ባህል ተገፋ በአፍጢሙ ተደፋ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ባህል ተገፋ በአፍጢሙ ተደፋ

Postby እሰፋ ማሩ » Mon Sep 18, 2017 4:55 am

ባህል ተገፋ ባፍጢሙ ተደፋ
ወያኔ ሲነግስ ባንዳ ሲከረፋ
የአማራ ክፋይ ቅማንትን አስከፋ
ከተከዜ ምላሽ ወራሪው ሲያናፋ
ለስራ ፍለጋ በጎንደር የተስፋፋ
የኤርትራ ሪፈርንደም ክፉ ጭንገፋ
በቅማንት ሊደግም ሃገር ሊያጠፋ
ድሮ የማናውቀው በዘር መባላቱ
በእንገት ቆረጣ ወገንን ማጥፋቱ
የአኖሌ ታሪክ ዛሬ ማስፋፋፋቱ
ህዝብ ለማባላት ወያኔ ጥረቱ
ባህላችን ተደፋ እጅግም ዘቀጠ
መጨካከን ባሰ ትውልድ ቀየጠ
የተወሃደ ህዝብ በጎጥ ተናወጠ
የእውነት ተሟጋች ተስፋ ቆረጠ
አምላክ ድረስልን ባህሉ ዘቀጠ
የሰልፍ ጩህቱ አልቆ ተሟጠጠ
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1518
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests