ጉድ እኮ ነው ዘንድሮ እንግጠም ካልን ለካ እንገጥማለን...

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ጉድ እኮ ነው ዘንድሮ እንግጠም ካልን ለካ እንገጥማለን...

Postby ክቡራን » Fri Feb 08, 2019 12:42 am

ጉድ ጉድ ጉ ድ ይሄ ቤት ባልታወቁ ዲጎኔ ( ዲያጎን ) ደቂቃናት ሲታመስ እያየን እንዳላየ ከመምሰል በሚል ስንኝ ቋጥሬ ነበር፡፡ የቋጠርኩትን ስንኝ ሳይ እኔ ነኝ ወይስ መንፈስ ነው የጻፈው ብዬ ተገረምኩ፡፡ ለካ የጸጋዬ ገብረ መድህን መንፈስ በውስጤ ነበር፡፡ ወይ ጉድ እስኪ በዲያጎን አጋንትታት ስተሰቃይ የነበረችው እቺ የስነ ጽሁፍ ክፍል ፈውስ ከማግኘቷ በፊት የተቀኘሁላትንም ላስነብባችሁ፡፡
ሊቀ መላእክት ክቡራን ነን፡፡

ኦ ጥበብ ሆይ ! እነሆ ማረፊያሽ የት አለ ..
መውጊያሽስ ወዴት ነው ..??
አዚም አዙሪት ሲፈነጨብሽ ..
ሉሱፈር ሰይጣን ሲጨፍርብሽ...
አታሞ ድቤ ሲመታብሽ ..
ልሳነ እርኩሳት ሲጎሰመብሽ..
ኦ ጥበብ ሆይ...
ማረፊያሽ የት አለ ..
መውጊያሽስ ወዴት ነው..??
የሰገባሽ ዘንጉ... የብእርሽ ሃሞቱ ..
የልሳንሽ አውድ ..የኪንሽ ምጥቀቱ ..
እያየሁት ሞተ... ወዘናሽ ድምቀቱ፡፡
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8093
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: MSN [Bot] and 2 guests