438 ቀናት፣ በአምባገነኖች መዳፍ ሥር የ.Martin & Johan መጽሐፍ በአማርኛ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

438 ቀናት፣ በአምባገነኖች መዳፍ ሥር የ.Martin & Johan መጽሐፍ በአማርኛ

Postby password » Mon Feb 24, 2020 4:50 pm

የዚህ መጽሐፍ ታሪክ መንስዔ አንድ ዩዋን የሚባል ተንከሲስ ፎቶግራፍ አንሺ ነው። በ2011 ወርሃ ሰኔ ላይ ኪንያ ውስጥ፥ ዳዳአብ ከሚገኘው የስደተኖች ካምፕ ተገኝቶ አንድ ጉድ ይሰማል። ስለ ጅምላ ግድያ፥ የመንደሮች መጋየት፥ የሴቶች መደፈርና ለዚህ ግፍ ምክንያት ስለ ሆነው የነዳጅ ዘይት ፍለጋ እያዳመጠ ፊልም ይቀርፃል።

አንድ አብዲ የሚባል ከኦጋዴን የተሰደደ የሶማሊ ክልል ልዩ ፖሊስ አባል የነበረ፥ ‘ከፊቴ የማይጠፋው’ ይላል፥ ‘ከፊቴ የማይጠፋው አንድ በወራት የሚቆጠር ዕድሜ ያለው ሕፃን ነው። እናቱን በጥይት ገድለን እሱን ሜዳ ላይ እንደ እቃ ጥለነው ሄድን። ሕፃኑ ያን ግዜ ያሰማ የነበርው ለቅሶ በየሄድኩበት ይከተለኛል። ይሄኔ ጅብ በልቶት ይሆናል። አሁን ሕፃናት ሳይ ራሴን ያመኛል፥ ሳላብድ አልቀርም።’

ዩዋን ይህን እንደ ሰማ መቀጠል አልቻለም፥ ቀረጻውን አቁሞ በቀጥታ ወደ ማርቲን ይደውል። ማርቲን እንደ ወያኔ ጋዜጠኞች የዘር ገንፎ እየሰለቀጠ ያደገ ሰው አይደለም፣ ሶማሌ ስዊድን፥ ሙስሊም ክርስቲያን ሁሉም አንድ ነው።
ማርቲን፣ ዩዋን የነገርውን ጉድ ሲሰማ ከአዲሲቱ ሚስቱ ጋር የነበረውን የሽርሽር ፕሮግራም እርግፍ አድርጎ ወደ አፍሪቃ ቀንድ ይተኮሳል።
በወቅቱ አንድ የስዊድን ኩባንያ ኦጋዴን ውስጥ ነዳጅ ፍለጋ ያነፈንፍ ነበር። ኩባንያው ነዳጅ አገኘሁባቸው የሚልባቸው ጉድጓዶች አቅራቢያ የሚገኙ መንደሮች ይጋይሉ። ህዝቡ ይፈናቀላል። ያንገራገረ ዘብጥያ ይወርዳል ወይም ይረሸናል። በነዩዋን እሳቤ፥ ህዝቡን ለመታደግ ያለው አንዱ አማራጭ፥ ነዳጅ አውጭዎቹን ከኦጋዴን ድራሽ አባታቸውን ማጥፋት ነው። ያን ለማድረግ ደግሞ ኦጋዴን ውስጥ ገብተው በቃልና በምስል የተደገፈ ተጨባጭ ማስረጃ መሰብሰብና በህዝቡ ላይ የሚፈጸመውን አሰቃቂ ጭፍጨፋ ለስዊድንና ለዓለም ህዝብ ማጋለጥ ይኖርባቸዋል።

ለዚህ ነው ሁለቱ ወጣት ጋዜጠኖች በሶማሊያ በኩል ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ጥሰው የገቡት። ግን እግራቸው ኦጋዴንን እንደረገጠ በወያኔ መንግስት ወታደሮች ቁጥጥር ሥር ይውላሉ። ስለ ኦጋዴን ህዝብ ስቃይና ስለ ስግብግቡ የዘይት ኩባንያው ሚና ሊጽፉ ያሰቡበትን ራፖርታዥ የኦጋዴን በረሃ ይበላዋል፥ ከዚያ በረሃ ውስጥ ግን ሌላ ያላሰቡት አስደናቂና አስደማሚ ታሪክ ይፈልቃል። ያን ታሪክ በመጽሐፍ አሳትመውታል። ‘438 ቀናት’ በአገርኛ ቋንቋ ተተርጉሟል።

ጉዳችንን አንብቡት።


ስዊድን የምትኖሩ በአቅራቢያችሁ የሚገኝ ቤተ መጻሕፍትን "438 qanat" ብላችሁ ጠይቁ።


http://www.babile.wordpress.com

https://www.bokus.com/bok/9789197706735/438-qanat/

https://www.smakprov.se/bok/pocket/438-qanat-9789197706735/
Last edited by password on Mon Mar 02, 2020 12:28 am, edited 3 times in total.
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 330
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Re: 438 ቀናት፣ በአምባገነኖች መዳፍ ሥር

