ፍቼ ጨምበላላ በወያኔ አልሞት ባይ ርዝራዦች በሁከት ተካሄደ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ፍቼ ጨምበላላ በወያኔ አልሞት ባይ ርዝራዦች በሁከት ተካሄደ

Postby እሰፋ ማሩ » Wed Jun 13, 2018 1:07 am

በውጭው አለም ቻይናና ሌሎችም የየራሳቸው የዘመን መለወጫ ያላቸውን ያህል በሃገራችን ኢትዮጲያም የሲዳማ ህዝብ የራሱ ዘመን መለወጫውን ያከብራል፡፡
HOMEESAT TVRADIO AMHARICOROMIFFAENGLISHSUPPORT ESATEVENTSCONTACT
በሃዋሳ ከተማ የጨምበለላን በዓል ተከትሎ ግጭት ተነሳ
(ኢሳት ዜና ሰኔ 5 ቀን 2010 ዓ/ም) በተለያዩ ደማቅ ዝግጅቶች የሚከበረው የሲዳማ ማህበረሰብ የዘመን መለወጫ በዓል ፣ ጨምበለላ፣ በአዋሳ ከተማ በሚከበርበት ወቅት ያልታሰበ ግጭት ተነስቷል። በግጭቱ የተገደሉ ሰዎች መኖራቸውን ነዋሪዎች ይገልጻሉ።
ከተማዋ በታጠቁ ሀይሎች ተሞልታለች። ሲዳማ ወጣቶች በባህላዊ ዜማ በቡድን በቡድን ሆነው እየዘመሩ ተቃውሞአቸውን ቢያሰሙም፣ ባለ ቀይ መለዮ ወታደሮች በዱላ እና በሰደፍ እየደበደቡ ለመበተን ሲጥሩ መታየታቸውን ነዋሪዎች ይገልጻሉ።
ግጭቱ ሆን ተብሎ በደኢህዴን ባለስልጣናት እንደተነሳ፣ በተለይም የአዲሱን ጠ/ሚኒስትር ወደ ስልጣን መምጣት ያልተቀበለው የደኢህዴን ቡድን ፣ የዶ/ር አብይን ምስል የያዘ ቲሸርት እንዳይለበስ በመከልከላቸው ውዝግብ መፈጠሩን ይናገራሉ። የሲዳማ ተወላጆች ሃዋሳ በክልል ደረጃ እንዲዋቀር ጠ/ሚኒስትሩ ከተማዋን በጎበኙበት ወቅት መጠየቃቸውን፣ ይህንኑ ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ ሲጠየቁ መዋላቸውን ነገር ግን የክልሉ ባለስልጣናት ግጭት እንዲፈጠር ሆን ብለው የተደራጁ ቡድኖችን መላካቸውን ስፍራው ላይ የነበሩና ድርጊቱን ሲከታተሉ የነበሩ ለኢሳት ገልጸዋል።
በጉዳዩ ላይ የደኢህዴን ባለስልጣናት የሰጡት መግለጫ የለም። ጨምበለላ የሲዳማ ተወላጆች ባህላዊ ልብሶችን ለብሰው፣ አዛውንቱ መልካም ምኞታቸውን በምርቃት እየገለጹ፣ ወጣቶች እየጨፈሩ የሚያከብሩት ባህል ነው።
ከተለያዩ ወረዳዎች የተውጣጡ የሃገር ሽማግሌዎች “የቄጣላ” ጨዋታ፣ የፈረስ ጉግስን ጨምሮ የተለያዩ ዝግጅቶችን ያከናውናሉ።
ይህ አለማቀፍ እውቅና ያገኘው በዓል፣ ለሚቀጥሉት 2 ሳምንታት ይከበራል።
ለሀዋሳ ከተማ የእግዚአብሔር ምህረት ይብዛላት (ትንቢተ ሕዝቅኤል 35 )
------------
6፤ ስለዚህ እኔ ሕያው ነኝና ለደም አሳልፌ እሰጥሃለሁ ደምም ያሳድድሃል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ደምን ስላልጠላህ ደም ያሳድድሃል።

