ኢትዮጵያዊው ድምጻዊ አቤል ተስፋዬ እና ሰሌና ጎሜዝ ተጣሉ!!

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ኢትዮጵያዊው ድምጻዊ አቤል ተስፋዬ እና ሰሌና ጎሜዝ ተጣሉ!!

Postby አርሴማ123 » Tue Oct 31, 2017 11:03 am

«ውድ ተመልካቾችን ይህ በቀጥታ የምታዳምጡት ጉራማይሌ የሚለው በሳምንት ሁለቴ ወደ እናንተ የምናቀርበው ዝግጅታችንን ነው:: ፕሮግራሙን በመምራት እኔ ገጀራው ከእንግዶቼ ከስፖርት ጋዜጠኛው ሰለሞን ገ/እግዚአብሔር እና ከወጣት ትሁኔ ጋር ለተወሰኑት ደቂቃዎች አብሬያችሁ እዘልቃለሁ መልካም ቆይታ ::

እንግዲህ ወደ መጀመሪያችን ወሬ ስንመጣ በቀጥታ የምናገኘው የአለም መነጋገሪያ ሁኖ ያደረውን የኢትዮጵያዊው አርቲስት አቤል ተስፋዬን እና የአሜሪካዊቷን ድምጻዊት ሰሌና ጎሜዝን መለያየት ይሆናል:: አቶ ሰለሞን በእድሜ ትንሽ ገፋ ስለሚሉ ጥያቂዬን ከእርሶ ልጀምር እስኪ:: የሁለቱ ጥንዶችን መፋታንት እንዴት ነበር ያዩት? እንደ አንድ ኢትዮጵያዊስ ምን ተሰማዎት?»

«አመሰግናለሁ ሄርሜላ፣ በመጀመሪያ በእድሜ ከወ /ሮ አያንቱ የማንስ እንጂ የምበልጥ አየደለሁም::ገና አንድ ፍሬ ልጅ ነኝ:: ኑሮ ነው እንደዚ ያለእድሜዬ ያጎሳቆለኝ::ስለዚህ አንቱታውን ትተህ አንተ በለኝ::ወደ ጥያቄህ ስመጣ ያው የፌመሶች ሪሌሽንሽፕ እንደማይበረክት ሁላችንም እናውቀዋለን:: ደግሞም ደርሶብን አይተነዋል:: እንዲያውም ከፌመሶች ሪሌሽንሽፕ ይልቅ የቻይና ጫማ ይበረክታል የሚባል አባባል አለ:: ስለዚህ የሁለቱ መፋታት ምንም ሰርፕራይዝ አላደረገኝም:: እንዲያውም በጣም ቆይተዋል ነው የምለው:: አይ ቲንክ የሰሌና በጣም ረጅሙ ሪሌሽንሽፕ የሚባለው ከእኛው ጉድ አቤል ጋር ያደረገችው ይመስለኛል:: ከዚ በፊት ከካናዳዊው ፖፖ ስታር ጇስቲን ቫይበር ጋ ሪሌሽንሽፕ ጀምራ ገና አልጋ ለይ ሳይሞካከሩ ነበር የተፈታቱት:: ከአቤል ጋር ግን አልጋ ለይ ከመሞካከር አልፈው ገላቸውን የሚታጠቡት አብረው በአንድ ሳፋ እንደነበር ዘ ጋርድያን በተባለ አለማቀፋዊ ጋዜጣ ማንበቤን አስተውሳለሁ:: ይሄም የሚያሳየው በጣም መላመደቸውን ነው::»

«ወጣት አያንቱ ወዳንቺ ልምጣ እስኪ:: አንቺስ የሁለቱን ተዋቂ አርቲስቶች መፋታት ስሰሚ በሆድሽ ምን አይነት ስሜት ነበር የተፈጠረው? እንደ አንድ ኢትዮጵያዊስ ምን ተሰማሽ?»

«አመሰግናለሁ ገጀራው፣ በመጀመሪያ ጥያቄህን ከመመለሴ በፊት ጋዜጠኛ ሰለሞን ባሉት አንዳንድ ነገር ለይ እርማት ማድረግ እፈልጋለሁ:: የአወያያችን ስም ሔርሜላ ሳይሆን ገጀራው ነው ::ይሄም የሚያሳየው ዛሬም ድረስ በሔርሜላ ፎንቃ መጠለፎዎትን ነው:: እንዲሁም ካናዳዊው አርቲስት ስሙ ጇስቲን ቫይበር ሳይሆን ጀስቲን ባይበር ነው:: በመቀጠል ፖፕ ስታር እላለሁ ብለው ፖፖ ስታር ማለታቸው ስህተት ነው:: ይሄም የሚያሳየው አቶ ሰለሞን ዛሬም ድረስ በዚ እድሚያቸው ከፖፖ አለመላቃቃቸውን ነው:: እላይ ጋ ደሞ ንግግራቸውን ሲጀምሩ "የፌመሶች ሪሌሽንሽፕ እንደማየበረክት እኛም ለይ ደርሶብን አይተነዋል" ብለዋል:: በጣም ይገርማል:: በእርግጥ ሚስታቸው የነበረችው ጠጂቱ አቶምሳ ፣ከባህር የወጣው አሳ የሚለው ድራማ ለይ ባጋጣሚ ለ 10 ሰከንድ የሚሆን እበት ስትጠፈጥፍ ታይታለች:: በተቀረ ሴትየዋ እንኳን ፌመስ ልትሆን ቀርቶ ተዋቂ ሰው ባለፈበት አልፋ አታውቅም:: በመቀጠል እኔን የእርሳቸው ታላቅ አድርገው ለማየት የሞከሩበትም መንገድ በጣም አስቆኛል:: ምነው አቶ ሰሎሞን እርሶ'ኮ በጣም ከማርጀተዎ የተነሳ ጆሮት ውስጥ የበቀለው ነጭ ጥጥ የሚመስለው ጸጉር ከሩቅ ሲታይ ነጭ ኤርፎን ሰክተውበት ነው የሚመስለው:: ስለዚህ.....»