Postby ክቡራን » Mon Feb 24, 2020 9:06 pm

" በወያኔ መንግስት ወታደሮች ቁጥጥር ሥር ይውላሉ።"
ጠሃፊው ሆይ ያሁኑን ዘመን ወታደሮች ምን ስም እንስጣቸው ? የህዝብ አለኝታዎች?? ሱማሌ ኦሮሞን ኦሮም ሱማሌን ሲግድል ፊርማ ለመጠየቅ በሚመስል ስሜት ቆመው የሚያዩትን ምን እንበላቸው?? ያማራና የትግራይ ክልልን መንገድ ዘግቶ ታክስ የሚሰበስብን ጎረምሳ አይዞህ የሚል ወታደርስ ምን እንበለው ? አማራና ትግራይ ከሚገናኙ ይልቅ በኦም ሃጀር በኩል ወደ ኤርትራ ግኑኝነቱ ቢሆን ይሻላል አይደል?? ምን ትላለህ ጠሃፊው ?? ለመሆኑ ጉጂ ውስጥ ለተራቡ ኢትዮጵያውያን እንዲደርስ የተላከውን እርዳታና ስንቅ ከነ መኪናው ያዘረፈውን ባለኩምቢ ወታደር ምን ቢባል ይሻል ይመስልሃል?? ወደ ጃፓን የ የሚላከውን ቡና አምቦ ላይ ያዘረፈውን ወታደር ስም እስኪ ስጠው፡፡ በሰላም እጦት ስንት ህጻናት መንገድ ላይ የቀሩባትን ህጻናት እንባ ማን ያብስላቸው ትላለህ ?? የህግደፍ ሰራዊት ??? ሻቢያዎች በወያነ ጊዜ አንገት ደፍተው ነበር፡፡ ዛሬ እድሜ ለኮለኔሉ ኢሳያስ ኢትዮጵያን ክርስትና አንስቷታል፡፡ ናቅፋም ከብር በላይ ሆኗል፡፡ እሰማለሁ ጠሃፊው?? BTW, በዛች ኢትዮጵያዊት የሱማሌ እናት ላይ የደረሰውን ሃዘን ሃዘኔ ነው እጋራዋለሁ፡፡
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9240
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Re: 438 ቀናት፣ በአምባገነኖች መዳፍ ሥር ... Martin & Johan

Postby password » Tue Feb 25, 2020 11:06 pm

ጤና ይስጥልኝ፣ ክቡር።
ያነሳካቸው ጥያቄዎች ከዚህ ገጽ ጉዳይ ጋር የተያያዙ ባይሆንም፣ በውነቱ ትኩረት የሚገባቸው መሆናቸውን አምናለሁ።
በኦጋዴን ግዳጅ ላይ የነበረውን መለዮ ለባሽ የወያኔ ወታደሮች ያልኩበትን ምክንያት መጽሐፉን ስታነብ ትረዳዋለህ። ሃገር እንዳትደፈር ነቅቶ የሚጠብቅ ወታደር፣ ዘርና ብሄር ሳይለይ ለወገን ሁሉ ደራሽ የሆነ ሠራዊት የሃገር መከላከያ ይባላል።
ከላይ የዘረዘርካቸውን ታጣቂዎች ዓይነት ግን ምን እንደምላቸው አላውቅም። የሃገር መከላከያ ወይም የፖሊስ ሠራዊት ናቸው የሚል ሰው ይኖራል ብዬ አላምንም። አንድ ግልጽ መሆን ያለበት ነገር ቢኖር፣ ዛሬ የምናየው ቅጥ የለሽ ሥርዓት አልበኝነት ትላንት በመላ ኢትዮጵያ ተንሰራፍቶ የነበረው የወያኔ ሥርዓት ውርስ መሆኑ ነው።

ሻዕቢያን፣ ኦማሃጀርን፣ ኢሳያስን ያነሳህበት ምክንያት ግልጽ ነው። በወያኔ የዘር ቆጠራ በሽታ የተለከፉ ሰዎች አንዱ ችግር ሁሉንም ነገር በዘር መነጽር ማየታቸው ነው። ፈስን ጭምር የትግሬ ፈስ፣ የኦሮሞ ፈስ እስከማለት ተደርሷል።
እና እኔ ሰው መሆኔን እስካልካድክ ድረስ ከውጭ የፈለከውን ብትለጥፍብኝ ስሜት አይሰጠኝም፣ እውስጤ ያለችውን ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ማንም ሊቀማኝ እንደማይችል አውቃለሁና።

በተረፈ የሰው ማንነት የሚቀረጸው በአስተዳደጉና በአካባቢው እንጂ በዘሩ ወይም ነገዱ ወይም በቀለሙ እንዳልሆነ አንተም የምታጣው አይመስለኝም።


ከአክብሮት ጋር

ፓስ

http://www.babile.wordPress.com
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 330
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe


Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot], Google Adsense [Bot] and 3 guests

cron