛም አበላል ቀላል አይደለም፡፡
•ያው ተረቱ ያልበላ ተጐዳ ስለሚል እኮ ነው፡፡
•እሱማ እኔም ሲሾም ያልበላ የሚለውን ተረት ይዤ ነው የጨረገድኩት፡፡
•እና የተሳለ መጥረቢያ ነው የሚጠብቅህ እያልከኝ ነው?
•በሚገባ ይዘጋጁበት፡፡
•ገና ከአሁኑ መጨመር ጀመረ፡፡
•ምኑ ክቡር ሚኒስትር?
•ደምና ስኳሬ!

[ክቡር ሚኒስትሩ ዶክተራቸው ጋ ደወሉ]
•ሄሎ ክቡር ሚኒስትር፡፡
•ኧረ አንተ ጋ መምጣት አለብኝ፡፡
•ምነው ክቡር ሚኒስትር?
•በጣም ጨምሮ ነው፡፡
•ደመወዝ ተጨመረልዎት እንዴ ክቡር ሚኒስትር?
•ኧረ ደምና ስኳሬ ነው፡፡

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሾፌራቸው ጋር መሄድ ጀመሩ]
•ወዴት እንሂድ ክቡር ሚኒስትር?
•ሆስፒታል ነው የምንሄደው፡፡
•ውይ ምነው ክቡር ሚኒስትር?
•በቃ ሁሉ ነገር ደስ አላለኝም፡፡
•ምን ሆኑ?
•ስኳሬ ጨምሮ ነው፡፡
•ስኳር ይልሳሉ እንዴ ክቡር ሚኒስትር?
•ምን ለማለት ፈልገህ ነው?
•ስኳሬ ጨመረ ሲሉኝ ብዬ ነው፡፡
•ሙሰኛ እያልከኝ ነው?
•እሱን እርስዎ አሉ፡፡

[ክቡር ሚኒስትሩና ሾፌሩ የሆስፒታሉ ግቢ ውስጥ ሲገቡ በርካታ ቪ8 መኪኖች ቆመዋል]
•ኪኪኪ…
•ምን ያስገለፍጥሃል?
•የሚኒስትሮች ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት እዚህ ሆነ እንዴ?
•ምን እያልክ ነው?
•እስቲ መኪኖቹን ይመልከቱ አብዛኞቹ ሚኒስትሮች እዚህ ናቸው ማለት ነው፡፡
•እ…
•ሁላችሁም ታማችኋል ማለት ነው?
•እ…
•ለነገሩማ ሕዝቡም ታሟል፡፡
•ምን ሆኖ?
•በእናንተ ምክንያት፡፡
•እኔ አሁን ከአንተ ጋር የማወራበት አቅም የለኝም፡፡
•የእርስዎ በሽታ እኮ ይታወቃል፡፡
•ምንድነው?
•ሙሌት!

[ክቡር ሚኒስትሩን ዶክተራቸው እያናገራቸው ነው]
•ምን ሆኑ ክቡር ሚኒስትር?
•ጥሩ ስሜት እየተሰማኝ አይደለም፡፡
•ከሁለት ቀን በፊት ነው እኮ የመረመርኩዎት?
•ሁሉም ነገሬ ከፍ ብሏል፡፡
•በቃ እሺ ደምዎትን ልውሰድ፡፡

[የክቡር ሚኒስትሩን የምርመራ ውጤት ዶክተራቸው ይዞ መጣ]
•ምንድን ነው በሽታዬ?
•ክቡር ሚኒስትር የሁላችሁም በሽታ ተመሳሳይ ነው፡፡
•እንዴት?
•ሌሎቹም የእርስዎ ጓደኞች ተመሳሳይ በሽታ ነው የያዛቸው፡፡
•አንድ ዓይነት ነገር ነው እንዴ የምንበላው?
•የምትበሉት አገርማ ተመሳሳይ ነው፡፡
•የምትበሉት አገር ነው ያልከኝ?
•የምትበሉት ነገር ተመሳሳይ ነው፡፡
•ለመሆኑ በሽታችን ምንድን ነው?
•ሙሌት ነው፡፡
•ሙሌት ደግሞ ምንድን ነው?
•ሙስና፣ ሌብነትና ትምክህት!
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1548
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Re: ከወያኔ ባለስልጣን ጋር ቃለመጠይቅ

Postby ጌታህ » Sun Aug 13, 2017 9:09 am

ቅቅቅቅቅቅ....አሰፋ ማሩ የዶንኪው ጏደኛ የሆነውን ጉድ አዳምጡ

አንዲት ወያኔ አሮጊት ውሻዋን በሰንሰለት አሰራው ይዛ ቁጭ ብላለች.. አሰፋ ማሩ ባጠገቧ አልፎ እንዲህ ሲል ያሾፍባታል ፡-

አሰፋ ማሩ ፡- አንች ጨርጫሳ ወያኔ ያሰርሸው ውሻ ክህደትን ነው የምታሰተምሪው ወይሰ ውሻው ታማኝነትን ነው የሚያሰተምርሸ ብሎ ያፈዘባታል

ወያኔ አሮጊት ፡- ልጄ አርፈህ ጸባይህን ባታሰተካከል ይህን ውሻ ፈትቼ የ 400 ሜትር መሰናክል እንዲያስተምርህ አደርጋለሁ ሰትለው እግር አውጪኝ ብሎ ፈረጠጠ

ጌታህ ከፒያሳ (አራዳ)
ጌታህ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1209
Joined: Sat May 30, 2009 3:05 pm


Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests

cron