7፤ የሴይርንም ተራራ ውድማ አደርገዋለሁ፥ የሚሄደውንና የሚመለሰውንም ከእርሱ አጠፋለሁ።

8፤ ተራሮቹንም በተገደሉት ሰዎች እሞላለሁ፤ በኮረብቶችህና በሸለቆችህ በፈሳሾችህም ሁሉ ላይ በሰይፍ የተገደሉት ሁሉ ይወድቃሉ።

9፤ ለዘላለምም ባድማ አደርግሃለሁ ከተሞችህም ሰው የማይኖርባቸው ይሆናሉ፥ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።

10፤ እግዚአብሔርም በዚያ ሳለ፥ አንተ፦ እነዚህ ሁለቱ ሕዝቦች እነዚህም ሁለቱ አገሮች ለእኔ ይሆናሉ እኛም እንወርሳቸዋለን ብለሃልና

11፤ ስለዚህ እኔ ሕያው ነኝና እንደ ቍጣህ መጠን እነርሱንም ጠልተህ እንዳደረግኸው እንደ ቅንዓትህ መጠን እኔ እሠራለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ በፈረድሁብህም ጊዜ በእነርሱ ዘንድ የታወቅሁ እሆናለሁ።(ትንቢተ ሕዝቅኤል 36 )
------------
17፤ የሰው ልጅ ሆይ፥ የእስራኤል ቤት በምድራቸው በተቀመጡ ጊዜ በመንገዳቸውና በሥራቸው አረከሱአት፥ መንገዳቸውም በፊቴ እንደ መርገም አደፍ ነበረ።

18፤ በምድር ላይ ስላፈሰሱት ደም በጣዖቶቻቸውም ስላረከሱአት መዓቴን አፈሰስሁባቸው፤

19፤ ወደ አሕዛብም በተንኋቸው ወደ አገሮችም ተዘሩ፤ እንደ መንገዳቸውና እንደ ሥራቸው መጠን ፈረድሁባቸው።

20፤ ወደ መጡባቸውም ወደ አሕዛብ በመጡ ጊዜ፥ ሰዎች እነርሱን፦ ከምድሩ የወጡ የእግዚአብሔር ሕዝብ እነዚህ ናቸው ሲሉአቸው ቅዱስ ስሜን አረከሱ።

21፤ እኔ ግን የእስራኤል ቤት በመጡባቸው በአሕዛብ መካከል ስላረከሱት ስለ ቅዱስ ስሜ ስል ራራሁላቸው።
የፍቼ ጨምበላላ በአል በሰላም መከበሩን ኢሳት ካስተላለፈ ብሁውላ በዚያው ሚዲያ ደም መፋሰስ መከሰቱ ተዘገበ፡፡


የሲዳማ ፍቼ ጨምበላላ በዓል መከበር ጀመረ
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 5/2010) የሲዳማ ብሄረሰብ የዘመን መለወጫ በዓል መከበር መጀመሩ ተገለጸ።
ፍቼ ጨምበላላ በሚል መጠሪያ የሚከበረው በዓል በብሄረሰቡ ዘንድ ትልቅ ስፍራ ያለው ባህላዊ ፌስቲቫል ነው።

ከሀዋሳ ዙሪያ በሺዎች የሚቆጠሩ የብሄረሰቡ ተወላጆችና የአከባቢው ነዋሪዎች በባህላዊ አልባሳት ደምቀው እያከበሩት መሆኑንም የደረሰን ዜና ያመለክታል።

ፍቼ ጨምበላላ የማይዳሰሱ ቅርሶች በሚል በመንግስታቱ ድርጅት የባህልና የሳይንስ ተቋም ዩኒስኮ ከተመዘገቡ የሀገራችን በዓላት አንዱ እንደሆነም ይታወቃል።
የሲዳማ ሴት ከጋብቻ በኋላ በዓመት አንድ ጊዜ ወደ ቤተሰቦቿ የምታደርገውን ጉዞ በማስታወስ የሚከበር በዓል ነው ፍቼ ጨምበላላ። ይህቺ ሴት ወደ ቤተሰቦቿ ስታመራ በቆጮና በቅቤ የሚሰራ ቡርሳሜ የተሰኘ ባህላዊ ምግብ አዘጋጅታ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ። ቡርሳሜውን ቤተሰቦቿ ከጎረቤቶቻቸው ጋር በመሆን እየተመገቡ ጊዜውን በደስታ የሚያሳልፉበት ልዩ ወቅት ነው። ይህ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲሸጋገር የቆየው ታሪክ የሲዳማ ህዝብ በዓመት አንድ ጊዜ የሚውለውን የፍቼ ጨምበላላ በዓል መነሻ ተደርጎ ተመዝግቧል። ፍቼ ጨምበላላ የሲዳማን ህዝብ አንድነትና ፍቅር የሚያንጸባርቅ መድረክ ሆኖ ለዘመናት ሲከበር የቆየ በዓል ነው።