«እባካችሁ፣ እባካችሁ እንግዶቻችን ያለነው ሚድያ ለይ ነው:: ስለዚህ እርስ በርስ መነቋቆሩን ትተን ወደ ውይይታችን እንግባ:: አቶ ሰሎሞን ይቀጥሉ::»

«ማንን ነው ሽማግሌ የምትይው? አንቺ ፎቅ ራስ አሮጊት!! ድሮ እናቶቻችን ሊቀመጡ ሲሉ ነበር ቀሚሳቸውን የሚሰበስቡት አንቺ ግን ቦርጭሽን ሰብስበሽ ነው የምተቀመጪው የሆንሽ ደመራ አቋም!! ስሚ እኔ ኮ....»

«አቶ ሰለሞን፣ አቶ ሰለሞን እንዴ ስርአት ይያዙ እንጂ?! ያለነው'ኮ ሚዲያ ለይ ነው!! እንደዚ ስትሰዳደቡ ተመልካቾቻችንስ ምን ይላል? አሁንም መነቋቆሩን ተውትና ውይይታችንን እንቀጥል:: አቶ ሰለሞን አሁንም ከእርሶ ነው የምጀምረው:: ለአቤል እና ለሰሌና ጎሜዝ መፋታት ምክንያታቸው ምን ይመስለዎታል? ጎምዝዛው ነው ጎምዝዟት የተለያዩት?»

«እንደሚመስለኝ በየቀኑ እናቱ ቤት እየወሰደ የሚያበላት ሽሮ ጎምዝዟት ይመስለኛል የተጣሉት:: ሽሮ እንኳን እሷን ለመሰለ ፈረንጅ ይቅርና ለእኛም አድገንበት እራሱ አንዳንዴ በጣም ይሰለቸናል:: ስለዚህ የፍቺያቸው ዋናው ምክንያት ሽሮ ነው ብዬ ነው የማስበው:: ዘ ኒዎርክ ታይምስ የሚለው ጋዜጣም ይሄንን ነው የሚያረጋግጠው::»

«ወጣት ትሁኔ ወዳንቺ ልምጣ እስኪ:: የአቤል ቤተሰቦች እና የሰሌና ቤተሰቦች የሁለቱ ጥንዶችን መለያየት ሲሰሙ ምንድን ነበር ያሉት?»

«የአቤል ቤተሰቦች ከእናትየው በቀር ሁሉም በጉዳዩ በጣም አዝነዋል:: ማዘርዬው ግን እሰይ ስለቴ ሰመረ እያሉ ሰፈሩን በእልልታ ሲቀውጡት እንዳመሹ ነው ጎረቤቶቻቸው የሚናገሩት:: "ከድሮም ውቃቢዬ አሎደዳትም:: ልጅቷ እናኳን ለ አቤል ይቅርና ለቃዬልም አትሆንም:: ልጁ አልሰማ አለኝ እንጂ መጀመሪያውንም'ኮ ነግሬው ነበር :: የሀገርህ ልጆች እነ ብርቄ፣ እነ ወለላ፣ እነ ጫልቱ፣ እነ ቀለሟ እያሉልህ ምን ፈረንጅ ለይ ፊጥ አረገህ ብዬ ነበር:: ነገር ግን አልሰማኝም:: አሁን ግን ስለቴ ሰምሮ በመጣላታቸው ደስ ብሎኛል" ሲሉም ተጠምደዋል:: የሰሌና ቤተሰቦች ግን በጉዳዩ ለይ ምንም ነገር ከማለት ተቆጥበዋል:: »

«ውድ ተመልካቾቻችን ከሰአት አኳያ የዛሬውን ውይይታችን እዚ ለይ ለመቋጨት እንገደዳልን:: ሁለቱ እንግዶቼ ሰአቱን በጭቅጭቅ ባይጨርሱት ኑሮ ሌሎች ጉዳዮችን እያነሳን እንዲሁ በሰፊው እንወያይ ነበር:: ለማንኛውም በሚቀጥለው ከሌሎች እንግዶቼ ጋ በሌላ ጉዳይ ለይ እስከምንገናኝ አማን ያሰንብተን:: »
አርሴማ123
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 6
Joined: Sun Sep 11, 2016 1:07 pm

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 2 guests