በየዓመቱ የብሄረሰቡ አዋቂዎች መክረው ኮከብ ቆጥረው የበዓሉን ዕለት የሚወስኑ እንደነም ለማወቅ ተችሏል። አዋቂዎች ፍቺ ጨምበላላ የሚውልበትን ቀን ከወሰኑ በኋላ ለሀገር ሽማግሌዎች ያሳውቃሉ። ለበዓሉ የሚደረግ ዝግጅት ቀኑ ከታወቀበት ጊዜ አንስቶ ይጀመራል። ለአንድ ሳምንት ያህል የሚቆየውና በጭፈራና ዳንስ የሚከበረው ፍቼ ጨምበላላ በብሄረሰቡ አባላትና በአከባቢው ነዋሪዎች ዘንድ ልዩ ስፍራ የተሰጠው በዓል ነው። የዕድሜና የጾታ ልዩነት ሳይገድብው ሁሉም የህበረተሰብ ክፍል በእኩል ስሜት የሚያከብሩት በዓል እንደሆነም ይነገራል። በዓሉ በሚከበርበት ሳምንት የመጀመሪያው ቀን ልጆች ቤት ለቤት በመሄድ ለጎረቤቶቻቸው መልካም ምኞትና ሰላምታ በማቅረብ የበዓሉ ጊዜ ይጀምራል። ጎረቤትም ለበዕሉ የተዘጋጀውን ቡርሳሜ የተሰኘ ባህላዊ ምግብ በማቅረብ ልጆቹን ያስተናግዷቸዋል። በበዓሉ ላይ የሀገር ሽማግሌዎችና የብሄረሰቡ መሪዎች ለህዝቡ ምክርና የመልካም ምኞት መልዕክት ያስተላልፋሉ። ጠንክሮ ስለመስራት ስለመከባበር፡ በዕድሜ የገፉትን ስለመርዳት፡ በሀገር ሽማግሌዎቹ ከሚተላለፉት መልዕክቶች የሚጠቀሱ ናቸው። የተጣሉ የሚታረቁበት የዕርቅ በዓልም እየተባለ የሚጠቀስ ነው ፍቼ ጨምበላላ። ወላጆች ለልጆቻቸው የበዓሉን ትክክለኛ ትርጉም በማስተማር ሳይበረዝና ሳይከለስ ከትውልድ ትውልድ እንዲተላለፍ እንደሚያደርጉም ይነገራል።
ፍቼ ጨምበላላ በማይዳሰዱ ቅርሶች በሚል በመንግስታቱ ድርጅት የሳይንስና የባህል ተቋም ዩኔስኮ ከተመዘገቡ የሀገራችን ክብረበዓላት አንዱ መሆኑም ታውቋል። በዓሉ በዋዜማው ዛሬ በተለይ በሀዋሳ ከተማ ዋና ዋና መንገዶች ላይ በጭፈራና ዳንስ እየተከበረ መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል። በተያያዘ ዜና የፍቼ ጨምበላላ በዓል በሚከበርባት በሀዋሳ ከተማ ብሄርን መነሻ ያደረገ ጥቃት መፈጸሙን የኢሳት የመረጃ ምንጮች ገልጸዋል። ዛሬ በሀዋሳ ከተማ ገበያ ብሄር ላይ ያተኮረ ጥቃት የተፈጸመ ሲሆን በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ለማወቅ ተችሏል። ኢሳት ያነጋገራቸው የሲዳማ ሀርነት ንቅናቄ አመራር አባል አቶ ለገሰ ላንቃሞ ፍቼ ጨምበላላ የሰላምና የፍቅር በዓል ነው፡ ይህን መልካም ገጽታ ለማበላሸት የሚንቀሳቀሱ ሃይሎችን አጥብቀን እናወግዛለን ብለዋል።
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1550
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests